Amanual Gebremariam Yfter

Amanual Gebremariam Yfter - ሞት በአዳም ፣ ሕይወት በክርስቶስ🙏 ሰላም ለመላው አለም
Peace for the whole world
(6)

Both cute 🥰
12/19/2024

Both cute 🥰

የአንድ ሳምንት ልጇን አን*ቃ የገደለች*ው የ14 ዓመት ታዳጊ እናት በቁጥጥር ስር ዋለችበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በባስኬቶ ዞን ተጠርጣሪዋ የ14 ዓመት ታዳጊ ስትሆን  በላስካ ከተማ 02 ቀበሌ ...
12/19/2024

የአንድ ሳምንት ልጇን አን*ቃ የገደለች*ው የ14 ዓመት ታዳጊ እናት በቁጥጥር ስር ዋለች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በባስኬቶ ዞን ተጠርጣሪዋ የ14 ዓመት ታዳጊ ስትሆን በላስካ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ባዳይስ መንደር ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ሰናይት እንዳለ የተባለችዉ ታዳጊ የባስኬቶ ዞን ኗሪ ስትሆን በቁጥጥር ስር ልትዉል የቻለችዉ ልጇን በመግ*ደልና በመጣል ወንጀል ተጠርጥራ መሆኑን የባስኬቶ ዞን ፖሊስ መምርያ አስታውቋል።

ግለሰቧ የመዉለጃ ጊዜዋ ሲቃረብ ከባስኬቶ ወደ ጅንካ በመሄድ ከቀናት በኋላ በጅንካ ሆስፒታል የወለደች ሲሆን የሆስፒታሉ ሰራተኞች ብቻዋን መሆኗን አይተዉ ቤተሰብ የለሽም ወይ በማለት ሲጠይቋት ዘመድ የለኝም የሚል ምላሽ በመስጠቷ ሰራተኞቹ ልዩ ድጋፍና ክትትል ቢያደርጉላትም በሶስተኛዉ ቀን ከሆስፒታሉ በማምለጥ ወደ ባስኬቶ መመለሷ ተገልጿል።

በመቀጠልም ተከሳሽዋ የማሽላ እርሻ ዉስጥ ልጇን አን*ቃ በመግ*ደልና በመጣል ወደ ትዉልድ ስፍራዋ መመለሷን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

የእርሻዉ ባለቤቶች ለስራ ወደስፍራዉ ሲመጡ የህፃን ልጅ አስክሬን ማግኘታቸዉን ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ፖሊስ አስክሬኑን በማንሳት አስፈላጊዉን ምርመራ በማድረግ ከላስካ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር ስረአተ ቀብር መፈፀሙን ገልጿል።ፖሊስ ተጠርጣሪዋን ለመያዝ ባደረገዉ ክትትል በባስኬቶ ዞን ቦክቡጫ ቀበሌ በቁጥጥር ስር አዉሎ በምርመራ እያጣራ መሆኑን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

(ዳጉ ጆርኔል)

Tigray 👌📍
12/13/2024

Tigray 👌📍

❤️👌🙏
11/24/2024

❤️👌🙏

አይሪሽ ቦክሰኛ " " ስለ ሚስቱ ስናገር "ለ 8 ዓመታት አብረን ቆይተናል እና ከደብሊን 30 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው አየርላንድ ውስጥ ያለ ስፍራ ተከራይተን አፓርታማ ውስጥ እንኖር ነበር...
11/23/2024

አይሪሽ ቦክሰኛ " " ስለ ሚስቱ ስናገር "ለ 8 ዓመታት አብረን ቆይተናል እና ከደብሊን 30 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው አየርላንድ ውስጥ ያለ ስፍራ ተከራይተን አፓርታማ ውስጥ እንኖር ነበር. እኔ አልሰራም ምክንያቱም ሁሉንም ጊዜዬን በስፖርት አሳልፌያለሁ. ሁልጊዜም ጀግና መሆን ህልሜ ነበር...እናም የገንዘብ እጥረት ቢኖርም, አመጋገቤን ለመንከባከብ ብብዙ ጥረት ታደርጋለች..ቆንጆ የአትሌት ምግብም በሷ ልፋት አገኛለሁ ...

ከጠንካራ ስልጠና ወደ ቤት ያለ ጉልበት እና በብዙ ድካም ስመለስ ሁልጊዜ እንዲህ ትለኝ ነበር፡- "ኮኖር ማክግሪጎር፣ ይህን ማድረግ እንደምትችል አውቃለሁ እናም ታደርገዋለህ።"

አሁን ከ 50 እስከ 70,000 ተመልካቾች ፊት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር በመታገል አገኛለሁ። አሁን የትኛውንም መኪና፣ የትኛውንም ልብስ፣ የትኛውንም ቤት መግዛት እችላለሁ፣ እሷ ግን ምንም አልጠየቀችኝም፣ ግን በዚህ አለም ላይ ምርጡን ይገባታል።

እሷ ሁል ጊዜ ከጎኔ ነች እና ማንኛውንም ነገር ማድረግ እንደምችል ትነግረኛለች ! ወደዚህ ቦታ ደርሻለሁ ለእርሷ ምስጋና አለኝ....ብቻዬን አልተወችኝም። "

MP Ethiopia መልካም ቀን ❤

#ሼር 👈

አሜን በሉ 🙏
11/21/2024

አሜን በሉ 🙏

Beautiful kid ❤️🎯
11/18/2024

Beautiful kid ❤️🎯

Dreamer ❤️
11/13/2024

Dreamer ❤️

11/12/2024
ሀላፊነት በማይሰማው አሽከርካሪ ህይወታቸውን በግፍ ከተነጠቁ የመስከረም 15ቱ የትራፊክ አደጋ ሰለባዎች ውስጥ (ብላቴናው ማሙሸና አክስቱ ማያ)😭😭😭በትላንትና እለት በመኪና አደጋ ከሞቱት ውስጥ...
09/27/2024

ሀላፊነት በማይሰማው አሽከርካሪ ህይወታቸውን በግፍ ከተነጠቁ የመስከረም 15ቱ የትራፊክ አደጋ ሰለባዎች ውስጥ (ብላቴናው ማሙሸና አክስቱ ማያ)

😭😭😭
በትላንትና እለት በመኪና አደጋ ከሞቱት ውስጥ ትንሽዬው ማሙሽ ይገኝበታል😭

እድሜው ገና 2ዓመት ሲሆን የቤት ስሙ "ውሹ" ተብሎ የሚጠራው ይህ ትንሽዬ እንብቅቅል ልጅ አንዱ ነው።
ከእናቱ ጋር በመሆን ቤተሰቦቹ ጋር መስቀል ለማክበር ነበር ወደ ዳውሮ ታርጫ እየሄደ ሳለ ነበረ የህዝብ ማመላለሻው የተገለበጠውና ውሃ ውስጥ በመግባቱ ህይወቱን የተነጠቀው😭

ማሙሽ ወይንም በቤት ስሙ " ውሹ " ላይመልስ በዛው ያሸለበ ሲሆን ወላጅ እናቱ ተርፋ በህክምና ላይ ትገኛለች..እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ እጁ ይጎበኛት።

በዚህ ፎቶ ላይ የምትታየው የእናቱ እህት
አክስቱ ማያ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ በሌሞ ወረዳ በሌሣ ጤና አ/ጣቢያ የሥራ ባልደረባ ስትሆን እሷም ከማሙሽ ጋር ላትመለስ እስከወዲያኛው አሸልባለች😭

አደጋውን አስከፊ የሚያደርገው ጉዳይ ተሽከርካሪው በወቅቱ አቀበት እየወጣ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞት ስትራፕ ስያደርግ ማትረፍ እየተቻለ ሀላፊነት የማይሰማው አሽከርካሪ ከመኪናው ዘሎ በመውረድ ይህ ያህል ዘግናኝ አደጋ እንዲደርስ ሆኗል ተብሏል። ለዳውሮ የትራንስፖርት ችግር ዋነኛ ምክንያቶች ስግብግብ ባለሀብቶች፣ ኃላፊነት የማይሰማቸው ደምብ አስከባሪዎች እና አሽከርካሪዎች እንዲሁም መልከዓ ምድር ለማሽከርከር ጥንቃቄ የሚሻ መሆኑ ተቀዳሚ ምክንያቶች ናቸው።

በግፍ ለሞቱት ወንድም እህቶች እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳችሁን በአፀደ ገነት ያኑር። በዚህ አሰቃቂ አደጋ ወደጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ እና መላው የዳውሮ ህዝብ መጽናናትን እንመኛለን።
😭😭😭

"ተወዳጇ ድምፃዊት ጂጂ የሕይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ናት" ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ!!👉"በቅርቡ ወደ ሀገሯ ትመለሳለች " ተብሎ ሲነገር የነበረው ከእውነታ የራቀ ነው"ወንድወሰን ከበደ ከዋሽንግተ...
09/25/2024

"ተወዳጇ ድምፃዊት ጂጂ የሕይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ናት" ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ!!

👉"በቅርቡ ወደ ሀገሯ ትመለሳለች " ተብሎ ሲነገር የነበረው ከእውነታ የራቀ ነው"

ወንድወሰን ከበደ ከዋሽንግተን ስለ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው መልዕክት አስተላልፏል።

እኔና ጂጂ እዉቂያችን በ1987 አ.ም የሚጀምር ሲሆን በዚያን ግዜ የአስቴር አወቀና ፡የቡዙዬ ጥሩ አድርጋ ትጫወት ነበር ።

ብዙም ሳትቆይ ወደ አሜሪካን ሀገር ሀገር ሄደች ፡እሷ ከሄደች ከጥቂት አመታት በኋላም እኔም ወደ አሜሪካን ሀገር አቀናሁ የተለያየ ስቴት እንኖር ስለነበር ሳንገናኝ ቆየን ከአመታት በኋላ ከኒዮርክ አንድ ወዳጄ ያለችበትን ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ ስለነገረኝ በስልክ እየተገናኘን ማውራት ያዝን

በየቀኑ በሚባል በስልክ እናወራለን ወደ ቀልቧ ስትመለስም በትዝታ የኢትጽያ የመድረክ ቆይታዋንም አንስተን እንጨዎወታለን ፡ተወዳጁ ድምፃዊ አያሌው መስፍንና፣ ሻምበል በላይነህን በስልክ አገናኝቻትም ተጨዎውተዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት እሁድ ማለዳ ወደ ምትኖርበት ኒውዮርክ ብሮክስ ሁለት የሚዲያ ባልደረቦቼንና አንድ ወዳጄን አስከትዬ መንግስት በሰጣት ቤቷ ተገኝተን ተጨዎወትን ለሚወዳት ህዝብም በቪዲዮ መልክት አስተላልፋለች ፡ሆኖም በተለያየ ምክንያት እስክ አሁን ያለቀኩትን ቪዲዮ ከነምክንያቱና ተጨማሪ መረጃ ጋር የማጋራችሁ ይሆናል ።

ዛሬም ድረስ ጂጂ ወደ ሀገሯ ልትገባ ነው እየተባለ የሚነገረው ሁሉ ከሀቅ የራቀ ሲሆን ያለችበት ሁኔታ ህዝብ እንዳያቀው የሚደረገው ሴራም እጅግ ያሳዝናል።

ጂጂ ካለችበት የህይወት ጥልፍልፍ ወጥታ የምናይበት ቀን እንዲመጣ እግዚአብሔር ይርዳን።

ዶ/ር   ትማፀናችኋለች‼️  #ሼር አድርጉ🙏ትላንት መስከረም 10 ከሚኒሊክ ወደ መገናኛ በሚሄድ ታክሲ ውስጥ ሆና መውረጃዋ ሲደርስ መልስ ከሹፌር ተቀብላ በጣም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎቿን ግን ...
09/24/2024

ዶ/ር ትማፀናችኋለች‼️ #ሼር አድርጉ🙏

ትላንት መስከረም 10 ከሚኒሊክ ወደ መገናኛ በሚሄድ ታክሲ ውስጥ ሆና መውረጃዋ ሲደርስ መልስ ከሹፌር ተቀብላ በጣም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎቿን ግን ወንበሩ ላይ ትታ ወርዳለች😭በፕላስቲክ ፋይል መያዣ ውስጥ ሙሉ የትምህርት ማስረጃና የህክምና ፍቃድ ዶክመንቷን ጥላለች!! በጣም ተጨንቃለች‼️ #ሼር በማድረግ እናግዛት🙏

የታክሲው ምልክት ሠማያዊና ነጭ ቅብ የተቀባ ሲሆን ሹፌሩም ቀይ ቲሸርት የለበሰ ጎልማሳና ፀጉሩ ትንሽ ገባ ያለ ነው።

"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0947900060
0975018722

"ንቅለ ተከላው ተሳክቷል"እንኳን ደስ ያላችሁ ሐኒቾ እና ቢኒ❤🙏ሰው ለ እህት፣ ለወንድሙ ኩላሊቱን ለመስጠት በሚሰስትበት በዚህ ዘመን ኩላሊቷን ለባሏ ነቅላ የሰጠች የእውነተኛ ፍቅር ምሳሌየገባ...
09/23/2024

"ንቅለ ተከላው ተሳክቷል"
እንኳን ደስ ያላችሁ ሐኒቾ እና ቢኒ❤🙏

ሰው ለ እህት፣ ለወንድሙ ኩላሊቱን ለመስጠት በሚሰስትበት በዚህ ዘመን ኩላሊቷን ለባሏ ነቅላ የሰጠች የእውነተኛ ፍቅር ምሳሌ
የገባችውን ቃልኪዳን በተግባር ያሳየች ድንቅ ሴት♥

" ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 31:10)

ለ11 ዓመታት ዲያሌሲስ ሲያደርግ የነበረው ቢኒያም ከባለቤቱ ሙሉ ሴት ሀና አንዱ ኩላሊት ሰጥታ ንቅለ ተከላውም ተሳክቶ በሰይፉ ebs ቀርበው ደስታቸውን ገልፀዋል!

ከፍቷል ዘመኑ ......ተጠንቀቁ ‼️ አፍዝ አደንዝዝ በ2017 በሌላ ሿሿ Style  ቀጥሏል❗️ ዛሬ አጎና አካባቢ ሌቦች ለዚህች እህታችን ፌክ ሎተሪ ያሳዩአትና ሎተሪ ደርሶን መታወቂያ ስለሌ...
09/17/2024

ከፍቷል ዘመኑ ......ተጠንቀቁ ‼️
አፍዝ አደንዝዝ በ2017 በሌላ ሿሿ Style ቀጥሏል❗️

ዛሬ አጎና አካባቢ ሌቦች ለዚህች እህታችን ፌክ ሎተሪ ያሳዩአትና ሎተሪ ደርሶን መታወቂያ ስለሌለን አውጪልን እና ለመተማመኛ የሚሆን ሞባይሏን እና ተጨማሪ 11,000 ብር ከባንክ አውጥታ ሰጥታቸው እነሱም ሸውደዋት ትተዋት ሄደዋል። እና ሌቦች በፌክ ሎተሪ መታወቂያ ስለሌለን ነው ብር አውጡልን ብር እንስጣችኋለን እያሉ የያዙትን ገንዘብ እና ሞባይል አጭበርብረው እየወስዱ ይገኛል::

ሼር አድርጉት ለሌሎችም ማስተማሪያ ይሆናል::
በስንታየሁ ከስፍራው

ስንት ወንጀለኛ በለበት ሀገር የራሱን ሕዝብ የሚጨፈጭፍ መሪ በለበት ሀገር  ምንም የማያቁ ወጣቶች ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ መጠቀምያ ቢደረጉ ምንም የሚገርም አደለም። ፍትህ በሌለበት ሀገር ፍትህ ...
09/17/2024

ስንት ወንጀለኛ በለበት ሀገር የራሱን ሕዝብ የሚጨፈጭፍ መሪ በለበት ሀገር ምንም የማያቁ ወጣቶች ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ መጠቀምያ ቢደረጉ ምንም የሚገርም አደለም። ፍትህ በሌለበት ሀገር ፍትህ መጠበቅ ጅልነት ነው።

🌼አባትና ልጅሶፎኒያስ ሞላልኝ የፕሮቴስታንት ፓስተርመምሬ ሞላልኝ የኦርቶዶክስ ሐይማኖት አባት
09/16/2024

🌼አባትና ልጅ
ሶፎኒያስ ሞላልኝ የፕሮቴስታንት ፓስተር
መምሬ ሞላልኝ የኦርቶዶክስ ሐይማኖት አባት

1ኛ ቆሮ 6 ÷ 10
09/16/2024

1ኛ ቆሮ 6 ÷ 10

Address

5707 Foothills Boulevard
Oakland, CA
694601

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanual Gebremariam Yfter posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amanual Gebremariam Yfter:

Share