TGEthiopianBroadcasting

TGEthiopianBroadcasting TG Ethiopian Broadcasting, LLC is a media company based in Alexandria, Virginia (United States). TG

TG stands for the late Dr. Artist Tilahun Gessesse who is the King of Ethiopian music

ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የብር ሜዳልያ አገኘችዛሬ ጠዋት (August 11, 2024)  በፓሪስ ኦሎምፒክ በተደረገው የሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት ትግስት አሰፋ ሁለተኛ በመውጣት (2፡22፡58)...
08/11/2024

ኢትዮጵያ ሶስተኛውን የብር ሜዳልያ አገኘች
ዛሬ ጠዋት (August 11, 2024) በፓሪስ ኦሎምፒክ በተደረገው የሴቶች የማራቶን ውድድር አትሌት ትግስት አሰፋ ሁለተኛ በመውጣት (2፡22፡58) ለኢትዮጵያ ሶስተኛውን የብር ሜዳልያ አስገኝታለች። አትሌት አማኒ ሻንቁሌ አምስተኛ በመውጣት ውድድሩን ጨርሳለች። አትሌት መገርቱ አለሙ ውድድሩን ሳትጨርስ አቋርጣ ወጥታለች።
የኔዘርላንዷ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሃሰን አንደኛ በመውጣት (2፡22፡55) የወርቅ ሜዳልያ ለኔዘርላንድ አስገኝታለች።
የኬንያዊዋ አትሌት ሄለን ኦቢሪ ሶስተኛ በመውጣት ለኬንያ የነሃስ ሜዳልያ አስገኝታለች።

በዚህም የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ አንድ የወርቅ ሜዳልያ (በወንዶች ማራቶን)፣ በ800 ሜትር፣ በ10000 ሜትርና በሴቶች ማራቶን ሩጫ ሶስት የብር ሜዳልያዎችን በአጠቃላይ አራት ሜዳልያዎችን በማግኘት የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክን በ45ኛ ደረጃ አጠናቃለች።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን

ዛሬ (August 10, 2024) በተደረገው የወንዶች የ5000 (5ሺ) ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ውድድር የኖርዌው አትሌት Jakob INGEBRIGTSEN (13፡13፡68) አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜ...
08/10/2024

ዛሬ (August 10, 2024) በተደረገው የወንዶች የ5000 (5ሺ) ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ውድድር የኖርዌው አትሌት Jakob INGEBRIGTSEN (13፡13፡68) አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ አግኝቷል;። የኬንያው አትሌት Ronald KWEMOI (13፡15፡04) ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ሲያገኝ ፣ አሜሪካዊው Grant FISHER (13፡15፡13) ሶስተኛ በመሆን የነሃስ ሜዳልያ አግኝቶአል። በዚህም ውድድር ላይ የተሳፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን፣ አትሌት ሃጎስ ገብረህይወት (13፡15፡32) አምስተኛ፣ አትሌት ቢኒያም መሃሪ (13፡15፡99) ስድስተኛ በመውጣት ውድድሩን ጨርሰዋል።

እንዲሁም ቀጥሎ በተደረገው የሴቶች የአንድ ሺ አምስት መቶ (1500) ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ውድድር የኬንያዋ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን (3፡51፡29) አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች;። የኣውስትራሊያዋ አትሌት ጄሲካ ሁል ሁለተኛ፣ እንዲሁም የእንግሊዟ ጆርጂያ ቤል ሶስተኛ በመሆን ጨርሰዋል። በዚህም ውድድር ላይ የተሳፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን፣ አትሌት ደርቤ ወልተጂ አራተኛ ((3፡52፡75)፣ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ (4፡01፡27) 12ተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሰዋል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊ ናኦሚ ግርማ የተሳተፈችበት የአሜሪካ ብሔራዊ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በፓሪስ ኦሎምፒክ ከብራዚል የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገው የፍጻሜ ግጥሚያ ብራዚልን አንድ ለባዶ...
08/10/2024

ትውልደ ኢትዮጵያዊ ናኦሚ ግርማ የተሳተፈችበት የአሜሪካ ብሔራዊ የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን በፓሪስ ኦሎምፒክ ከብራዚል የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገው የፍጻሜ ግጥሚያ ብራዚልን አንድ ለባዶ በማሸነነፍ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ሆኗል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በፓሪስ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘችየዛሬው የAugust 10, 2010  የፓሪስ አየር ሁኔታ አጅግ በጣም ሞቃታማና (brutal heat and humidit...
08/10/2024

ኢትዮጵያ ሀገራችን በፓሪስ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
የዛሬው የAugust 10, 2010 የፓሪስ አየር ሁኔታ አጅግ በጣም ሞቃታማና (brutal heat and humidity) የነበረበት ነበር። ታዲያ ይህን በጣም አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ በመቋቋም አትሌት ታምራት ቶላ የኦሎምፒክን ማራቶን ሬከርድ በመስበር በ2፡06፡26 በመጨረስ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቶአል። የቤልጅየሙ ባሽር አቢዲ ሁለተኛ በመውጣት ሲጨርስ፣ የኬንያው ቤንሰን ኪፕሩቶ ሶስተኛ ወጥቶአል።
World Athletics በዚህ መልክ ነበር የታምራት ቶላን ማሸነፍ የገለጸው...
“Ethiopia’s late sub Tola wins marathon in Olympic record in brutal conditions over hugely challenging course”.
France 24 ደግሞ የአትሌት ታምትራት ቶላን ማሸነፍ በዚህ መልክ አስቀምጦታል፣ “Ethiopian Tamirat Tola delivered a masterclass in solo front running to win the Olympic men's marathon in Paris on Saturday as Eliud Kipchoge's bid for a third gold went up in smoke”.
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 2፡12፡24 በሆነ ግዜ 39ጠነኛ ሆኖ ሲጨርስ፣ የሁለት ግዜ የኦሎምፒክ ማራቶን የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ የሆነው ኬንያዊው Eliud Kipchoge 19 ማይልስ ከሮጠ በኋላ ውድድሩን አቋርጦአል።

ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን ባይቀናችሁንም ብርታቱን ይስጣችሁዛሬ (August 9, 2024) በፓሪስ ኦሎምፒክ በተደረገው የሴቶቸ የ10000 ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ፣ አት...
08/09/2024

ኢትዮጵያውያን አትሌቶቻችን ባይቀናችሁንም ብርታቱን ይስጣችሁ
ዛሬ (August 9, 2024) በፓሪስ ኦሎምፒክ በተደረገው የሴቶቸ የ10000 ሜትር የፍጻሜ ሩጫ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ፣ አትሌት ጽጌ ገብረሰላማና አትሌት ፎትየን ተስፋይ ተሳትፈው ነብር። በዚህም ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ስድስተኛ፣ ፎተን ተስፋይ ሰባተኛ በመሆን ጨርሰዋል። የኬንያ አትሌት ቢትርስ ቺበት አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሚዳልያ ለኬንያ ስታገኝ፣ የጣሊያኗ አትሌት ናዲያ ባቶስሌቲ 2ተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታገኝ፣ የኔዘርላንዷና ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነችው ሲፋን ሃሰን ሶስተኛ በመውጣት የነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች።

ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀችው የኬንያ አትሌት የብር ሜዳሊያዋን ተነጠቀችበፓሪስ በሚደረገው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ሀገራችን እስካሁን ድረስ ሁለት (2) የብር ሜዳልያዎችን አግኝታለች። ዛሬ...
08/05/2024

ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቀችው የኬንያ አትሌት የብር ሜዳሊያዋን ተነጠቀች

በፓሪስ በሚደረገው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ ሀገራችን እስካሁን ድረስ ሁለት (2) የብር ሜዳልያዎችን አግኝታለች። ዛሬ ማለትም August 5, 2024 በተደረገው የ800 ሜትር ሩጫ የፍጻሜ ውድድር አትሌት ጽጌ ድጉማ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።
እንዲሁም ዛሬ በተደረገው የሴቶች የአምስት ሺ (5000) ሜትር ሩጫ የፍጻሜ ውድድር የኬንያ አትሌት ቢትርስ ችቤት አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ ስታገኝ ሌላዋ የኬንያ አትሌት ፌይዝ ኪፕዬጎን ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ያገኘች ብትመስልም በሩጫው ጊዜ የኦሎምፒክን ደንብ በሚጥስ ሁኔታ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬን በመጋፋቷ disqualified በመሆን በሷ ምትክ የኔዘርላንዷ ሲፋን ሃሰን ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳልያ ስታገኝ የጣሊያኗ አትሌት ናዲያ ደግሞ ሶስተኛውን ቦታ በመያዝ የነሃስ ሜዳልያ ባላቤት ሆናለች። ኢትዮጵያ ሀገራችንን በመወከል በዚህ የ5000 ሺ ሜትር የፍጻሜ ውድድር የተሳፉት አትሌት እጅጋየሁ ታዬ (5) አምስተኛ፣ መዲና ኤልሳ (6) ሰድስተና እንዲሁም ጉዳፍ ጸጋይ (8) ስምንተና በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል። ማሽነፍና መሸነፍ ያለ ስለሆነ አትሌቶቻችን እንኮራባችኋለን አሁንም በርቱ እንላለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን እያልን የዛሬውን የፓሪስ ኦሎምፒክ የሩጫ ውድድር የሚያሳየውን ቪድዮ ሊንኩን በመጫን እንድታዩ እንጋብዛለን።እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን

https://youtu.be/YrYyytkMmqU?si=wss0vFXf64K8NWix
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን

ዛሬ በፓሪስ ኦሎምፒክ  በተደረገው የአስር ሺ (10000)ሜትር ሩጫ በሪሁን አረጋዊ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አስገኝቶአል። ኡጋንዳዊው ቺፒቴገል አንደኛ በመውጣ...
08/02/2024

ዛሬ በፓሪስ ኦሎምፒክ በተደረገው የአስር ሺ (10000)ሜትር ሩጫ በሪሁን አረጋዊ ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አስገኝቶአል። ኡጋንዳዊው ቺፒቴገል አንደኛ በመውጣት ለኡጋንዳ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አስገኝቶል። በዚህም የ10000 ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት ከጀላ ዮሚፍ ስድስተኛ፣ ሰለሞን ባረጋ ሰባተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን በሚቀጥለው የፕሬዝዳንትነት ምርጫ እንደማይወዳደሩ በX(formerley twitter) ገጻቸው ላይ በማሳወቅ እንዲህ ብለዋል።“My fellow Democrats, I have de...
07/21/2024

ፕሬዝዳንት ባይደን በሚቀጥለው የፕሬዝዳንትነት ምርጫ እንደማይወዳደሩ በX(formerley twitter) ገጻቸው ላይ በማሳወቅ እንዲህ ብለዋል።
“My fellow Democrats, I have decided not to accept the nomination and to focus all my energys on my duties as president for the reminder of my term. My very first decision as the party nominee in 2020 was to pick Kamala Haris as my Vice Peresident. And it’s been the best decision I’ve made. Today I want to offer my full suppport and endorsement for Kamala to be the nominee of our party this year. Democrats-it’s time to come together and beat Trump. Let’s do this.”
ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ውሳኔያቸውን በተመለከተ ለአሜሪካን ሕዝብ በቅርቡ ንግግር ያደርጋሉ። ሪፐፕሊካኖች ደግሞ ለፕሬዚዳንት እጩ ሆኖ የቀረበውንም መተካት አይቻልም በማለት ከአሁኑ ክስ እንመሰርታለን እያሉ ነው።
https://x.com/JoeBiden/status/1815087772216303933

በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገለሚቀጥለው የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ በሪፓፕሊካን በኩል በዋነኛነት የሚወዳደሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በButler, Pennsylvani...
07/14/2024

በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ
ለሚቀጥለው የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ በሪፓፕሊካን በኩል በዋነኛነት የሚወዳደሩት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ትራምፕ በButler, Pennsylvania የምረጡኝ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ጊዜ የመግደል ሙከራ ቢደረግባቸውም የተተኮሰባቸው ጥይት የቀኝ ጆሮቸውን መትቶ በማለፉ ተርፈዋል።
በዚህም የግድያ ሙከራ ጊዜ በስብሰባው ላይ ከነበሩት ተሳታፊዎች መካከል አንዱ ሲገደል ሁለት ሰዎች ደግሞ በጠና መቁሰካቸው ሲገለጽ፣ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ የመግደል ሙከራ ያደረገው በBethel Park, Pennsylvania ነዋሪ የሆነው የ20 ዓመቱ ወጣት ቶማስ ማቲው ክሩክስ (Thomas Matthew Crooks) ደግሞ በሴክሬት ሰርቪስ አነጣጣሪ ተኳሽ መገደሉ ተገልጿል።

https://abcnews.go.com/Politics/video/trump-rushed-off-stage-shots-heard-rally-shooter-111915965

https://youtu.be/iMIbPXS3e7Y?si=xOYs_Pxq9duKlVvc

Waiting for the Fourth of July celebration at the White House. The journalists seated next to me are from 7 news Austral...
07/04/2024

Waiting for the Fourth of July celebration at the White House. The journalists seated next to me are from 7 news Australia.
Proud to be the only Ethiopian correspondent at the White House.
Happy 4th of July!

07/03/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተደጋጋሚ ሽልማቶችን በማግኘት አሁንም ኢትዮጵያ ሀገራችንን በዓለም ላይ በሚያምር ሁኔታ እያስጠራ ነው...
ኢትዮጵያውያንን በብዛት በማሰባሰብ እስከአሁን ተወዳዳሪ ያልተገኘለት የስፖርትና የባህል ዝግጅት...

በጣም አሳዛኝዜናው የቢቢሲ ነው.።በአድዋ ከተማ ለወራት ታግታ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ።በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ባልታወቁ ግለሰቦች ታግታ ሦስት ሚሊዮን ...
06/19/2024

በጣም አሳዛኝ
ዜናው የቢቢሲ ነው.።
በአድዋ ከተማ ለወራት ታግታ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ።
በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ባልታወቁ ግለሰቦች ታግታ ሦስት ሚሊዮን ብር ተጠይቆባት የነበራችው የ16 ዓመቷ ታዳጊ መገደሏን ፖሊስ ተገለጸ።
የአድዋ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ አማረ ረቡዕ ሰኔ 12/2016 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ ማኅሌት ተኽላይ ተቀብራበታለች በተባለበት ቦታ በተካሄደ ቁፋሮ አስክሬኗን ማውጣቱን ገልጸዋል።
ፖሊስ ታዳጊዋ ተቀብራበታለች የተባለው ቦታ ጥቆማ የደረሰው ማኅሌት ተኽላይን በማገት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ታዳጊዋን ገድለው መቅበራቸውን አምነው የቀብር ቦታውን መርተው ካሳዩ በኋላ መሆኑን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።
የ16 ዓመት ታዳጊዋ ማኅሌት ተኽላይ በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን አድዋ ከተማ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም. ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከታገተች በኋላ ሦስት ሚሊዮን የማስለቀቂያ ብር ተጠይቆባት ነበር።
ኃላፊው ፖሊስ የታዳጊዋ አስክሬን ተቀብሮበታል በተባለው ቦታ ላይ ቁፋሮ በማድረግ አስከሬን ያወጣ ሲሆን፣ ከስፍራው የታጋቿ ልብስ እና ጫማን ማግኘቱንም ገልጸዋል።
የአድዋ ከተማ ፖሊስ ኃላፊ ተስፋዬ አማረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት አስክሬኑ በቁፋሮ ከወጣ በኋላ የታዳጊዋ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ በባለሙያ ምርመራ እየተደረገበ መሆኑንም ተናግረዋል።
በአድዋ ከተማዋ የሚገኙ የቢቢሲ ምንጮች እንደተናገሩት የማኅሌት ተኽላይ ቤተሰቦች መርዶው በፖሊስ ተነግሯቸው ሐዘን ተቀምጠዋል።
ማኅሌት ከሦስት ወራት በፊትን ነበር ወደ ትምህርት ቤት ብላ ከቤቷ ከወጣች በኋላ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታፍና መወሰዷን ታላቅ እህቷ ሚሊዮን ተኽላይ ከዚህ ቀደም ለቢቢሲ ተናግራ ነበር።
ማኅሌት ታግታ በነበረችበት ወቅት ለቢቢሲ ቃለ መጠይቅ ያደረችው እህቷ ሚሊዮን፣ አጋቾቹ ታዳጊዋን ለመልቀቅ ሁለት ጊዜ ወደ አባቷ ስልክ ደውለው ነበር።
“ድምጿን አልሰማንም . . . አባታችንም ምን እንደሚፈልጉ እና እንዴት እንደሚሰጣቸው ጠይቋቸው ነበር። እነሱም ‘የምንልህን ለመስጠት ታዘጋጃለህ’ ካሉ በኋላ ስልካቸውን እየጠበቅን ነው” ብላ ነበር።
ማኅሌት በዚህ ዓመት ወደ ሁለተኛ ደረጃ የሚያሸጋግራትን የ8ኛ ክፍል ፈተና ለመውሰድ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተማረች ሳለ ነበር የታገተችው።
ቤተሰብ ወደ ቋንቋ ትምህርት ቤት በባጃጅ ስትጓዝ ታግታ የተወሰደችባቸውን ልጃቸውን “ሥነ ምግባር ያላት የቤት ልጅ” ሲሉ ይገልጿታል።
ከእገታው በኋላ አጋቾቹ በማኅሌት ስልክ ወደ ወላጅ አባቷ ስልክ በመደወል “ልጅህን በሕይወት ማየት የምትፈልግ ከሆነ ሦስት ሚሊዮን ብር አዘጋጅ” የሚል ትዕዛዝ ሰጥተው እንደነበረ ሚሊዮን ለቢቢሲ ገልጻ ነበር።
ማኅሌት ከታገተች በኋላ ቤተሰብ ልጃቸው ያለችበትን ቦታ እና አጋቾቿን ለማወቅ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ የትግራይ ክልል አካባቢዎች በታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም እገታ እየተበራከተ ይገኛል።
ድርጊቱን የሚፈጽሙ ግለሰቦች አብዛኛውን ጊዜ እገታውን ለመፈጸም ባለ ሦስት ጎማ ተሽከርካሪዎችን እንደሚጠቀሙ ይገለጻል።
ቀደም ብሎ በመቀለ ከተማ በሚገኙ የተለዩ ክፍለ ከተሞች ከትምህርት ቤት ልጆች አግተው ሲወስዱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ የከተማዋ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ ገልጾ ነበር።
ባለፈው ወር መጋቢት አቶ መሃሪ ከበደ የተባሉ ግለሰብ ልጅ የሆነ ህጻን ታግቶ ተወስዶ ቤተሰቦች አራት ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው ነበር።
ህጻኑ ከአንድ ሳምንት በላይ በእገታ ስር የቆየ ሲሆን፣ ቤተሰቦች ከከተማዋ ፖሊስ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት ህጻኑ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም. ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር መቀላለቁን ቢቢሲ በወቅቱ ዘግቦ ነበር።
ምንጭ፡ ቢቢሲ

05/27/2024

የኬንያው ፕሬዚዳንት በአሜሪካ ያደረጉት አስገራሚ ጉብኝት...

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ። መልካም የፋሲካ በዓል።የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደንም የፋሲካ በዓልን በተመለከተ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል።THE WH...
05/05/2024

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ። መልካም የፋሲካ በዓል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደንም የፋሲካ በዓልን በተመለከተ የሚከተለውን መልእክት አስተላልፈዋል።

THE WHITE HOUSE
FOR IMMEDIATE RELEASE
May 5, 2024

Statement from President Joe Biden on Orthodox Easter

Jill and I send warm wishes to Orthodox Christian communities around the world as they celebrate Easter.

The Resurrection of Jesus Christ reminds us of God’s abundant love for us and the power of light over darkness. We join Orthodox Christians in giving thanks for these and other blessings and rededicate ourselves to caring for those most in need.

In this sacred season, we hold people who are suffering from war and persecution especially close to our hearts. We will continue to pray and work for peace and justice for all people.

May the Lord bless and keep you this Easter Sunday and in the year ahead.

አትላንታ እንዲሆን ተወሰነ41ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ስፖርትና የባህል ዝግጅት “ኢትዮጵያዊነት ይቅደም” በሚል መርሆ ከJune 29 ጀምሮ እስከ July 6, 2024, በአትላንታ ይካሄዳል። The...
05/04/2024

አትላንታ እንዲሆን ተወሰነ
41ኛው ዓመት የኢትዮጵያ ስፖርትና የባህል ዝግጅት “ኢትዮጵያዊነት ይቅደም” በሚል መርሆ ከJune 29 ጀምሮ እስከ July 6, 2024, በአትላንታ ይካሄዳል።
The 41st Ethiopian Sports Federation in North America Annual Festival will be held in Atlanta city from June 29 to July 6, 2024.
For more information visit www.esfna.org
Ethiopia First!

በጣም አሳዛኝበትናትናው ቀን በአትላንታ የተፈጠረው ድርጊት እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። በጣም ተወዳጅና ሰው አክባሪ ዶክተር አርቲስት ትግስት ልዑልሰገድ በተተኮሰባት ጥይት ምክንያት ከዚህ ዓለም...
04/29/2024

በጣም አሳዛኝ
በትናትናው ቀን በአትላንታ የተፈጠረው ድርጊት እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። በጣም ተወዳጅና ሰው አክባሪ ዶክተር አርቲስት ትግስት ልዑልሰገድ በተተኮሰባት ጥይት ምክንያት ከዚህ ዓለም ድጋፍ አርፋለች። ዶክተርም የተባለችው እንደሌሎች አርቲስቶች የክብር ዶክትሬት አግኝታ ሳይሆን የህክምና ትምህርቷን በሚገባ አጠናቃ ያገኘችው ዶክተርነት ነው። ዶክተር አርቲስት ትግስት በድምጻዊነት ብቻ ሳይሆን በህክምና ሙያዋ በጣም የተሳካላት ዶክተር ነበረች።
የዶክተር አርቲስት ትግስት ልዑልሰገድ ሞትን በተመለከተ በአትላንታ የሚገኙ ሚዲያዎች The Atlanta Journal Constitution፣ Fox News ዶ/ር አርቲስት ትግስት በቀድሞ ባሏ እንደተገደለችና በተጨማሪም የቀድሞ ባሏ አሁን 62 ዓመት የሆናቸውን ባላቤቷ ላይ በመተኮስ እግራቸውን እንዳቆሰለ ዘግበዋል። ይህ ፍፁም ከእውነት የራቀ ዘገባ ነው። ዶክተር አርቲስት ትግስት የታዋቂው ጋዜጠኛ የዳዊት ከበደ ዋይሳ ባለቤት የነበረች ሲሆን ባሏም ከሞተ በኋላ ሌላ ባል አላገባችም።
ዶ/ር አርቲስት ትግስት ልዑልሰገድ የተገደለችው በታላቅ እህቷ የቀድሞ ባል በተተኮሰ ጥይት ነው። የዶ/ር አርቲስት ትግስት እህት የቀድሞ ባል ዶ/ር ትግስት ላይ በተደጋጋሚ ከተኮሰ በኋላ እንዲሁም በጣና ማርት በነበሩት የ62 ዓመት አዛውንት ላይ በመተኮስ እግራቸውን ካቆሰለ በኋላ ራሱን ለማጥፋት በራሱ ጭንቅላት ላይ ቢተኩስም ለሞት አልተዳረገም። ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት Lawrenceville, Georgia በሚገኘው Northside Hospital Gwinnett ውስጥ በከፍተኛ ሕክምና ላይ ይገኛል።
ዶ/ር አርቲስት ትግስት በጣም ብዙዎችን የምትረዳ ታላቅ ሰው ነበረች። በደረሰባት ድንገተኛ ሞት የተሰማን ሀዘን በጣም ጥልቅ ነው። እግዚአብሔር ለቤተሰቦቿ ለዘመዶቿና ለጓደኞቿ ጽናቱን ይስጥልን። እግዚአብሔር ነፍሷን ይማርልን፣ በገነትም ያኑርልን።

በሼክ መሐመድ አላሙዲና በአቶ አብነት ገብረ መስቀል መካከል የተጀመረውን ክስ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቶአል። ይህንንም በተመለከተ የኢትዮጵያን ሪፖርተር ጋዜጣ እንደሚከተለው አውጥቶታል...
04/14/2024

በሼክ መሐመድ አላሙዲና በአቶ አብነት ገብረ መስቀል መካከል የተጀመረውን ክስ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቶአል። ይህንንም በተመለከተ የኢትዮጵያን ሪፖርተር ጋዜጣ እንደሚከተለው አውጥቶታል።

ከቦሌም (በስተቀኝ በኩል) ሆነ ከመስቀል አደባባይ (በስተግራ) ሲኬድ ወሎ ሠፈር ማዞሪያ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የግል ማኅበር፣ 60 በመቶ ባለድርሻ የሆኑትን ሼክ መሐመድ ዓሊ አላሙዲንን፣ ከባለድርሻነት እንዲወጡ ወይም ማኅበሩ እንዲፈርስ፣ አቶ አብነት ገብረ መስቀል ክስ የመሠረቱ ቢሆም፣ ክሱን የመረመረው ፍርድ ቤት እራሳቸው አቶ አብነት ከባለድርሻነት እንዲወጡ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ውሳኔ ሰጠ፡፡
የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የንግድና ኢንቨስትመንት ችሎት፣ አቶ አብነት ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ያቀረቡትን የክስ አቤቱታ ሲመረምር ቆይቶ በተጠቀሰው ቀን ውሳኔ የሰጠው፣ ስለክሱ አነሳስ፣ በተመሳሳይ ጉዳዮችን ላይ ሰበር ስለሰጣቸው አስገዳጅ የሕግ ውሳኔዎች፣ የንግድ ሕጉንና ሌሎች ተዛማች ሕጎች፣ በስፋት ከመረመረ በኋላ መሆኑን የፍርድ ሀተታው ያሳያል፡፡
ቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የተቋቋመው ከ22 ዓመታት በፊት በሼክ መሐመድ 60 በመቶ ባለድርሻነትና በአቶ አብነት 40 በመቶ የባለድርሻነት በአሥር ሚሊዮን ብር በተከፈለ ካፒታል ቢሆንም፣ እ.ኤ.አ. ካፒታሉ ወደ 545 ሚሊዮን እንዲያድግ መደረጉንም የክሱ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡
አቶ አብነት በክሳቸው ስለተቋሙ ሲያስረዱ፣ ሁለቱም ባለድርሻዎች እንደ ድርሻቸው መጠን ባሳደጉት ካፒታል መጠን ክፍያ ለመፈጸም በተስማሙት መሠረት፣ እሳቸው ከ1992 እስከ1997 ዓ.ም. ድረስ በሊዝ ይዘውት የቆዩትን የግል ይዞታ ለማኅበሩ በመክፈል (በመስጠት) የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡ ነገር ግን ክስ የተመሠረተባቸው ሼክ መሐመድ ወይም ማኅበሩ ግን ምንም ነገር እንዳልከፈሉ ክሱ ያስረዳል፡፡ ማኅበሩ (ቦሌ ታወርስ) በ5,189 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እያስገነባ ባለው ሕንፃ፣ ሼክ መሐመድ ባላቸው የድርሻ መጠንና ሁለቱም ባለድርሻዎች በስምምነት ባሳደጉት ካፒታል (545,000,000 ብር) ለግንባታው እንዲከፍሉ የተስማሙ ቢሆንም፣ ሼክ መሐመድ ሊከፍሏቸው አለመቻላቸውን አቶ አብነት በክሳቸው ገልጸዋል፡፡ አቶ አብነት የማኅበሩን ሕንፃ ለማስጨረስ ከዳሸን ባንክ 425,000,000 ብር በመበደር የሕንፃውን ቦሌ ኤ እና ቦሌ ቢ ተብለው ከተሰየሙት ውስጥ ቦሌ – ኤ የሚባለውን የተወሰነውን አስገንብተው መጨረሻቸውንና የተወሰነውን ክፍል ለኪራይ እንዲውል መደረጉንም አብራርተዋል፡፡
ከሳሽ በክሱ እንዳብራሩት እሳቸው (አቶ አብነት) ያላቸውን ልምድ፣ ገንዘብና ዕውቀት ተጠቅመው ሕንፃውን ቢያጠናቅቁም፣ ሼክ መሐመድ በድርሻቸው መጠን ክፍያ እንዲፈጽሙላቸው ሲጠይቋቸው ባለመስማማታቸው፣ ማኅበሩ ከዳሸን ባንክ የተበዳሪውን 425,000,000 ብርና ሌች ወጪዎችን እንዲከፍሏቸው ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ጉዳዮች ምድብ ችሎ ክስ መሥርተው በሒደት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
ሼክ መሐመድም በተመሳሳይ ሁኔታ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ጉዳዮ ችሎት ክስ መሥርተው፣ ክሱ በሒደት ላይ መሆኑን አቶ አብነት በክሳቸው ጠቁመው፣ ማኅበሩ ቦሌ – ሲ እና ቦሌ – ዲ ተብለው የሚታወቁ 3,383 ካሬ ሜትርና 1,971 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ይዞታዎች ላይ ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው፣ ለግንባታው 120,000,000 ብር ያወጡ በመሆኑ እንዲከፈላቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መመሥረታቸውንም በክሱ አካተዋል፡፡
አቶ አብነት መልካም ስማቸው እየጠፋና ማስፈራራት እየደረሰባቸው መሆኑን፣ ከአገር እንዳይወጡ ዕግድ እንደወጣባቸው፣ ከቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅነት እንዲነሱ መደረጋቸው አግባብ አለመሆኑን፣ ሼክ መሐመድ በእሳቸው ላይ (አቶ አብነት ላይ) በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከስምንት በላይ የክስ ፋይል እንደከፈቱባቸውና በርካታ የማይንቀሳቀሱና የሚንቀሳቀሱ ንብረቶቻቸው ዕግድ በማውጣት እንቅፋት እንደፈጠሩባቸው በዝርዝርና በስፋት በክሳቸው አቅርበዋል፡፡
አቶ አብነት በእሳቸውና በሼክ መሐመድ መካከል በመከባበርና በመተማመን ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንደነበራቸው አስታውሰው፣ ከጊዜ በኋላ ግን መልካም ግንኙነታቸው እየሻከረና እየከረረ በመምጣቱ፣ ‹‹ብርቱ›› ያለመግባባት በመፈጠሩ የማኅበሩን ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ የሚያስደርግ ደረጃ ላይ መድረሳቸውንና ግንኙነታቸው ወደ ጠላትነት ስሜት መሸጋገሩን የሚያሳዩ ስሜቶች መፈጠራቸውን አብራርተዋል፡፡ ጉዳዩ በሽምግልና እንዲታይ ቢደረግም፣ በሼክ መሐመድ በኩል ፍላጎት ባለመኖሩና ሊሳካ ስላልቻለ፣ ከሼክ መሐመድ ጋር ባለድርሻ ሆኖ ማኅበሩን ማስቀጠል የማይቻል ደረጃ ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም አቶ አብነት ማኅበሩን በሥራ አስኪያጅነት በመምራት፣ እንዲሁም የ40 በመቶ ባለድርሻ በመሆን ለረዥም ዓመታት በመሥራት ግዙፍ ሀብት እንዲኖረው ማድረጋቸውን አስረድተው፣ ሼክ መሐመድ ድርሻቸውን ይዘው በማኅበሩ እንዲወጡና እሳቸው በሕጉ መሠረት ማኅበሩን ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አድርገው ማስቀጠል እንዲችሉ ወይም ማኅበሩ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤቱ የክስ አቤቱታ ማቅረባቸውን ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍርድ አብራርቷል፡፡
ሼክ መሐመድ ለቀረበባቸው ክስ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጡት ምላሽ፣ ማኅበሩ ከተቋቋመበትን 10,000 ብር ውስጥ የድርሻቸውን መክፈላቸውን፣ አቶ አብነት ግን አለመክፈላቸውን፣ (ገቢ አለማድረጋቸውን)፣ የማኅበሩ ካፒታል 545,000,000 ብር እንዲሆን ቢወሰንም ለማኅበሩ ገቢ አለማድረጋቸውን፣ የማኅበሩ ሕንፃ የተገነባው በእሳቸው (በሼክ መሐመድ) ሙሉ ወጪ መሆኑን፣ አቶ አብነት ከ1992 እስከ 1997 ዓ.ም. በግል ይዞታነት ይዤዋለሁ የሚሉትና ለማኅበሩ እንደሰጡ የሚናሩት ትክክል እንዳልሆነና በርካታ ቁጥር ጨ0430 በሊዝ የተሸጣቸው 2,000 ካሬ ሜትር ብቻ መሆኑን በመግለጽ፣ ክሱን ክደው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍ ላይም በግልጽ መቀመጡንም አክለዋል፡፡
አቶ አብነት በመመሥረቻ ጽሑፍ በተቀመጠው መሠረት በተሰጣቸው የሥራ አስኪያጅነት ሥልጣን ግዴታቸውን መወጣት ሲገባቸው፣ ከላይ የተጠቀሰውን ይዞታ የራሳቸው እንደሆነ አድርገው ለማኅበሩ ማስፋፊያ የተሰጠውን 3,189 ካሬ ሜትር ይዞታ ከራሳቸው ይዞታ (2,000 ካሬ ሜትር) ጋር ቀላቅለው የይዞታ ምስክር ወረቀት ማውጣታቸውንም በምላሻቸው አብራርተዋል፡፡ ማኅበሩ ከተመሠረተ 1994 ዓ.ም. ወዲህ የአቶ አብነት ማናቸውም መብትና ግዴታዎች ወደ ቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መተላለፋቸውንና አቶ አብነት ግን ምንም ዓይነት ክፍያ አለመክፈላቸውን አክለዋል፡፡ አቶ አብነት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ በርካታ ጥፋቶች መሥራታቸውንና ያቀረቡት ክስ ሐሰት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
አቶ አብነት የማኅበሩን ሕንፃ ለማስጨረስ 425,000,000 ብር ተበድሬያለሁ ቢሉም፣ ሼክ መሐመድ ግን ክደው ተከራክረዋል፡፡ በክርክራቸውም አቶ አብነት በከፍተኛ ዕውቀት ቀርቶ ዕውቀት የሌለው ሰው እንኳን በሚመራው አኳኋን ማኅበሩን እንዳልመሩት፣ በመመሥረቻ ጽሑፍ በተጠቀሰው መሠረት መሥራት ሲገባቸው፣ የንግድ ማኅበሩ በክፍለ ከተማው ማኅደር እንዳይኖረው በማድረግ ይዞታውን ወደ ግላቸው በማዞር እምነት ማጉደላቸውን ሼክ መሐመድ በመልሳቸው ገልጸዋል፡፡
ሼክ መሐመድ ከላይ ለጠቀሷቸው ችግሮች ክስ መመሥረታቸውን ጠቁመው፣ አቶ አብነት በማጭበርበር ያወጡት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲሰረዝ ከመክሰሳቸውም በተጨማሪ፣ ማኅበሩ ከዳሸን ባንክ 425,000,000 ብር እንዲበደር አድርገው፣ ገንዘቡን ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውንና በማኅበሩ ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን አብርራተዋል፡፡
በመሆኑም አቶ አብነት ማኅበሩ እንዲፈርስ ወይም እሳቸው (ሼክ መሐመድ) ከባለድርሻነት እንዲወጡ የጠየቁበት ክስ፣ የሕግ መሠረት ወይም የፍሬ ነገር ምክንያት እንደሌለው አስረድተው ክሱን ተቃውመዋል፡፡
አቶ አብነት በክሳቸው እንደገለጹት ሼክ መሐመድ በዝርዝር ባቀረቡት የመቃወሚያ መልሳቸው ላይ፣ አቶ አብነት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ የማኅብሩን ይዞታዎች ወደ ግላቸው በማዛወርና በመሸጥ፣ እንዲሁም ማኅበሩ ከዳሸን ባንክ የተበደረውን 425,000,000 ብር ወደ ራሳቸው፣ ባለቤታቸው፣ ልጃቸው፣ ወንድማቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና ጉዳይ ፈጻሚዎቻቸው በማስተላለፍ፣ በማኅበሩ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳት ማድረሳቸውን በመግለጽ፣ ስምንት የክስ ፋይሎች ከፍተው ክሱ በሒደት ላይ መሆኑን በመግለጽ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
አቶ አብነት ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም እሳቸው (ሼክ መሐመድ) በየወሩ 25,000 ዶላር ደመወዝ እንደሚከፍሏቸው በመግለጽ 14,000,000 ብር መውሰዳቸውንና አዲስ ፓርክ ከተባለው ድርጅት (ሚሊኒየም አዳራሽና ሌሎች ድርጅቶች) 35 ሚሊዮን ብር በመውሰዳቸው በሁለት ፋይል ክስ ማቅረባቸውንም በምላሻቸው አካተዋል፡፡
አገራዊ ጠቀሜታ ያለውን የንግድ ማኅበር በባለድርሻዎች አለመግባባት እንዲፈርስ መጠየቅ ተገቢ አለመሆኑን አስረድተው፣ አቶ አብነት ከማኅበሩ ጋር መቀጠል ካልፈለጉ ‹‹እሳቸው ባለድርሻነታቸውን ለቀው ወይም በሽያጭ አስተላልፈው›› ከሚወጡ በስተቀር፣ ተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) የሚወጡበት ወይም ማኅበሩ የሚፈርስበት የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር ምክንያት እንደሌለ አስረድተዋል፡፡
በከሳሽ (አቶ አብነት) በተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) በስፋትና በዝርዝር የቀረበውን ክስና ምላሽ የተመለከተው ፍርድ ቤት፣ ‹‹በከሳሽና ተከሳሾች መካከል ብርቱ አለመግባባት አለ ወይስ የለም? አለ የሚባል ቢሆን አለመግባባቱ የማኅበሩ ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ የሚያስተጓጉል ነው ወይስ አይደለም?፣ ሼክ መሐመድ ከማኅበሩ የሚወጡበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?፣ ማኅበሩ ሊፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም?፣ በተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) ከሳሽ (አቶ አብነት) ክስ ላይ የተገለጹትን ጥፋቶች፣ አቶ አብነት ፈጽመዋል ወይስ አልፈጸሙም? እና ጥፋቶችን ፈጽመዋል የሚባል ቢሆን (አቶ አብነት) ከማኅበሩ አባልነት እንዲወጡ የሚያበቃ ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም? የሚሉ ጭብጦችን ይዞ ክሱን መመርመሩን የፍርድ ትንታኔው ያሳያል፡፡
ፍርድ ቤቱ የከሳሽ (አቶ አብነት) ሁለት ምስክሮችን በማስቀረብ እንዲመሰክሩ አድርጎ፣ ቦሌ ታወር ‹‹ኤ›› የሚባለው ሕንፃ ግንባታ 75 በመቶ መሠራቱን፣ ሌላው ግንባታ መቆሙን፣ አቶ አብነት ሲከታተሉ እንደነበርና ማሠሪያ ገንዘቡ ከማኅበሩና ከራሳቸው ወጪ ሲያደርጉ እንደነበርና ሌሎች ክፍያዎችንም ሲፈጽሙ እንደነበር ገልጸው፣ በሁለቱ ባለድርሻዎች መካከል አለመግባባት ቢኖርም ምክንያቱን እንደማያውቁ መመስከራቸውን የፍርድ ሰነዱ ያብራራል፡፡
ፍርድ ቤቱ በከሳሽና ተከሳሽ መካከል ‹‹ብርቱ›› አለመግባባት አለ ወይስ የለም? ማኅበሩ ሊፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ሲመረምር፣ ያስቀደመው ‹‹በማኅበሩ አባላት መካከል ብርቱ አለመግባባት አለ ወይስ የለም?›› የሚለውን ከንግድ ሕጉ አንቀጽ 181 እና አንቀጽ 531 ድንጋጌ መሠረት፣ እንዲሁም የሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 153981 ላይ ከሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንፃር ነው፡፡ በመሆኑም ‹‹ብርቱ አለመግባባት አለ›› በማለት አቶ አብነት የጠቀሷቸው ጉዳዮችና ዝርዝር የክርክር ወይም የክስ ሒደቶች፣ በማኅበሩ አባላት መካከል ብርቱ አለመግባባት አለ የማያስብሉ ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ እንዳደረሰው ገልጿል፡፡
ክሱ በዋናነት በአቶ አብነትና በሼክ መሐመድ መካከል በመሆኑ፣ የቀረቡትም ክሶችና ክርክሮች በሚያዩዋቸው ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት የሚያገኙ ቢሆን፣ ማኅበሩን የሚጠቅሙ እንጂ የማይጎዱ በመሆኑ፣ ሼክ መሐመድ በአቶ አብነት ላይ ክስ መመሥረታቸው በማኅበሩ አባላት ላይ ብርቱ አለመግባባት አለ የማያስብል መሆኑንም አብራርቷል፡፡ የማኅበሩን ዓላማ ከግብ እንዳይደርስ የሚያስተጓጉል ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን በሚመለከት ደግሞ፣ ፍርድ ቤቱ ብርቱ አለመግባባት እንደሌለ ብይን በመስጠቱ ጭብጡን አልፎታል፡፡
ሼክ መሐመድን ከማኅበሩ አባልነት ማውጣት የሚያስችል የሕግ መሠረት ወይም ፍሬ ነገር መኖር አለመኖሩን ሲመረምር፣ ከላይ በተጠቀሱ ሕጎችና አስገዳጅ የሰበር የሕግ ትርጉሞች አንፃር ‹‹በቂ ምክንያት›› አለመኖሩንና ከላይ ብይን በተሰጠበት ‹‹ብርቱ አለመግባባት›› ስለሌለ፣ አቶ አብነት የጠየቁት ሼክ መሐመድ ከአባልነት ይውጡ ጥያቄን ውድቅ አድርጎታል፡፡
አንዳቸው ሌላኛቸውን ከማኅበሩ እንዲወጡ ወይም ማኅበሩ እንዲፈርስ ያቀረቡት የክስ አቤቱታ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 498 ድንጋጌ መሠረት ፍርድ ቤቱ እንዳልተቀበለው በፍርዱ ገልጿል፡፡
ቦሌ ታወር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሊፈርስ አይገባም በመባሉ፣ በማኅበሩ አባልነት ሊቀጥል የሚገባው ከሳሽ (አቶ አብነት) ወይስ ተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) የሚለውን በሚመለከት፣ ፍርድ ቤቱ ሼክ መሐመድ ባቀረቡት በተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) ከሳሽ (አቶ አብነት) ክስ ላይ፣ አቶ አብነት የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲሠሩ ፈጽመዋቸዋል በሚል የተገለጹ ጥፋቶች እንዲሁም ከማኅበሩ መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ሁኔታ አንፃር፣ ማኅበሩ የተቋቋመበትን ዓላማ እንዲያሳካ፣ ከተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) ይልቅ ከሳሽ (አቶ አብነት) ከአባልነት ቢሰናበቱ እንደሚሻል ፍርድ ሰጥቷል፡፡ ይኼ ሲባልም ተሰናባቹ (አቶ አብነት) ካለ በቂና ሕጋዊ ምክንያት እንዳይሆን የሕግ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባም አብራርቷል፡፡
አቶ አብነት በተከሳሽ (በሼክ መሐመድ) በቀረበባቸው የተከሳሽ ከሳሽ ክስ ላይ እንደተብራራው፣ ማኅበሩን በሥራ አስኪያጅነት ሲመሩ ከፈጸሟቸው ጥፋቶች አንፃር፣ ተከሳሽ (ሼክ መሐመድ) ጥፋት ስለመፈጸማቸው በማስረጃ የቀረበባቸው የተረጋገጡ ፍሬ ነገር እንደሌለ ፍርድ ቤቱ በፍርዱ ተንትኖ አቅርቧል፡፡
ፍርድ ቤቱ ባለ 24 ገጽ የፍርድ ትንታኔ ሕጉን መሠረት አድርጎ የሰጠ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ሼክ መሐመድ ጥፋት ማጥፋታቸውን የማስረዳት ሸክም የአቶ አብነት ቢሆንም፣ ሊያስረዱና በበቂ ማስረጃ ሊያረጋግጡ ባለመቻላቸው፣ ከአክሲዮን ባለድርሻነታቸው እንዲወጡ፣ ነገር ግን ድርሻቸው በንግድ ሕጉ አንቀጽ 403(1) በግልጽ እንደተደነገገውና በአንቀጽ 403(3) መሠረት የማኅበሩ የመጨረሻው ዓመት ሒሳብ የሀብትና ዕዳ ሒሳብ መግለጫ መሠረት፣ በማኅበሩ አክሲዮናቸው በሚወከሉበት መጠን ታስቦ እንደሚከፈላቸው በፍርዱ ተገልጿል፡፡ አቶ አብነት ከማኅበሩ እንዲወጡ የተወሰነው በፈጸሙት ጥፋትና በፍርዱ በተገለጹት ጥፋቶች ቢሆንም፣ የድርሻቸው አከፋፈል ግን የንግድ ሕጉን አንቀጽ 403(3) ድንጋጌን መሠረት ባደረገ ሁኔታ መሆኑን በፍርዱ አብራርቷል፡፡ ማኅበሩ ሊፈርስ እንደማይገባ፣ አቶ አብነት ግን ድርሻቸው ተከፍሏቸው ከቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አባልነት እንዲወጡ ውሳኔ በመስጠት፣ ሼክ መሐመድ ዓሊ አላሙዲንን ከማኅበሩ ለማስወጣት ወይም ማኅበሩ እንዲፈርስ ባቀረቡት ክስ ተረትተው እራሳቸው ከማኅበሩ ባለድርሻነት ወጥተዋል፡፡

Source: Ethiopian Reporter

የቀድሞ ሚስቱንና የወንድ ጓደኛዋን ገድልሃል ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ በነጻ የተለቀቀው ኦጄ ሲምሰን (O.J. Simpson) ዛሬ በ76 ዓመቱ አርፏል:: ነፍስ ይማር
04/11/2024

የቀድሞ ሚስቱንና የወንድ ጓደኛዋን ገድልሃል ተብሎ ከተከሰሰ በኋላ በነጻ የተለቀቀው ኦጄ ሲምሰን (O.J. Simpson) ዛሬ በ76 ዓመቱ አርፏል:: ነፍስ ይማር

እግዚአብሔር ነፍስህን ይማርልን፣ በገነትም ያኑርልን
04/10/2024

እግዚአብሔር ነፍስህን ይማርልን፣ በገነትም ያኑርልን

አሁንም አለን! ስለምትጠይቁን በጣም እናመሰግናለን። ለዛሬው ይህን ፎቶ ላጋራችሁ። በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ከክቡር አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር በአዲስ አበባበጣም አክብሮት በተሞላ...
02/18/2024

አሁንም አለን! ስለምትጠይቁን በጣም እናመሰግናለን። ለዛሬው ይህን ፎቶ ላጋራችሁ። በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ከክቡር አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር በአዲስ አበባ
በጣም አክብሮት በተሞላበት ሁኔታ ነው ያነጋገሩኝ...
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን

01/26/2024

የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደመቀ መኮንንን ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸው አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዋል።

01/07/2024

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አስመልክቶ የጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አስመልክተው ለመላው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻቸው መልእክት አስተላልፈዋል።

የቅዱስነታቸው ቃለ በረከት ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣

ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣

የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ

በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤

እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡

በፍጹም ፍቅሩ እኛን ወደ ሰላም ለማምጣት በእኛ ሰውነት በዚህ ዓለም የተወለደው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በደኅና አደረሳችሁ!

“ትእምርተ ሰላምነ ወልድ ተወልደ ለነ፡ የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነው ወልድ ወይም ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተወለደልን'' (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)

ዓለም ሁሉ በተለይም የክርስቲያኑ ዓለም በትክክል እንደሚያውቀው ቅዱስ መጽሐፍ በሰዎች የቋንቋ ዘይቤ የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ርእዮት ቋንቋ የመልእክት ማስተላለፊያና መግባቢ መሳሪያ እንደሆነ ይታወቃል፤ እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ መልእክቱን በዚህ መንገድ ለሰዎች ሲያስተላል ኖሮአል፤ የሚያስተላልፈውም መልእክት እንዲሁ ተሰምቶ እንዲቀር ሳይሆን እንዲታወቅ፣ እንዲታመን እንዲተገበርና ሰዎች እንዲጠቀሙበት ነው፤ ከሚፈለገው ጥቅም ለመድረስም ሰዎች መልእክቱን በሚገባ መረዳት የግድ ይሆናል፤ ሰዎች እንዲረዱት ደግሞ በቋንቋቸውና በባህላቸው ዘይቤ ሊነገራቸው ይገባል፤

በመሆኑም እግዚአብሔር ቃሉን በሰዎች ቋንቋ ባህላዊ ዘይቤ መልእክቱን ለዓለም ሲያስተላልፍ ኖሮአል ቤተክርስቲያንም ይህንን መሠረት አድርጋ የእግዚአብሔርን ቃል በሰው ቋንቋ ዘይቤ ታስተምራለች፤ ከዚህ አንጻር በሰው ልማዳዊ የዘይቤ ቋንቋ ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም "የሰላም ሰንደቅ ዓላማ" የሚል ቅፅል ተሰጥቶታል፡ ምክንያቱም ንጉሥም ወታደርም ተራው ሕዝብም የሀገሩ ነጻነትና ክብር፤ አንድነትና ሉዓላዊነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ተከትሎ ስራ ይሰራል ክብሩንም ይገልፃልና ነው፤ ተከተል አለቃህን ተመልከት ዓላማህን የሚለው ብሂልም ይህንን ያንፀባርቃል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን

ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን በመድኅንነቱ የሁላችን የሰላም ሰንደቅ ዓላማ በመሆኑ መምህራችን ቅዱስ ያሬድ የሰላማችን ሰንደቅ ዓላማ የሆነ ልጅ ተወለደልን ብሎ ይገልፀዋል፤ ጌታችን በዛሬው ዕለት በቤተልሔም ሰውነታችንን ሰውነት አድርጎ መወለዱ ራሱ የሰላም ማሳያ ምልክት ነው፤ ምክንያቱም ሳይወደን አይቀርበንም፤ አይዋሐደንምና ነው፤ በልደቱ ዕለት "ለዕጓለ እመሕያው ሠምሮ የሰው ልጅን ወደደው" ተብሎ በቅዱሳን መላእክት የተዘመረበትም ምክንያት ይኸው ነው፤

እንደ እውነቱ ከሆነ ጌታችን የተዋሐደው ሰውነት የወዳጁ አልነበረም የጠላቱ እንጂ፤ ቅዱስ መጽሐፍ ይህንን ሲገልፅ "ጠላቶቹ ሳለን እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን" ይላልና ነው፡ በዚህ ዓለም የኖረውም ከሚያሳድዱት፣ ከሚከሱት፤ ስሙን ከሚያጠፉና ሊገዱሉት ከሚከጅሉ ጋር እንጂ ከወዳጆቹ ጋር ብቻ አልነበረም፤ እሱ ግን ሁሉንም በፍቅር ይቀበል ነበረ፤ ይፈውስና ያድን ነበረ፤ ያስተምርም ነበረ፤ ለሁሉም ስርየተ ኃጢአትን ሰጠ ለጠላቶቹም ጸለየ፤ ጌታችን በዚህ ሁሉ ለኛ አርእያና የተግባር መምህር በመሆኑ የሰላም ሰንደቅ ዓላማችን ነው፡

ምእመናንና ምእመናት

ዓለም በጌታችን ዕለተ ልደት የተዘመረውን ሰማያዊውን የሰላም መዝሙር መዘመር ከጀመረች እነሆ ዛሬ ድፍን ሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመት ሆነ፤ የሰላሙ መዝሙር ዛሬም በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ይዘመራል፤ ይሁን እንጂ በዚህ ዓለም ሰላም ሰፍኖ እየታየ አይደለም፤ ይህ ለምን ሆነ ቢባል ደምበኛ መልስ ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔርን አለማመንና አለመፍራት ያመጣው ችግር ነው የሚል ነው፤ ምክንያቱም ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚአብሔር ከሌለ ፍትሕ ይጐድላል፣ ፍትሕ ከጐደለ ብሶት ይፈጠራል፣ ብሶት ካለ ሰላም ሊኖር አይችልም፤

በሁሉም የዓለማችን ክፍል ሃይማኖትና ፈሪሐ እግዚብሔር እየተዘነጋ በመሄዱ ቀውሱ ተባብሶ ይታያል፤ የሰው ልጅ ኑሮ በየትም ይሁን በየት በስጋት የተሞላ ሆኖአል፤ የሚወራው ሁሉ ስለ ግጭት ስለአየር ብክለት ስለ ረኃብና እልቂት ሆኖአል፤ ዓለም የጉልበተኞችና የባለ ሀብቶች ብቻ እንድትሆን የተፈጠረች እስክትመስል ድረስ ከባድ የፍትሕ መዛባት አጋጥሞአታል፤ የዝቅተኛው ማኅበረሰብ ሰብአዊ መብት ተዘንግቶአል፣ ከዚህ አኳያ ዓለም በዚህ እስከ ቀጠለች ድረስ ሰላም የማግኘቷ ዕድል በጣም አጠራጣሪ ነው፡ የክርስቶስ ልደት ያስተማረን ግን እንደዚህ አልነበረም፤

ጌታችን የተወለደው በተዋበና ምቹ በሆነ የሀብታም ቤት ሳይሆን በከብቶች በረት ነበረ፤ የተገለጠውም ለባለሥልጣኖች ሳይሆን ዝቅተኞች ለሚባሉ እረኞች ነበረ፤ ልዑላኑ ሰማያውያንና ትሑታኑ ምድራውያን በአንድነት አገናኝቶ ስለ ሰላም በጋራ እንዲዘምሩ አደረገ፤ አሳዳጅ ሳይሆን ተሳዳጅ ሆኖ በግብጽ አገር በመንከራተት አደገ፤ ይህን ሁሉ ያደረገው እኛ እሱን እያየን እንደ ሰንደቅ ዓላማ እንድንከተለው ነበር፤ ጌታችን ከባለሥልጣናቱና ከባለሀብቶቹ ይልቅ በድሆቹ ደረጃ የተወለደው ለድሆቹና ለዝቅተኞቹ ትኩረት እንድንሰጥ ለማስተማር ነው፤ የእኛ ድርጊት ግን ግልባጩ ሆኖ እየተስተዋለ ነው፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ክርስቲያን ነኝ ብሎ፤ በስመ እግዚአብሔር ተሰይሞ፤ መስቀልን በአንገቱ ተሸክሞ የእሱ መሰል በሆነው ወይም መስቀል በተሸከመው ወንድሙ እና እኅቱ እንዲሁም በመሰል ፍጡር ላይ ያለ ርኅራኄ ሲጨክን መታየቱ ነው፡ እንዲህ እየሆነ እንዴት ሰላም ይምጣ? እግዚአብሔርስ እንዴት በረከቱ ይሰጣል? ይህ እጅግ በጣም ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን

ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ኢትዮጵያውያን ከእንዲህ ዓይነቱ የሃይማኖትና የሞራል ዝቅጠት በአስቸኳይ መውጣት አለብን፤ ጠቡ፤ መለያየቱ፣ መጨካከኑ፤ ለኔ ለኔ መባባሉ ከረምንበት፤ ሆኖም ያመጣልን ነገር ቢኖር ሁለንተናዊ ውድመት ብቻ ነው፡ ያስገኘልን ትርፍ ይህ መሆኑ እያወቅን በዚሁ ልንቀጥል አይገባም፡ ሰው ችግሩን በልቡ እያወቀ በዓይኑ እያየ እንዴት ገደል ውስጥ ይገባል? ዕርቅና ይቅርታ ማንን ጐዳ? ሰላምና አንድነት ማንን አከሰረ? ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በሆነውም ባልሆነውም ከመተላለቅ ለምን ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በእኩልነትና በስምምነት መኖር አቃተን?

ሦስት ሺሕ ዘመናት አብረው የኖሩ ሕዝቦች እንዴት ችግራቸውን በጠባይና በብልሐት ማስወገድ አቃታቸው? ይህ ከቶ ሊሆን አይገባም፤ ሁላችንም ሰክን ብለን እናስብ፤ ለሁሉም የማሰቢያና የመመካከሪያ ጊዜ ፈጥረን ችግሩን በስፍሐ አእምሮ እንፍታው፡ ችግርን በምክክርና በይቅርታ መፍታት አማራጭ የሌለው ጥበብ ነው፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፤ ምሁራንና ልኂቃን በዚህ ተግተን ልንሰራ ይገባል፤ መንግሥትና የፓለቲካ ፓርቲዎችም ለዚህ የበኩላቸውን ድጋፍ ያድርጉ፤ በዚህም ሰላማችንን እንመልስ፡፡

በመጨረሻም

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በተከሠተው የድርቅና የሰው ሰራሽ ምክንያት በችግር ላይ የወደቁ ወገኖች በርካታ ናቸው በመሆኑም የወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁሉም ካለው ብቻ ሳይሆን የቀን ቍርሱን ለተቸገሩ ወገኖች እንዲለግስና በመተጋገዝ ረኃቡን እንድንከላከለው ጥሪያችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የልደት በዓል ያድርግልን

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

01/07/2024

እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን

Address

PO Box 11061
Alexandria, VA
22312

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TGEthiopianBroadcasting posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to TGEthiopianBroadcasting:

Videos

Share


Other Broadcasting & media production in Alexandria

Show All