Ermiyas Girma - ዘማሪ

Ermiyas Girma - ዘማሪ "እኔ ታናሽና የተናቅሁ ነኝ ትእዛዛትህን ግን አልረሳሁም"
መዝ:- 118 - 141

ለአገልግሎት የምትጋብዙት መምህራን ዘማርያን አገልጋዮች ከእኔ በላይ ልትገልጹት ትችላላችሁ ..!በጣም ትሑት ነው የተረጋጋ ነው ሰው አክባሪ ነው ይኽንን አውቃለሁ ደግሞም ፈሪሐ እግዚአብሔር እ...
01/02/2025

ለአገልግሎት የምትጋብዙት መምህራን ዘማርያን አገልጋዮች ከእኔ በላይ ልትገልጹት ትችላላችሁ ..!

በጣም ትሑት ነው
የተረጋጋ ነው
ሰው አክባሪ ነው ይኽንን አውቃለሁ
ደግሞም ፈሪሐ እግዚአብሔር እና
ፍቅረ ቤተ ክርስቲያን እንዳለውም እረዳለሁ...!
“አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች (ግብዝነት በሌለው ፍቅር) ራሳችን እናማጥናለን”
(፪ኛ ቆሮንቶስ ፮፥፫)
በማለት እውነተኛ ፍጹም ፍቅር ከግብዝነት በነጻ ሕይወት ኑሮ የሠመረ አገልግሎት በምድር ፈጽሞ በሰማይም እንዲቀጥል ለወንድሜ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ከልቤ እመኝለታለሁ ..🙏

የተወደዳችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን በዕለቱ በመገኘት በዝማሬ እግዚአብሔርን አክብሩ ..!!
"ዐዲስ ቅኔም ተቀኙለት በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ"
(መዝሙር . ፴፪ - ፫)

👉"እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ" ኢሳ. 40፥31👉"በዚህችም ዕለት [ታኅሣሥ 24] የተመሰገነና የከበረ አዲስ ሐዋርያ አባታችን ተክ...
01/02/2025

👉"እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ" ኢሳ. 40፥31

👉"በዚህችም ዕለት [ታኅሣሥ 24] የተመሰገነና የከበረ አዲስ ሐዋርያ አባታችን ተክለ ሃይማኖት ተወለደ፤ በጸሎቱ የምትገኝ በረከቱ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን።" - ስንክሳር ዘታኅሣሥ 24 ቁጥር 49

#ለአቡነ #ጌታችንና #አምላካችን #መድኃኒታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #የሰጣቸው #ቃል #ኪዳን

#የጻድቅ #ሰው #ጸሎት #በሥራዋ #እጅግ #ኃይል #ታደርጋለች (ያዕ.5፥16)

“ክቡር አባታችንንም ፈጣሪው እንዲህ አለው፤ ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ እንዴት አለህ፤ ከድካምና ከኃዘን ወደ ዘላለም ድሎትና ወደ ዘላለም ዕረፍት ከባርነት ወደ ነጻነት ላወጣህ ወዳንተ መጣሁ፤ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ስምህንም ለሚጠራ ሰው ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምረዋለሁ ብዬ በእውነት እነግርሃለሁ።

ቤትህንም ለሠራ በሰማይ የመንግሥት ቤት እኔ እሠራለታለሁ፤ የገድልህንም መጽሐፍ ለጻፈ አንተን በመታመንም ላጻፈው በሰማይ በሕይወት መጽሐፍ ስማቸውን እኔ እጽፋለሁ።

በስምህ እንግዳ የተቀበለውን እንግዳ ሆኖ ወደኔ በመጣ ጊዜ እኔ እቀበለዋለሁ በቤቴም ጥላ አሳርፈዋለሁ፤ በስምህ የተራበውን ላጸገበ የሕይወትን እንጀራ እኔ አጠግበዋለሁ በስምህ ለተጠሙት ያጠጣውንም ከጎኔ ከፈሰሰው ደም ምንጭ እኔ አጠጣዋለሁ።

ደስ ብሎት በዓልህን ያከበረውን ሁሉ በሽሁ ዓመት ምሳ ካንተ ጋራ እኔ አስቀምጠዋለሁ፤ በስምህ የታረዘውን ለአለበሰ ላንቃ የሚባለውን የብርሃን ግምጃ እኔ አለብሰዋለሁ ለቤተ ክርስቲያንህም ነጭ ዕጣን የሚያገባውን እኔ ጸሎቱን እሰማዋለሁ ኃጢአቱንም ይቅር እለዋለሁ።

ከዚህ ሁሉ ደሀ የሆነ ሰው ቢኖር በመታሰቢያህ ቀን አዘንተኛውን ቢያጸና ድውዩንም ቢጠይቅ በሆነም ሆኖ ቢያገለግል ቅጠል መቁረጥም ቢሆን ዕንጨት በመፍለጥ ውኃ በመቅዳትም ቢሆን በዚህ ሁሉ ቢረዳ እኔ በመንግሥተ ሰማያት አበቃዋለሁ።

ከሩቅም ከቅርብም ቢመጣ ወደ መቃብርህ የሄደውን እኔ ወደ መቃብሬ ኢየሩሳሌም እንደሄደ አደርገዋለሁ፤ በመታሰቢያህ ቀን ሥጋውን ደሙን የተቀበለውንም ስማቸው ከተጠራው ገድላቸው ከተነገረው ልጆችህ ጋራ እኔ እቆጥረዋለሁ።

ሥጋውን ደሙን ባይቀበል ከመታሰቢያህ ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ቢበላ እኔ ኢየሱስ ቃሌ የማያብለው በሰማያዊት ኢየሩሳሌም በባለሟልነት መቍረብን እሰጠዋለሁ ስለ ሃይማኖቱም በመንግሥተ ሰማያት ካንተ ጋራ አኖረዋለሁ።

አንተ ከተቀበርክበት ቤተ ክርስቲያንህም በታነጸበት ቦታ የተቀበረ ሁሉ በኔ ዘንድ አይጎዳም ገሃነመ እሳትንም ከቶ አያይም ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈውም ሁሉ በቦታህ አይቀበርም ከጉር እስከ ሸምን ወንዝ የተቀበረውንም ሁሉ ምሬልሃለሁ ላንተም ለዘላለም መታሰቢያ ይሆንልህ ዘንድ ቃል ኪዳን ሰጠሁህ። .........

ጌታዬ አሁንም ልጆቼ በዓለም ሁሉ ስምህ በተጠራበት የኔም የባሪያህ የኃጢአተኛው ባሪያህ ስም በተጠራበት መታሰቢያዬን የሚያደርጉትን አስባቸው እንደባሕር ዳር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ ልጆችህን አበዛቸዋለሁ ስላልከኝ ሥጋዬ የሚቀበርበት ቦታ ሆኖ አይበቃቸውምና።

ከመቃብሬ መንፈስ ቅዱስ አይለይ እስከ ዘላለምም በአጥንቴ ላይ ድንቅ ተአምራትህ ይታይ በእውነት እስከ ዘላለም ፍጹም ምስጋና ለአንተ ነውና አለ፤ ጌታም መለሰ ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ እውነት እልሃለሁ ሁሉ እንዳልከው ይሁንልህ።”

ምንጭ፦
ገድለ ተክለሃይማኖት፤ ገጽ 193-194 ምዕራፍ 57 ቁጥር 5-12 ፣ ገጽ 212 ምዕራፍ 64 ቁጥር 9-10፤ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1989ዓ.ም፤ አዲስ አበባ

“ክርስቲያኖች እዚህ (በምድር) መላእክትን ከሆኑ፤ ካረፉ በኋላማ እንዴት ይሆኑ?! እንግዳ በሆኑባት ዓለም እንዲህ እጅጉን ካበሩ፤ የገዛ ሃገራቸውን ሲቀዳጁማ እንዴት ታላቅ ይሆኑ!”
- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

01/01/2025

-ደብር ቅድስት ሥላሴ ሊመረቅ 12 ቀናት ናቸው የቀሩት ጥቂት ነገሮች ይቀሩናል የሥላሴ ልጆች እባካችሁ ..🙏

👉 የደብር ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በምታዩት መልኩ በዕናንተ እርዳታ እዚህ ደረጃ ደርሷል ቸሩ አምላካችን ቅድስት ሥላሴ ቅዱስ ስሙ ይክበር ይመስገን

👉 ይህ ቤተክርስቲያን በሰሜን ወሎ ሐገረ ሥብከት በጋዞ ወረዳ በ08 ቀበሌ የሚገኝ ነው

👉ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000522352757
yedebir silasie betekirstian hintsa maseria

01/01/2025
👉"እግዚአብሔርም . . . ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም። እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።" ሐዋ.13፥21-22...
12/31/2024

👉"እግዚአብሔርም . . . ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም። እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ አለ።" ሐዋ.13፥21-22/መዝ. 88(89)፥20

👉"በዚህችም ቀን [ታኅሣሥ 23] የእሴይ ልጅ ዳዊት ንጉሥ አረፈ ይህም ከብንያም ነገድ የቂስ ልጅ ሳኦል ከነገሠ በኋላ በእስራኤል ላይ የነገሠ ነው።" - ስንክሳር ዘታኅሣሥ 23 ቁጥር 10

👉"በዚህችም ቀን [ ዘታኅሣሥ 21] በበግ እረኛ አምሳል መድኃኒታችን የተገለጸበት ነው፤ ለእርሱም ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።" ስንክሳር ዘታኅሣሥ 21 ቁጥር 14መዝሙረ ዳዊት 231 እግ...
12/30/2024

👉"በዚህችም ቀን [ ዘታኅሣሥ 21] በበግ እረኛ አምሳል መድኃኒታችን የተገለጸበት ነው፤ ለእርሱም ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።" ስንክሳር ዘታኅሣሥ 21 ቁጥር 14

መዝሙረ ዳዊት 23
1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።

2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።

3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።

4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

5 በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።

6 ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

የዮሐንስ ወንጌል 10፥
11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።

12 እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል።

13 ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።

14-15 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።

16 ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።

የአምላክ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ👉"በሰውና መላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ። በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ። ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ። ከ...
12/29/2024

የአምላክ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ

👉"በሰውና መላእክት ጉባኤ መሐከል ራቁቴን መቆሜን አሰብሁ። በዓይነ ልቡናዬ እመለከት ዘንድ ወዲህና ወዲያ ተመላለስሁ። ምናልባት የሚረዳኝ ባገኝ። ከዚህ እጅግ የሚያስፈራው ከሠራሁት ኃጢአት ፍዳ የተነሣ ምናልባት የሚዋሰኝ ባገኝ ብዬ። ነገር ግን በማማለድ እኔን ለማዳን የምትቸይውን አንቺን አማላጅ አገኘሁ። ዘወትርም ከኔ እንዳትርቂ ዐወቅሁ። እንዲህ በፍቅር ያዝሁሽ በጣቶቼ አይደለም በሃይማኖት ያዝሁሽ በመዳሰስ አይደለም በእደ ሕሊና ያዝሁሽ በእደ ሥጋ አይደለም። እደ ሕሊናየን ግን የሰው ኃይለኝነት ሊያስተወው አይችልምና። የሰይፍ ስለትም ሊቆርጠው አይችልም። ልትደገፊኝ ያዝሁሽ ልትጥይኝ ግን አይደለም ወደላይ ከፍ ከፍ ልታደርጊኝ ያዝሁሽ ወደ ታች ልታወርጅኝ ግን አይደለም። ለዘለዓለሙ ያዝሁሽ ለዕድሜ ልክ ብቻ አይደለም። እናቴ ሆይ ነፍሴ ባንቺ ዘንድ ትክበር ስለቸርነትሽም እመቤቴ ነሽ። ስለ ፍቅርሽ የታመንሽ ስለ ልጅሽም የመድኃኒት ቀንድ ሆይ አስቢኝ እንደ ወደቅሁም እቀር ዘንድ አትርሺኝ።"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ
አርጋኖን ዘሠሉስ ፩፥፯-፲፪

👉"በኋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ፥ ባልንጀሮችዋንም ወደ አንተ ያቀርባሉ፤ በደስታና በሐሴት ይወስዱአቸዋል፥ ወደ ንጉሥ እልፍኝም ያስገቡአቸዋል።"
መዝ. ፵፬፥፲፬-፲፭

12/28/2024

ዓመለ ሸጋ ነው የቅኔ የድጓ መምህር ነው ደግሞም የቲዎሎጂ ምሩቅ ነው በሚገባ በግሌ የማውቀው የምመሠክርለት ወንድም ታሟል..!!
ስለ ቅዱስ ገብርኤል እኔ ወንድማችሁ ኤርምያስ ግርማ ዝቅ ብዬ እለምናችኋለሁ አንድ የቤተ ክርስቲያን
መምህር እናተርፍ ዘነድ አደራ ለማለት እወዳለሁ ..🙏🙏🙏

መምህር ሙሉጌታ ዘወዱን ማግኘት የምትፈልጉ - 0920231064
0920108466

ድጋፍ ለማድረግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ
1000179608956

12/27/2024

የብሥራተ ገብርኤል የግእዝ መዝሙራት ስብስብ በዲ.ን ኤስሮም ተሾመ ፤ ዲ.ን ሳሙኤል ሠረጎወርቅ ፤ ዲ.ን ጸጋ ሥላሴ እና ዲ.ን በአምላክ ይልማ👇🏼የተካተቱ መዝሙራት00:00 ፩-ሃሌ ሉያ እንዘ ትፈ...

👉"ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ"              ዳን. 9፥21👉"ታኅሣሥ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው እርሱም በባቢሎን ሀ...
12/27/2024

👉"ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ"
ዳን. 9፥21

👉"ታኅሣሥ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን የመላእክት አለቃ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው እርሱም በባቢሎን ሀገር ከነደደ እሳት ውስጥ በጨመሩአቸው ጊዜ አናንያን አዛርያን ሚሳኤልን ያዳናቸው ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም [በቅዱስ ገብርኤል] በአማላጅነቱ ይማረን ለዘለዓለሙ አሜን።" - ስንክሳር ዘታኅሣሥ 19 ቁጥር 1-2

ትንቢተ ዳንኤል 3
1 ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው።

2 ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፥ መጋቢዎችንም፥ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ።

3 በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፥ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፥ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፥ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ።

4 አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፦ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ፥

5 የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፥ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል።

6 ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል።

7 ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።

8 በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ።

9 ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ። ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።

10 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ። የመለከትንና የእንቢልታን፥ የመሰንቆንና የክራርን፥ የበገናንና የዋሽንትን፥ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ

11 ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ።

12 በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ ንጉሥ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም።

13 ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው።

14 ናቡከደነፆርም። ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ፥ አምላኬን አለማምለካችሁ፥ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን?

15 አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።

16 ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡንም። ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም።

17 የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ!

18 ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ አሉት።

19 የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፥ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው እርሱም ተናገረ፥ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ።

20 ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ።

21 የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ።

22 የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፥ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው።

23 እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ።

24 የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም። ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት።

25 እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ።

26 የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ። እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም፥ ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።

27 መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ።

28 ናቡከደነፆርም መልሶ፦ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።

29 እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፥ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ አለ።

30 የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው።

+++   አታስመስል      +++    ( በዲ/ን አቤል ካሳሁን ) ጌታችን ከአደገባት ናዝሬት ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቃ ያለች ሴፎሪስ (Sepphoris) የምትባል በገሊላ የምትገኝ ከተማ ...
12/26/2024

+++ አታስመስል +++
( በዲ/ን አቤል ካሳሁን )

ጌታችን ከአደገባት ናዝሬት ወደ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቃ ያለች ሴፎሪስ (Sepphoris) የምትባል በገሊላ የምትገኝ ከተማ ነበረች። ይህችም ከተማ በጣም ደማቅ በመሆኗ "የገሊላ ጌጥ" ተብላ ትጠራለች። በውስጧም ታላቅ የቴያትር አዳራሽ ነበራት። በጥንታውያን የሮምና የግሪክ ቴያትር ታሪክ ልክ እንደ ዛሬው ገጸ ባሕርይን ለመላበስ (ለመምሰል) የሚረዳ የሜካፕ ሙያ ሳይመጣ በፊት፣ ተዋናይዎቹ የኃዘንና የደስታ መልክ ያላቸውን ጭንብሎች ለብሰው ነበር የሚተውኑት። እነዚህም ጭንብሎች "persona" የሚል መጠሪያ ሲኖራቸው ትርጉሙም "ጭንብል"/"mask" ማለት ነው። (በነገራችን ላይ personality የሚለው ቃል persona or mask ከተባለው ከዚሁ ግንድ መውጣቱን ልብ ይሏል።)

የሥነ ቅርስ ተመራማሪዎችን ትኩረት ከሳቡ እና በብዛት የኀሠሣ ቁፋሮ ከሚደረግባቸው የዓለማችን ክፍሎች አንዷ ሴፎሪስ ነች። ታዲያ ጌታችን ላደገባት ናዝሬት ቅርብ በሆነች በዚህች ከተማ በተደረገ የarcheology ቁፋሮ የተለያዩ የቴያትር ጭንብሎች ተገኝተው ነበር።

ጌታችን በወንጌል ጻፎችና ፈሪሳውያንን "ግብዞች"
እያለ ይጠራቸው ነበር። ግብዝ የሚለው ቃል ደግሞ በግሪኩ "Hypocrite" የሚለው ሲሆን ትርጉሙም "ተዋናይ"/"Actor or play maker" ማለት ነው። በመሆኑም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገሩትን የማይኖሩ ነገር ግን በሰው ፊት ፍጹም መስለው ለመታየት የሚፈልጉትን አይሁድ፣ በዘመኑ በነበሩትና ጭንብል ለብሰው በሚጫወቱት የቴያትር ባለሙያዎች ስም "ተዋናይ" ብሎ መጥራቱ ያለ ምክንያት አይደለም።

ኑሮው በግልጽ የሚታወቅ እውነተኛ ሰው ቢሳሳት እንኳን ተመክሮ የመታረምና የመመለስ እድል አለው። የሚያስመስል ሰው ግን ለትምህርትና ለተግሳጽ እንኳን ያስቸግራል። እንዲሁ እንዳስመሰለም የእውነት ሳይኖር ይሞታል። ታዲያ ከዚህ ሰው በላይ ራሱን የሚበድል ከየት ይገኛል?

ጻድቅ መስሎ በሕዝብ ተከብሮ ከመኖር ይልቅ ድክመቱን ያመነ ኃጥእ ሆኖ በሰው ፊት መመላለስ ይሻላል። ፈጣሪ አንድ ቀን የኃጢአቱን ብዛት የሚቀንስለት፣ ከእሳት ነጥቆ የሚያወጣው ቸር መካሪ አያሳጣውምና።

ከአስመሳይ ጻድቅ እውነተኛ ኃጥእ ይሻላል!
አናስመስል!!!

( በዲያቆን አቤል ካሳሁን )

12/26/2024

Address

Lancaster, PA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ermiyas Girma - ዘማሪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ermiyas Girma - ዘማሪ:

Videos

Share