ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media

ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media የቴክኖሎጂ ፈረስ በፈለገበት እንዳይዘውረን በሃይማኖት ልጓም ይዘን የሚጠቅመውን እናስተላልፍበታለን
(2)

♦️ለጥምቀት ዝግጁ ነው። አሁኑኑ እየደወላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ።
31/12/2024

♦️ለጥምቀት ዝግጁ ነው። አሁኑኑ እየደወላችሁ ማዘዝ ትችላላችሁ።

♦️ይኽች ታኅሣሥ ፳፪ ቀን ልዩ ቀን ነች።ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕ...
31/12/2024

♦️ይኽች ታኅሣሥ ፳፪ ቀን ልዩ ቀን ነች።

ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕለት ታኅሣሥ ፳፪ ‹‹ብሥራተ ገብርኤል›› ታላቅ በዓል ነው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሐርና ወርቅ አስማምታ በምትፈትልበት ሰዓት ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ ‹‹ደስ ይበልሽ፣ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፤ ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ›› አላት፤ ድንግል ማርያምም "እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንዴት ይደረግልኛል? " ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም "ማርያም ሆይ አትፍሪ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና፤

እነሆ ትፀንሺያለሽ፤ ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፤ ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው፤ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል፤ ወንድ ሳለውቅ?›› አለችው፡፡ መልአኩ ገብርኤልም ‹‹መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል፤ የልዑል ኃይልም ያድርብሻል›› አላት፡፡ እርሷም የመልአኩን ቃል ተቀብላ ‹‹እንደ ቃልህ ይደረግልኝ›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ አካላዊ ቃል በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተፀነሰ፡፡

ቅድስት ማርያም እምነቷን በእግዚአብሔር ላይ አድርጋለችና በትንቢተ ነቢያት መሠረት በድንግልና ፀነሰችው፡፡ (ሉቃ. ፩፥፳፰-፳፱፣ ኢሳ. ፯÷፲፬ )
ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ስለ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራትና ስለ አምላክ ሰው መሆን ሲመሰክር ‹‹እርሱ እግዚአብሔር አብ ንጽሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ቅዱስ ገብርኤል የሚባል መልአክ ወደ አንቺ ላከ፤ መንፈስ ቅዱስ በላይሽ ያድራል፡፡ የልዑል ኃይልም ይጋርድሻል አለሽ፤ ከአባቱ ሳይለይ ቃል ወደ አንቺ መጣ ሳይወሰን ፀነስሽው፤ በላይ ሳይጎድል በታችም ሳይጨመር በማሕፀንሽ ተወሰነ፤ መጠንና መመርመር የሌለበት እሳተ መላኮት በማሕፀንሽ አደረ›› (ቅዳሴ ማርያም ቁ. ፵፭) ብሏል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን የብሥራት ቀን በማሰብ ታከብረዋለች፡፡
https://yt.psee.ly/6wnx9q

♦️የኮተቤው ገብርኤል እንዲህ ነበር
30/12/2024

♦️የኮተቤው ገብርኤል እንዲህ ነበር

♦️በዚህ ዘመን እየጠፋ ያለውን ትውልድ የመታደግ ትግል " በሚል በቅርቡ ከብዙ ፈተናዎች በኋላ እጃችሁ ትገባለች ተዘጋጁ!!!ዘመኑን በትክክል እየዋጀ ይህንን ትውልድ ለመታደግ ዕለት ዕለት የሚ...
29/12/2024

♦️በዚህ ዘመን እየጠፋ ያለውን ትውልድ የመታደግ ትግል " በሚል በቅርቡ ከብዙ ፈተናዎች በኋላ እጃችሁ ትገባለች ተዘጋጁ!!!

ዘመኑን በትክክል እየዋጀ ይህንን ትውልድ ለመታደግ ዕለት ዕለት የሚደክመውን ወንድማችን መምህር ውብሸት ክብር ያድልልን እድሜ ይስጥልን።

ምን አነበባችሁ ?♦️የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ክብር በደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ገብርኤልኮተቤ።
28/12/2024

ምን አነበባችሁ ?
♦️የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ክብር በደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ገብርኤል
ኮተቤ።

♦️ምድራዊ እሳት በሰማያዊ እሳት የጠፋበት ታላቅ ቀንዛሬም በዓለም ላይ በተለይም ደግሞ በሀገራችን ላይ ያለውን የመለያየት፣ የመገዳደል፣ የረሃብ፣ የዘረኝነት፣ የመከፋፈል እሳት ይጠፋልን ዘንድ...
28/12/2024

♦️ምድራዊ እሳት በሰማያዊ እሳት የጠፋበት ታላቅ ቀን

ዛሬም በዓለም ላይ በተለይም ደግሞ በሀገራችን ላይ ያለውን የመለያየት፣ የመገዳደል፣ የረሃብ፣ የዘረኝነት፣ የመከፋፈል እሳት ይጠፋልን ዘንድ ሰማያዊው እሳት ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ለሠለስቱ ደቂቅ ፈጥነህ እንደደረስክ ለእኛም ድረስልን።

እንኳን አደረሳችሁ
https://yt.psee.ly/6wd3yy

27/12/2024

♦️ከመጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ መንግሥቱ ጥላሁን (የእናቴ ልጅ) ጋር ቆይታ
ስለ አጥማቂነት እና የአጠማመቅ ሥርዓት
https://yt.psee.ly/6w67zk

26/12/2024

♦️የበረታች ነፍስ የደከመን ሥጋን ታበረታለች
♦️የበረታ ሥጋ ግን የደከመችውን ነፍስ ማበርታት አይችልም
መ/ር ውብሸት ተሾመ

https://yt.psee.ly/6vxpsuአይዞሽ እናት ዓለም ቀን አለው እግዚአብሔር ቀና ያደርግሻል ያቆምሻል በክብርዛሬ የምታይውን ጭንቅ እና መከራዳግመኛ አታይውም እግዚአብሔር ሲሰራ
25/12/2024

https://yt.psee.ly/6vxpsu
አይዞሽ እናት ዓለም ቀን አለው እግዚአብሔር
ቀና ያደርግሻል ያቆምሻል በክብር
ዛሬ የምታይውን ጭንቅ እና መከራ
ዳግመኛ አታይውም እግዚአብሔር ሲሰራ

ሁሉም ሰው ይስማው

♦️አንተ ብቻ አልነበርክም የታሰርከው ኩኒ  ብዙ የተዘጉ እና የተጀመሩ አብያተ ክርስቲያናትም ጭምር ነበር የታሰሩት።እንኳን ተፈታህ። የሐዋርያት በረከት ያድርግልህ።
25/12/2024

♦️አንተ ብቻ አልነበርክም የታሰርከው ኩኒ ብዙ የተዘጉ እና የተጀመሩ አብያተ ክርስቲያናትም ጭምር ነበር የታሰሩት።

እንኳን ተፈታህ። የሐዋርያት በረከት ያድርግልህ።

ከ13 ቀናት እስር በኃላ ተፈተናል።

ሳንደባልቅ፣ሳንለይ ዝንት ዓለም ርዕሳችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት።

ክብሯ ብርሃን፣ቅድስናዋ ጸዳል፣ንጽህናዋ ምልክት ከሆነችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ውጪ ምን የሚያከብር ርዕስ አለ?

ወደ መስዋትነት እና መከራ በፍጹም አንሄድም። መሰዋት እና መከራ ግን አፍጦ ከመጣ መንፈስቅዱስ ያጸናንን ዘንድ ብቻ እንማጸናለን!!!

ከነገድ ከቋንቋ፤ከዓለም ክብር እና ሞገስ ነጥቆን የብርሃን ልጆች ላደረገን የድንግሊቱ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባው።

🙏🙏🙏

Kune Demelash kassaye -Arba Minch

♦️ዘመኑ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ለጥፋት እየፈጠነ ነው♦️መቅሰፍቱ እና ርኩሰቱ እንደ ጎርፍ እያጥለቀለቅን ነው♦️እናት ትጸንሳለች፣ ታምጣለች፣ ትወልዳለች፣ ታሳድጋለች ... ከዚያስ ...
25/12/2024

♦️ዘመኑ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ ለጥፋት እየፈጠነ ነው
♦️መቅሰፍቱ እና ርኩሰቱ እንደ ጎርፍ እያጥለቀለቅን ነው
♦️እናት ትጸንሳለች፣ ታምጣለች፣ ትወልዳለች፣ ታሳድጋለች ... ከዚያስ ...

   ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል። ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ ...
24/12/2024



ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!!

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #ብፁዕአቡነኤርምያስ #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!


Adress

Asogatan 79 I Stockholm
Stockholm
11829

Webbplats

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Affären

Skicka ett meddelande till ቋንቋዬ ነሽ ሚዲያ Quanquayenesh Media:

Videor

Dela