08/21/2024
ሙሉ መስዋዕት እንከን የሌለው ኦሆ
ለአማልክት አምላክ ይዣለው ይሄው አሃ
የማያነክስ ወይ ያልታወረ ኦሆ
ለጌቶች ጌታ ለተከበረ አሃ
በፊቱ የተወደደ በፊቱ ከቶ ያልተናቀ
ሚያሸተው በአምላኬ ዘንድ ዘወትር የተናፈቀ
ቅዱሱን ሕያው መስዋዕት የራሴን ሰውነቴ
ላፍስሰው እና ልሰዋ ደስ ይበለው መድሃኒቴ
ለአምላኬ ምስጋናዬን እሰዋለው
ለንጉሡ ስዕለቴን እከፍላለው
ይህ ለኔ ስራዬ ነው ልማዴ
በወቅቱ ክብርን መስጠት ለውዴ
ይሄ ነው ልማዴ ክብርን መስጠት ለውዴ
ኢየሱስ ጌታ ነው
ድንቅ አምልኮ
የዕሮብ ቀን መዝሙር ግብዣዬ