Yom Media ዮም ሚድያ

Yom Media ዮም ሚድያ your Best media. we deliver real info with evidence . follow us and share our content.

12/19/2024

በቅንነት ሼር አድርጉልኝ ወዳጆች

12/19/2024
12/09/2024

👉ስለ ሚመለሱ ሰዎች ጥያቄ አለኝ ❓
ጥያቄው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ጉባዔ የየአገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም ስራ አስኪያጆች ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ እስከ ወራዳ የየመምሪያው ኃላፊዎች የየአጥቢያ አብያተክርስቲያናት አለቆች የመሳሰሉ።

ከሁሉ አስቀድሜ ከላይ ለተጠቀሱ አካላት ታላቅ ክብር እና ፍቅር አለኝ በትእቢት በንቀት እንዳይታይብኝ አደራ እላለሁ ።
መቼውም ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥንቅቅ ብላ የተሰራች ንጽሕት እና ክብርት በየዘመናቱ የምንቀይረው የምናስተካክለው የምናድሰው ነገር የለም ። አባቶቻችን ሁሉንም ቀኖና አዘጋጅተውልን ስላለፉ ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንድ ሰው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ርቆ ፣ወጥቶ፣ ተሳድቦ፣ አንቋሾ በተለይ ከእርሱ ጋር ብዙ ሰው አሸፍቶ ሲመለስ የአመጣጡ አይነት ምን መመስል አለበት ❓ ለዚህ የቤተክርስቲያን ቀኖና ምን ይላል።
ይህን የምለው ቤተክርስቲያን ወደ እርሷ በንስሐ የመጣውን በፍቅር እጇን ዘርግታ በደስታ ፍሪዳ ጥላ ፣ቀለበት አድርጋ፣ ነጭ ልብስ አጥልቃ እንደም ትቀበል አልዘየጋሁትም።

ነገር ግን ብዙ ከዚህ ቀደም አገልጋይ የነበሩ አሁን ደግሞ አጥፍተናል እኛም ጠፍተናል ብለው የተመለሱ ወነድሞች እና እህቶች
1ኛ እንዴት ነው የሚመለሱት?
2ኛ ኃላፊነቱን የሚቀበለው ክፍል ማነው?
3ኛ መመለሳቸውን አረገግጦ ፈቃድ የሚሰጠው ክፍል ማነው?
4ኛ ካህናት እና ዲያቆናት ከነበሩ በዚያው ይቀጥልል ወይስ ክህነቱ ይቋረጣል?
5ኛ አገልግሎት መዘመርም ይሁን መቀደስ መስበክም ቢሆን የሚጀምሩት በማግስቱ ነው ከቀናት በኋላ ወይስ አያገለግሉም?
6ኛ የንስሐ ቅጣት ነው የቀደር ጥምቀት የሚያስፈልጋቸው?
እነዚህን ስድስት ጥያቄ ያነሳሁት ለዘመናት ከቤተክርስቲያን ፈተና ለነበረው የመናፍቃን ክንፍ በመሆን አሁንም እያተገላት ካለው ከተሐድሶ ብሎም ከፕሮቴስታንት የመጡ ሰዎች ።
አንዳንዱ በፊስቡክ ንስሐ ገብተው ፣አንዳንዱ በታክቶክ ተናዘው፣ ሌላው ጉዳዩ በሲኖዶስ እና በቅዱስ ፓትርያርኩ እውቅና አግኝቶ አንዳንዱ በአገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ፈቃድ ተሰጥቶት የተወሰኑት ደግሞ በንስሐ አባት ቀኖና የተወሰኑት ደግሞ በማህበራት ፈቃድ እየመጡ ጥቂቶች ደግሞ ራሳቸውን በጉልበት መልሰው አልነበርንም እያሉ ክህነቱም እንዳለ ሳይውሉ ሳያድሩ በማግስቱ በየሐገሩ እየተዘዋወሩ ሲያገለግሉ ሳይ ይህ ጥፍታ አንዱ ሲሆን። አንዳንዱ ሲጠመቁ ሌላ ወደ ገዳም ለሱባኤ ሲሄዱ ይህ አሰራር አንዳ አይነት አለመሆኑ ጥያቄ ፈጠረብኝ ። ስለመመለሳቸው ዋጋ የከፈሉ ይኖራሉ ይህንን አላጠለሽም በእነሱ መመለስ ክሪዲት የሚፈልግ ይኖራል ይህም እንደፍላጎታቸው ይህ ።
እኔ የምለው ይህ አሳራር ነገም ተመለስኩ ብለው እንደገና ለመንጠቅ፣ ለመበረዝ ፣ለመስረቅ ፣የሚመጡ ተሐድሶ መናፍቃንን ለጥፋት የልብ ልብ አይሰጥም ? ቤተክርስቲያን ሥርአት እንደሌለ መቁጠርስ አይሆንም ማስተማር ፣መመስከር ፣መምከር፣ የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳውያን አባላት እንዲሁም ማህበረት ግዴታ ነው በዚህ ጉዳይ ለተሰማሩም ሁሉ ክብር ይገባቸዋል ። ነገር ግን የእኔ ጥያቄ መላሹ ፈቃድ ሰጪው ማነው? የሚለው የየእለት ጥያቄዬ ነው ። እግዚአብሔር ያክብርልኝ

👉👉👉👉👉ጥያቄው ለሁሉ እንዲደርስ ሼር ያድርጉ🛑🛑
መጋቤ ምስጢር ቡሩክ አሳመረ
ህዳር 17/2017
Yom MediYom Media ዮም ሚድያour media
Like and Share

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምድረ ቻይና የመጀመሪያውን ደብር በመሰየም፣ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች!ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ለሁለተኛ ምዕራፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገ...
12/08/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምድረ ቻይና የመጀመሪያውን ደብር በመሰየም፣ ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች!

ባሳለፍነው ሳምንት ሐሙስ ለሁለተኛ ምዕራፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በዕለቱ ከተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በማስከተል የአስተዳደር ሥራዎችን ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ፤ በዕለተ እሑድ በቻይና ምድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያ የሆነውን ቤተ ክርስቲያን "ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም" ብለው በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈፀም ምዕምናንን አቁርበዋል።

በዕለቱም አንድ ኢ-አማኒ የነበረች ግለሰብ እና ሕፃን በማጥመቅ የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ያደረጉ ሲሆን የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆንም ሹመት አከናውነዋል።

በዕለቱም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምዕመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው የተሳተፉ ሲሆን መጋቤ ሐዲስ ለይኩን ብርሃኑ "ሔዶም ታጠበና እያየም ተመለሰ" በሚል ርዕስ አስተምረዋል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ ብፁዕነታቸው ለቀጣይ አገልግሎት ወደ ቤይጂንግ ከተማ አቅንተዋል።

መረጃውን ያደረሰን የብፁዕነታቸው ጽ/ቤት ነው
Yom Media ዮም ሚድያ

enkuan le kidus mikael ametawi beal adresachehu melkam ken
11/21/2024

enkuan le kidus mikael ametawi beal adresachehu
melkam ken

ስለትዳር ጠቃሚ ትህምርት ነው ላገቡ ትዳራቸውንበብልሀት  ጠበቅ አድርገው እንዲይዙ ላላገቡት ደግሞ ወደትዳር ሲገቡ ሊተገብሯእው የሚችሉት ድንቅ ጥበብ subscribe our channel for ...
11/13/2024

ስለትዳር ጠቃሚ ትህምርት ነው ላገቡ ትዳራቸውንበብልሀት ጠበቅ አድርገው እንዲይዙ ላላገቡት ደግሞ ወደትዳር ሲገቡ ሊተገብሯእው የሚችሉት ድንቅ ጥበብ
subscribe our channel for more

በዚህ ቪድዮ ላይ ስለ ትዳር እና ትዳርን እንዴት አጥብቀን በብልሀት መያዝ እንደንችል እናያለን 7 ቱ የተባረክ ትዳር እንዲኖራችሁ የሚያደርገው የህይወት ህግጋቶች #ትዳር #ሰርግ #ጋብቻ ...

30-2-2017
11/09/2024

30-2-2017

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል በቦሌ ደብረ ሳሌም ቤተ ክርስቲያን የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር  አዘጋጀ።(   ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፯ ...
11/09/2024

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል በቦሌ ደብረ ሳሌም ቤተ ክርስቲያን የእውቅናና የምስጋና መርሐ ግብር አዘጋጀ።
( ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ዓ.ም)
ዘጋቢ መ/ር ነገሠ ሣህለ
በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣መምህራነ ወንጌል፣ ተጋባዥ እንግዶች የተገኙበት ሲሆን መርሐ ግብሩ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ጸሎተ ቡራኬ ተጀምሯል።
በትረ ትጉኃን ፋንታ ገላው የኅብረቱ ሰብሳቢ ስለ ሰባክያነ ወንጌል ኅብረት ስለ ተመሠረተበት ዓላማና ተግባር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያሬዳዊ ጣዕመ ዜማ አሰምተዋል።
በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቡራኬ ከሰጡ በኃላ ኅብረቱን ለመቋቋም ብዙ ዋጋ ለከፈሉና አሁን በሕይወተ ሥጋ ለሌሉ በብፁዓን አባቶች ጸሎት ተደርጎላቸዋል።
መልአከ ምሕረት አብነት ዓሥራት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ክፍልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል ሐላፊ መልእክት በማስተላለፍ ለኅብረቱ አስተዋፅዖ ያደረጉትን አመስግነዋል።
በመጨረሻም ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልእክት ያስተላለፋ ሲሆን ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ ምክርና ቃለ ቡራኬ በመስጠት መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

በሁሉም የሶሻል ሚድያ ገጾች ያገኙናል
በ YouTube
በ Facebook
በ Tiktok በ Telgram

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋ...
11/05/2024

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ መልእክት አስተላለፉ።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ መልእክት አስተላለፉ።

የቅዱስነታቸው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል፦

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ክቡር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም
የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር፤
ክቡራን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች፤
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ወኤጲስ ቆጶሳት፤
ክቡራን የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ አምባሳደሮች፤
ክቡራን ታሪካዊ በሆነው ዓለም ዐቀፍ የሃይማኖት ጉባኤ ለመሳተፍ በዚህ የተገኛችሁ በሙሉ፤

"ሰላምየ አኀድግ ለክሙ ወሰላመ አቡየ እሁበክሙ፡- ሰላምን እተውላችኋለሁ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፡፡" ዮሐ. ፲፬፥ ፳፯

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ሥጋ ለብሶ በሚታይ ሰውነት የተገለጠው ሰላምን ለማምጣት ነው፡፡ የማዳን ተግባሩን አከናውኖ፤ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በምድርና በሰማያት ላሉ ሰላምን አድርጎ ባረገ ጊዜም ዓለም እንደምትሰጠው ሰላም ያይደለ ልቡናን የሚያሳርፍ፣ መንፈስን የሚያረጋጋ እውነተኛ ሰላምን ሰጥቶናል፡፡ ልዑል አምላክ ትሑት ሥጋን በመዋሐዱም ታላላቆች ለይቅርታ ዝቅ በማለት የሰላም ምክንያት መሆን እንደሚችሉ በተግባር አስተምሮናል።

ሰላም የሰው ልጆች ፍላጎት፣ የብዙ ምንዱባን የየዕለት ናፍቆት ነው። የበርካታ ዘመናት ቅርሶች፤ ጊዜ፣ ገንዘብ እና የሰው ጉልበት የፈሰሰባቸው ግንባታዎች በሰላም ማጣት በቅጽበት ይፈርሳሉ። ሰላም ካለ የዓለም ሀብት ለሁሉም በቂ ነው። ሰላም ማጣት ግን ብዙ ሠራዊት፣ ብዙ የጦር መሳሪያ እንዲዘጋጅ እያደረገ ሀብትን ያወድማል። ጦርነት ማለት ሀብትና ሕይወትን ወደሚነድ እሳት ውስጥ መጣል ነው። የአንደኛና የሁለተኛ ዓለም ጦርነት፣ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ጠባሳው አሁንም የዓለምን መልክ አበላሽቶታል። ሰላም በውስጥዋ ገራምነት፣ ትዕግሥት፣ ታዛዥነትና በትህትና ዝቅ ማለት ስለሚገኙ መራራ ትመስላለች፤ በውጤቷ ግን ሀገርን ከጥፋት፣ ሕዝብን ከመከራ ማትረፍ የሚቻል በመሆኑ ዋጋዋ ከፍ ያለ ነው።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላም የሆነው ክርስቶስ የሚሰበክባት፣ የሰላም መልእክተኞች በውስጥዋ የሚመላለሱባት፣ በግብረ ኃጢአት የወደቁት በንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቁባት የሰላም ድልድይ ስለሆነች በሥርዓተ ቅዳሴዋ ሰላምን ደጋግማ ታውጃለች፤ በጸሎቷ ለመላው ዓለም ሰላምን ትለምናለች፤ በጉልላትዋ ላይ የሰቀለችው መስቀልም ሰላምን የሚሰብክ ነው፤ የመስቀሉ ቅርፅ ወደ ላይና ወደ ጎን መሆኑም ከእግዚአብሔርና ከሰው ጋር ሰላም መሆን እንዳለብን የሚያስገነዝበን ነው። ታሪካችን እንደሚነግረን ወንድማማቾች ሲጋደሉ፣ በሕዝብ መካከል መተላለቅ ሲመጣ ቤተ ክርስቲያን ታቦት አክብራ፣ በእሳት መካከል ገብታ ሰላምን ስታወርድ የኖረች ናት። በሀገር ውስጥ ግጭቶች በተፈጠሩበት ጊዜም የሰላም ጥሪን ያላስተላለፈችበት ቀንና ሰዓት አይገኝም፡፡

ክቡር ሚኒስትር
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ክቡራንና ክቡራት የዚህ ታላቅ ጉባኤ ተሳታፊዎች

ሰላምን የመወያያ ርእስ አድርገን ስንሰባስብ በጦርነት መካከል የተጨነቁ ሕዝቦች፣ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ እና ምን እየተደረገ እንዳለ በውል የማይገነዘቡ ደካሞች ተስፋ ያደርጉናል። ስለዚህ ሰላም ከአንገት በላይና ዝም ላለማለት ያህል የምንናገረው ሳይሆን ዋጋ ከፍለን የምናመጣው ስለሆነ ይህ ጉባኤ ከውይይት ባሻገር በተግባር ጭምር የሰላም ተምሳሌት መሆን እንደሚገባው ለማሳሰብ እንወዳለን።

ዓለም በዚህ ወቅት አስጊ በሆኑ ጦርነቶች ውስጥ እያለፈች ነው፡፡ በሩሲያና በዩክሬን ያለው ጦርነት የዓለምን ኢኮኖሚ አናግቷል፤ ከሁሉ በላይም ክቡር የሆነውን የሰው ሕይወት እየቀጠፈ ነው። በእስራኤል፣ በፍልስጤም እና በመካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ያለው አለመረጋጋት ሁሉንም የሚነካ ነውና በጦርነቱ የሚሳተፉት በሙሉ ወደ ሰላም እንዲመለሱ፤ የዓለም መሪዎችም ልበ ሰፊ ሆነው ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በመጨረሻም በሀገራችን ውስጥ ያሉት ግጭቶች የመቆሚያ ድንበራቸውን ያገኙ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር የተባረከ ጉባኤ ያድርግልን!
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!አሜን፡፡

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፳፭ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ማኅበረ ቅዱሳን በሁሉም የሶሻል ሚድያ ገጾች ያገኙናል                                       በ YouTube   በ Facebook በ Tiktok   በ Telgram     ...
11/04/2024

ማኅበረ ቅዱሳን
በሁሉም የሶሻል ሚድያ ገጾች ያገኙናል
በ YouTube
በ Facebook
በ Tiktok በ Telgram

Yom Media ዮም ሚድያ

በማኀበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል ኤስድሮስ ሥነ መለኮት ሰሚናሪ በሥነ መለኮትና ግእዝ ቋንቋ ለሦስት ዓመታት ያስተማራቸውን 33 ደቀመዛሙርት አስመረቀ !ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ...
11/03/2024

በማኀበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል ኤስድሮስ ሥነ መለኮት ሰሚናሪ በሥነ መለኮትና ግእዝ ቋንቋ ለሦስት ዓመታት ያስተማራቸውን 33 ደቀመዛሙርት አስመረቀ !

ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ኤስድሮስ ሴሚናሪ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በሚዙሪ ግዛት ሴንት ሉዊስ ከተማ 21 ወንዶችና 12 ሴቶችን በድምሩ 33 ደቀ መዛሙርትን ማስመረቁ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተስፋቸው መሆኗን የገለጹት ተመራቂ ደቀ መዛሙርት ወደፊትም ብዙ አገልግሎት እንደሚያበረክቱና በሰሚናሪው ቆይታቸው ያገኙት ትምህርት ለአገልግሎታቸው ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግላቸው ጠቅሰው ኤስድሮስ ሴሚናሪ ላደረገላቸውም ድጋፍ ምሥጋና አቅርበዋል።

ከምርቃት ሥነ ሥርዓቱ አስቀድሞም ለተመራቂ ደቀ መዛሙርት ተጨማሪ የሕይወትና የአገልግሎት ስንቅ የሚያገኙበት ሥልጠና መሰጠቱ ተጠቅሷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የኦሃዮና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ለተመራቂዎች ዲፕሎማና የምስክር ወረቀት የሰጡ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳንን ከምሥረታ ጀምሮይ እንደሚያውቁትና አገልግሎቱን እንደሚደግፉ ገልጸዋል፡፡

የኤስድሮስ ሥነ መለኮት ሰሚናሪ በ2011 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካ አህጉረ ስብከቶች እውቅና አግኝቶ ማስተማር የጀመረ ሲሆን ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ ያስመረቀ ሲሆን ሴሚናሪው በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች የግእዝ ቋንቋንና ቤተ ክርስቲያንን የበለጠ እንዲያውቋት ጠንካራ ሥራ እየሠራ እንደሆነ የማኅበረ ቅዱሳን አሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል የሰጠን መረጃ ያመላክታል። በሁሉም የሶሻል ሚድያ ገጾች ያገኙናል
በ YouTube
በ Facebook
በ Tiktok በ Telgram

11/02/2024

🕊

[ † እንኳን ለጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† 🕊 ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት አባ ዮሴፍ 🕊 †

† በእስክንድርያ [ግብጽ] ሊቀ ዽዽስናን ከተሾሙና በጐ ሥራን ከሠሩ አበው አንዱ አባ ዮሴፍ ነው:: እርሱ ለግብጽ ፶፪ኛ ፓትርያርክ ነውና በ9ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ እንደ ነበር ይታመናል::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በግብጽ የሚኖሩ የዘመኑ ክርስቲያን ባልና ሚስት ወደ ፈጣሪ ለምነው ልጅ ሲወልዱ 'ዮሴፍ' አሉት:: እጅግ ሃብታሞች ቢሆኑም እርሱ ገና ልጅ እያለ ሁለቱም ዐረፉ:: ሕጻኑ ዮሴፍም ዕጓለ ሙታን [ወላጅ አልባ] ሆነ:: ሕጻኑ ሲያለቅስ የተመለከተ አንድ ደግ ጐረቤቱ ግን ወደ ቤቱ ወሰደው::

እንደ ልጁ ተንከባክቦ: ክርስትናንም አስተምሮ አሳደገው:: እድሜው ፳ ሲደርስም "የወላጆችህን ንብረት ንሳ" ብሎ አወረሰው:: ወጣቱ ዮሴፍ ግን "አኮኑ ዝንቱ ኩሉ ኃላፊ-ይህ ሁሉ ሃብት ጠፊ አይደለምን" ብሎ ናቀው::

ለነዳያንም በትኖት እያመሰገነ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ገሰገሰ:: በዚያም የአሞክሮ ጊዜውን ፈጽሞ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበለ:: ለዓመታትም በዲቁና ገዳሙን እያገለገለ: እየተጋደለ ኖረ::

የአባ ዮሴፍን ደግነት የሰማው የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ማርቆስም ከገዳም አውጥቶ በመንበረ ዽዽስናው እንዲራዳውና ሕዝቡን እንዲያስተምርለት ወደ ከተማ አመጣው::

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን አባ ዮሴፍ ወደ ፓትርያርኩ አባ ማርቆስ ቀርቦ "አባቴ! ወደ ገዳሜ አሰናብተኝ:: ለመነኮስ በከተማ መኖር ፍትሕ አይደለምና" ሲል ተማጸነው:: ፓትርያርኩም "እሺ" ብሎ ቅስናን ሹሞ አሰናበተው::

ወደ ገዳመ አስቄጥስ ከተመለሰ ጀምሮ አባ ዮሴፍ በዓት ለየ:: እስከ ፶፱ ዓመቱም ድረስ በጾምና በጸሎት በበዓቱ ጸንቶ ኖረ:: በአጠቃላይ በገዳም የኖረባቸው ዓመታትም ፴፱ ደረሱ::

በዚህ ጊዜ ግን የወቅቱ ፓትርያርክ አባ ስምዖን [ከአባ ማርቆስ በኋላ ፫ ፓትርያርኮች ዐርፈዋል] በማረፉ ግብጽ እረኛን ስትፈልግ ነበር:: 'ማንን እንሹም' እያሉ ሲጨነቁ አንድ ሰው ጉቦ ሰጥቶ ሊሾም መሆኑን አበው ሰሙ:: ይህ ሰው ደግሞ ጭራሹኑ ልጅ ያለው ነው::

አባቶች ተሯሩጠው ያ ጉቦኛ ባለ ሚስት እንዳይሾም አደረጉ:: ቀጥለው ማንን እንደ ሚሾሙ ሲጨነቁ የሁሉም ሕሊና ስለ አንድ ሰው [አባ ዮሴፍ] ያስብ ነበር:: ሁሉም ተሰብሳቢዎች ስለ ነገሩ ተጨዋውተው አባ ዮሴፍን ይሾሙ ዘንድ ቆረጡ::

ተሰብስበው በመንገድ ላይ ሳሉም እንዲህ ተባባሉ:: "ወደ በዓቱ ስንደርስ ቤቱ ክፍት ከቆየን ፈቃደ እግዚአብሔር ነው:: ዝግ ከሆነ ግን ፈጣሪ አልፈቀደም ማለት ነው" ሲሉ ተስማሙ:: ምክንያቱም የአበው በዓት ቶሎ ቶሎ አይከፈትምና::

ነገሩ ጥበበ እግዚአብሔር ነበረበትና ልክ ሲደርሱ እንግዳ ሊሸኝ በዓቱን ከፍቶ አገኙት:: እንዳያመልጣቸው ተረባርበው ያዙት:: ግጥም አድርገው አሥረው "አክዮስ-ይደልዎ-ይገባዋል" እያሉ ሥርዓተ ሲመት አደረሱለት:: እርሱ [አባ ዮሴፍ] ግን "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ: አይገባኝም: ልቀቁኝ" እያለ ይጮህ ነበረ::

አበው ግን ሥርዓተ ሢመቱን ፈጽመው ወስደው በመንበረ ዽዽስና: በቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ዙፋን ላይ አስቀመጡት:: በቁጥርም ፶፪ኛ ሁኖ ተቆጠረ:: አምላክ ደጉን ሰው ጠቁሟቸዋልና ለቤተ ክርስቲያን ይተጋ ጀመር::

ሕዝቡን እያስተማረ: አብያተ ክርስቲያናትን እያነጸ: መጻሕፍትን እየተረጐመ: ተአምራትን እየሠራ: በመንኖ ጥሪት ለ፲፱ ዓመታት አገልግሏል:: ወቅቱም ተንባላት [አማሌቃውያን] በምድረ ግብጽ የሰለጠኑበት ነበርና ብዙ ችግሮችን አሳልፏል::

የግብጹ ሱልጣንም ሊገድለው ፪ ጊዜ ሞክሮ አልተሳካለትም:: ፪ ጊዜም ለአባ ዮሴፍ የሰነዘረው ሰይፍ በመልአክ እየተመለሰ ተመልክቶ ትቶታል:: አባ ዮሴፍ በዘመኑ ተሰዶ የነበረውን የኢትዮዽያ ዻዻስ አባ ዮሐንስንም ከተሰደደበት ወደ ሃገራችን
እንደ መለሰው በዜና ሕይወቱ ተጽፏል:: አባ ዮሴፍ እንዲህ ተመላልሶ በ፸፰ ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል::

† ቸር አምላክ በጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ጸሎት ይማረን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

🕊

[ † ጥቅምት ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ ዮሴፍ ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት
፪. ቅዱስ ዲዮናስዮስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ኢላርዮስ
፬. ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት

[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
፪. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፫. ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን [ንጉሠ እሥራኤል]
፬. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፭. ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
፮. አባ ሳሙኤል
፯. አባ ስምዖን
፰. አባ ገብርኤል


† " ኤዺስ ቆዾስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና:: የማይኮራ: የማይቆጣ: የማይሰክር: የማይጨቃጨቅ: ነውረኛ ረብ የማይወድ: ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ: በጐ የሆነውን ነገር የሚወድ: ጠንቃቃ: ጻድቅ: ቅዱስ: ራሱን የሚገዛ ይሁን:: " † [ቲቶ.፩፥፯] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
Follow our social medias

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵ...
11/02/2024

የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
ምልዓተ ጉባኤው ልዑል እግዚአብሔርን አጋዥና መሪ በማድረግ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት፣ ስለምጣኔ ሀብት እድገት፣ በሀገራችን እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን
አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ 43ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ተሳታፊዎች የቀረበው ቃለ ጉባኤና የአቋም መግለጫ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱ የሥራ መመሪያ እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
2. በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡
3. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በሥሩ ባሉ ገዳማትና አድባራት ውስጥ እየቀረቡ ያሉ መጠነ ሰፊ የአስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ ለማድረግ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ በክፍላተ ከተሞችና ችግር አለባቸው ተብለው በጥናት በሚለዩት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ላይ የማጣራት ሥራ እንዲሠራና ውጤቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ በሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
4. የኦሲኤን ቴሌቪዥን ስርጭት የተቋረጠ በመሆነ በአዲስ መልክ ሁሉንም የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪዎች ማህበረሰብ ባቀፈ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ኔትወርክ በሚል ስያሜ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ውል ተፈርሞ በአዲስ መልክ የሳተላይት ግዥ እንዲፈጸም ሆኖ አስተዳደሩን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን ድርጅት ጋር በአንድ ሊቀ ጳጳስና ቦርድ ራሱን በቻለ ሥራ አስኪያጅ እየተመራ አገልግሎቱ ከነበረው በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ
ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5. የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለደቀ መዛሙርት የሚሰጠው የምስክር ወረቀት አድቫንስ ዲፕሎማና ዲግሪ እንዲሆን ሥርዓተ ትምህርቱ ለሚሰጠው የትምህርት ማስረጃ በሚመጥን መልኩ ተሟልቶ፣ ሊኖረው የሚገባው የሰው ኃይል በየዘርፉ ተጠናክሮ ወደ ትግበራ እንዲገባ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፣
6. የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሥነ ሕንጻና በኪነ ጥበብ በዓለም ደረጃ ከፍተኛ አድናቆትና ክብር የሚሰጠው ከመሆኑ በተጨማሪ በመዐርገ ጵጵስና ፕትርክና የሚሾሙ አባቶች ሥርዓተ ሲመት የሚፈጸምበት፣ ጥንታዊና ታሪካዊ ካቴድራል መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ለዕድሳት ሥራው የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤ በተጨማሪም ምእመናን እስከ አሁን እንደሚያደርጉት ሁሉ ለእድሳት ሥራው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ
ያሳስባል፡፡
7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዐቢይ ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና በንቃት እንዲሳተፍ ሁሉንም አህጉረ ስብከት ባቀፈ ሁኔታ የአጀንዳ መረጣና ተሳታፊ የመለየት ሥራ እንዲከናወን ሆኖ ዐቢይ ኮሚቴው የሥራ ዕቅዱንና አፈጻጸሙን ለቋሚ ሲኖዶስ እያቀረበ በማስወሰን እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በአጠቃላይ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ላለፉት ተከታታይ ቀናት በመንፈሳዊ፣ በማኀበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ በማስተላለፍ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት በጸሎት አጠናቅቋል፡፡ መሐሪና ሁሉን ቻይ የሆነ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን፣ ለሕዝባችን፣ ለዓለሙ ሁሉ ሰላሙን፣ ፍቅሩንና አንድነቱን ይስጥልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት ፳፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
credit: EOTC TV

ማስታወቂያ ++++++++++++++++++++++++++++++++++200ብር  ለገዳማውያን በከፋ ዞን ሀገረ ስብከት  የሚገኝው የጊንቦ ወረዳ በአርጉባ መካነ ቅዱሳን አብነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ...
10/31/2024

ማስታወቂያ
++++++++++++++++++++++++++++++++++
200ብር ለገዳማውያን
በከፋ ዞን ሀገረ ስብከት የሚገኝው የጊንቦ ወረዳ በአርጉባ መካነ ቅዱሳን አብነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ቅድስት አርሴማ የመነኮሳት አንድነት ገዳም
200 ብር ለገዳማውያን የበኩላችንን እንድርግ
206290088አቢሲንያ
1000481792553 ንግድ ባንክ
አርጎባ አቡነ ገ መንፈስ ቅዱስና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም
ለበለጠ መረጃ
+251906930472
+251980131721
♨♨♨♨♨♨♨♨

በሁሉም የሶሻል ሚድያ ገጾች ያገኙናል
በ YouTube ♦️ https://www.youtube.com/
በ Facebook 🔺 https://www.facebook.com/yommediacompany
በ Tiktok ?? https://www.tiktok.com/ በ Telgram 📣 https://t.me/yommedia
ፎሎው እና ሼር በማድረግ ያበረታቱን ።

+++  እንኳን አደረሳችሁ +++መስቀል ብርሃን ነው  የሚል አዲስ ዝማሬ እነሆ በይባቤ ልጅ ቲዩብ   shere & subscribe  እንዳይረሳ
09/26/2024

+++ እንኳን አደረሳችሁ +++
መስቀል ብርሃን ነው የሚል አዲስ ዝማሬ እነሆ
በይባቤ ልጅ ቲዩብ shere & subscribe እንዳይረሳ

🔴 መስቀል ብርሃን ነው ሊቀዲያቆናት ተመስገን ይባቤ 2024 ‎ ...

" የልባችሁን አእምሮ አድሱ " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵ...
09/10/2024

" የልባችሁን አእምሮ አድሱ " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት " ሁለመናችንን በሐዲስ ምግብ እየመገበ የሚጠብቀን አምላካችን እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ 2016 ዓ.ም ወደ ዘመነ ማቴዎስ 2017 ዓ.ም በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ " በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም " በገሃዱ ዓለም የማያረጅ እና የማይታደስ የለም መታደስ ባይኖር ኖሮ ሕይወታውያን ፍጡራን በሕይወት መካከል መቀጠል አይችሉም ነበር፤ የዘመን መታደስ የስነ ፍጥረት አንዱ አካል ስለሆነ በየጊዜው ይታደሳል። እኛ ሰዎችም በየጊዜው እንድንታደስ እግዚአብሔር አዞናል ፤ ዘመንም እንደሌላው ያረጃል ይታደሳል ፤ ዛሬ አሮጌውን ሸኝተን አዲሱን የምንቀበልበት ዘመን ላይ እንገኛለን።

የተወደዳችሁ ምእመናን ፍጥረታትን ማደስ የእግዚአብሔር ሥራ ቢሆንም ከፈጣሪ በተሰጠው ሥልጣን ሰውም የማደስና የመምራት ሥልጣን አለው። ዛሬ ዓለማችን በመታደስ ሳይሆን በማርጀት ላይ የምትገኘው ከሰዎች ድርጊት የተነሳ ነው። እየተፈጠረ ያለው ችግር ከሰው አጠቃቀም ስህተት እንደሆነ እየሰማን እና እያየን ነው።

ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ሰው ምደረ በዳውን ወደ ሐመልማለ ገነት የሚቀይርበትንም ሁኔታ እያየን ነው ፣ይህ ሰው የማልማትም ሆነ የማጥፋት ሚና እንዳለው ያሳያል። ሰዎች የላቀ እድገትን ሲያስመዘግቡ በመታደስ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል። የዚህን ተቃራኒ ይዘው የተጓዙ ከሆነ ማርጀትን ይዘው እየተጓዙ ስለሆነ በመታደስ መኖር አለብን።

የተወደዳችሁ ምእመናን የክርስትና ሃይማኖት የመጨረሻ ግብ የፍጥረታት መታደስ ነው። ከሞት በኋላ ትንሳኤ ፤ ከዚያም እንከን የሌለው ጣዕመ ሕይወት አለ ብሎ ሰውን ለዘለዓለማዊ ሕዳሴ ማብቃት ነው። ከዚህ አንጻር ሰው ማርጀት ሳይሆን መታደስ እንዳለበት ፤ እግዚአብሔር የፍጥረቱን መታደስ በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድርም ስለሚፈልገው ዘመንን እየለወጠ ይመግበናል። ስለዚህ እኛስ ለመታደስ ተዘጋጅተናል ወይ ብለን ራሳችንን መጠየቅና መልሱን ማግኘት ወሳኝ ነው። ለመታደስም ቆራጥ ውሳኔ በመወሰን አዲሱን ዘመን ልንጠቀምበት ይገባናል።

እኛ ኢትዮጵያን ቀድሞ እንበልጣቸው ከነበሩት ሁሉ ወደ ኋላ እየቀረን ከችግሮቻችን ላለመላቀቅ ውል የገባን እስኪመስል ድረስ እየቀጠልንበት ነው። ኢትዮጵያን የመሰለች ሀገር ይዘን እንዲህ ሆነን ስንገኝ ከስንፍናችን በቀን ምንም የጎደለን እንደሌለ ሌሎችም የሚያውቁት ነው። ስለዚህ ለእኔ ለእኔ በመባባል የሕዝባችንን ሰቆቃ አናስረዝም። ኢትዮጵያ የሁሉም ናት ፤ በእኩልነት እና በአንድነት ሀገራችንን እናድስ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከ3000 ዓመታት ውስጥ ከእግዚአብሔር ተለይተን አናውቅም። በዚህም ተጠቃሚዎች እንጂ ተገጂዎች የሆንበት ጊዜ የለም ፤ ሕዝቡም በፈጣሪው የሚያምን ስለሆነ ከዚህ ውጭ እንምራው ብንል ግን ያጋጠመንን ችግር ማስቀጠል ነው የሚሆነው ስለዚህ የሁሉም መነሻ ውጣዊ አእምሮአችኝ ነውና እሱን በማደስ በአዲሱ ዓመት ሀገራችንን እንድናድስ ጥሪ እናቀርባለን።

አዲሱ ዘመን በውይይት ፣ መለያየትን በአንድነት ፣ አለመግባባትን በእርቅ ፈትተን ሁላችንም በመታደስ ማማ ላይ የቆመ ማኅበረሰብን ለመገንባት ጥረት እንድናደርግ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።"

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

ጳጕሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ፤
በሁሉም የሶሻል ሚድያ ገጾች ያገኙናል
በ YouTube ♦️ https://www.youtube.com/
በ Facebook 🔺 https://www.facebook.com/yommediacompany
በ Tiktok 🔴 https://www.tiktok.com/ በ Telgram 📣 https://t.me/yommedia
ፎሎው እና ሼር በማድረግ ያበረታቱን ።

Address

California City, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yom Media ዮም ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yom Media ዮም ሚድያ:

Videos

Share