03/24/2024
የማይሰበረው ጎጃም!
==============
ጀግናውን የጎጃምን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ከ80,000 በላይ የመከላከያ ሰራዊት: አየር ወለድ: የብአዴን ልዩ ኃይል ወዘተ ተመድቦበት እንዲጨፈጨፍ እየተደረገ ነው ነገር ግን ጀግናው የጎጃም ህዝብ ለክብሩ እየተዋደቀ ይገኛል::
የእስካሁኑ ጭፍጨፋቸው አልበቃቸው ብሎ ተጨማሪ አንድ ዕዝ ወደ ጎጃም እንዲገባ ተጠይቋል::
የጎጃምን ህዝብ መቋቋም ያቃተው የአብይ አህመድ ወራሪ መንጋ የማዕከላዊ ዕዝ ወደ ጎጃም እንዲገባ ጠይቋል::
እስካሁን ድረስ ጎጃም ውስጥ
ምስራቅ ዕዝ (መሃመድ ተሰማ)
ምዕራብ ዕዝ (መሰለ መሰረት)
ስሜን ምዕራብ ዕዝ (ብርሃኑ በቀለ)
6ኛው ዕዝ (ብርሃኑ ጥላሁን)
2 ኮሜንዶ ክፍለ ጦር(ታደሰ ሌባቦ)
4 የብአዴን አድማ ብተና ክፍለ ጦር (ኮሎኔል ጌታቸው) ተሰማርቶ የጎጃምን ህዝብ እየወጋው ነው::
አሁን ላይ በሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ የሚመራው ማዕከላዊ ዕዝም ጎጃም ውስጥ እንዲገባ ተጠይቋል