DMN_Dorze Media Network

  • Home
  • DMN_Dorze Media Network

DMN_Dorze Media Network _Find News and Events about Dorze and South people's socio-economic, and political news.

11/05/2023

DMN
የ2015 ዓ.ም የጋሞ ዞን እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ውጤትና ከምድባቸው ያለፉ ክለባት

⚽ምድብ -ሀ-
ደረ...ክለብ......ተጫ..አሸ..ተሸ...አቻ...አስቆ...ተቆ..ግብ..ነጥ
1. ገረሴ ከነማ 3 2 1 - 5 4 1 6
2. ጋ/ሠላምበር 3 1 1 1 2 2 0 4
3. አ/ም ምኞት 3 1 1 1 4 4 0 4
4. ም/ዓባያ 3 - 1 2 1 2 -1 2

N.B ጋሞ ሠላምበር ከአ/ም ምኞት ጋር በነጥብና በግብ ክፊያ እኩል ቢሆኑም በውድድር ደንብ አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 7.6 መሠረት በምድብ ማጣሪያ በአንድ ምድብ ውስጥ ያሉ ቡድኖች በነጥብና በግብ ክፊያ እኩል ከሆኑ እርስ በርስ ባደረጉት ጨዋታ አሸናፊው ቡድን ለቀጣይ ዙር እንዲያልፍ ይደረጋል በሚለው መሠረት ሠላምበር ከተማ በእርስ በርስ ግንኙነት አ/ምንጭ ምኞትን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፉ ምክንያት የሠላምበር ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከምድብ -ሀ- ገረሴ ከነማን በመከተል 2ኛ ሆኖ አልፏል።
👌የምድብ -ሀ-
1ኛ. ገረሴ ከነማ
2ኛ. ጋሞ ሠላምበር
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
⚽ምድብ -ለ-
ደረ...ክለብ......ተጫ..አሸ..ተሸ...አቻ...አስቆ...ተቆ..ግብ..ነጥ
1.አ/ም ዙ/ወረዳ 3 2 - 1 7 1 6 7
2. ብርብር ከተማ 3 1 1 1 2 3 -1 4
3. አ/ም ሴቻ 3 - - 3 3 3 0 3
4. ቦረዳ ባይራ 3 - 2 1 1 6 -5 1
👌የምድብ -ለ-
1ኛ. አ/ም ዙ/ወረዳ
2ኛ. ብርብር ከተማ
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
⚽ምድብ -ሐ-
ደረ...ክለብ.......ተጫ..አሸ..ተሸ...አቻ...አስቆ...ተቆ..ግብ..ነጥ
1. ቁጫ ወረዳ 3 3 - - 3 0 3 9
2. አ/ም አቢ 3 2 1 - 5 3 2 6
3. ዲታ ዛዳ 3 1 2 - 4 5 -1 3
4. ካምባ ከተማ 3 - 3 - 2 6 -4 0
👌የምድብ -ሐ-
1ኛ. ቁጫ ወረዳ
2ኛ አ/ም አቢ ተስፋ
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
ምድብ -መ-
ደረ.. ክለብ......ተጫ..አሸ..ተሸ...አቻ...አስቆ...ተቆ..ግብ..ነጥ
1.ብርብር ሞሌ 3 2 - 1 6 2 4 7
2. ጨንቻ ከተማ 3 2 1 - 11 3 8 6
3. አ/ም አጩ 3 1 - 1 8 2 6 4
4. ገረሴ የነጌው 3 - 3 - 0 17 -17 0
👌የምድብ -መ-
1ኛ. ብርብር ሞሌ
2ኛ. ጨንቻ ከተማ

👉ለክቡራን ስፖርት አፍቃሪያን በሙሉ🏆👌የ2015 ዓ.ም የጋሞ ዞን ወንዶችና ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ሻምፒዮና ውድድር በአርባ ምንጭ ከተማ ሲቀላ ዋናው ሜዳና አ/ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፖስ ...
06/05/2023

👉ለክቡራን ስፖርት አፍቃሪያን በሙሉ🏆
👌የ2015 ዓ.ም የጋሞ ዞን ወንዶችና ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ሻምፒዮና ውድድር በአርባ ምንጭ ከተማ ሲቀላ ዋናው ሜዳና አ/ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፖስ የሚካሄደውን ጨዋታ ያለ ምንም ችግር ለመከታተልና የምትወዱትን ክለብ በአካል በመገኘት በፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት ለመደገፍ ያስችላችሁ ዘንድ የውድድሩን ሙሉ ፕሮግራም እነሆ እንላችኋለን!

የጋሞ ዞን እግር ኳስ ክለቦች ሻምፒዮና የውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ
ሚያዚያ 28/2015 ዓ.ም
አርባ ምንጭ

የጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ
09/04/2023

የጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ

መፍራት ጉልበት ያለውን ሰው አይደለም፣ መፍራት ካለብን የተበዳይን እንባ ነው። ተበዳይዎች የሚጮሁት ለፈጣሪ ነው። አላህም ለነሱ ቅርብ ነው። መንግስትንም ከሰሜኑ ጦርነት በላይ የነዚህን እናቶ...
31/03/2023

መፍራት ጉልበት ያለውን ሰው አይደለም፣ መፍራት ካለብን የተበዳይን እንባ ነው። ተበዳይዎች የሚጮሁት ለፈጣሪ ነው። አላህም ለነሱ ቅርብ ነው። መንግስትንም
ከሰሜኑ ጦርነት በላይ የነዚህን እናቶች እንባ ነው የሚጎዳው። ተው እናቶቻችንን አናስለቅስ
ግዴላችሁ ይቺ እናት ምንም ስለ ፖለቲካ አታቅም። ደሀ ሆና ለደሀ አገር ከደሀ መቀነቷ የምትገብር ድህነቷ ብቻ የበደላት እናት ናት። ይችን እናት ጎጆ የሚሰራ መንግስትና ስረአት እንጅ ይችን እናት ቤቷን አፍርሶ እጎዳና ላይ የሚጥል አመራር አይጠቅመንም። ተው ሰውን አታስለቅሱ፣

✍ሱሌማን አ.

ድምፅ ለሰጠው ሕዝብ ድምፅ ሁኑለተ አሁን! ዋ!
26/03/2023

ድምፅ ለሰጠው ሕዝብ
ድምፅ ሁኑለተ አሁን!

ዋ!

ጥያቄ ጣልያን Pizzaን 🍕 ከኛ ኮፒ አድረገው ይሆን?👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
24/03/2023

ጥያቄ

ጣልያን Pizzaን 🍕 ከኛ ኮፒ አድረገው ይሆን?

👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

 #ዝምታ  #ይሰበር!!::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::: #ከዝህ በላይ ጭንቅ ዘመን ለህዝብ አይመጣምና እባካችሁ ዝምታችሁን ስበሩ፡፡ እያያችሁ እንዳላዬ፡ እ...
23/03/2023

#ዝምታ #ይሰበር!!
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
#ከዝህ በላይ ጭንቅ ዘመን ለህዝብ አይመጣምና እባካችሁ ዝምታችሁን ስበሩ፡፡ እያያችሁ እንዳላዬ፡ እየሰማችሁ እንዳልሰማ ብትሆኑ "ጎሜ" ነዉ፡፡ ድምፅ መሆን የምትችሉ በተለያዩ እርኬኖች ህዝብን የወከላችሁ፡ በአውሮፕላን ጣቢያ ሳር ይዛችሁ የክልል እና የፌዴራል ባለስልጣናትን አቀባበል የምታደርጉ ሽማግሌዎች እና የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች በሙሉ፡ እባካችሁ ለህዝብ ድምፅ ሁኑ፡፡

#ለዘመናት ለመንግስት ገብረዉ፡ የልማት መዋጮ ከፍለዉ እና ሀገሬ ነዉ በማለት ከኖሩበት አከባቢ በግፍ ለተፈናቀሉ፡ እየተፈናቀሉ ላሉ እና ልፈናቀሉ ላሉ ለዞኑ ተወላጆች ከቻላችሁ ድምፅ በመሆን የተሰጠዉን የህዝብ አደራ ተወጡ ምክንያቱም ለህዝብ ከዝህ በላይ ጭንቅ ወቅት ልመጣ አይችልምና፡፡

ከ fb

19/03/2023

ዶርዜነተን ያላከበረ
ማንነተን ያለተቀበለ

ኢትዮጵያዊነት አይሰራም

መጀመሪያ ዶርዜነት
ስቀጥል ኢትዮጲያዊነት ይመጣል::

ግዜ እየጠበቅን እንጂ ዝም አላልንም

  #ድንጉዛ  #ዶርዜ
10/03/2023


#ድንጉዛ

#ዶርዜ

የዶርዜ ዱንጉዛ #ዶርዜ  #ድንጉዛ
05/03/2023

የዶርዜ ዱንጉዛ
#ዶርዜ
#ድንጉዛ

ሰኞ ገበያ
01/03/2023

ሰኞ ገበያ

ሚሽሮ
01/03/2023

ሚሽሮ

የህዝበ ውሳኔ ውጤት ይፋ ተደረገ
20/02/2023

የህዝበ ውሳኔ ውጤት ይፋ ተደረገ

ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ስለ ዶርዜነቴ ሳወራ የበታችነት ስሜት ተሰምቶሀል 🤪 ይሰማሀል ለምትሉ ክቡራን ኢትዮጵያዊ ነኝ ባዮች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ !!! ሲጀመር ከእናንተ የተሻለ ሀሳብ ይዞ...
19/02/2023

ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ስለ ዶርዜነቴ ሳወራ የበታችነት ስሜት ተሰምቶሀል 🤪 ይሰማሀል ለምትሉ ክቡራን ኢትዮጵያዊ ነኝ ባዮች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ !!!

ሲጀመር ከእናንተ የተሻለ ሀሳብ ይዞ የመጣን ሰው ለማሸማቀቅ የምትቀለድ የድሮ ፈሊጥ ናት

እኔ ዶርዜ ነኝ የኔ ዘሮች ኢትዮጵያን በሽመና ጥበብ ያለበሱ የእንቁ እጆች ባለቤት ናቸው የራሴ ባህላዊ አለባበስ ያለኝ :የራሴ የሰርግ :የለቅሶ ስርአት :ያለኝ የራሴ መሬትና ግዛት ያለኝ የራሴ ቋንቋ ያለኝ ብዙ ባህል ያለኝ የኩሩህ ዝቦች ዘር ነኝ በዚህ ውስጥ ምንም የበታችነት ስሜት እንዲሰማኝ የሚያደርግ የታሪክ ቀፋፊ ገፅ የለኝም

ወተት በቂጣ በቦይና ጥሬ ስጋ ጎመን በስጋ ማሽላ እና ስንዴ ፍራፍሬ ጨምሮ ስበላ ያደግኩ የምግብ ችግር የሌለብኝ ምርጥዬ ዶርዜ ነኝ በዜግነቴ ደግሞ ኢትዮጵያውያዊ ነኝ

*የበታችነት ስሜት ሊያጠቃኝ የሚችለው ሰው ፊት የማያቀርበኝ የተበላሸ የኃላ ታሪክ ካለኝ ብቻ ነው

እኔ ደግሞ እግዚአብሔር ይመስገን ከዚህ ነፃ ነኝ

03/11/2022

ሽመና

ሽመናበጥበብ ስራቸው ከሚያኮሩን የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ውስጥ የዶርዜ ማህበረሰብ አንዱ ነው። የዶርዜ ሕዝብ °° የሰላም የአንድነትና የአብሮነት ተምሳሌት ሕዝብ  ነው :: ጥበበኞቹ የዶርዜ ማ...
03/11/2022

ሽመና

በጥበብ ስራቸው ከሚያኮሩን የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች ውስጥ የዶርዜ ማህበረሰብ አንዱ ነው።

የዶርዜ ሕዝብ °° የሰላም የአንድነትና የአብሮነት ተምሳሌት ሕዝብ ነው :: ጥበበኞቹ የዶርዜ ማህበረሰቦች ከእጅ ጥበብ ስራቸው ባሻገር የራሳቸው የሆነ ባህላዊ ስርዓቶች አሏቸው።

በተቻለ መጠን በዚህ ስራችን የማህበረሰቡን እሴቶች ለማስተዋወቅ ሞክረናል።

ያረድ ነጉ

DMN ምክር ቤቱ በዚህ ዓመት ስድስት የማንነት ጥያቄዎችን ለመፍታት አቅዷል - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር***************************የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዚህ ዓመት ስድስት ...
14/10/2022

DMN
ምክር ቤቱ በዚህ ዓመት ስድስት የማንነት ጥያቄዎችን ለመፍታት አቅዷል - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር
***************************

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በዚህ ዓመት ስድስት የማንነት ጥያቄዎችን ለመፍታት ማቀዱን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

ምክር ቤቱ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ሲሆን የማንነት አስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ የ2015 ዓ.ም ዓመታዊ እቅድን አቅርቧል።

ቋሚ ኮሚቴው የሚቀርቡ የማንነት ጥያቄዎች ላይ ጥናት ማካሄድ እንደሚያስፈልግ እና አሳታፊ ሊሆኑ እንደሚገባ የገለፀ ሲሆን ውሳኔ ተሰጥቷቸውም ጭምር ከአፈጻጸም ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች መኖራቸውን ገልጿል።

በርካታ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች እየቀረቡ መሆናቸውን የተናገሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ፣ ትክክለኛውን ጥያቄ መለየት እንደሚያስፈልግ ገልፀው፣ ክልሎች ግን ለሚነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንደሚኖርባቸው ገልፀዋል።

በዚህ ዓመት 6 የማንነት ጥያቄዎችን ለመፍታት መታቀዱን የተናገሩት አፈ ጉባኤው፣ ክልሎች መግባባት እና ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

በአሸናፊ እንዳለ

ለ ዶርዜ መስቀል በዓል ማንም እንዳይቀር || ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል ከየትኛዉም ቦታ በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በራችን ክፈት ነው:: ዶርዜ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይ ነው::
19/09/2022

ለ ዶርዜ መስቀል በዓል ማንም እንዳይቀር || ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል

ከየትኛዉም ቦታ በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በራችን ክፈት ነው::

ዶርዜ ሰው አክባሪና እንግዳ ተቀባይ ነው::

DMNዮ ዶርዜ ማስቃላለደማቁ የዶርዜ መስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ!!!ዮዮ.....ዮዮ...ዶርዜ ማስቃላ
19/09/2022

DMN
ዮ ዶርዜ ማስቃላ

ለደማቁ የዶርዜ መስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ!!!
ዮዮ.....ዮዮ...ዶርዜ ማስቃላ

ዮ ዶርዜ ማስቃላእንኳን ደህና መጣቹልን ወደ ምርጧ ዶርዜ ምድር ሸዊት ከበደ እና ይገረም ደጀኔ  ትልቅ ፍቅር እና አክብሮት አለንመልካም ቆይታ ይሁንላቹ !!!ዮ ዶርዜ ማስቃላ
31/08/2022

ዮ ዶርዜ ማስቃላ

እንኳን ደህና መጣቹልን ወደ ምርጧ ዶርዜ ምድር

ሸዊት ከበደ እና ይገረም ደጀኔ

ትልቅ ፍቅር እና አክብሮት አለን

መልካም ቆይታ ይሁንላቹ !!!

ዮ ዶርዜ ማስቃላ

    🏄‍♂️🚴‍♂️🏊🧗🤸🚶🏃🚶🚶
14/08/2022


🏄‍♂️🚴‍♂️🏊🧗🤸🚶🏃🚶🚶

    🚶🚴‍♂️🤸🧗🏊🚴‍♂️🏄‍♂️🏃
14/08/2022


🚶🚴‍♂️🤸🧗🏊🚴‍♂️🏄‍♂️🏃

     Hiking 🚶‍♂️ 🚵🤸🚴‍♂️🏄‍♂️🏃🚶🏊
14/08/2022



Hiking 🚶‍♂️ 🚵🤸🚴‍♂️🏄‍♂️🏃🚶🏊

    🧗🏄‍♂️🏊🚴‍♂️🤸🚵🏃🚶
12/08/2022


🧗🏄‍♂️🏊🚴‍♂️🤸🚵🏃🚶

  በሀዋሳ የማንነት፣ አስተዳደር ወሰን እና ግጭት አፈታት አቤቱታ አቀባበል፣ አያያዝና ምላሽ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደየፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ቀደ...
18/03/2022

በሀዋሳ የማንነት፣ አስተዳደር ወሰን እና ግጭት አፈታት አቤቱታ አቀባበል፣ አያያዝና ምላሽ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር

ቀደም ባሉት ጊዜያት የአቤቱታ አቀባበል፣ አያያዝ እና ምላሽ አሰጣጥ መመሪያ ባለመኖሩ ምክንያት የታዩትን ክፍተቶች በመሙላት ሥርዓቱን ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ፍትሐዊ እንዲሆን ለማድረግ መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

ለዚህም አቤቱታ አቅራቤዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተግባራቸውን ስርዓት ባለው መልኩ እንዲያከናውኑ የሚያስችል የአቤቱታ አቀባበል፣ አፈታትና ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓት አስፈላጊ መሆኑን በማብራራት ዝርዝር ረቂቅ መመሪያውን አቶ ጴጥሮስ አቅርበዋል።

የአስተባባሪውና የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላቱ በረቂቅ መመሪያው ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ሊካተቱ የሚገባቸውን ግብዓቶች እንዲካተቱ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አባላቱ ምክር ቤቱ አስጠንቶ ተግባራዊ ያደረገውን ሪፎርም መሠረት በማረግ የምክር ቤቱን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድና በ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ

ትኩረት ‼️‼️ በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በተለይ የእግዜር ድልድይ ላይ የእሳት ቃጠሎ   የአ/ምንጭ ከተማ እሳት አደጋ መቆጣጠር በአፋጣኝ የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ አለበት ። 📛📛📛📛📛ሼር ይደ...
07/03/2022

ትኩረት ‼️‼️
በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ በተለይ የእግዜር ድልድይ ላይ የእሳት ቃጠሎ የአ/ምንጭ ከተማ እሳት አደጋ መቆጣጠር በአፋጣኝ የመፍትሔ እርምጃ መውሰድ አለበት ።
📛📛📛📛📛
ሼር ይደረግ

የኑሮ ውድነት ነገርእዚህ ላይ ስለመካራና ከመከራ ስለማያወጣን ፖለቲካችን ትንሽ መነጋገር ያስፈልጋል። በአፍሪካ የሰሊጥ መሬት ኳላት ቁንጮ አገር ውስጥ እየኖርን የምንበላው ዘይት አጣን ብለን ...
06/03/2022

የኑሮ ውድነት ነገር
እዚህ ላይ ስለመካራና ከመከራ ስለማያወጣን ፖለቲካችን ትንሽ መነጋገር ያስፈልጋል። በአፍሪካ የሰሊጥ መሬት ኳላት ቁንጮ አገር ውስጥ እየኖርን የምንበላው ዘይት አጣን ብለን እያለቀስን ነው።

የአገሬ ህዝብ ሁሌም የሚነዳበትን ፖለቲካ ወጣ ብሎ የልቡን የሚነዳለት ፖለቲከኛ መምረጥ ካልቻለ የግፍ ቀማሹ እሱ ነው። ከችጋርና ከውርደት ከባርነት የማያወጣ የብሔር ፖለቲካ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ አንዱ የተደራጀ ኢኮኖሚ እንዳይፈጠር በመከላከሉ ነው።

በህዝብ ቁጥሯ ከአፍሪካ ሁለተኛውን ቦታ የያዘችው አገር የተደራጀ የኢኮኖሚ አሰራር የላትም። ለተደራጀ ኢኮኖሚ አሰራር ከምትሰጠው ትኩረት ይልቅ፣ በየክልሉ የሚዋጉ ልዩ ሀይሎችን ለማስመረቅ
የምትበጅት ቢሊዮን ብር ላይ ትኩረት ሰታ ትሰራበታለች።
የብልጠታችን ልክ እስከዚህ ድረስ ነው። እኛ ማለት የሚጠቅመንን ነገር የማንፈልግ የማይጠቅመንን ነገር ተከትለን የምንኖር
አለም ወደፊት እየተራመደ እኛ ወደኋላ የምናይ ብኩኖች ነን። 120 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር የተደራጀ የገበያ ስረአት የላትም። የተደራጀ የምርት ማምረቻ የላትም። የተደራጀ የጥላቻ ሰባኪ ሚዲያዎችና አንድም ቀን ስለዚህ ችግር የማይተነፍሱ ልጆች ግን አለንላት።

ይህ የሚሆነው የአለማችን የውሃ እናት ናት ተብላ በምትጠራው አገር ላይ ነው። ምንም የውሃ መሰረት የሌላቸው አገሮች ግን እኛን ዞረው ይቀልባሉ። እንኳን እንደኛ ዝናብና የተደራጀ ጦም አዳሪ መሬት ሊኖራቸው ይቅርና እልም ያለ አሸዋና በረሀ ይዘው ከራሳቸው አልፈው ሌሎችን ይቀልባሉ። ግብፅ ቀዳሚዋ የዘይት አምራች አገር ናት ከአፍሪካ። ዛሬ ግን ከግብፅ ወጣ እንልና ሌላ አንዲት በረሃ አገርን መርጠን ትንሽ እናወራለን።
ሳኡዲ አረቢያ ናት።

ዋሲሁን ተስፋየን ስለ ሳኡዲ የፃፈውን መነሻ
አድርገን፣ ሳውዲ ውስጥ ምንም አይነት ወንዝም ሆነ የተደራጀ ሃይቅ የለም። ጥቂት ዝናብ ከሚያገኙ የአለም ሃገራት መሃከልም አንዷ ሳውዲ ናት። ዝናብ ከዘነበም አመታዊ የዝናብ መጠኗ ከ4 ኢንች አይበልጥም ። ይህ ማለት በዚህ ዝናብ ተጠቅሞ ምንም አይነት የግብርናም ሆነ የመጠጥ ውሃ ማግኘት አይቻሉም ማለት ነው።

በአመት 4 ኢንች ዝናብ ብቻ የምታገኘው ሳውዲ አንድም ወንዝና አንድም ሃይቅ ያልተፈጠረባት አገሬ ናት። በአለም ላይ ካሉ ግንባር ቀደም ስንዴ ላኪ አገሮች ውስጥ አንዷ ሳኡዲ ናት። እንደውም የዛሬ አስር አመት አካባቢ በአለም ካሉ አምስት ስንዴ ሻጭ ሃገራት መሃከል ሳውዲ አረቢያ አንዷ ነበረች። ስንዴ ብቻ አይደለም ። ቴምር ፣የወተት ተዋፅኦ ፣እንቁላል ፣አሳና አበባም ወደ ውጭ ትልካለች። ሽንኩርትና ቲማቲም
ድንች ከውጭ ማስገባቷን አቁማ ራሷ ነች እራሷን የምትመገብው። 27 ሚሊየን የሬሷ ዜጋ ያላት ሳኡዲ 13 ሚሊየን የውጭ ዜጋ በሀገሯ ውስጥ የሚኖረውን ጨምራ ለ40 ሚሊየን ህዝብ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ድንች ሎሚ ስጋ ወተት ድንች ስንዴ ገብስ
ወዘተ እራሷ ናት የምታቀርበው። ሳኡዲ ይሄም ብቻ አይደለም። በእንስሳት ሀብቷ ከአለም ሁለተኛዋ አገር ናት። እነዚህ እንስሳቶች የሚበሉትን መኖ ከአገሯ ነው የምታመርተው። የእንስሳቶቹ መኖ ሳር ወይም ሌላ ነገር አይደለም። ንፁህ የስንዴና የገብስ ምርት ነው።

ታዲያ ይሄ ውሃ ከየት ተገኘ ? ውሃው የሚገኘው ከከርሰ ምድር ውስጥ ተቆፍሮ ነው። ይህ ሲባል በሳውዲ ውሃ ለማግኘት የሚቆፈረው እንደ እኛ ሃገር 20 እና 30 ሜትር አይደለም። በበረሃማይቱ ሳውዲ አረቢያ ውሃ ለማግኘት ከተፈለገ ወደ ታች አንድ ኪሎ ሜትር እና ከዛ በላይ መቆፈር ግድ ነው።
የደራጀ የኢኮኖሚ አሰራራቸው
በረሃውን አገር ለምለም ምድር (OASIS)
እንዲያደርጓት አመችቷቸዋል። የምግብ ፍጆታቸውን ሙሉ ለሙሉ በራሳቸው አቅም ችለው ለሌላ ሀገራትም ግንባር ቀደም ስንዴና ገብስ ስጋ ወተት ላኪ ሆነዋል።
እንደኛ ከተራደ ኢኮኖሚ አሰራር ይልቅ የተደራጀ ልዩ ሀይልን ቢሊዮን ብር በጅተው አያስመርቁም።
እነዚህን ነገሮች ያስተዋለ ሰው እኛስ ብሎ መጠየቁ አይቀርም። አውሮፓውያንና አሜሪካ እጃችንን ለመጠምዘዝ ከሚሞክሩባቸው ነገሮች አንዱ በምግብ እህል ራሳችንን ባለመቻላችን በሚሰጡን ድቅል ስንዴ ምክንያት ነው።

እናም አንድ ኪሎ ሜትር ወደታች ቆፍረው በረሃማነትን ተረት ካደረጉት ሳውዲዎች ትምህርት እንውሰድ። በከተማ ግብርና በየጓሮው በትናንሽ የፕላስቲክ እቃዎች አምርተው የሃገራቸውን የምግብ ፍጆታ ሴኪውር ካደረጉት እስራኤላውያን እንማር
የምንኖርባትን አገር ጥቅምና ማንነት የማናውቅ ከሆነ እሱን ለማወቅ እንጣር። ከችጋር የማያወጣን ፖለቲካ አርፈን እንተወው። ማርሻና መፍር በሬን አንድ አድርገን ከማረስ ወደ ዘመናዊ የእርሻ አስተራረስ ዜዴ የሚቀየርንን መሪና ፖለቲካ ሚዲያ እንገንባ። ከዛውጭ በቢሊዮን ብር ልዩ ሀይል አስልጠንነን፣ እያለ፣ ብንፎክር ዋጋ የለውም።

^ሱሌማን አብደላ^

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DMN_Dorze Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share