08/11/2022
ጉራጌ ለምን ክልልነትን ይጠይቃል ?
ጉራጌ በሀገራችን ካሉት ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር አላቸው ከሚባሉት ቀጥሎ ከፊት መስመር የሚሰለፍ ሰርቶና ለፍቶ በማደር የፊት መስመር ተሰላፊና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዋልታ የማይክሮ ኢኮኖሚን በባህሉ የተረጎመና ለሌሎች ያሰተማረ በፖለቲካውም እረገድ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበረው ሆኖም በተጠናና በተጠናከረ በተቀናጀ መንገድ መንግሥታዊ የሆነ ስልታዊ systematical discriminationየተፈፀመበትና እየተፈፀመበት ያለ ቢሆንም ከኢትዮጵያዊነት ከፍታው ሳይወርድ ከኢኮኖሚውም ወድቆ እየተነሳ ለዛሬ ቢደርስም ዛሬም ባሉት የመንግስት አስተዳደር ሥልጣን ባለቤቶች ቀንቀው እንዲጠፋ ባህሉ እንዲሸረሸር የአሰተዳደር ወሰን እንዳይኖረው ስራ እንጂ ፖለቲካን ለእናንተ አይሆንም ክልልም አያስፈልጋችሁም የሚል ለገጣ/ለበጣ የተያያዙበት ወቅት ላይ በመሆኑ ሰው እንደ ሰው የመኖር የመስራትና የመማር ንፅሁ ውሃ የማግኘት መብት አለማቀፋዊ ቢሆን ይህ ግን ለጉራጌ የተከለከለ ያልተፃፈ ህግ ሆኖ እየተተገበረ ይገኛል ከዋና ከተማ በ 100 ኪሎሜትር ራዲየስ ላይ ያለ ትምህርት ቤት የለውም ውሃ አያገኝም ሲባል ምን ይሰማ ይሆን ይህ ሁሉ ባለፊት 35 ዓመታት አንድምትምህርት ቤት በመንግስት ያልተገነባበት ይበልጥ የመንስት ፅ/ቤት እንካን ህብረተቡ በጉልበቱ የገነባበት የፖለቲካው ተሳትፎው 0%የሆነበትየፌዴራል መንገድ ሆኖበ 30 ዓመት ውስጥ አንዴ ደረጃውንባልጠበቀ ኮንትራክተርየታደሰበት ሆስፖታል የሌለው ማህበረሰብ ሆኖ ሲበደል ቢኖርም ዝምታን መርጦ ለሀገር አንድነት ቢያስብም እንደሞኝና የማይረባ ህዝብተቆጥሮ በመጥፋትና በመመናመን ላይ የሚገኝ ማህበረሰብ በመሆኑና ዘመኑ በብሔር ተደራጅቶ ኢትዮጵያን መገንባት የፖለቲካው ስልት ስለሆነ ይህንን የክልልነት ጥያቄ አቅርባል በዘመነ ምንልክ ደጃች በቀለየ ወያ ባልቻ አባነብሶ ኃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ እምዬ ምንልክ መስል ኃይለሥላሴ ራሳቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንህስት አመራሮችን በኮነሬል መንግስቱ ዘመነ መንግስት እነ ተስፋዬ ወልደማርያምን በራሪ ነብርን ጨምሮ ለኢትዮጵያ ታሪክ እንደ የቃቄ ውርዶት አጋዝ ፍርችየ የሴቶች መብትና ነፃነት የትዳር ክቡርነትን የሚያስተምሩ በአገር ሽምግልና ዕቁብና ዕድርን ለመሰረተ ማህበረሰብ ይህ አይገባውም ነበር ወከባውና ግርግሩንአቁሞ የተጠየቁትን ጥያቄውች ለሀገር ከሰራው ውለታ ጋር እንዲሁም ከተበደለው ካሳ ጭምር መንግስት ለያመቻችና በራሱ እንዲለማ የህዝብን የክልልነት ጥያቄ ሊመልስ ይገባዋል የጉራጌ ክልላዊ መንግሥት ለጉራጌ ::
ተፃፈ በተስፋዬ ወጂ
ነሐሴ 2 2014
ሚኖሶታ