Ethio Media Network

Ethio Media Network Ethio Media Network(EMN) is an Ethiopian media and entertainment media outlet serving the Ethiopian c

" እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ! " - አበባው ደሳለው (ዶ/ር)የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አበባው ደሳለው ...
10/31/2024

" እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው ! " - አበባው ደሳለው (ዶ/ር)

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ምንድነው ?

አበባው ደሳለው (ዶ/ር) ፦

" በባለፈው ዓመት መጨረሻ የበጀት ዓመቱ መዝጊያ ሰኔ 28 ወቅት ያነሳናቸው በርካታ ከህዝብ ጥያቄዎች ነበሩ።

ነገር ግን እነዛ ጥያቄዎች ስላልተመለሱ ከዛ ብዙም ለየት ያለ ጥያቄ አይደለም የምንጠይቀው ምክንያቱም ችግሮቹ እየተባባሱ ስለመጡ።

በመላው ሀገሪቱ ያለው ጅምላ የንጻሃን ግድያ፣ ህጋወጥ ጅምላ እስር ፣ እገታ ፣ ጾታዊ ጥቃት ፣ መፈናቀል ፣ ከፍተኛ ከኑሮ ውድነት ፣ አግባብ ያልሆነ የቤቶች ፈረሳ ያኔም ነበረ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

በአሁን ሰዓት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የህዝብ ብሶት አለ። በተለይ በአማራ ክልል ያለው ችግር ደግሞ አጠቃላይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ምስቅልቅል እንዲሆን ያደረገ ነው።

በአማራ ክልል የመንግስት ኃይሎች ፀጥታውን በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር ነበር ዘመቻ የጀመሩት ነገር ይኸው ከአንድ ዓመት በላይ ሆነ እንጂ ችግሩ ይበልጥ እየከፋ ሄደ እንጂ እየተሻሻለ አይደለም።

አሁንም ንጹሃን ዜጎች በከባድ መሳሪያ እና በድሮን እየሞቱ ነው ፣ ሲቪል ተቋማት የሆኑ ጤና ጣቢያዎች ፣ ትምህርት ቤቶች እየወደሙ ነው።

በአዲስ አበባ ፣ በአማራ ክልል እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እስር ቤቶች የተጨናነቁት ያለ ፍርድ በታጎሩት አማራዎች ነው።

የኛ የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ የክልል ምክር ቤቶች አባላት ሳይቀሩ ከአንድ አመት በላይ ሆነ ተብሎ በሚመስል ሁኔታ ያለ ፍርድ እየተመላለሱ ነው ያሉት። ፍርድ ሳያገኙ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል። ከዚህም የሚብሱ አሉ። ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞች፣ አንቂዎች ለሁለት ዓመት ያክል ያለ ፍርድ የተቀመጡ አሉ በወይኒ ቤቶች።

ከፍተኛ የኑሮ ውድነቱን ስናይ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አድርገናል፣ የብር የመግዛት አቅምን አዳክመን ኢኮኖሚው እንዲንሰራራ እናድረጋለን በሚል የተለያዩ ድጎማዎችን ተደርገዋል የደመወዝ ጭማሪ እስካሁን መንግስት ሰራተኛው ክሲ ውስጥ አልገባም ኑሮ ውድነቱ ግን እጅግ በጣም አሻቅቧል።

በኮሪደር ልማት ሰበብ በብዙ ሺዎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ፈርሰው የተለያየ አቤቱታ በተለያየ መገናኛ ብዙሃን ዜጎች እያሰሙ ነው በተለይ አዲስ አበባ ችግሩ በጣም የገዘፈ ነው።

በአጠቃላይ እነዚህን ችግሮች ስናይ ከሰላምና ፀጥታው ጋር አብረው የሚሄዱ ናቸው።

ቅድሚያ የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ብንፈታው ሌሎች ችግሮችን አብረን እናስወግዳለን። እዛ ላይ ማተኮር አለብን።

🔵 መንግስት የሰላምና ፀጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደ ያለው አካሄድ እስካሁን ወታደራዊ ነው ፤ ፖለቲካዊ አካሄድ ለምን አልደፈረም ? ለምንድነው ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ የደከመው ?

🔵 ለእውነተኛ ድርድርና ውይይት በይፋ ጥሪ አቅርቦ ችግሩን ለምንድነው ለመፍታት የማይጠጋው ?

🔵 የሰላም መፍትሄ አካል አንዱ የጅምላ እስር ፣ የጅምላ ግድያ ማቆም ነው። ይሄ መቼ ነው የሚቆመው?

🔵 የኢኮሮሚ ችግሩን ለመፍታት ዜጎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው መስራት አለባቸው ያን ላለፉት በርካታ ዓመታት ማድረግ አልተቻለም ዜጎች በነጻነት እና በሰላም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው እንዲሰሩ መንግስት የሚያስችለው መቼ ነው ? "

በተጠየቀው ጥያቄ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰጡትን ምላሽ ተከታትለን እናቀርባለን።

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ
10/07/2024

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አረጋ ከበደ

የአማራን ህዝብ በሁለት ሳምንት ትጥቅ አስፈታላሁ ብሎ አማራ ክልል ዘው ብሎ የገባው የብርሃኑ ጁላ ወታደር
09/15/2024

የአማራን ህዝብ በሁለት ሳምንት ትጥቅ አስፈታላሁ ብሎ አማራ ክልል ዘው ብሎ የገባው የብርሃኑ ጁላ ወታደር

09/08/2024

የአይምባው ድል..💚💛❤️💪💪💪

ህወሀት በሽሬ እንደስላሴ በቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት በተለየ ሁኔታ ይጠቀሳል። በተመሳሳይ በኤርትራ አፋበት ላይ የተፈጸመው ጥቃትም እንዲሁ ማርሽ ቀያሪ በሚል የሚወሳ ነው። ዓርብ ዕለት ጎንደር አይምባ ላይ ፋኖዎች ያደረሱት ጥቃት እነዚህን ሁለት የውጊያ አውድማዎች የሚያስታውስ ነው። የፋኖ ትግል ከተጀመረ ወዲህ ዓርብ ዕለት አይምባ ላይ የተመዘገበው ድል እጅግ አስደማሚ ነው።

30 የሚጠጉ ስንቅና ትጥቅ የጫኑ፥ ወታደሮችን ያሳፈሩ ተሽከርካሪዎች እንደጧፍ ነደዋል። ከ700 በላይ የአብይ አህመድ ወታደሮች ምርኮኛ ሆነዋል። ስፍር ቁጥር የሌለው ተተኳሽ በፋኖ እጅ ገብቷል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሜካናይዝድ ሰራዊት ለመገንባት የሚያስችል ግዙፍ መሳሪያም ተሟርኳል። ከምርኮኞች በተጨማሪ ከ100 በላይ ወታደሮች የተደመሰሱ ሲሆን አንድ አዋጊ ኮሎኔል ይገኝበታል። አስገራሚ ነው። የፋኖ አመራሮች የማረኳቸውን የአብይ አህመድ ወታደሮችን ቀይ መስቀል እንዲጎበኛቸውና እንዲረከባቸው እየጠየቁ ነው። ዛሬም የአብይ ጀነራሎች 'የተማረከ ወታደር የለንም' የሚል ምላሽ እየሰጡ ነው።

mekonen

አዲስ ነጠላ ዜማ በቅርብ ቅን ይጠብቁ!
08/25/2024

አዲስ ነጠላ ዜማ በቅርብ ቅን ይጠብቁ!

08/10/2024
ጌታቸው አሰፉ በፎቶ ተከስቷል
08/09/2024

ጌታቸው አሰፉ በፎቶ ተከስቷል

ሕዝብ በሰላም መብቱን ሲጠይቅ፦"የጅራፍ አብዮት"እያሉ ተሳለቁበት።እነሆ የጅራፉ አብዮት ወደ ዝናር አብዮት ተለውጦ እዚህ ደረጃ ደርሷል።@ Dereje Habtewold
08/08/2024

ሕዝብ በሰላም መብቱን ሲጠይቅ፦"የጅራፍ አብዮት"እያሉ ተሳለቁበት።
እነሆ የጅራፉ አብዮት ወደ ዝናር አብዮት ተለውጦ እዚህ ደረጃ ደርሷል።

@ Dereje Habtewold

07/09/2024

Ethio Media Network(EMN) is an Ethiopian media and entertainment media outlet serving the Ethiopian c

በሽዋ አናብስቶች የተማረከው የ48 ክፍለ ጦር አዛዥ እጩ ጀነራል ኮ/ል ትንፋሼ ገላዬ ይሄን ይመስላል !
07/03/2024

በሽዋ አናብስቶች የተማረከው የ48 ክፍለ ጦር አዛዥ እጩ ጀነራል ኮ/ል ትንፋሼ ገላዬ ይሄን ይመስላል !

ጃዋር የሄን ከቀመሰ በኃላ ነው ፖለቲካ እርግፍ አድርጎ የተወዉ :)
06/06/2024

ጃዋር የሄን ከቀመሰ በኃላ ነው ፖለቲካ እርግፍ አድርጎ የተወዉ :)

ይሄን አስገራሚ ወጣት እንተባበረው!"  ...ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ በመግባት https://www.facebook.com/share/p/rb8Jrw5FkinHeCNK/?mibextid=oFDknkሲ...
05/16/2024

ይሄን አስገራሚ ወጣት እንተባበረው!

"
...
ከታች ያለውን ሊንክ ተጭናችሁ በመግባት
https://www.facebook.com/share/p/rb8Jrw5FkinHeCNK/?mibextid=oFDknk
ሲከፍት፣ ኮሜት ቦታውላይ ሂዳችሁ የኔ ስምና ምስል ያለበት ላይ፣ ኮሜት ላይክ፣ በማድረግ የበኩላችሁን አግዙኝ አደራ።

ተጀምሯል ውድድሩ። አሁኑኑ በሊንኩ ገባ ገባ እያላችሁ የኔ ስም ያለበት ላይ በሉ ለይኩ ኮምቱ ቸር ተመኙልኝ። አመሰግናለሁ።

ወዛደር ነኝ (ተሸካሚ)
...
!
ሰላም እንደምን ናችሁ፣ አብይ ዋሲሁን(ደስታው)
እባላለሁ።

ጫማ ማሳመር፣ የታክሲ ረዳትነት፣ የንጣፋ ድንጋይ መጥረብ (ኮብል ስቶን)፣ ጥበቃ፣ የመንገድ ላይ ንግድ፣ ሸክም፣ ወ.ዘ.ተ. ሥራዎችን ሰርቻለሁ። የነገን ህልም ለመኖር ዛሬን መሻገር ግድ ይላልና ዛሬም ላይ ቢሆን ዋነኛ መደበኛ የገቢ ምንጨ የሸክም ሥራ ነው።

በዚሁ ሥራ ላይ ሁኘ ታዲያ ራሴን ለማሻሻል አልቦዘንኩም። ትምህርቴን ተምሬ ጨርሻለሁ፤ የትወና እና፣ ዳይሬክቲንግ ሥልጠናዎችን ወስጀ፣ ለተመልካች በቀረቡ በርካታ የጥበብ ሥራዎች ላይ ተሳትፋለሁ።

ብቻዬን በልፋት እናትም አባትም ሁኘ በኪራይ ቤት፣ የማሳድገው አንድ ልጅ አለኝ፣ ይህ አንድ ልጀ "ጥንካሬዬም ድካሜም ነው"።

በሥድስት ኪሎ ቅዳሜና እሁድ ገበያ ለ12 ዓመታት ጠዋት ገበያው ሲዘረጋ ዕቃ ማውጣት እና ማታ ገበያው ሲነሳ መልሶም ዕቃዎችን በሸክም ማስገባት ዋነኛ የገቢ ምንጬ ሆኖ ስሰራ ቆይቻለሁ። ዛሬም ከሥራው አልወጣሁም።

ግን ትልቅ ስኬት፣ ትልቅ ተስፋ አግቻለሁ...

ከአምስት ወራት በፊት ማሕበሩና አስተዳደሩ ''ለረዥም ጊዜ ለዘለቀው አገልግሎትህ፣ ታማኝነትህና ጥንካሬህ" ሲሉ አነስተኛ የመስሪያ ቦታ በዛው እንዳገኝ ረዱኝ።
ዛሬ ከ12ዓመታት በላይ በተሸካሚነት ሳገለግልበት በቆየሁት የገባያ ቦታ፣ ግማሽ ነጋደ ግማሽ ተሸካሚ ነኝ።

እነዚህን አምስት ወራት እዛው ካሉ ነጋዴዎች ልብሦችን በዱቤ በመውሰድ የተሰጠኝን የሥራ ቦታ ለማፅናት ሞከርኩ። ግማሽ ነጋደ፣ ግማሽ ተሸካሚ፣ ሁኘ እየሰራሁ።

አሁን ደሞ ይህንን የመቶ ሽህ ብር፣ ውድድር ባሸንፍ፣ አንደኛ ከ12 ዓመታት በላይ የሸክም ሥራ ስለሰራሁ ድካምም፣ ትንሽ እግሬላይ ህመም እየተሰማኝ ስለሆነ፣ የሸክም ሥራውን ለሌሌች ለቅቄ፣ እኔ ንግዱላይ ሙሉ በሙሉ በማተኮር፣ ልብሦቹ በቀጥታ ከሚወጡበት ቦታ ተገኝቸ፣ በጨረታ ተወዳድሬ በማሸነፍ፣ ሥርው በሚጠይቀው ደረጃ እየሰራሁ፣ በአንድ ወር ውስጥ፣ ለውጥ አሳያለሁ። ብዙ ልምዱና ጥንካሬው አለኝ፣ ያነሰኝ መነሻ ካፒታል ነው። አመሰግናለሁ።"

ለህፃኖቹ ህክምና 400ሺህ ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል።ኢንጂነር Bejai Nerash Naiker 500ሺህ ብር፣ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ 100ሺ ብር በመስጠት ለህክምናቸው የሚውል ገንዘብ መሰብሰብ ተጀ...
04/22/2024

ለህፃኖቹ ህክምና 400ሺህ ዶላር ያስፈልጋል ተብሏል።
ኢንጂነር Bejai Nerash Naiker 500ሺህ ብር፣
ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ 100ሺ ብር በመስጠት ለህክምናቸው የሚውል ገንዘብ መሰብሰብ ተጀምሯል።

ሁላችንም የአቅማችን በማድረግ የትዕግስት ሶስት መንታ ልጆች የዐይን ብርሃናቸው እንዲመለስ የበኩላችንን እናድርግ።

የባንክ አካውንቶች👇

* СВЕ 1000622473872
* Dashen Bank 5563671317021
* Abyssinia bank 91613069
* ኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ 1023500172828
* አዋሽ ባንክ 013471254339600

ትግስት ካሳ ቀፀላ

ስልክ
* 0911868306
* 0911137097

ሼር ማድረግ እና የሚያግዙ ሰዎች ጋር ማድረስም አንዱ የእርዳታው አካል ነው። እባክችሁ ሼር በማድረግ እና በመለገስ ይተባበሩ🙏

የጎፈንድ ሚ ሊንክ ከስር ተያይዟል
go fund me
* https://gofund.me/42557274

ሰውዓዊነት!- ‹‹ባለቤቴን ‹ስትሮክ› የተባለ በሽታ ገደለው፤ የሦስት ሕፃናት እናት ነኝ፤ ሁሉ ነገራችንን በሕክምና ወጪ ጨርሰናል፤ የቤት ኪራይ መክፈል ተስኖን ኪራይ ቤታችንን ለቀናል፤ ወገኖ...
04/21/2024

ሰውዓዊነት!

- ‹‹ባለቤቴን ‹ስትሮክ› የተባለ በሽታ ገደለው፤ የሦስት ሕፃናት እናት ነኝ፤ ሁሉ ነገራችንን በሕክምና ወጪ ጨርሰናል፤ የቤት ኪራይ መክፈል ተስኖን ኪራይ ቤታችንን ለቀናል፤ ወገኖቼ አግዙኝ!›› ወ/ሮ ሠላማዊት ብርሃኑ፤

- ‹‹ሰዎች! አባቴ አልፏል፤ ጎዳና ከመውጣታችን በፊት እናቴን አበርቱልኝ!›› በአምላክ ፍቃዱ (የ10 ዓመት ልጅ፤ ጎበዝ ተማሪ)፤

- ‹‹አባ የለም፤›› ቅዱስ ፍቃዱ (6 ዓመት፤ ገና አፍ አልፈታም፤ ልዩ- ፍላጎት ተማሪ /ኦትስቲክ/)፤

ቤተሰባችን እንዲህ ነበር!

| ባለቤቴ፣ አቶ ፍቃዱ ገበየሁ፡ በ‹‹ሶሲዮሎጂ›› ሁለተኛ ዲግሪ ያለው ሲሆን፣ በአንድ ግብረ ሠናይ ድርጅት በፕሮግራም ማኔጀርነት የሥራ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ፤ ቤተሰቡን በማስተዳደር ላይ ነበር፡፡

በኅዳር 2015 ዓ.ም በገጠር በመሥክ ሥራ ላይ ቆይቶ፣ ከአንዲት አነስተኛ የገጠር ምግብ ቤት እንደ አጋጣሚ ጨው የበዛበት ጎመን በሥጋ ከባልደረቦቹ ጋር ይመገባሉ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ትንሽ ቆየት እንዳለ ‹‹ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም›› ብሎ ከማረፊያ ክፍሎ እንደ ገባ የደም ግፊቱ ጨምሮ ተዝለፍልፎ ይወድቃል፡፡
ባልደረቦቹ በአካባቢው ካለው ጤና ጣቢያ ወስደውት ሲታከም፣ የደም ግፊት ህመሙ እጅግ ጨምሮ በ‹‹ስትሮክ›› በመጠቃቱ አካሉን በከፊል ማዘዝ እንደተሳነው ተረዳ፡፡

በጊዜው፣ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመመለስ በ‹‹ጥሩነሽ ቤጂንግ›› ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ፤ ትንሽ ሻል ሲለው ደግሞ ደፋ ቀና እያለ፤ ወደ ቢሮው እና ወደ መስክ ገባ- ወጣ እያለ ሥራውን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ሆኖም፣ ከነሐሴ 2015 ዓ.ም ወዲህ ግን አልቻለም፤ ሙሉ አካሉን ማዘዝ ተስኖት፤ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ተኝቶ ሕክምና ማድረግ ጀመረ፡፡

ከጊዜ በኋላም፣ በኪራይ በምንኖርበት ‹‹ገላን ኮንዶሚኒየም›› በአልጋ ላይ በመዋሉ ወደ ሥራ ገበታው መመለስ ሳይችል ቀረ፡፡
ከዚያም፣ አንደበቱ መናገር ተስኖት፣ ሙሉ ሰውነቱ አልታዘዝ አለው፤ ይሰራበት የነበረው ግብረ ሠናይ ድርጅት ደግሞ እስከ ታኅሳስ 30 2016 ዓ.ም ድረስ ሙሉ ደመወዙን ሲከፍል የቆየ ቢሆንም፣ ከዚያ ወዲህ ግን የሥራ ውሉ መታደስ ስላልቻለ እና በሥራ ገበታው ላይ መገኘት ባለመቻሉ እና ሌላ ሰው ስለተቀጠረበት የወር ደመወዝ ተቋረጠብን፡፡

የአምስት ቤተሰብ የገቢ ምንጫችን በመቋረጡ፣ የቤት ኪራይ መክፈል ተስኖን፣ ሦስት ልጆቼን ይዤ ከኪራይ ቤታችን ወጥተን፤ ጎዳና ልንወድቅ እቃችንን በመሸከፍ ላይ ሳለን ነበር የ‹‹ገላን አዲስ ሕይወት የጋራ ቤቶች ማኅበር ኮሚቴ›› ተሰባስቦ ባለቤቴ አቶ ፍቃዱ እስኪሻለው ለጊዜው ማኅበሩ ለሀዘን፣ ለሠርግ እና ለልዩ ልዩ ማኅበራዊ ግልጋሎት የሚጠቀምበትን ‹‹ኮሚዩናል ቤት›› ፈቅደውልን ነበር ባለቤቴን አስተኝቼ በማስታመም ላይ የነበርኩት እና የገላን ጤና ጣቢያ ነርሶች ደግሞ በየሦስት ቀኑ እየመጡ ወደ ኢንፌክሽን የተቀየረውን ቁስል ያጸዱለት ነበር፡፡አሁን ሕይወቱ አልፏል፡፡

የቤቱ አባወራና የገቢ ምንጭ አቶ ፍቃዱ ገበየሁ አሁን አልፈዋል፡፡ ቤተሰቡ በገቢ ማጣትና በቤት እጦት እንዳይበተን የተቻላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉላቸው በፈጣሪ ሥም እንጠይቃለን፡፡

ወ/ሮ ሰላማዊት ብርሃኑ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡-
1000268281936

- ስልክ ቁጥር፡-
+251926718068
+251911117594

እግዚአብሔር ይስጥልን!!!
(ቤተሰቡ)

Address

Denver, CO
80202

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Media Network:

Videos

Share

Nearby media companies


Other Media/News Companies in Denver

Show All