Anchor Media Ethiopia

Anchor Media Ethiopia Anchor
(2)

07/29/2024

የአብይ አገዛዝ ዛሬ የወሰደው እርምጃ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሞት አዋጅ ነው። መጪው ጊዜ በድቅድቅ ጨለማ የሚዋጥ መሆኑን የመርዶ ያህል የሚወሰድ አስደንጋጭ ዜና ነው። አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ስር የሰደደ ንቀትና ጥላቻ ያሳየበት ደግሞ ይህን የሞት አዋጅ 'እንኳን ደስ አለን' ብሎ ህዝቡን ለእልልታ መጥራቱ ነው። ለቅሶህን ጨፍርበት፥ ሀዘንህን ቦርቅበት፥ የመጣብህን መከራ በፌሽታና ዳንኪራ ተቀበለው፥ ዓይነት ጥሪ ማድረጉ በእርግጥም የሰውዬውን የጭካኔ ጥግ የሚያሳይ ነው።

የብልጽግና ግሪሳ ፈንዲሻ እየነሰነሰ ነው። ካድሬው ባዶ ሆዱንና ጭንቅላቱን ይዞ ከበሮ እየደለቀ ነው። ወዶ ገቡም እጁን በጭብጨባ ብዛት አዝሎታል። የብልጽግና ሹማምንትም የውስኪ አንገት አንቀው ብርጭቆ አጋጭተው እየፈነጠዙ ነው። መከረኛው ህዝብ ግን ከነገ ጀምሮ የሞት አዋጁ ተፈጻሚ ይሆንበታል። ከድጡ ወደ ማጡ ዘው ብሎ ይገባል። በእንቅርቱ ላይ በጆሮ ደግፍ ተይዞ የሲቃ ጣሩን ማሰማት ይጀምራል።

ኢትዮጵያዬ ሆይ መቼ ይሆን ከዚህ ሰው እጅ ላይ የምታመልጪው? የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዲህ የምታመነው ፈጣሪ ከጎንህ ይሆን። የኬኒያና የኡጋንዳ በረከት ይደርብህ።

07/28/2024

ከከበሮው ድለቃና ከአብይ ሚዲያዎች የ'እንኳን ደስ አለን' ስላቅ ባሻገር የዛሬውን የአብይን አርምጃ አንድ የኢኮኖሚ ባለሙያ በአጭሩ በምሳሌ እንዲህ አስረዳኝ።

አንድ ቁማርተኛ ሁሉን ነገር ቁማር በልቶበት፥ ገንዘቡን ጨርሶ፥ ያፈራውን ንብረትና ሀብት በሙሉ ለቁማር አሲዞ ተበልቶ እሱ ብቻ ይቀራል። እዳ አለበት። የሚከፍለው የለውም። ተበድሮ እንዳይጫወትና እንዳይመልስ አንድ የሚያበድረው ሰው ያጣል። እዳውን ለመክፈል የቀረው ብቸኛ ምርጫ ያበደሩት ሰዎች የሚሉትን መቀበል ብቻ ነው። እነሱ ደግሞ ኩላሊት ፈልገዋል። አይን ፈልገዋል። ልብ ፈልገዋል። ቢያንስ ሁለት የሰውነት ኦርጋኖቹን እንዲሰጥ ጠየቁት። ምርጫ አልነበረውም። የሰውነት አካሉን እየቸረቸረ ለመስጠት ተስማማ።

አብይ ያደረገው ይህንን ነው። እንዲህ ዓይነት እርምጃ ወስዶ ነው የኢትዮጵያን ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ የሚለው። ጨካኝ ነው። አረመኔ።

07/27/2024

በጎንደር ለአብይ አህመድ ድጋፍ ሰልፍ ተደረገ የሚል ዜና ስሰማ በዩክሬን መዲና ኪዬቭ ለሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን ድጋፍ ትዕይንተ ህዝብ ይደረጋል እንዴ? ብሎ አንዱ ቢጠይቅ ''ለእኔ ደግሞ አይሁዶች የአዶልፍ ሂትለርን ቲሸርት ለብሰው በቴለቪቭ ሰልፍ ያደረጉ ያህል ነው የተሰማኝ'' ብሎ መለሰለት። ሁለቱም ልክ ናቸው።

#ብልጽግና የቀነጨረ ፓርቲ

07/22/2024

ኮማንደር አሰግድ መኮንን ለአገዛዙ እጁን ሰጠ የሚለው የብልጽግናው ዲጂታል ሰራዊትን ወሬ ለማጣራት የተወሰኑ ሙከራዎች አድርጌአለሁ። ማረጋገጫ ማገኘት አልቻልኩም። ሆኖም አንድ የሰሜን ሸዋ እዝ ከፍተኛ አመራር ሊሆን የማይችል የካድሬዎች ጫጫታ ነው የሚል መልስ ሰጠኝ። ማታ በስልክ እንደተገናኙና በዚህ አጭር ሰዓታት ውስጥ ሊለወጥ የሚችል ተአምር እንደሌለም ነገሩኝ። ለጊዜው የኮማንደሩና አጠገቡ ያሉት ሁለት ሰዎች ስልክ ዝግ በመሆኑ አሁን ያለውን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ነገር ግን ''ኮማንደር አሰግድ እጅ ከሚሰጥ ራሱን ቢያጠፋ እንደሚመርጥ'' በመግለጽ አመራሩ እርግጠኝነቱን አሳየኝ። ''ብዙ ጊዜ ኔትወርክ ስለማይኖር እንዲህ ዓይነት በስልክ አለመገናኘት የተለመደ እንደሆነና ዛሬ ምን ተፈጥሮ ወሬው እንደተዛመተ አላውቅም'' በማለትም አብራራልኝ። ወደኋላ ላይ የሆነ ነገር እንደሚኖር ነግሮኝ ተለያየን።

እንግዲህ ስለጉዳዩ የማሳመን ሸክሙ የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊት ላይ ወድቋል። ያዝን፡ እጁን ሰጠን ካሉ ያቅርቡና ያሳዩን። በተረፈ ቢሆንም ባይሆንም ትግል ነውና ትግሉ ይቀጥላል። ግለሰቦች በትግሉ ላይ የሚኖራቸው ሚና እንደተጠበቀ ሆኖ የመኖራቸውና ያለመኖራቸው ተጽዕኖ ለህልወና ሲባል በተጀመረ ትግል ላይ የሚፈጥረው ኪሳራ ኢምንት ነው። የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ግለሰቦች አላስጀመሩትም። ግለሰቦችም አያስቆሙትም። የጥቂት ቀናት ወሬ ሆኖ ይጠፋል። ትግል ይቀጥላል። ብልጽግናዎች ከበሮ መደለቁን በልኩ አድርጉት። ደረት መድቃትም ይኖራልና።

የአቡሽ ዘለቀ አዲሱ ነጠላ ዘፈን ድንቅ ነው። አቡሽ ኪነጥበብን ለህዝብ ልሳን በማድረግ ከፊት ረድፍ ከሚጠቀሱት ዋናው ድምጻዊ እየሆነ ነው። የወቅቱን የኢትዮጵያን ህዝብ አስከፊ ሰቆቃ በግልጽ ...
07/13/2024

የአቡሽ ዘለቀ አዲሱ ነጠላ ዘፈን ድንቅ ነው። አቡሽ ኪነጥበብን ለህዝብ ልሳን በማድረግ ከፊት ረድፍ ከሚጠቀሱት ዋናው ድምጻዊ እየሆነ ነው። የወቅቱን የኢትዮጵያን ህዝብ አስከፊ ሰቆቃ በግልጽ አስቀምጦታል። ትልቅ ስራ ነው። አቡሽ በርታ!

ሁሉም በእኩልነት፣ ካልኖረ በሀገሩ
ከምን ሊያድነን ነው፣ ዘንባባ እና ሳሩ
አለባብሶ ቢያርሱ፣ አረሙ አይቀር ነገር
እውነቱን ተናግሮ፣ የመሸበት ማደር
ባዶ ይሁን ኪሴ፣ ኖሬ ከሰው ጋራ
ህሊናዬን ሸጬ፣ አልበላም እንጀራ
ከቂም ከጥላቻ፣ እስካልወጣን ድረስ
ነገራችን ሁሉ፣ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ
እንዴትም ቢታሰብ፣ እንዴትም ቢሰላ
ጎብዝ ከዛፉ ይልቅ፣ ሰው ነው የሰው ጥላ
ሁሉም በእኩልነት፣ ካልኖረ በሀገሩ
ከምን ሊያድነን ነው፣ ዘንባባ እና ሳሩ

“Abush Zeleke - HAGER ENA SEW (ሀገር እና ሰው)” is more than just a song; it’s an anthem for Ethiopian hearts. Abush’s soulful voice resonates with those who cher...

Address

4921 Seminary Road
Alexandria, VA
22311

Telephone

+15713094278

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anchor Media Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Anchor Media Ethiopia:

Videos

Share


Other News & Media Websites in Alexandria

Show All