Ethio Daily ኢትዮ ዴይሊ

Ethio Daily ኢትዮ ዴይሊ Ethio daily is a way to get your Ethiopia-related videos to the people that matter to you. Follow us if you need hot news update

01/16/2025

#የራሱን መቃብር አስቆፍሮ ሲያበቃ ለመሞት ተዘጋጀ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በበርካታ ስሞች ከሚጠሩ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው። በግሪኩ "ታዎሎጎስ" በግእዙ "ነባቤ መለኮት" የመለኮትን ነገር የሚናገር በሚል ስያሜ ይታወቃል። በፍፅሞ ደሴት በመጻኢው ጊዜ የሚሆነውን በራዕይ ተገልፆለት በመጻፉም "አቡቀለምሲስ" ወይም "የራዕይ አባት" ተብሏል። በዕለተ አርብ ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሸሹ እርሱ ግን ከመስቀሉ ስር ሳይለይ በንጹሁ ጌታ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ አይቷልና ቀሪ ዘመኑን ፊቱ በሀዘን እንደተቋጠረ በመዝለቁ "ቁጽረ-ገጽ" ተብሎ ይጠራል። በ81ዱ መጽሐፍ ቅዱስም 5 መጻሕፍት አሉት። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ወይም ጌታ የሚወደው ዮሐንስ ፍቁረ አግዚእ።

ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤትስ፣ ምሥጢረ መንግስትን ወይም መለኮትን በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ ይህም በዮሐ 13፡÷23 ተጠቅሷል።

የሮሙ ንጉስ ጢባርዮስ ቄሳር በጌታችን ላይ የደረሰውን መከራ እያሰበ ያዝን ነበር። እመቤታችንን ወደ ሮም ወስዶ እርሱ አገልጋይ፣ ሚስቱ ደንገጡር ሆነው ሊያገለግሉ በመፈለጉ ሰራዊት ላከ። ጌታችን የእመቤታችንን ተድላ ስጋዋን አይወድምና ነጥቆ ወደ ገነት ወሰዳት። በንጉሱ ላይ ግን ሀዘን እንዳይጸናበት ቅዱስ ዮሐንስን ሄደህ አስተምረው ብሎ ልኮታል፣ በዚህ ወቅትም አይሁድ በዕለተ አርብ በቀራንዮ እንደሰቀሉት አድርገህ ስለህ አሳየኝ ብሎት የመጀመሪያውን የጌታ ስዕል ስሎለታል። ሲስለው እንደ ዕለተ አርቡ ዕርቃኑን ቢስለው ጌታ " አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቆቴን እንደሰቀሉኝ አንተ ዳግም በሮም ራቁቴን ትሰቅለኛህ" ሲለው ከለሜዳ አልብሶ ስሎታል።

ከዚያ በኋላ ነው ከለሜዳ አልብሶ መሳል የተጀመረው። ከጌታ እርገት በኋላ 70 ዘመን የኖረው፣ በርካታ አህዛብን አስተምሮ ያጠመቀውና በመላው ዓለም ዞሮ ያስተማተው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የእረፍቱ መታሰቢያ ጥር 4 ሲሆን በዚህ ዕለት ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስንና ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ ካደረገ በኋላ ወረዶ ቆመ ልብሱንም አወለቀ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር ፡፡ እየጸለየም ደቀ መዛሙርቱ ወደ ከተማ እንዲሔዱ አሰናበታቸው፡፡

ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ መቃብሩም ሲሄዱ ልብስና ጫማውን ብቻ ነበር ያገኙት። በዚህም በወንጌል የተገረውን ቃል አስተዋሉ። በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 21 "ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም" ተብሎ እንደተጻፈ። የጸሎቱ በረከት ከሁላችን ጋር ይኑር። ለዓለም ፈቃድ የሞቱ በነፍሳቸው ሕያው ይሆናሉና፣ ዓለምን የተው መናንያን ያሉባቸውን ገዳማት እንርዳ።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ ነውበመዲናዋ የሚገኙ የነዳጅ ማዲያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ የሃይል መሙ...
01/16/2025

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት እየተደረገ ነው

በመዲናዋ የሚገኙ የነዳጅ ማዲያዎችን ወደ ኤሌክትሪክ የሃይል መሙያ ጣቢያ ለመቀየር ጥናት ተጀምሯል ያለው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ነው፡፡

የቢሮ ምክትል ኃላፊ ወርቁ ደስታ የኤሌክትሪክ ሃይል መሙያ ጣቢያዎችን ከከመስራት ባለፈም በሁለተኛው ምዕራፍ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት በመኪና ማቆሚያዎች የኃይል መሙያ እየተሠራ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ዴዔታ በርኦ ሀሰን ደግሞ ከዚህ በኃላ የተሽከርካሪ አስመጪና የሚገጣጥሙ ድርጅቶች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የኃይል መሙያ ሳይተክሉ በሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም ብለዋል።

ወ/ሮ ብርቄ ቤት ሰርተው ይሆን?
01/16/2025

ወ/ሮ ብርቄ ቤት ሰርተው ይሆን?

ከአፍሪካ ህብረት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለመመዝበር ሙከራ በማድረግ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ ተባሉየፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት...
01/15/2025

ከአፍሪካ ህብረት ሂሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ለመመዝበር ሙከራ በማድረግ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ ጥፋተኛ ተባሉ

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በነ ቀሲስ በላይ መኮንን መዝገብ ላይ የቀረቡ የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን መርምሮ በዛሬው የችሎት ቀጠሮ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ የምስክሮችን ቃል መርምሮ በክሱ ዝርዝር የተጠቀሰው የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ ማረጋገጡን ጠቅሶ በተከሰሱበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ በሰጠው ብይን ተከሳሾቹ ባቀረቡት የመከላከያ ማስረጃ በተገቢው ማስተባበል አለመቻላቸውን ጠቅሷል።

በዚህም በዛሬው ቀጠሮ 1ኛ ተከሳሽ ቀሲስ በላይ መኮንን በሙሉ ድምጽ የጥፋተኝነት ፍርድ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በአንድ ዳኛ የሀሳብ ልዩነት በአብላጫ ድምጽ ጥፋተኛ ተብለዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት ተመልክቶ የቅጣት ውሳኔ ለመወሰን ለጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጥሯል።

ምንጭ ፥ ፋና

አንዳንድ ነገሮችን ለባለሙያዎች መተው ጥሩ ነው በጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን         የጎንደር ፋሲለደስ እድሳት አንዳንዶችን "እያጠየቀ" ነው። "መልኩን ለቀቀ" ዓይነት ጥያቄ። ይህ ነገ...
01/15/2025

አንዳንድ ነገሮችን ለባለሙያዎች መተው ጥሩ ነው
በጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን

የጎንደር ፋሲለደስ እድሳት አንዳንዶችን "እያጠየቀ" ነው። "መልኩን ለቀቀ" ዓይነት ጥያቄ። ይህ ነገር የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ እድሳት የተነሳ የተረዳሁትን አስታወሰኝ።

የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ሊጠናቀቅ አካባቢ የምረቃውን መፅሔት ለማዘጋጀት (ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር) ከአንድም ሶስት አራት ጊዜ ካቴድራሉን ውስጣ ውስጡን የመጎብኘት ዕድል ገጥሞኝ ነበረ። ከኢንጂነሮቹ ጋር የማውራት፣ የመጠየቅ፣ ነገሮችን የመረዳት እድል ነበረኝ። በዚህ ጊዜ እጅጉን በሰማሁት፣ በተረዳሁት ተደምሜአለሁ።

ለምሳሌ ያህል ከዚህ ፅሁፍ ጋር የለጠፍኩት የኋለኛው የቤተክርስቲያን ክፍል ነው። የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ሥራ ማለት ነው። በነገራችን ላይ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሶስት ጊዜ ነው የተሰራው። የመጀመሪያው ከጣሊያን ወረራ በፊት፣ ሁለቱ ማስፋፊያ ከወረራ በኋላ ነው የተገነባው።
ይኼ የመጀመሪያው ግንባት (ቢጫ ቀለም የተቀባ የሚመስለው) በኖራ ነው የተሰራው። (እኛ የምናውቀው የግድግዳ ቀለም ሌላ መልክ ነበረው) ይህ እድሳት የጥንቱን መልክ እና ልክ እንዲይዝ ነው የተደረገው። ኖራው እንደ ጭቃ ከሁለት ወር በላይ ተቦክቶ ማለት ነው።
"ይህ ሕንፃ እንደ ሰው ገላ ነው ይተነፍሳል" ነበር ያለኝ ኢንጂነሩ። የሰው ሰውነት ላይ እንዳሉ የቆዳ ቀዳዳዎች አየር ያስወጣል ያስገባል አለኝ፦ ሲያስደንቀኝ። ለምሳሌ ከስሩ ሰፊ መቃብር ቤት አለ፤ አይሞቅም፤ አይቀዘቅዝም። ይህ ሊሆን የቻለው በጥንታዊው የአገነባብ ዘዴ የተነሳ ነው። እድሳቱ ያንን ጥንታዊ ሁኔታ እና መልክ ይዞ በጥንቃቄ ነው የተሰራው፦ እንደገባኝ።

የካቴድራሉ ጥገና አማካሪ ፋሲል ጊዮርጊስ በዚህ መፅሔት ውስጥ ካቴድራሉ ከመታደሱ በፊት 325 ገፅ ጥናት እንደተደረገ ይገልፃል።
"ለምሳሌ ከላይ ዶሙ ከመዳብ ነው የተሰራው። ከጊዜ ብዛት የመዳቡ መልክ ተቀይሯል። ስለዚህ ያንኑ የመዳብ መልክ መልሰን ማምጣት ነበረብን፤" ይላል።
አሁን ከእድሳት በኋላ የሆነውም ያ ነው።
መውጫ
የካቴድራሉ ጥገና አማካሪ ፋሲል ጊዮርጊስ የጎንደሩ ቤተመንግስት እድሳትም አማካሪ ነው። በጥናት እንደሚሰራ የተመሰከረለትም ባለ ሙያ ነው።
እና ...ምን ለማለት ነው?!
አንዳንድ ነገሮችን ለባለሙያዎች መተው ጥሩ ነው ለማለት ነው።

❤️ እናትዋ ጎንደር ❤️
01/15/2025

❤️ እናትዋ ጎንደር ❤️

የሹፌሩን ብልት ሽፍታዎች ቆረጡት ❗️ይህ የሆነው በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።ግለሰቡ የተወለደው ጅማ መስመር ጮራ ነው ። ስራው ደግሞ ሹፍርና። በስራ ላይ እያለ ሽፍቶች ያገኙታል አግኝተው...
01/15/2025

የሹፌሩን ብልት ሽፍታዎች ቆረጡት ❗️

ይህ የሆነው በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።

ግለሰቡ የተወለደው ጅማ መስመር ጮራ ነው ። ስራው ደግሞ ሹፍርና። በስራ ላይ እያለ ሽፍቶች ያገኙታል አግኝተው እንዲሁ አለቀቁትም የላይኛውን የብልቱን ክፍል ቆረጡት። ከዚህ በኋላ የታችኛው የብልቱ ቱቦ ተጎድቶ ፈሳሽ መቆም አይችልም እንዲሁ ይፈሳል። ከዛ በኋላ ለዳይፐር እና ለህክምና በቀን በቀን ወጪ ያወጣል። ይህ ቢኒያም የተባለ ሹፌር ቃል በቃል እንደሚናገረው «ፈሳሹ እንኳን ቢቆምልኝ እና ወ ደሹፍርና ስራዬ ብመለስ ደስተኛ ነበርኩ» ይላል።

- የሶስት ልጆች አባት የሆነው ይህ ግለሰብ ሁለቱ ልጆቹ ከአክስቱ ጋር የተቀረው ደግሞ ከእናቱ ጋር ሆነው መበታተናቸውን ይገልፃል። ለህክምና በቀን 1050ብር በሳምንት 7350 ብር ያወጣል።

- ሀኪሞች ህክምናውን በአግባቡ ከተከታተልክ የሚድን ነገር ነው ሲሉ ተናግረዋል። አቅም ያላችሁ ሁሉ ለነፍስ ይሆናችኋልና ተባበሩት።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት⬇️⬇️⬇️
1000514797351
( BINIYAM JEMANEH LIGDI)

01/15/2025

#ኑ እንውረድ… ልዩ ሦስትነት

ቅድስት ሥላሴ ተብለው በሴት አንቀጽ የሚጠሩት አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ፣ በሴት መጠራታቸው የፍጹም ርህራሄያቸው፣ የቸርነታቸው ማሳያ ነው፡፡ አንድም ሦስትም ብላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምረናለች፡፡ ይህ አንድነትና ሦስትነት እደምን ነው ቢሉ… በስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በመለኮት፣ በሕልውና፣ በመፍጠር በመሳሰሉት አንድ ናቸው እንላለን፡፡ ልዩ ሦስትነታቸውም በስም “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” ብለን፣ በግብር “አብ ወላዲ ወይም አባት፣ ወልድ ተወላዲ ወይም ልጅ፣ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ፣ ከአብ የሰረጸ የወጣ” ማለት ነው፡፡ በአካል “ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው ነው፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው” ብለን እናምናለን፡፡

የሥላሴ ገጽ አካልና ፊት እንደ ሰው ነውን? የሚል ጥይቄ ቢነሣ መልሱ “አዎ፤ እንደ ሰው ነው” የሚል ነው፡፡ ነገር ግን የሰው ገጽ አካልና ፊት ውሱን፣ ጠባብ፣ ፈራሽና በስባሽ ነው፤ የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ በሰማይና በምድር፣ በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ሕያው ባሕርይ ነው፡፡ ታላቁ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በምዕራፍ 86 ፥ 1-2 እንደጻፈው “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው” ይለናል በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን የሚመሰጠር ቅዱስ እግዚአብሔር፡፡

ይህም አንድነትና ሦስትነት በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ መልኩ የተነገረ ነው፡፡ በየዓመቱ ጥር 7 የሚከበረው የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል የአመጽ ግንብን ያፈረሱበት ነው፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11፥1-9 ተጽፎ እንደምናገኘው የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ “ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ከተማይቱንም መሥራት ተው። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ። እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።

በዚህ የመጽሐፍ ክፍል ውስጥ “እግዚአብሔርም አለ” ብሎ አንድነቱን ከነገረን በኋላ “ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” የሚል ከአንድ በላይ መሆንን የሚያመለክት ዓረፍተ ነገር ያስቀምጥልናል፡፡ ይህም በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተገለጸ ሦስትነት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በዘፍ 1÷26 “እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር” የሚለው ቃል “እግዚአብሔርም አለ” ብሎ አንድነቱን “ሰውን በመልካችን እንፍጠር” ብሎ ልዩ ሦስትነትን ይገልጻል፡፡ በዚህ ልዩ ሦስትነት አምነን የተጠመቅንና እኛ ክርስቲያኖች የሥላሴን በረከት ለመቋደስ በበረከት ስራ እንሳተፍ፡፡ የትምህርቱ ምንጭ የሆኑትን ገዳማት እንርዳ፣ የገዳማውያኑን በዓት እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

 #ኑ እንውረድ… ልዩ ሦስትነትቅድስት ሥላሴ ተብለው በሴት አንቀጽ የሚጠሩት አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ፣ በሴት መጠራታቸው የፍጹም ርህራሄያቸው፣ የቸርነታቸው ማሳያ ነው፡፡ አንድም ሦስትም ብላ ቅድ...
01/15/2025

#ኑ እንውረድ… ልዩ ሦስትነት

ቅድስት ሥላሴ ተብለው በሴት አንቀጽ የሚጠሩት አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ፣ በሴት መጠራታቸው የፍጹም ርህራሄያቸው፣ የቸርነታቸው ማሳያ ነው፡፡ አንድም ሦስትም ብላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምረናለች፡፡ ይህ አንድነትና ሦስትነት እደምን ነው ቢሉ… በስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በመለኮት፣ በሕልውና፣ በመፍጠር በመሳሰሉት አንድ ናቸው እንላለን፡፡ ልዩ ሦስትነታቸውም በስም “አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ” ብለን፣ በግብር “አብ ወላዲ ወይም አባት፣ ወልድ ተወላዲ ወይም ልጅ፣ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ፣ ከአብ የሰረጸ የወጣ” ማለት ነው፡፡ በአካል “ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው ነው፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው” ብለን እናምናለን፡፡

የሥላሴ ገጽ አካልና ፊት እንደ ሰው ነውን? የሚል ጥይቄ ቢነሣ መልሱ “አዎ፤ እንደ ሰው ነው” የሚል ነው፡፡ ነገር ግን የሰው ገጽ አካልና ፊት ውሱን፣ ጠባብ፣ ፈራሽና በስባሽ ነው፤ የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ በሰማይና በምድር፣ በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ሕያው ባሕርይ ነው፡፡ ታላቁ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በምዕራፍ 86 ፥ 1-2 እንደጻፈው “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው” ይለናል በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን የሚመሰጠር ቅዱስ እግዚአብሔር፡፡

ይህም አንድነትና ሦስትነት በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያየ መልኩ የተነገረ ነው፡፡ በየዓመቱ ጥር 7 የሚከበረው የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በዓል የአመጽ ግንብን ያፈረሱበት ነው፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11፥1-9 ተጽፎ እንደምናገኘው የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ “ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ከተማይቱንም መሥራት ተው። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ። እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።

በዚህ የመጽሐፍ ክፍል ውስጥ “እግዚአብሔርም አለ” ብሎ አንድነቱን ከነገረን በኋላ “ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።” የሚል ከአንድ በላይ መሆንን የሚያመለክት ዓረፍተ ነገር ያስቀምጥልናል፡፡ ይህም በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የተገለጸ ሦስትነት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በዘፍ 1÷26 “እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር” የሚለው ቃል “እግዚአብሔርም አለ” ብሎ አንድነቱን “ሰውን በመልካችን እንፍጠር” ብሎ ልዩ ሦስትነትን ይገልጻል፡፡ በዚህ ልዩ ሦስትነት አምነን የተጠመቅንና እኛ ክርስቲያኖች የሥላሴን በረከት ለመቋደስ በበረከት ስራ እንሳተፍ፡፡ የትምህርቱ ምንጭ የሆኑትን ገዳማት እንርዳ፣ የገዳማውያኑን በዓት እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ድህነትን የሚያባብስና ዜጎችን ለተደራራቢ የወጪ ጫና የሚዳርግ ነው በሚል ሲያከራክር የነበረው የንብረት ታክስ አዋጅ ፀደቀ፡፡የህንፃዎች የገበያ ዋጋ ተገምቶ የዋጋው 25 በመቶውን መነሻ በማድረ...
01/15/2025

ድህነትን የሚያባብስና ዜጎችን ለተደራራቢ የወጪ ጫና የሚዳርግ ነው በሚል ሲያከራክር የነበረው የንብረት ታክስ አዋጅ ፀደቀ፡፡

የህንፃዎች የገበያ ዋጋ ተገምቶ የዋጋው 25 በመቶውን መነሻ በማድረግ ታክስ እንዲከፈልበት የሚያስገድደው የንብረት ታክስ አዋጅ የመንግስት ተቋማትን እና በጎ አድራጊ ድርጅቶችን ከታክስ ነፃ አድርጓል፡፡

የሃይማኖት ተቋማትም ለአምልኮ እና ለቀብር አገልግሎት የሚጠቀሙባቸው ህንፃዎች ብቻ #የንብረት _ክስ እንደማይከፈልባቸው ተነግሯል፡፡

በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ አዋጁ ሲፀድቅ እንደሰማነው የዝቅተኛ ገቢ ባለቤት የሆነ የአንድ ቤተሰብ መኖሪያ ቤት ያለው ታክስ አይከፍልም ይላል አዋጁ፡፡

ይሁንና ዝቅተኛ ገቢ ያለው ማን ነው? የሚለው አለመወሰኑ አሻሚ ያደርገዋል ሲሉ የፓርላማ አባላት አንስተዋል፡፡

ከባንክ ብድር ወስዶ መኖሪያ የገነባ ከደመወዙ 35 በመቶ የገቢ ግብር ተቆርጦበት የሊዝ የጣሪያና የግድግዳ ግብር ከፍሎ፣ የአከራይ ተከራይ ተቆርጦበት፣ በዚያ ላይ የባንክ ወለድና ብድር እየከፈለ የንብረት ታክስ ቢጣልበት መክፈል ይችላል ወይ? ሲሉ እንደራሴዎች ጠይቀዋል፡፡

ብዙ ያከራከረው ይኸው አዋጅ በ4 ተቃውሞ፣ በ10 ድምፀ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

Via Sheger fm

ወደ ሌላ ጦርነት እየሄድን ነው ? ህወሓት በወልቃይት በኩል ጦርነት ለመጀመር ለህወሓት ቅርብ የሆነው   Daniel Berhane  መፃፉ አነጋጋሪ ሆኗል ዳንኤል ብርሃኔ እንዲህ ሲል በፌስቡክ ...
01/14/2025

ወደ ሌላ ጦርነት እየሄድን ነው ?

ህወሓት በወልቃይት በኩል ጦርነት ለመጀመር ለህወሓት ቅርብ የሆነው Daniel Berhane መፃፉ አነጋጋሪ ሆኗል

ዳንኤል ብርሃኔ እንዲህ ሲል በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል

"ወደ ከባድ ምዕራፍ እየሄድን እንዳለን በተደጋጋሚ በተለያየ መንገድ ለመናገር እየሞከርኩ ነበር። ይህን ምዕራፍ ከባድ የሚያደርገው በማይሆን ስሌትና #በእውር ድንብር እየገባንበት ያለ መሆኑ ነው።
ደብረጺዮን ወደ 9ሺህ የሚጠጉ ታጣቂዎችን ይዞ ካስገባን እሳት የበለጠ እሳት ነው ከፊት ለፊታችን እየጠበቀን ያለው። ፈጣሪ ይሁነን እንጅ ሌላ ምን እንላለን ምንስ ማድረግ እንችላለን?"
ወደ ሌላ ዙር ጦርነት እየሄድን ይሆን ?

የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ተመረቀእድሳቱ ሁለት ዓመታትን የፈጀው የታሪካዊዉ የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እ...
01/14/2025

የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ተመረቀ

እድሳቱ ሁለት ዓመታትን የፈጀው የታሪካዊዉ የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ህንጻ ቤተክርስቲያን እድሳት ተጠናቆ ዛሬ ተመርቋል ፡፡

ህንፃ ቤተ ክርስቲያኑን መርቀው የከፈቱት ብፁእ ወ ቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ ኢትዮጵያ ወ እጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሀይማኖት ናቸው።

መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን 81 አመታትን ያስቆጠረ ባለ ታሪክ ቤተክርስቲያን ነው።

01/14/2025

#ሕግ የሚያከብረው… ሕግንም የሰራው

ጌታችን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሲወለድ በድንግልና ማኅፀኗ አድሮ በድንግልና ተወለደ፡፡ ከትንሳኤው በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሲገለጽ በተዘጋ ቤት በሩን ሳይከፍት በመካከላቸው ተገኘ፡፡ እንደ ገባም እንዲሁ ሳይከፍት ወጣ፡፡ ይህ ድንቅ ምስጢር በቤተ ልሔም ከተወለደ በኋላ በስምንተኛው ቀን በተደረገ በማይመረመር ግዝረቱም ታይቷል፡፡ እርሱ በሚያውቀው ረቂቅ ጥበብ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቈረጥ፣ ምንም ደም ሳይፈሰው መገረዙ ተገለጠ፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 15፥8 ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፡፡ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ፤›› በማለት እንደተናገረው በስምንተኛው ቀን ስርዓተ ግዝረትን ፈጸመ፡፡

በቅዱስ ሉቃስ 2፥21-24 ተጽፎ እደምናገኘው “በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡

ስሙም ገና በሥጋ ሳይፀነስ የእግዚአብሔር መልአክ ባወጣለት ስም ‹‹ኢየሱስ›› ተብሎ ተጠራ፡፡ ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ። እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ በጌታ ሕግ። የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተጻፈ በጌታ ፊት ሊያቆሙት በጌታም ሕግ። ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት።

በኢየሩሳሌም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅ ስምዖን የሚባል ሰው ነበረ፣ ጻድቅና ትጉህና መንፈስ ቅዱስም ያደረበት ነበረ። የተቀባውን ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር። በመንፈስም ወደ መቅደስ ወጣ፤ ሕፃኑን ኢየሱስ በግዝረቱ ቀን ተቀብሎ አቀፈው እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ። ጌታ ሆይ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤ ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው። ዮሴፍና እናቱም ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም። እነሆ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።

የጌታችን ግዝረት እንደማንኛውም ወንድ ደም በመፍሰስ ተከወነ አልነበረም እንደ ስርዓቱ ወደ ቤተመቅደስ ቢገባም ከእለተ አርብ አስቀድሞ ደሙ አይፈስምና በመንፈስ ቅዱስ ያለ ሰው እጅ በጌታችን ላይ ግዝረት ተገለጠ ወይም የግዝረት ምልክት ታየ፡፡ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ የግዝረትን ሕግ የሰራው እርሱ ሰው ሆኖ በግዕዘ ሕጻናት ቢወለድ ሕጉን ፈጸመ፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት ይህን ጨምሮ ስርዓት ሁሉ ባይፈጽም አይሁድ ከኛ ወገን አይደለህም ለማለት ምክንያት ያገኙ ነበር ይላሉ፡፡ የጥበብ ቤት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን እያፈራች ሕግና ስርዓትን ጠብቃ ትኖራለች፤ ለዚህም መሰረቷን ማጽናት፣ ገዳማቷን መደገፍ ይገባል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

+ከአእላፋት ማግስት+Credit: ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው ()''ይሄን ስእል እያመለክሽ ነው ሳታገቢ የቆየሽው በጌታ በእየሱስ ስም መንፈስሽን ወጋሁት'' እናቴ ናት በጠዋት እንዲህ የምትለው። አ...
01/13/2025

+ከአእላፋት ማግስት+

Credit: ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው ()

''ይሄን ስእል እያመለክሽ ነው ሳታገቢ የቆየሽው በጌታ በእየሱስ ስም መንፈስሽን ወጋሁት''

እናቴ ናት በጠዋት እንዲህ የምትለው። አሁንማ ገና እየደረሰ በመሆኑ፥ አእላፋት ዝማሬ ብቻ ሆኗል ወሬው እሱ ይረብሻታል።

ስለ እናቴ ትንሽ ላውራቹህ...

ኤልሳ ትባላለች። ሲበዛ ተጫዋች፥ ረጅም፥ በጣም ቀይ፥ ስትስቅ ጥርሷ የሚያምር፥ በዛ ላይ ዲምፕል ያላት ውብ ናት። አባቴ ደግሞ ሱራፌል ይባላል፤ ዲያቆን ነበር። በእርግጥ እኔ 16 አመቴ እያለ ነው የሞተው። ሰዎች ስለ እርሱ አውርተው አይጠግቡም። ሰው ቀና ብሎ የማያይ፥ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፥ ጸሎተኛ ነበር ፤ መምህሩ ሲቀሩ እርሱ ነበር ጉባኤ ዘርግቶ የሚያስተምረው። ሁሉም ነበር የሚወደው። እኔን ራሱ ውዳሴ ማርያም፥ ዳዊት፥ ቅዳሴ፥ ሰዓታት አስተምሮብኛል። '

'ሰበኔ... ሴት ሆንሽብኝ እንጂ አንቺን ዲያቆን ነበር የማደርግሽ'' የሁል ጊዜ ንግግሩ ነበር።

እናቴ አባቴ በእግዚአብሔር ላይ ያለው መተማመን ይገርማታል። እኔ ልክ 15 አመት ሲሆነኝ አባቴ በጠና ታመመ። የሳንባ ካንሰር ያዘው። ከቤት መውጣት ከበደው፤ ቀኑን ሙሉ የሚያሳልፈው አልጋ ላይ መጽሐፈ መነኮሳትን እያነበበ ነበር። ትንሽ ህመሙ ባስ ሲልበት ደግሞ መጽሐፉን ደረቱ ላይ አድርጎ ለሰአታት መተንፈስ የከብደው ነበር። ከእርሱ ህመም በኋላ ቤታችን ውስጥ ሳቅ የሚባል ጠፋ። እናቴ ቀይ ፊቷን ማድያት ወረሰው።
......የሆነ ማክሰኞ ቀን ጠዋት ላይ ''ኡኡኡኡኡኡኡኡ'' የሚል ጩኸት ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ። እናቴ ነበረች። ብርድ ልብሱን ከራሴ ላይ በስርአት ሳላወልቅ ሮጥኩኝ። ኤልሲ አባቴን አቅፋ ፥-

"ጌታዬ ጉድ አታድረገኝ ባክህ ጉድ አታድርገኝ"

"እማ አባቴ ምን ሆነ?" ......እምባዬ ከየት እንደመጣ አላውቅም። ፊቴ ርሷል...

"የልጀነት ፍቅሬ ኧረ ተው" ትላለች።

"እማ አባቴ ምን ሆኗል?!"

"ጉድ አረከኝ! ብቻዬን ለማን ጥለከኝ! ኧረ ያላንተ አይሆንልኝም! ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ ኧረ ጉዴ"

ጩኸታችንን የሰሙ ጎረቤቶቻችን ቤታችንን ሞሉት። በአንዴ ግማሹ ቲቪ ይሸፍናል፥ ግማሹ ስለ ድንኳን ያወራል......ራሴን ሳትኩ፤ ስነቃ ቀብር ሊሄዱ ህዝብ መጥቷል። ቤቱ ውጪው ግጥም ብሏል። ያ ሁሉ ህዝብ አንድ አባቴን አልሆን አለኝ.....

አባቴ ካረፈ ጊዜ ጀምሮ ቤታችን የማይቀሩ የማይቀሩ 3 ሰዎች ነበሩ። እነዚህ የእናቴ የስራ ባልደረቦች ታዲያ በመጡ ቁጥር ለእናቴ እንፀልይልሽ ብለዋት ነው የሚሄዱት፤ የሆነ ቀን ላይ ከታናናሾቼ ጋር ጸሎት እያደረግን "ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቤት ሃይማኖት ተቀይሯል!" አለችን።

"ወደምን?" አልን

"ጌታን ተቀብለናል! ነገ ትጠመቃላችሁ። አቁሙ አሁን!"

"እንዴ ኤልሲ! እኛ እኮ ልጅ እያለን ተጠምቀናል"

"አንቺ ልጅ! ተናገርኩ በቃ!"

"አልቀይርም! አባቴ ያስተማረኝ ያወረሰኝ ነው፤ አልቀይርም!" አልኩ።

ኤልሲም መልሳ "ነው? ከሆነ ከቤቴ ውጪ! እናንተም እንደዛ ነው?

ታናሽ እህቴም አዎ አለች።

"ውጡ! ችግር እና ረሃብ ሲፈራረቅባችሁ ትመጡ የለ!" አለችን በቁጣ።

ስልኬን አንስቼ ለአያቴ ደወልኩ። አያቴ ብቻዋን የምትኖር፥ በጣም ትልቅ ጊቢ ያላት፥ እሱ ላይ ወደ 20 ምናምን ቤት ሰርታ የምታከራይ ሴት ናት። ስደውል ኑ ኧረ ኑ አለች
........ እናቴ ሃይማኖቷን ቀየረች። ሁሉንም እኛ ክፍል የነበረ ስእለ አድኅኖ አውጥታ አቃጠለች። የአባቴን ግን ከበዳት። የእርሱን ዳዊት፥ የጸሎት መጻሕፍት፥ ሁሉን ነገሩን በአንድ ላይ አድርጋ አንድ ክፍል ውስጥ ቆለፈችበት። እኛም አያታችን ጋር መኖር ቀጠልን።

---------------------------------------------------

እናቴን ሃይማኖቷን ያስቀየሯት ሰዎች Theology እንድትማር አደረጉና ፓስተር ሆነች ።

ዛሬ...

"እሺ ባክሽ... አእላፋት ምናምን እያላችሁ ነው ደግሞ በነጭ ልብስ ጣኦት ልታመልኩ"

"ተይ እንጂ እማዬ... የማይሆን አትናገሪ። ለምን ዛሬ አብረን አንሄድም?"

"ማን? እኔ? ሆሆሆሆሆሆሆሆ... ሥራ አልፈታሁም"

"ምን ችግር አለው? ከደበረሽ ቶሎ እንወጣለን።"

"ቆይይይይይ እሄዳለው። የምሄደው ግን እንዴት ልክ እንዳልሆናችሁ ላሳይሽ ነው!"

ሁላችንም ለባብሰን ወጣን። በጊዜ ነበር የደረስነው፤ ቦሌ መድኃኔዓለም ሞልቷል። እንደምንም ብለን ፊት ተጠጋን። ዲያቆኑ "እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ" ይላል። ቁርጥ የአባቴን ድምፅ! ኤልሲ ደነገጠች። አባቴን ያየችው መስሏት ተንጠራርታ ፈለገችው፤ የለም። የሚፀየውን ጸሎት በግእዝም በአማርኛም ስታየው ቆየች። እምባዋ ይፈስ ጀመር። ጸሎቱ ተጠናቆ ነጫጭ የለበሱ ዘማሪያን መድረኩን ሞሉት። መዝሙር ቀጠለ። ቸሩ ሆይ የሚለው መዝሙር ዘማሪዎቹ መዘመር ጀመሩ። የአባቴ የሚወደው መዝሙር ነበር። የሲቃ ድምጽ አውጥታ አለቀሰች። አሳዘነችኝ ደስም አለኝ። መዝሙሩ አለቀ። በአባቶች ብራኬ ተጠናቀቀ። ኤልሲ ሙሉ ሰአት እያለቀሰች ነበር ።

"ኤልሲዬ በቃ አንቺ ሂጂ፥ እኛ እናስቀድሳለን።"

"ልምጣ?"

"የምርሽን ነው?"

"አዎ ልምጣ"

"ነይ" ድንጋጤዬ ያስታውቃል።

ማህሌቱ አልቆ፥ ቅዳሴው አልቆ፥ ቤት ገባን። እኛ ቤት ከመጣሁ 10 አመት አልፎኝ ነበር። ያው ነው፥ ምንም አልተቀየረም። እናቴ ሮጣ ጸሎት ቤት ገባች። ሁሉ ነገሩ አባቴን አባቴን ይላል። ትልቅ የእመቤታችን ምስለ ስዕል ፊት ወድቃ አለቀሰች።

"ሰበኔ አሁን ገባኝ! ልቤ ተሰብሬ ሲያገኙኝ ዓለም ገደል ስትሆንብኝ አግኝተውኝ ነው! ልጆቼ ይቅር በሉኝ! በጎደለኝ በኩል ሲቆሙ ወዳጆች መሰሉኝ ......"

ተቃቅፈን ተላቀስን። ምን ተረዳሁ መሰላችሁ? እግዚአብሔር ስራው Mysterious ነው። እንዲህ ነው ብለን Define የማይደረግ። ዛሬ ላይ ቤተሰቤ ሙሉ ሆኗል፤ እናቴም ወደ ክርስትና ለመመለስ ትምህርት ለመማር ከመምህሬ ጋር አገናኝቻለሁ። ከ 10 ዓመት ከብዙ ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ። እጆቼን ከፍ አድርጌ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ...

"የእኔን እምባ ያቆምክ እግዚአብሔር... እምባቸውን ለሚያወጡ ድረስ" ብዬ። "ሰላም ለናፈቁ ሁሉ ሰላም ስጥ። አባቴ የደከሙ ልቦችን አሳርፍ፥ ፈገግታን የናፈቁን ሁሉ ሳቅ አጥግብ፥ ለደስታ የተግደረደሩትን ሁሉ አላምዳቸው ...ባለቀሱበት ቦታ እንባቸውን አብስ። ሁሉን ቻይ ሆይ፥ የመዳናቸውን ቀን አታርቅ።"

ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው (Instagram: - )
ጥር 1 / 2017

01/13/2025

#ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ካሉ ከሶስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት የመጨረሻው አረጋወ መንፈሳዊ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የጻፈው ታላቁ ገዳማዊ ጻድቅ አባት አረጋዊ መንፈሳዊ ወይም ዮሐንስ ሳባ ነው፡፡ ይህ ታላቅ አባት እየቀደሰ እያለ በተገለጸለት ታላቅ ምስጢረ ምክንያት ነበር ዓለምን ትቶ የመነነው፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ሆኜ ይህን ካሳየኝ ከዓለም ብሸሽ የበለጠ ለእርሱ እቀርባለሁ ብሎ፡፡

ገዳማውያን አባቶቻችን እንዲህ ናቸው ወደ ፈጣሪያቸው ለመቅረብ ዓለማዊ ክፋት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ መገለጥም ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ገዳማትን ስንደግፍም የእነዚህን አባቶች በረከት ነው የምናገኘው፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፣ ታዲያ አረጋዊ መንፈሳዊ በየጊዜው በዓለም ላለው ለታናሽ ወንድሙ መንፈሳዊ ደብዳቤ ይጽፍለት ነበር፡፡ ዓለምን እንዲተው ስላስወሰነው ምስጢር፣ ስለነበረበት፣ ስላለበት፣ በአጠቃላይም ስለ ገዳማዊ ሕይወት ነበር የሚጽፍለት፡፡

እነዚህን #”ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ የሚጻፉ ደብዳቤዎች እኔ ሳልሞት ለማንም እንዳታሳይ ብሎ ቢያዘውም ወንድሙ ግን በመጽሐፍ መልክ ለማጻፍ ደብዳቤዎቹን ለጸሐፊ ሊሰጣቸው ሲል አጣቸው፡፡ ከአስራ ስንት ዓመታት በኋላ ግን ደብዳቤዎቹን መጀመሪያ ያስቀመጣቸው ቦታ አገኛቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ወንድሜ ሞቷል ብሎ አለቀሰ፡፡ በረከቱ ይደርብንና ይህን ታላቅ ጸጋ የታደለው አባት ነው እንግዲህ ራሱን በትሕትና የዱር አውሬ ብሎ የሚጠራው፡፡

ገዳማውያን አባቶች መሻታቸው አንድ ብቻ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ለሀገርና ለሕዝብ መጸለይ፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን እናጽና፣ ድጋፍ እናድርግ ስንል በሌላ አባባል በረከት እንፈስ እያልን ነው፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ልጅ ሚካኤል ለአርቲስት ማሀሙድ በሰጠው የኢትዮጵያ ቅርፅ ጀርባ ላይ የሚከተለው መልዕክት ሰፍሯል።  " ጋሼ ዘመን ለማይሽራቸውና እጅግ ለምንኮራባቸው ለምንወዳቸው የሙዚቃ ስራዎችህና እንዲሁም ...
01/12/2025

ልጅ ሚካኤል ለአርቲስት ማሀሙድ በሰጠው የኢትዮጵያ ቅርፅ ጀርባ ላይ የሚከተለው መልዕክት ሰፍሯል።

" ጋሼ ዘመን ለማይሽራቸውና እጅግ ለምንኮራባቸው ለምንወዳቸው የሙዚቃ ስራዎችህና እንዲሁም
ላበረከትክልን ሙያዊ አስተዋጾ ሁሉ እጅግ አድርገን እናመሰግንሀለን ! "

Address

4320 Cascade Falls Court
Royse City, TX
75189

Telephone

+12404687690

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Daily ኢትዮ ዴይሊ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share