Balderas Tube

Balderas Tube Welcome to Balderas's Official page.

02/03/2023

ይህች የማትጠገብ መልከ መልካም እቡጥ ህፃን ከፈጣሪ በታች የመዳን ተስፋዋ በእኛ እጅ ነው።ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ የልብ ቀዶ ህክምና እንድታደርግ በህክምና ባለሙያዎች ተረጋግጦ ህክምና ለማድረግ በተደጋጋሚ የእርዳታ ጥሪ ብናደርግም እስካሁን ገንዘቡ አልሞላላትም የሚያስፈልገው ገንዘብ ከ1,300,000 እስከ 1,500,000 ሲሆን እስካሁን 600,000 ብቻ ነው የተሰበሰበው።

የመዳን ተስፋዋ ጨልሞባት የነበረችው ዮሀና ከኮርያ በመጡ የልብ ሀኪሞች በእጅጉ ተስፋዋ ለምልሞላታል።የመጀመሪያ ዙር ቀዶ ህክምና ሳልና መሰል አስቸጋሪ የነበሩ ህመሞች ቀንሶላታል።ይሁንና አሁንም ብዙ ወጭዎች ወላጆቿ በየቀኑ ያወጣሉ።ዮሀና የምትተነፍሰው በኦክስጅን ታግዛ ነው።በዛ ላይ ውድ መድሀኒቶችን በየቀኑ ትወስዳለች።የግድ በዚህ ስድስት ወር ውስጥ ሁለተኛውን ቀዶ ህክምና ማድረግ አለባት። ስለፈጠራችሁ እንተባበር ይህችን ውብ የነገ ሃገር ተረካቢ ውድ ልጅ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ።
👇👇👇

ምንም ማድርግ ባትችሉ እንኳ ሼር አድርጉ!
ማንም ግን በልጅ አይፈተን🙏🏻
👇👇👇👇👇👇
#አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000177189018-በላቸው አያልነህ(አባት)
#ስልክ
0923224494-በላቸው አያልነህ(አባት)
0988248319-አፀደማርያም ይግዛው(እናት)

02/03/2023
02/03/2023

"ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም በሕያው እና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። " 1ኛ ጴጥ፣ም 1፣23-24

"አምላካችን እስኪገለጥ በያለንበት እንፅና " እንዳለ አብሳሪው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል

ሁላችንም በፀሎት ሆነን በያለንበት ፀንተን መንፈስቅዱስ ከሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስን እንጠብቅ !! መንፈስ ቅዱስ አንድ እንደሆነ ሁሉ ቅዱስ ሲኖዶስም አንድ ነው::

01/27/2023
Wow wow.... The new king ....
12/18/2022

Wow wow.... The new king ....

10/18/2022

ህፃን ከድር መሐመድ ከሶስት ዓመት በፊት በደረሰበት ከመሰላል ላይ የመዉደቅ አደጋ የጀርባ አጥንቱ በመጎዳቱ በምታዩት መልኩ አንገቱን በእጁ እየደገፈ ነዉ የሚንቀሳቀሰዉ ። የአራት ዓመት ልጅ እያለ የደረሰበት አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎበጠዉ በመሆኑ ህፃኑ ሕክምና የሚያገኝበት መንገድ ቢመቻችለት ቀና ብሎ እንደ እድሜ እኩዮቹ መቦረቅ መጫወት መማር ይችላል ። ህፃኑን በአካል ለማግኘት የምትፈልጉ ሰዎች አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 በተለምዶ ሻንቅላ ወንዝ አዲስ በሚሰራዉ መንገድ ወይም በስልክ ቁጥር 0912985631 አቶ ስንታየሁ ዓለሙ ።

08/21/2022

 #ዜና #  ባልደራስ አገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ክልሎች ደብዳቤ ፃፈ! /ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን በአገር አቀፍ ደረጃ ለ...
03/20/2022

#ዜና

# ባልደራስ አገር አቀፍ ፓርቲ ለመሆን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ክልሎች ደብዳቤ ፃፈ!
/
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን በአገር አቀፍ ደረጃ ለመመዝገብ የሚያስችለውን ፊርማ ለማሰባሰብ ህጋዊ ድጋፍ እንዲሰጠው ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው ጥያቄ ምላሽ እንዳገኘ የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ክልሎች በፃፈው ደብዳቤ፣ የባልደራስ አባላት ፊርማ ለማሰባሰብ በክልሎች ሲንቀሳቀሱ የክልል መስተዳድሮች አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጠይቋል።

ባልደራስ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤውን የሚያደርግ ሲሆን፣በዚያ ጉባዔው በአዲስ አበባ ደረጃ ከሚንቀሳቀስ ድርጅት ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምርጫ ቦርድ የፃፈውን ደብዳቤ እታች ይመልከቱ።

#መረጃ #ትኩረት

03/17/2022

Ethiopia: የባልደራስ አመራሮች ተከለከሉ | ተረኞቹ ህዝብን መሰቃየታቸውን አጠናቅረው ቀጥለዋል |በቃ ሊባል ይገባል | Balderas | Addis Ababa

 #ትኩረት   #መረጃየሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!መጪው ሐሙስ፣ March 17 ፣ ከጠዋቱ 9 am፣ በዋሽንግተን ዲ. ሲ፣. የኢትዮጰያ ኤምባሲ ፊት ለፊት!/ #ኢትዮጵያ
03/17/2022

#ትኩረት #መረጃ

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!

መጪው ሐሙስ፣ March 17 ፣ ከጠዋቱ 9 am፣ በዋሽንግተን ዲ. ሲ፣. የኢትዮጰያ ኤምባሲ ፊት ለፊት!
/
#ኢትዮጵያ

 #ሰበር  #ዜና  # ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ በመሃል አዲስ አበባ የሚፈርሱ ቤቶች በቪዲዮ እንዳይቀረፅ ተከለከለ! # ክልከላውን የአዲስ አበባ ፖሊሶች አስፈፅመዋል!/የባልደራስ አመራሮች እስክን...
03/16/2022

#ሰበር #ዜና

# ለሽመልስ አብዲሳ ቢሮ በመሃል አዲስ አበባ የሚፈርሱ ቤቶች በቪዲዮ እንዳይቀረፅ ተከለከለ!

# ክልከላውን የአዲስ አበባ ፖሊሶች አስፈፅመዋል!
/
የባልደራስ አመራሮች እስክንድር ነጋና ስንታየሁ ቸኮል የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ለቢሮ ማስፋፊያ እያፈረሰ ባለው ሰፈር ቀረፃ እንዳያርጉ በፖሊስ ተከለከሉ፡፡

በተለምዶ ቦሌ-ፍላሚንጎ በሚባለው አካባቢ ያሉ ቤቶች ነባር ይዞታዎች፣ "ለርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ ማስፋፊያ ያስፈልጋሉ" ተብሎ በ3 ቀን ውስጥ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ተገቢውን ካሣና እና ምትክ ቦታ እስካሁን አልተሰጣቸውም፡፡

ይህን አስመልክቶ የመስክ ጉብኝት ለማድረግ የተንቀሳቀሰው የባልደራስ አመራር ቡድን፣ ቦታው ላይ እንደደረሰ በአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተከቦ ቀረፃ እንዳያደርግ ተከክልሏል፡፡

ቀረፃው ለምን እንደተከለከለ ጥያቄ አቅርቦ በፖሊሶቹ የተሰጠው ምላሽ፣ “ወደ በላይ አካል ደውለን ካላስፈቀድን ቀረፃ ማድረግ አትችሉም፡፡ እኛ ታዘን ነው፡፡ ቀረፃ እንዳይደረግ ተነግሮናል፡፡ ስለዚህም፣ ከመቅረፃችሁ በፊት የበላይ አካልን ማሳወቅ አለብን” ብለዋል፡፡ በዚህም መሠረት ወደ በላይ አካል ደውለው ካነጋገሩ በኋላ፣ ቀረፃ ማድረግ እንደማይቻል ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል፡፡

የቤት ፈረሳው ህጋዊ ከሆነ ቀረፃ የሚከለከልበት ምንም ምክንያት እንደሌለ የባልደራስ አመራሮች ተናግረዋል፡፡

እንደሚታወቀው፣

የኦሮሚያ እና የአዲስ አበባ መስተዳድሮች በቅንጅት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ ኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ አላት የሚሉትን የባለቤትነት መብት /ልዩ ጥቅም ያንሰናል እያሉ ናቸው/ አጉልተው ለማሳየት የኦሮሚያ መስተዳድር መስሪያ ቤቶችን በከተማዋ እምብርት ላይ እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ሂደትም ከመንገድ ወጣ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን እየፈረሱ እና ነባር የከተማዋ ባለ ይዞታዎች ወደ ከተማዋ ዳር እየተፈናቀሉ ይገኛሉ፡፡

በቦታው ላይ የነበረውን ሂደት በከፊል በቪዲዮ የተቀረፀ ሲሆን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይለቀቃል፡፡ ይከታተሉት፡፡
#መረጃ

03/15/2022

Breaking News : Addis Ababa

 # የባለአደራው ምክር ቤት ምሥረታ ታስቦ ዋለ! # "በአዲስ አበባ ያለው የተረኝነት መንፈስ ከመቼውምጊዜ በላይ ተባብሷል"  እስክንድር ነጋ # “በግፍ የታሰሩት በመንፈስ ከእኛ ጋር ናቸው" ...
03/12/2022

# የባለአደራው ምክር ቤት ምሥረታ ታስቦ ዋለ!

# "በአዲስ አበባ ያለው የተረኝነት መንፈስ ከመቼውምጊዜ በላይ ተባብሷል" እስክንድር ነጋ

# “በግፍ የታሰሩት በመንፈስ ከእኛ ጋር ናቸው" ስንታየሁ ቸኮል
/
መጋቢት 1 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ በባልደራስ የስብሰባ አዳራሽ የተመሠረተው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት 3 ኛ አመት ክብረ በዓል በባልደራስ ዋና ጽ/ቤት ሻማ በማብራት ታስበ፡፡ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት በኢንጀር ታከለ ኡማ የከንቲባነት ዘመን የተጀመረውን የተረኝነት አካሄድ በመቃወም መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

ህወሓትን ተክቶ ገዥውን ፓርቲ በመምራት ላይ የሚገኘው ኦህዴድ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በመደፍጠጥ ከተማዋን በሃይል የኦሮሚያ አካል የማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የከተማውን ሕዝብ መብት የባለአደራው ምክር ቤት በነበረው የሲቪክ ማህበር ቁመና ማስጠበቅ የማይቻል ስለነበር፣ በሕዝቡ ጥያቄ በየካቲት 2012 ዓ.ም ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሆኖ መወለዱ ይታወሳል፡፡

ትላንት በነበረው ሥነ ስርዓት የታደሙት የባልደራስ አባላት፣ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙትን እህትና ወንድሞቻቸውን በማስታወስ፣ በግፍ መታሰራቸውን ጠቅሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እስከሚፈቱ ድረስ ያላሰለሰ ትግላቸውን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ያለው የተረኝነት እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተባብሶ እንደሚገኝ የጠቀሱት የፓርቲው ፕሬዘደንት እስክንድር ነጋ፣ “ገዥዎቻችን ጠብመንጃ ይዘዋል፣ እኛ ደግሞ እውነትን ይዘናል፡፡ እነሱ በጠብመንጃቸው ይመኩ፣ እኛ ደግሞ፣ ኃይል የእግዚአብሔር ነው እያልን በያዝነው እውነት እንመካለን፤ ያለጥርጥርም እናሸንፋቸዋለን” ብለዋል፡፡

የባልደራስ አደረጃጀት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው “በግፍ የታሰሩት የባልደራስና የአዲስ አበባ ወጣቶች በአካል ከእኛ ጋር ባይኖሩም በመንፈስ ግን ከእኛ ጋር መሆናቸውን አውቀን አደራቸውን ተቀብለን መታገል አለብን፡፡ እነሱ ታስረው እኛ እዚህ የደመቀ ስነ ስርዓት ለማድረግ ስለከበደን ለብዙዎች ጥሪ ከማድረግ ተቆጥበናል” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም፣ ስነ ስርዓቱ ሻማ በማብራት እለቱ ታውሶ የእለቱ መርሃ ግብር ተፈጽሟል፡፡
#ዜና #ኢትዮጵያ #ባልደራስ

03/12/2022

Balderas Official Intro

የብሔራዊ ባንክ ነገር(ሙሼ ሰሙ)ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ በቅርቡ ያወጣው መመርያ ቀነ ገደቡ በመተላለፉ ባንኮች ሌላ አገልግሎት መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ ...
03/12/2022

የብሔራዊ ባንክ ነገር
(ሙሼ ሰሙ)
ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ እንዲያሟሉ በቅርቡ ያወጣው መመርያ ቀነ ገደቡ በመተላለፉ ባንኮች ሌላ አገልግሎት መስጠት በማይችሉበት ሁኔታ እየተተራመሱ ነው። ሕዝቡም እንደፈረደበት የገዛ ገንዘቡ ታግቶበት በጠራራ ጸሃይ ሰልፍ ተራ ገብቶ እየተተራመሰ ነው። ለማን አቤት ይባላል?!

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የተከማቹና በአስር ሚሊየኖች የሚቆጠሩ ደንበኞችን መረጃ የማሰባሰብ ውዝፍ ስራ በወራት እንደማይገባደድ እየታወቀ ቀኑን ከማራዘም ይልቅ የሕዝቡን ገንዘብ አግቶ ማተራመስ ሕዝብ እንደለመደው ይሰለፋል እንጂ ምን ያመጣል የሚል ንቀት ይመስላል።

በዚህ ምክንያት ከሰኞ ጀምሮ የየባንኩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው በመታገዱ ምክንያት ገንዘቤ ሊወረስ ነው የሚል ስጋት ላይ የእለት ፍላጎታቸውን ለመሸፈን የሚያስፈልጋቸውን ገንዘቡ ማግኘት ባለመቻላቸው እራሳቸው ተሸብረው ባንኮችን እያሸበሩ ነው።

የሀገራችን ተቋማት ስራቸውን በእቅድና በአግባቡ ከመስራት ይልቅ ስራን ለዘመናት ወዝፈው እየኖሩ በድንገት ከእንቅልፉቸው ሲነቁ ሕዝብ ላይ ሱሪ ባንገት ቀጭን ትዕዛዝ እየጫኑ ማተራመስሳቸውን የሚያቆሙት መቼ ነው። በንህዝላልነታቸውስ ምክንያት ሕዝቡ ለሚደርስበት መጉላላት ተጠያቂነታቸውስ የት ድረስ ነው? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ለስንቱ ተቋም አምባገነንነት ጎበስ ቀና እያለ ይኑር?!

 #ትኩረት  #ሰበር ዜናአስቸኳይ መግለጫ ---ቁጥር 3--- የካቲቲ 26/2014 ዓ.ም #ባልደራስ እስረኞች እህልና ውሃ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ! # ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ ተነጥ...
03/05/2022

#ትኩረት #ሰበር ዜና

አስቸኳይ መግለጫ ---ቁጥር 3--- የካቲቲ 26/2014 ዓ.ም

#ባልደራስ እስረኞች እህልና ውሃ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ!

# ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ ተነጥለው ወደ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ተወሰዱ!

# ቀለብ ስዩም እና አስካል ደምሌ ከእስር ተለቀቁ!

ዛሬ የካቲት 26/2014 ዓ.ም የካራማራ የድል በዓልን ለማክበር በድላችን ሀውልት የተገኙት እና ለእስር የተዳረጉት የባልደራስ አባላት ምግብ እና ውሃ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ጠዋት ቁርስ ያልበሉ ሲሆን፣ ከታሰሩ ጀምሮ ምግብና ውሃ ሊደርስላቸው አልቻሉም፡፡ ለምን እንደዚህ እንደሚያደርጉ የተጠየቁት ፖሊሶች፣ “ከላይ በመጣ ትዕዛዛ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቀለብ ስዩም እና አስካል ደምሌ ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ቀደም ብለው እስክንድር ነጋ እና ስንታየሁ ቸኮል በመለቀቃቸው፣ 37 የነበረው የታሳሪዎቹ ብዛት ወደ 33 ወርዷል፡፡ በሌላ በኩል፣ ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ የሚባሉ የባልደራስ አባላት ከሌሎቹ እስረኞች ተነጥለው ጊዮርጊስ የሚገኘው አዲስ አበባ ፖሊስ ተወስዷል፡፡

ምንም አይነት የህግ ጥሰት ሳይፈጽሙ፣ ከህግ ውጭ የታሰሩት ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፡-

1. ታምራት በለጠ

2. ጌቱ መከተ

3. ቴዎድሮስ ስመኝ

4. ፍላጎት ፈለቀ

5. ፍፁም መንገሻ

6. ኤርሚያስ ብርሃኑ

7. ዮሐንስ እሱባለው

8. ናትናኤል ጌታቸው ናቸው፡፡

9. ፋሲል ማሞ

10. ፋሲል ውሂብ

11. ሳሙኤል ዲሚትሪ

12. አንተነህ አማረ

13. ሶስና ፈቃዱ

14. ማህሌት እሸቱ

15. ቢኒያም ታደሰ

16. ሰለሞን አላምኔ

17. ጌጥዬ ያለው

18. ወግደረስ ጤናው

19. አንተነህ ሞትባይኖር

20. መአዛ ታደሰ

21. አዶኒያስ ገሠሠ

22. ፍቅረማርያም ሙላቱ

23. ናትናኤል አቤል

24. ነብይልዑል ይልማ

25. ኩራ ገብሬ

26. አቤል አለምነህ

27. አለም ደመቀ /አሌክስ ሸገር/

28. ስንታየሁ ለማ

29. ብሩክ ጫኔ

30. ተስፋዬ ከበደ

31. ዳዊት ንጉሤ

32. ቴዎድሮስ አንተነህ

33. ሊዲያ አበበ

03/03/2022
የባልደራስ አመራሮች በምኒልክ አደባባይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል!የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች ማለትም ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮ...
03/02/2022

የባልደራስ አመራሮች በምኒልክ አደባባይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች ማለትም ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋ እና የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 22 ቀን 2014 ዓ.ም. አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የእምዬ ምኒልክ አደባባይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለድል በዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን ያስተላለፉት ለአዲስ አበባ ሕዝብና ለመላው የአድዋ ድል በዓል አክባሪዎች ነው። በዝርዝር እንመለስበታለን።

ባልደራስ ለ126ኛው ዓመት የአድዋ ድል በዓል ሰፊ ዝግጅት ጀመረ "ሴት ነኝ፤ ጦርነት አልወድም። ሆኖም ኢትዮጵያን የጣሊያን ጥገኛ የሚያደርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ" እቴጌ ጣይቱ ...
03/01/2022

ባልደራስ ለ126ኛው ዓመት የአድዋ ድል በዓል ሰፊ ዝግጅት ጀመረ

"ሴት ነኝ፤ ጦርነት አልወድም። ሆኖም ኢትዮጵያን የጣሊያን ጥገኛ የሚያደርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ" እቴጌ ጣይቱ ብርሐን ዘ ኢትዮጵያ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ለ126ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ጀምሯል። ፓርቲው የተለያዩ አዘጋጅ ግብረ ሃይሎችን አቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል። የአዲስ አበባ ኗሪ ወይም በዕለቱ በመዲናዋ መገኘት የሚችል ማንኛውም የድሉ አክባሪ የፊታችን ረቡዕ የካቲት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 2 ሰዓት ጀምሮ ስድስት ኪሎ ምስካየኅዙናን መድሃኒዓለም አጠገብ በሚገኘው የፓርቲው ዋናው ቢሮ በመገኘት የአደባባይ አከባባሩን እንዲቀላቀልም አዘጋጅ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።

ብሔራዊ የድል በዓሉ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ከ6 ኪሎ በቀጥታ ወደ አራዳ ጊዮርጊስ ምኒልክ አደባባይ በመሄድ ይከበራል።

02/27/2022

LOVE

02/11/2022
02/11/2022

Address

USA, New York
Golden Valley, MN

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Balderas Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share


Other News & Media Websites in Golden Valley

Show All

You may also like