Ethio Beteseb Media

Ethio Beteseb Media ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ እንዲሁም ወቅታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃን የሚያደርስ ሚዲያ ነው ።
501(c)(3) Registered
(5)

✏በሲያትል የነበረን ጉባዔ 🙏"ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን "                              ፪ኛ ቆሮ ፱፥፲፭👉በቅድሚያ በጉዞዬ ሁሉ ከፊት ቀድሞ የረዳኝን ፈጣሪ ...
12/04/2024

✏በሲያትል የነበረን ጉባዔ

🙏"ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን "
፪ኛ ቆሮ ፱፥፲፭

👉በቅድሚያ በጉዞዬ ሁሉ ከፊት ቀድሞ የረዳኝን ፈጣሪ አመሰግናለሁ ፣ በሰዎች ተወዶ ፣ በሰው ፊት ቆሞ ሞገስ ማግኘት ስጦታው ከላይ ካልሆነ በቀር ለማንም አይቻለውና ፣ ሞገስ የሆነኝን ጌታ ከልቤ አመሰግናለሁ ።

👉ይህ ጉባዔ ከዚህ ቀደሙ ለየት የሚያደርገው የዖዛ ስብራት መጽሐፍ ምንም እንኳን በምኖርበት ስቴት ቀድሞ ቢመረቅም ፣ በሲያትል በሚገኙ የልብ አባቶቼ እና ወንድሞቼ መልካም ፈቃድ በድጋሚ በሲያትል ስቴት እንዲመረቅ በተያዘው መርሀግብር ላይ መቼም የማልረሳውን ልዩ ፍቅር ያሳዩን አባቶቼ እና ወንድሞቼ ፦

♣ መምህር ሱራፌል ወንድሙ እና መጋቤ ምስጢር ቀሲስ ሙሉቀን ታዬ ፦ለዚህ መርሃግብር መከናወን የሀሳቡ አመኒጪ እና ባለቤቶች ጊዜአቸውን እና ገንዘባቸውን አውጥተው በሲያትል የሚገኙ አባቶች ካህናት እና ምዕመናናን በማስተባበር ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ላደረጋችሁት ታላቅ አገልግሎት አባቶቼ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ፣ ከልቤ አመሰግናሁ።

♣ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ወንድፍራው
የደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ፦ የደብሩን ሰበካ ጉባዔ አባላቱን በማስተባበር የጉባዔውን ቦታ (አዳራሹን) በማስፈቀድ እና ከዋዜማው ጀምሮ በማመቻቸት ፣ አዳራሹን በደብሩ ቅን አገልጋልዮች በማስዋብ ፣ የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን እና ምዕመናኑን በማስተባበር በልዩ መስተንግዶ ልባዊ ፍቅሮን ላሳዩን አባት እና ወንድም ምስጋናዬ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፣ ፈጣሪ በዕድሜ በጤና ይጠብቅልኝ ፣ ደብሩን እግዚአብሔር ያስፋልን።

♣ ዲያቆን መስፍን እና ቤተሰቡ በእውነት የልብ ወንድም ፣ ከነመላ ቤተሰቡ ጊዜውን እና ገንዘቡን ሰጥቶ እኔንም ፣ በዚህ ጉባዔ ላይ የወንድምነታቸው ፍቅር ሊገልጹ ከተለያዩ ስቴት የመጡ እንግዶቼን ጭምር ፣ ከኤርፖርት ከመቀበል እከ መሸኘት ድረስ በልዩ መስተንግዶ እና ማረፊያ አዘጋጅቶ ከነማላው ቤተሰቡ ላሳዩን ልዩ ቤተሰባዊ ፍቅር ምስጋናዬ ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል ፦ ብቻ እግዚአብሔር የልብህን መሻት ፈጣሪ ይፈጽምልህ ፣ ልጆችህን ከክፉ ነገር ሁሉ ፈጣሪ ይሰውርልህ፦ ወንድሜ ሌላ ምን እላለው ከመላው ቤተስብህ እወድሀለው ••• 🙏

♣ በዚህ መርሀግብር ላይ ከተለያየ ስቴት እና ከሲያትል ከተማ ውጭ ለምትኖሩ አባቶቼ ካህናት በጉባዔው ላይ ተገኝታችሁ ከጎኔ ለቆማችሁ ፦ ሊቀ ብርሃናት ቀሲስ ሔኖክ ያሬድ ( ከሜኒሶታ ) ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ ወንደሰን ( ከላስቬጋስ ) እና መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ ቴዎድሮስ ( ከኦሪገን) ገንዘባችሁን እና ጊዜአችሁን ሰውታችሁ ታላቁን የወንድምነት የፍቅር ጥግ ላሳያችሁኝ በእውነት እግዚአብሔር ያክብርልኝ ፣ አባቶቼ እንዳከበራችሁኝ እግዚአብሔር ያክብራችሁ ከልቤ አመሰግናለው ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ ወንደሰን በተፈጠረው የአሮፕላን መዘግኘት በርካታ ሰዓታትን ተንገላተው በመጨረሻም ዋጋ ከፍለው በመገኘቶ ከልብ አመሰግናለው ።

♣ ብዙ መስዋዕትነት ከፍላችሁ በጉባዔው ላይ ለተገኛችሁ እጅግ በጣም ለምወዳችሁ እና ለማከብራችሁ ካህናት ፦ መልአከ ስብስሐት ዐብይ ሥልጣን ፣ መምህር ዳንኤል ግርማ ፣ ሊቀ ስዮማን ቀሲስ ግሩም እና ቀሲስ ታዬ እግዚአብሔር በዕድሜ በጤና ይጠብቅልኝ እጅግ በጣም አከብራችኃለው ፣ ከልቤ አመሰግናለሁ ፦

♣ በብዙ የአገልግሎት ድካም በጉባዔው ላይ መገኘት ላልቻላችሁ ፣ ለደወላችሁልኝም፣ ላልደወላችሁልኝም አባቶቼ መነኮሳት ፣ ካህናት እና ዲያቆናት በጉባዔው ለመገኘት ስለተመቻቸላችሁ እንደሆነ ፍፁም በማመን ምስጋናዬ እና አክብሮቴ ዛሬም ከፍ ያለ ነው ፣ የሲያትል ማኅበረ ካህናት እወዳችኃለው።

♣ ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ካስተዋወቀኝ ቤተሰቦች መካከል ፍቅርተ ማርያም እና ብርሃነ ሥላሴ በብዙዎች የተወደዱ፣ ቅን ቤተሰቦች በፍቅር ተቀብለው ስላስተናገዱኝ ፣ በጉባዔውም ለተሳተፉ ዕድምተኞች የራት ግብዣ በማዘጋጀት ፣ የዖዛ ስብራት መጽሐፍን የአንዱን መጽሐፍ ዋጋ በ$2,000 ዳላር በመግዛት ልባዊ ፍቅራቸው ለሰጡኝ ቤተሰቦቼ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ፣ የልባችሁን መሻት ፈጣሪ ይሙላላችሁ ፣ ልጆቻችሁን በጥበብ በሞገስ ያሳድግላችሁ ፣ በጎደለው ሁሉ ፈጣሪ ይሙላላችሁ ፣ ከልቤ አመሰግናለሁ፣ እወዳችኃለው 🙏

♣ ከጠዋቱ የቅዳሴ እና የወንጌል አገልግሎት ጀምሮ እስከ ማታው ጉባዔ ድረስ ለተገኛችሁ የደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ምዕመናን እና ጥሪውን ሰምታችሁ ከተለያዩ አጥብያ ቤተክርስቲያን በዕለቱ በነበረው መርሀግብር ላይ ለተገኛችሁ ምዕመናን በሙሉ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ፣ በዕድሜ በጤና ፈጣሪ ይጠብቅልኝ ተባረኩ ።

♣ ከጠዋቱ መርኃ ግብር ጀምሮ በእውነት ያተለየኝ ወንድሜ አሹ ቪዲዮ እና ፎቶ በማንሳት አገልግሎት ለሰጠኝ ክብር ይስጥልኝ ፣ እግዚአብሔር ያክብርልኝ ፀጋውን ያብዛልህ ተባረክ። በሲያትል ለተለያዩ ዝግጅቶች ቪዲዮ እና ፎቶ ከፈለጋችሁ ምርጫችሁ 👇
AShu Video 206 422 7364 ይሁን ‼

መጋቤ ጥበብ ቀሲስ ሳሙኤል ግዛው

✏ የፓለቲካ ስብራትን ...👉ለሀገር  ስብራት ዋናውን ድርሻ የሚወሰደው የብልፅግና ፓርቲ ዛሬ የፓለቲካ ስብራትን እንጠግን እያለ ነው ፣ 👉በነገራችን ላይ የዖዛ ስብራት መጽሐፍ የሀገር ስብራት...
11/30/2024

✏ የፓለቲካ ስብራትን ...

👉ለሀገር ስብራት ዋናውን ድርሻ የሚወሰደው የብልፅግና ፓርቲ ዛሬ የፓለቲካ ስብራትን እንጠግን እያለ ነው ፣

👉በነገራችን ላይ የዖዛ ስብራት መጽሐፍ የሀገር ስብራትንን እና በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ስብራት በጥልቀት በመረጃ ያትታል ፣ የመፍትሔ ሀሳብንም ይጠቁማል ፣

👉 ነገ በስያትል ይመረቃል ልዩ ጉባዔ ተዘጋጅቷል ፣ ሲያትሎች እንዳትቀሩ

✏ምን ያስደንቃል .. ! 👉ይኽ ይሆን ዘንድ ግድ ነው ።  ገና በአዳራሻቸው ቆሞ ሊሰብክ ይችላል ። የሚገርመው ግን የእኛ ጉዶች ( ጳጳሳት እና ምንደኞች )  ይህንን ኅሊናውን የሸጠ ፣ ማንነ...
11/30/2024

✏ምን ያስደንቃል .. !

👉ይኽ ይሆን ዘንድ ግድ ነው ። ገና በአዳራሻቸው ቆሞ ሊሰብክ ይችላል ። የሚገርመው ግን የእኛ ጉዶች ( ጳጳሳት እና ምንደኞች ) ይህንን ኅሊናውን የሸጠ ፣ ማንነቱን የካዳ፣ ክፋቱ እና ነውሩ በብዙዎች እንዲጠላ ያደረገውን ይሁዳ "ዲያቆን" ብለው ዛሬም መጥራታቸው ብቻ ያስገርማል 😭 ።

ሲያትል ገብተናል ነገ እንገናኝ ቤተሰቦች ልዩ ጉባዔ እና የዖዛ ስብራት መጽሐፍ ምርቃት በሲያትል አድራሻው ፖስተሩ ላይ አለ👇

✏  "ታቦተ ጽዮን" ሕዳር ጽዮን  √"ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፣ የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው" ፡፡👉ታላቁ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ሰቆቃወ ድንግል ...
11/30/2024

✏ "ታቦተ ጽዮን" ሕዳር ጽዮን

√"ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፣
የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው" ፡፡

👉ታላቁ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጽጌ ድንግል ሰቆቃወ ድንግል በተባለው ድርሰቱ ፦

👉ፍህም የተሸከመች የወርቅ ማዕጠንት🙏

√ድንግል ሆይ ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍህም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ ። ፍህም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው፤ ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው ።√ (ቅዱስ ኤፍሬም)

👉እንኳን ለጽዮን ማርያም የተዋሕዶ ልጆች በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🙏

✏ዛሬም ያልቆመው የግፍ ግድያ 👉በሸርካ ወረዳ 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ !በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 ኦ...
11/29/2024

✏ዛሬም ያልቆመው የግፍ ግድያ

👉በሸርካ ወረዳ 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ !

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል፡፡

ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ማምለጣቸውን የገለጹት መረጃ ሰጭው የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ኗሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በርካታ የአካባቢው ምእመናን ከአካባቢው የሸሹ መሆኑን ያነሱት መረጃ ሰጭው ሰው ተወልዶ ባደገበት ሀገር በሃይማኖቱ ምክንያት እየተገደለ ነው ያሉ ሲሆን ሀብት ንብረታችንን ጥለን የምንኖርበት ሀገር ስለሌለን ከምድረ ገጽ እንድንጠፋ ተፈርዶብናል ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት የተዘጉ ሲሆን አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በስደት ላይ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡

በመጨረሻም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ወረዳ 140 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን ገልጸው መላው የዓለም ሕዝብና ኦርቶዶክሳውያን ሞታችንን ባታስቆሙልን እንኳን የነዚህን ሰማዕታት ምስክርነት በማሳወቅ የድርሻችሁን ተወጡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው

11/28/2024

ተመልሰናል_እንዴት እንቀበላቸው ...? // ቆይታ ከዘመዴ ጋር # ethiobetesebmedia

11/27/2024

ማድረግ የሌለብን ነገር? // በThanksgiving በዓል

የፊታችን እሁድ በሲያትል ከተማ
11/26/2024

የፊታችን እሁድ በሲያትል ከተማ

11/26/2024

ከምንኩስና እስከ ጵጵስና
አወዛጋቢው ? // ቆይታ ከሊቀ ካህናት ታደሰ ጋር

11/25/2024

✏ሰሞነኛው አጀንዳ

👉ከተሐድሶነት ( ከክህደቴ) ከሱሑት አስተምህሮ ወደ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተመልሻለው !

👉በዚህ የማይደሰት የለም እኛም መልአክትም ብሎም ቅድስት ቤተክርስቲያን ግን የሰሞነኛው አጀንዳ ተመልሻለው ካሉ በኃላ ድሮም አልነበርኩም ባዮች እየተበራከቱ ነው ?

👉ለምን እንዲህ ሆነ ብለን ስናይ አብዛኞቹ ተመልሻለው በምን በሚዲያ? ምን አግኝተው ወጡ ፣ምን ይዘው ተመለሱ? እንዴትስ ነው አመላለሱ ? እውን መመለሱ ከልብ ጸጸት እንደጠፋው ልጅ ?
የብዙዎች ጥያቄ ••• ?

👉በዚህ ጉዳዮች ላይ በጥልቅ መሰራት አለበት ፣ ለሚዲያ ግብዓት ብቻ ከሆነ አፍ ቢናገር ልብ ካልተቀየረ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላል ።

ለበለጠ መረጃ ቤተሰብ ይሁኑ
https://t.me/ethiobeteseb

11/20/2024

ከባዱ ፈተና በውጭ ሀገር // የወላጅ ምኞት? የልጆች ፍላጎት?

✏Tomorrow is last day! 👉Only 1 days are left to register for our 10 Commandments Class!To register visit:https://www.yib...
11/19/2024

✏Tomorrow is last day!

👉Only 1 days are left to register for our 10 Commandments Class!

To register visit:
https://www.yibel.org/courses/the-ten-commandments

This unique class is designed to provide your child with a deeper understanding of the Ten Commandments, not just as spiritual teachings, but as guiding principles they can apply in their daily lives—especially as they navigate challenges at school.

We’ll explore topics like:

Building integrity and character.
Handling peer pressure.
Balancing respect for authority with self-expression.
Our goal is to help students ages 9-16 see how the lessons of the 10 Commandments can empower them to make thoughtful, positive choices in their academic and spiritual lives.

We look forward to welcoming your child into this enriching experience!

This course will cover the events surrounding the Ten Commandments, with a focus on the contents of each commandment. Each week, one commandment will be examined and connected to our daily lives.

የገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በዕለተ ቀኑ 👇
11/16/2024

የገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በዕለተ ቀኑ 👇

11/14/2024

ከአህያው ሥጋ ባሻጋር_አደገኛው መርዝ?
ቆይታ ከዘመዴ ጋር # ethiobeteseb

Address

Maryland City, MD
20876

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Beteseb Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Beteseb Media:

Videos

Share


Other Social Media Agencies in Maryland City

Show All