RN05

RN05 ከኢትዮጵያ እና ዲያስፖራ የሚተላለፍ ሚድያ!
አዲሱን ዩቱብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://www.youtube.com/c/RN05channel

https://t.me/RNZeroFive

https://rnzerofive.com/

31/12/2024

❓ጠረጴዛዉን የገለበጠው ማነው? - የሁለቱ ከተሞች ወግ
~~~~~~~~~~~

ይህ የፈረንጆች አዲስ አመት 2025ን አቀባበል አስመልክቶ በቶሮንቶና በዱባይ የተከናወኑ ድርጊቶችን የሚያሳዩ 2 አጭር ቪድዮዎች ክሪቲካል አስተሳሰብን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ክሪቲካል አስተሳሰብ ማለት ደግሞ በጣም በአጭሩ ከጠረጴዛው ላይ የሚታየዉን ሳይሆን በዋናነት ከጠረጴዛው ስር ያለዉን ለማየት መሞከር ነው፣ ወይንም በአንድ ስሙ "ጠረጴዛዉን መገልበጥ" እንደማለት ነው፡፡
ነገሩ ወዲህ ነው! ይህ ጃንዋሪ 1 የሚጀምረው የአዲስ አመት ካሌንደርና በአሉ በዋናነት የፈረንጆች ነው፣ ያ ማለት የካናዳዎች፣ አረቦች ደግሞ በአላቸው ባይሆንም አጃቢ አክባሪዎች ናቸው፡፡

እናም

1️⃣የመጀመርያው ቪድዮ - አጃቢ አክባሪዎቹ ዱባይ ዉስጥ ፈረንጆቹ እንኳ የማይተኩሷቸዉን ምን የመሰሉ አሸብራቂ ርችቶችን እየተኮሱ የካናዳዎቹን አዲስ አመት በደማቁ ሲቀበሉላቸው የሚያሳይ ነው፡፡
2️⃣ ሁለተኛው ቪድዮ ደግሞ - ካናዳዎቹ ቶሮንቶ ዉስጥ "No celebration until Liberation!" (ከነጻነት በፊት የምናከብረው በዓል የለም!) የሚል መሪ ቃል በማነገብ - ጋዛ ነጻ እስክትወጣ፣ ፍልስጤም ነጻ እስክትወጣ ድረስ በአል የለም፣ ሪችት የለም!" እያሉ በዓሉ አንድ ሰአት ሲቀረው ተሰብስበው ዱባዬዎች በዉክልና ያዉም ቀድመዋቸው የተቀበሉላቸዉን የአዲስ አመት ዋዜማ ለጋዛ ህጻናትና ግፉዓን ትኩረት መሳብያ ሲያዉሉት የሚያሳይ ነው!
ታድያ ቶሮንቶዎች ጠረጴዛዉን በመገልበጥ ክሪቲካል አሳቢ አልሆኑም ትላላችሁን?
ሁላችንም ክሪቲካል ብናስብ ከልምዳዊ የደመነፍስ አስተሳሰብ ባህል ተላቀን የላቁና የመጠቁ ህሳቤዎችን የምናቀነቅንና በዚህም ሰበብ የተሻለ ሀገርንና አለምን በፈጠርን, ስለ ሰባዊነትና እኩልነትም የተሻለ ግንዛቤ በያዝን ነበር፡፡
በሌላ አባባል በአሁኑ ሰአት ቶሮንቶዎችም በአላቸውን ባከበሩ ዱባዮችም ስለ ጋዛ ወንድሞቻቸዉ በተጨነቁ ነበር!
.
እናም ወዳጄ ከጎርፍ ጋር በደቦና በጭፍን መጉረፍ ሳይሆን ብቻህንም ብትቀር ለማስተንተን ትጋ ለማለት ነው
ይሄው ነው!

-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

🚩ሀገርን ጠቅልሎ ለመዉረስ በሚሰራና ስለ ሂጃቡ መወረስ ብቻ በሚጨነቅ  መሃል ያለው ልዩነት!👉የመጅሊሱ ሮድማፕ ጉዳይ~~~~~~~~~~~  ከታች የተያያዘዉን ስክሪንሾት ተመልክተሃል! እናማ እን...
30/12/2024

🚩ሀገርን ጠቅልሎ ለመዉረስ በሚሰራና ስለ ሂጃቡ መወረስ ብቻ በሚጨነቅ መሃል ያለው ልዩነት!
👉የመጅሊሱ ሮድማፕ ጉዳይ
~~~~~~~~~~~

ከታች የተያያዘዉን ስክሪንሾት ተመልክተሃል! እናማ እንደመስታወት እራስህን ብታይበት ምን ይታይሃል?!
ጽሁፉ አንድ አቅዶና አልሞ የሚሰራ የሃይማኖት ተቋም ንብረት ከሆነ ገጽ የቀዳሁት ሲሆን ፡ ግፋ ቢል ከ 5 እና ከ 7 አመታት በኋላ..... ምድሪቷን (ኢትዮጵያን ከነህዝቦቿ በወንጌል እንደሚወርሷት ይናገራል፡፡ ይህ በደመነፍስ ሳይሆን አቅዶና አልሞ ከሚሰራ ተቋም የሚጠበቅ አዎንታዊ ህሳቤ ነው! ይህ አንድ ጠንካራ የቲንክ ታንክ ወይንም አሰላሳይ ስብስቦችን መፍጠር ከቻለ ተቋም የሚጠበቅ በጥናት ላይ የተመሰረተ ድምዳሜ ነው!
መጅሊስስ በዳእዋ ምድሪቷን መዉረስ ይቅርና የሚመራው ዜጋ ሙስሊምነቱ ተከብሮ የመማር ፣ የመስገድ፣ብሎም የመቀበር ተፈጥሯዊ መብቶቹን ለማስከበር የስንት አመት እቅድ ይዞ ይሆን?
ለዚህስ ምድሪቱን ለመዉረስ ለታቀደው እቅድ መከላከያ ይሆን ዘንድ ምን አይነት መርሃግብርና በጀት አዘጋጅቶ ይሆን?
ልብ በል! አንዳንዶች በስሌት ሌሎች በስሜት በሚንቀሳቀሱባት ሀገር - ባለስሌቶቹ የማይገመቱ ትላልቅ እቅዶችን ያቅዳሉ፣ ለሚሆነው ሁሉ ቀድመው ይዘጋጃሉ፣ ሁሌም Plan A, Plan B ይኖራቸዋል፣ በመሆኑም ለተግባር ቅርብ ይሆናሉ፡፡ ባለስሜቶቹ ወቅቱ ባመጣቸው ትናንሽ ነገሮች ይጠመዳሉ፣በጥቂቱ ይደነቃሉ፣ ብዛታቸዉን በማየት የተከበሩና የማይደረስባቸዉ አድርገው ራሳቸዉን ይስላሉ፣በጥቂቱ አመስጋኝና በጥቂቱም አኩራፊ ይሆናሉ፡፡ ለአደጋ ሁሌም አይዘጋጁም፣መፍትሄም አያበጁም፣ አያቅዱም በመሆኑም ደጋግሞ በሚነሳባቸው ማእበልም ሁሌም ያልተዘጋጁ፣ድንጉጦችና አቅመቢስ ሆነው ያማርራሉ!
ይሄው ነው!

-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

30/12/2024

አክሱምና ላሊበላ ውስጥ የሚያስፈልገው አጠቃላይ ለውጥ ነው! ሂጃብ ብቻ ሳይሆን መስገድና መቀበርም ለሙስሊሞች ክልክል ነውና! እንዲህ አይነት ዃላ ቀርነት እንጂ ቅድስና የለም! ይህም ሙስሊሞችም ሆኑ ማገናዘብ የሚችሉ ክርስትያኖች የሚቀበሉት አይደለም! ቅድስና ያለው ሁሉም እንደየእምነቱ መኖር በሚችልባችው ሙስሊም በዝ ክልሎች ውስጥ ነው ! ስልጣኔ ማለትም ይህ ነው!

🚩መጅሊሱም ፖለቲከኞቻችንም ሃላፊነታቸውን ይወጡ!~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በረጂም ጊዜ ትግላቸው ካገኙዋቸው ድሎች መካከል አንዱ መሪ ድርጅታቸውን መ...
29/12/2024

🚩መጅሊሱም ፖለቲከኞቻችንም ሃላፊነታቸውን ይወጡ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በረጂም ጊዜ ትግላቸው ካገኙዋቸው ድሎች መካከል አንዱ መሪ ድርጅታቸውን መጅሊሰል አእላ ከመንግሥት ተሿሚዎች መዳፍ ሥር መንጭቀው ማውጣትቅቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ በፖለቲካው አለም የሙስሊም ተመራጮች ቁጥር ከፍ እንዲል ማድረጉ ነው። ምንም እንኳን መጅሊሱ ከመንግሥት ቁጥጥር ሥር ሙሉ በሙሉ የወጣ ነው ባይባልም ቀደም ብሎ ከነበሩት በተሻለ ለሙስሊሙ ማህበረሠብ የቀረበ ነው ብሎ ለመናገር ያስደፍራል። መጅሊሱ ከቀድሞዎቹ በተለይ ከሙስሊሙ ህዝብና ተቋማት ጋር ቀርቦ መነጋገርና ተባብሮ መስራት የሚችል ስለመሆኑ በርካታ ማሳያዎችን ማንሳት ይቻላል። መሪ ድርጅቱ ከቀድሞዎቹ በተለይ በዲፕሎማሲውም ረገድ ሆነ ሃገሪቱን በአለም አቀፍ ደረጃ በወከል በኩል የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን እየተመለከትን ነው። ሆኖም ግን የሙስሊሙን ማህበረሠብ መሰረታዊ ጥቅሞችና መብቶች በማስከበሩ ረገድ አጥጋቢ ሥራ እየሰራ ነው ብሎ ለመናገር አይቻልም። ሙስሊሞች አሁንም በየቦታው ለተለያዩ አይነት ጥቃቶችና ጭቆናዎች ሰለባ እየተደረጉ ነው።
ሴቶች ልጆቻችን በሂጃብ እየተሳበበ ከትምህርትና ከሥራ እየታገድ ስለመሆናቸው እስከ አሁንም ድረስ እየሰማን ነው። እነኝህን ችግሮች ለመቅረፍ በመጅሊሱ በኩል እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ደብዳቤዎችን ከመፃፍና ጨቋኞቹን ከመማፀን የዘለለ አይደለም። እንዲያውም መጅሊሱ ደብዳቤ መፃፉን ወይንም ጨቋኞቹን ሄዶ ማነጋገሩን እንደ ታላቅ እመርታ አድርጎ የወሰደው ይመስላል። ከወራት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሙስሊም ሴቶችን ይጨቁናልና አንድ በሉት ሲባሉ የእየር መንገዱ ባለሥልጣናትን አነጋረው ሲያበቁ ይህንኑ እንደ ትልቅ ቁም ነገር ቆጥረው ጥያቄውን በዚያው አድበስብሰው ሊያልፉት ሲሞክሩ ተስተውለዋል። የሴቶቹን መብት ከማስከበር ይልቅ ለአየር መንገዱ ዝና የተቋረቋሩ በሚያስመስል መልኩ አየርመንገዱ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ያለው ዝና እንዳይጎድፍ ጉዳዩን አለስልሰን ይዘነዋል ብለዋል።
በእየትምርት ቤቱም የሚከሰቱትን የመብት ረገጣዎች እያስተናገዱ ያለበትም መንገድ ተስፋ ሰጪ አይደለም። ችግሩ ከሥር መሠረቱ የሚፈታበትን መንገድ ቀይሰው ከመንቀሳቀስ ይልቅ እሳት በተነሳ ቁጥር እሳቱን ለማጥፋት በደም ነፍስ፣ እምብዛም ውጤታማ ባልሆነ አግባብ ሲወራጩ ታይተዋል። ይሄ በእውነቱ ልብ ሰባሪ ነው። ከሃምሳ ሚሊዮን በላይ ምእመናንን የወከለ፣ መጅሊስን የሚያክል ትልቅ ተቋም ምእመናኑን ከድርጅት ሃላፊዎች፣ ከትምርት ቤት ዴያሬክተሮችና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጥቃት እንኳን መከላከል የማይችል ሆኖ ሲገኝ ሙስሊሙ ለዚህ ነበር እንዴ ደሜን ያፈሰስኩት ብሎ መጠየቁ አይቀሬ ነው።
መጅሊሱም ብቻ ሳይሆን ሙስሊም የፓርላማ አባላትም ቢሆኑ መስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና ጭቆና በመከላከሉ ረገድ ይህ ነው የሚባል አስተዋፅኦ እያበረከቱ አይደለም። ሙስሊሙ በፖለቲካው መድረክ በበቂ ሁኔታ ልወከል ይገባል ብሎ የታገለው እኮ ለሙስሊም ፖለቲከኞች የሥራ እድል ለመክፈት ሳይሆን መብትና ጥቅሙን ለማስከበር በሚያደረው ትግል አጋዥ እንዲሆኑት ነው።
እርግጥ ነው አንዳንድ የፓርላማ አባላት ፓርላማው ውስጥ የሙስሊሙን ችግር አንስተው ሲናገሩ በቴሌቪዥን ታይተዋል። ከዚያ አልፎ ግን፣ ጥያቄውን ያነሱት ለይስሙላ እስከሚመስል ድረስ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ሲንቀሳቀሱ አይታዩም። ይሄ ተገቢ አይደለም። ሙስሊሙ ዘወትር በሂጃብ፣ በመስጊድ፣ በቀብር ቦታ ጥያቄና ብሶት ብቻ እንዲገደብ መፈቀድ የለበትም። እነኝህን ጥያቄዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልሶ ወደፊት መራመድ ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ መጅሊሱም ሆነ ፖለቲከኞቻችን ሃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ ሊወጡ ይገባል።

29/12/2024

🚩መከራ ያልመከራቸው የአክሱም ኤሊቶች ጉዳይ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ሁለት አመታትን በፈጀው የህወሃትና የብልፅና ጦርነት ከፍተኛ መስዋእትነትን ከከፈሉ የትግራይ ህዝቦች መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የአክሱም ህዝብ ነው። የአክሱም ህዝብ ቅድስት በሚላት ከተማና ቅድስት በሚላት ቤተክርስቲያኑ ውስጥ ሳይቀር በከፍተኛ ሁኔታ ተጨፍጭፏል፣ ሴቶቹ በጅምላ ተደፍረዋል፣ ከጭፍጨፋ የተረፉ ብዙዎች በዘላቂነት አካለ ስንኩላን ተደርገዋል። የአክሱም ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ ጭፍጨፋ የተፈፀመው ሃይማኖት እየተመረመረና እየተመረጠ ሳይሆን በጅምላ ነበር።
አእምሮ ላለው፣ አስተዋይ ልቦና ላለው ይህ አክሱም ህዝብ ላይ የደረሰ ጭፍጨፋ ትልቅ ትምህርት ሊቀሰምበት የሚችል ክስተት ነበር። አንድ ማህበረሰብ ይህንን በመሰለ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ሲይልፍ የደረሰበት መከራው አንድ እንዲሆን፣ ይበልጥ እንዲቀራረብ፣ እንዲረዳዳና እንዲተዛዘን ያደርገዋል። ትግራይ ውስጥ እያየን ያለነው ግን ከዚህ ፈፅሞ የተለየ ነው። መሪዎቹ ገና ላባቸው ሳይደርቅ በሥልጣን ሽኩቻ ተጠምደው የህዝባቸውን ቁስል ከመጠገን ይልቅ እንጨት እየሰደዱ ይበልጥ እያቆሰሉት ይገኛሉ፣ ሌብነትን አመላቸው ያደረጉት ባለሥልጣናቱ እህሉን ከመከረኛው ህዝባቸው አፍ ላይ እየነጠቁ በመቸብቸብ፣ ለሃገራቸውና ለህዝባቸው ጥቅም ሊውል የሚገባውን የተፈጥሮ ሃብት እየዘረፉ በኮንትሮባንድ በመቸብቸብ የማይጠረቃ ቀፈታቸውን ለመሙላት እየተጣደፉ ይገኛሉ፣ ካድሬዎቻቸው ሥልጣናቸውን ተጠቅመው ከብልፅናና ከሻአብያ የተረፉ ሴቶቻቸውን ይደፍራሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይደበድባሉ፣ ይገድላሉ። እነሆ መምህሮቻቸው ደግሞ ደሞዛቸውን እንኳን በቅጡ ተቀብለው ድሪቶዎቻቸውን መቀየር ሳይጀምሩ ጨቋኝ ጨቋኝ ይጫወታሉ! በርግጥም መከራ ያላስተማራቸው ኤሊቶች በመጽሃፍት ይማራሉ ብሎ ማለት ዘበት ነው፡፡ ይህ ምንኛ አሳፋሪ ባህሪይ ነው?! ፈጣሪ ... ከችግር የማይማር ኤሊት በሚመራው አጀብ ውስጥ ከመገኘት ይጠብቃችሁ!

በእርግጥም "መንግስትን ሳይገለብጡ" የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስትን ማዳን ይቻላልን? - የጃዋር ቀጣይ ትግል
29/12/2024

በእርግጥም "መንግስትን ሳይገለብጡ" የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስትን ማዳን ይቻላልን? - የጃዋር ቀጣይ ትግል

➤ ውድ ተከታታዮቻችን ለተጨማሪ ቪዲዎች➤ RN.05ን ሰብስክራይብ ያድርጉ➤ የ RN.05 ቤተሰብ ይህኑ➤ ስራዎቻችን ላይክ ሼር በማድረግ ቤተሰቦነትዎን ያጠናክሩ ጀዛከላህ ኼይረንከኢትዮጵያና አዉ...

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ‼️የአክሱም ሙስሊሞች በአክሱም ኑሯቸው ምድራዊ ጀሃነብ ነው። በመስጂድና መቀበሪ ስፍራ ክልከላ የሚሰቃዩት ስቃይ ሁላችንም እናውቀዋለን። የሁለት ደቂቃ አዛን ለማውጣት...
28/12/2024

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ‼️

የአክሱም ሙስሊሞች በአክሱም ኑሯቸው ምድራዊ ጀሃነብ ነው። በመስጂድና መቀበሪ ስፍራ ክልከላ የሚሰቃዩት ስቃይ ሁላችንም እናውቀዋለን። የሁለት ደቂቃ አዛን ለማውጣት እንኳ «ያልነበራችሁ ፀባይ አታምጡ ድምጹን ቀንሱት፤ መካና መዲና እንጂ እዚህ እኮ ምንም ነገር የላችሁም» እየተባሉ በስቃይና ሰቀቀን ተውጠው ይኖራሉ። ይህ ስቃይና እንግልት አልበቃ ያላቸው ደግሞ ልጆቻቸው በወሳኝ ጊዜ ከትምህርት ገበታ እያስቀሯቸው ይገኛሉ። በህመማቸው ሌላ ህመም በስቃያቸው ሌላ ስቃይ ያክሉባቸዋል😭

እንዲህ ዓይነት ጭካኔ ይህ የአውሬነት ባህሪ አክሱም የት ያደርሳት ይሆን? ይህ እብሪትና ማን አለብኝነት ይጠቅማት ይሆን?

ትግራይ ሙስሊም ሚድያ ፣ ትግራይ ሙስሊም ሚድያ

28/12/2024

በሀገሪቱ ያሉ ት/ቤቶች ሙስሊም ጠል ከሆኑ እንግድያው መሆን ያለበት ቀጣዩ እርምጃ በመላ ሀገሪቱ ማንንም በሀይማኖቱ ሰበብ የማያገሉና ሁሉንም የሚያስተናግዱ የሙስሊም ት/ቤቶችን በግብር ከፋዩ ዜጋ ሀብት እንዲገነባ፣ አልያም ያሉትን ት/ቤቶች ቆጥሮ እንዲያካፍል መንግስትን ማስገደድ ነው! - መብት በልመና አይከበርምና!

🚩የምእራባዊያን ሚድያዎችንና መንግስታትን ያስፈነደቁት አዲሱ የደማስቆ ከንቲባ👉"... እኛ የእስራኤልን የደህንነት ስጋት እንረዳለን!" ~~~~~~~~~~~~~~~ ደማስቆ አዲስ ገዥ ተሹሞላታል፡...
27/12/2024

🚩የምእራባዊያን ሚድያዎችንና መንግስታትን ያስፈነደቁት አዲሱ የደማስቆ ከንቲባ
👉"... እኛ የእስራኤልን የደህንነት ስጋት እንረዳለን!"
~~~~~~~~~~~~~~~

ደማስቆ አዲስ ገዥ ተሹሞላታል፡ ማህደር ማርዋን ይባላል፣ የኤችቲኤስ አባል ነው። አዲሱ የሶርያ መንግስት ባለስልጣናት መሃል የሆኑት እኚሁ የዳማስቆ አዲሱ ገዢ ስለ እስራኤል በተናገሩት ነገር በአሸባሪነት መድበዋቸው በጥርጣሬ የሚመለከትዋቸው የነበሩት አዉሮፓዊያኖችን አስፈንድቀዋል።
አዲሱ የደማስቆ ገዥ ማህደር ማርዋን አለም አቀፍ ሚዲያዎችን አቀባበል አድርገው ባነጋገሯቸው ወቅት "ከሳምንታት በፊት አሸባሪዎች እንባል ነበር" አሁን ግን ያ አይደለም!" “ወደ ደቡብ ስንጓዝ በሃማ እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሰዎች የአገዛዙን ጀሌዎች እንድንበቀል ጠይቀዉን ነበር እኛ ግን እነርሱን ከጥፋት ጥበቃ እያደረግንላቸው ነው።" ያሉ ሲሆን

ማርዋን ከአሜሪካው ሬዲዮ ጣቢያ NPR ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ምርንግስታቸው ከጎረቤታቸው እስራኤል ጋር ጥሩ ግንኙነት እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡ ማርዋን "የእስራኤልን ወይም የሌሎች ሀገራትን ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ነገር ውስጥ መሳተፍ አንፈልግም" ብለዋል። "እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እኛ የእስራኤልም ሆነ የማንም ጠላት መሆን አንችልም።" ብለዋል
የደማስቆ ገዥ ሆነው ከተሾሙት የ42 አመቱ ሰው ለአሜሪካው ጣብያ ሲናገሩ "እኛ ወደ ደማስቆ እንደገባን እስራኤል ድንበራችንን አልፋ የገባችዉና የደበደበው የእኛን አቋም ባለማወቅ ፈርታ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ለእስራኤል የሶርያ ወረራ ምክን ያታዊነት መስክረዋል፡፡
የእስራኤል ሃይሎች ወደ ሶሪያ የሚያደርጉት ግስጋሴ የአለም አቀፍ ህግን እንደጣሰ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በድንበራችንን በተመለከተ የተስማሙበትን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ ቀጣና የሚለዉን ዉል እንደመጣስ ቢቆጠርም አዲሱ የሶርያ መንግስት የእስራኤልን የደህንነት ስጋት ይረዳል ብለዋል፡፡ ።
አዲሱ የሶርያ መንግስት ዓለም አቀፍ እውቅና ለማግኘት ተስፋ እያደረገ ቢሆንም በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ በግልጽ አልቀረበም፣ ሆኖም እኚህ የሶሪያ ርዕሰ መዲና ገዥ ከዩኤስ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ እሳቸው የሚናገሩት የመሪያቸው አህመድ አል-ሻራ ፖሊሲንና የሶሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በመወከል እንደሆነ ገልጸው በአጠቃላይ እስራኤልን በተመለከተ "እኛ እስራኤልን አንፈራም፣ ችግራችንም እስራኤል አይደለችም።" ብለዋል

የደማስቆ ገዥ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ ከሽፒግል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲያብራሩ “ጦርነትና የአገራችን መበታተን ሰልችቶናል፣ የሶሪያ አብዮት አብቅቷል። ሀገራችንን መልሶ ለመገንባት ጊዜው አሁን ነው!" ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የማንም ጠላት አይደለንም ከማንም ጋር መዋጋት አንፈልግም የሚለው አዲሱ የሶርያ መንግስት ከኢራን ጋር ግን ለመዋጋት ዝግጁ መሆኑን በሚያሳብቅ መልኩ እሰጥ አገባ ዉስጥ መግባቱና ማስጠንቀቅያም መስጠቱ ይታወሳል፡፡

-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

👀🔴ገራሚው የትግራይ መጅሊስ፣ የትምህርት ቤቱ ሃላፊና  የተማሪዎቹ ምስክርነት!~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~                 _______________________________...
27/12/2024

👀🔴ገራሚው የትግራይ መጅሊስ፣ የትምህርት ቤቱ ሃላፊና የተማሪዎቹ ምስክርነት!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

______________________________________

➡️" እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው። ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሄ ይሰጠን " - ተማሪዎች

➡️ " የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም የሉም ከትምህርት ገበታ ላይ ወጥተዋል " - የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

➡️ " ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም " - የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
_____________________________________

በትግራይ ፣ አክሱም ከተማ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት 2 ሳምንታት ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት መግባት እንደተከለከሉና በዚህም ምክንያት ከትምህርት ገበታ ዉጭ መደረጋቸውን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አሳውቋል።

መጅሊሱ በዚህ ዓመት ከሂጃብ መልበስ ጋር በተያያዘ በአክሱም በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውዝግቡ የጀመረው ጥቅምት ወር ላይ ሲሆን ተቋሙ ለክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቆ አውንታዊ ምላሽ ቢሰጠውም በተግባር የተቀየረ ነገር ግን እንደሌለ ነው ያሳወቀው።

🚩 የምክር ቤቱ ፀሀፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ፡
👉 "ፀጉራቸውን ሸፍነው ትምህር ቤት ዉስጥ እንዲታዩ አልተፈቀደም> ፀጉሯን መሸፈን ደግሞ የአንድ ሙስሊም ሴት ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው።
👉"ሃይማኖት በፖለቲካ ጣልቃ አይገባም፣ ፖለቲካም በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚል አንቀጽ በህገ መንግስቱ ተቀምጦ እያለ አሁን ፖለቲካው በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ ነው።" "ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል የፀጉር መሸፈኛ ሂጃብ መጠቀም እንደሚችሉ በ2000 የወጣ ሀገር አቀፍ መመሪያ አለ። ስለዚህ ዝም ብለን የምናየው ነገር አይሆንም።"
👉በአሁኑ ሰአት ከአራት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለዋል።
👉ዋናው ደግሞ 3 ወር ሲማሩ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና የኦንላይ ምዝገባ የሚደረግበት በዚህ ወቅት ነው ያፈናቀልዋቸው እናም ምዝገባዉ በዚህ ሳምንት ያልቃል፡፡ የአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች በዚህ ምክኛት እስካሁን ድረስ አልተመዘገቡም። የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በአጠቃላይ ሁሉም ትምህርት ላይ የሉም፣ ከትምህርት ገበታ ላይ ተገለዋል፤ እስካሁን ተከልክለው አልገቡም። ችግሩ እንዲፈታ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ እና ከአክሱም ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር ውይይት እየተደረገ ነው " ብለዋል።
🚩ተማሪዎቹ በበኩላቸው ፡

👉" በጦርነት ምክንያት ለ2 ዓመታት ከሌሎች ተማሪዎች ወደኃላ ቀርተናል አሁን ደግሞ በሂጃብ ምክንያት ፈተና ሊያመልጠን ነው።
👉ፎርሙ እያመለጠን ነው። ሌሎች ተማሪዎች በሂጀብ ፎርም እንደሞሉ ነው የምናውቀው። እኛ የምንፈልገው ፍትህ ነው። ሂጃባችንን አድርገን ነው መማር የምንፈልገው።
👉ያለ ሂጃብ ሸሪዓም አይፈቅድም ፤ መፍትሄው ደግሞ በጣም አስቸኳይ እና ዘላቂ መሆን አለበት። እስካሁን መብታችን እየተከበረ አይደለም " ብለዋል።

🚩 የአክሱም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፡

ምክትል ርዕሰ መምህር ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሔር ፦

👉"ትምህርት ቤቶች ከሃይማኖት እና ከፖለቲካ ነጻ መሆን አለባቸው ' "የትግራይ ክልል የትምህርት ቤቶች አደረጃጀት መመሪያ ማንም ተማሪ በትምህርት ቤት ሃይማኖትን የሚያንጸባርቅ ነገር ማድረግ የለበትም።" ይላል

👉ክርስቲያኑ መስቀል ወይም መጠምጠሚያ ፤ ሙስሊሙም ሂጀብ ወይም ኮፍያ ማድረግ አይፈቀድለትም። የትምህርት ቤቱ መለያ ዩኒፎርም ብቻ ነው መለበስ የሚገባው።

👉የተወሰኑ ተማሪዎች ሂጃባቸውን አናውልቅም ብለው ነበር አሁን ግን ተማሪዎች የትምህት ቤቱን መመሪያ ተከትለው እየገቡ ናቸው። አሰራሩ ለዓመታት የቆየ ነው " ብለዋል።

🚩 አንድ በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን የሰጡ የክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኛ ፤

👉" በክልሉ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እየሆነ ያለው በ1995 የወጣ መመሪያ ነው በዚያ መመሪያ ትምህርት ቤቶች የራሳቸውን መተዳደሪያ ማውጣት እንደሚችሉ ይደነግጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
🚩🚩 የክልል ትምህርት ቢሮ እና የአክሱም ከተማ አስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆኑም።
@ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@የቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ትግርኛ አገልግሎት

27/12/2024

ይድረስ ለመጅሊስ! በልመናና በሽምግልና ከሚገኘው ይልቅ በህግ የተከለከለው መብት ይሻላል! ወደ አክሱም የሚያቀና ሽማግሌ በመፈለግ ከምትኳትን ወደ ፍ/ቤት የሚያደርስህን ጠበቃ መልምል!

27/12/2024

ብዙዎች "ለምን መንግስት አልዋጣ አለን? ለምን ሄዶ ሄዶ እዛው ይሆናል?" ይላሉ! ጎበዝ ሰዎች የሚሰጣቸው እኮ የሚገባቸውን ነው! አስሬ መንግስትን ከመቀያየር አንዴ ራስን መቀየር ሺ በላጭ ነው! ይሄው ነው።

አነጋጋሪውና ሃሳባቸው ትክክል ሆነም አልሆነ ኢትዮጵያ ከቀሯት ጥቂት ፖለቲካ አዋቂዎች መሃል የሆነው ጀዋር መሐመድ ዳግም ተከስቷል! የብልጽግናው ጎራ ዋነኛ አጀንዳም ሆኗል!
26/12/2024

አነጋጋሪውና ሃሳባቸው ትክክል ሆነም አልሆነ ኢትዮጵያ ከቀሯት ጥቂት ፖለቲካ አዋቂዎች መሃል የሆነው ጀዋር መሐመድ ዳግም ተከስቷል! የብልጽግናው ጎራ ዋነኛ አጀንዳም ሆኗል!

➤ ውድ ተከታታዮቻችን ለተጨማሪ ቪዲዎች➤ RN.05ን ሰብስክራይብ ያድርጉ➤ የ RN.05 ቤተሰብ ይህኑ➤ ስራዎቻችን ላይክ ሼር በማድረግ ቤተሰቦነትዎን ያጠናክሩ ጀዛከላህ ኼይረንከኢትዮጵያና አዉ...

አክሱም መስጂድን ብቻ ሳይሆን ሂጃብንም ማየት ተጠይፋለች!~~~~~~~~~~~  በሒጃባቸው ምክንያት በር የተዘጋባቸው የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የኛ ድምፅ ይሻሉ! እነዚህ የአክሱም ሙስሊም...
25/12/2024

አክሱም መስጂድን ብቻ ሳይሆን ሂጃብንም ማየት ተጠይፋለች!
~~~~~~~~~~~


በሒጃባቸው ምክንያት በር የተዘጋባቸው የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የኛ ድምፅ ይሻሉ!

እነዚህ የአክሱም ሙስሊም ሴቶች ዛሬም የኛ ድምፅ ይሻሉ! በሒጃባቸው ምክንያት አትገቡም ተብለው በር ላይ ከቆሙ ሳምንታት ተቆጠሩ! የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ናቸው በሒጃባቸው ምክንያት ፎርም እንዳይሞሉ ተከልክለዋል። ትምህርትቤቱ ውስጥ ጥቂት ሴቶች ናቸው ያሉት ሙስሊም ሴቶች ደግሞ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።

እነዚህ ሴቶች በተለያዩ በደሎች አልፈው ነው እዚህ የደረሱት! በድርብርብ በደል እና ጭቆና አልፈው እዚህ ቢደርሱም በሒጃባቸው ምክንያት በሩ ተዘግቶባቸዋል።

Mohammedawel Hagos

🚨 ስለታፋኙ ድምጻችን ይሰማ ክሪቲካል ስናስብ!~~~~~~~~~~~~~~  ድምጻችን ይሰማ ሰሞኑን በሚደረግና ሚልዮን ብሮችን በሚያሸልም ውድድር ላይ በሰላም ዘርፍ ተሳታፊ እንደሚሆን ተገልጾ ነበ...
24/12/2024

🚨 ስለታፋኙ ድምጻችን ይሰማ ክሪቲካል ስናስብ!
~~~~~~~~~~~~~~

ድምጻችን ይሰማ ሰሞኑን በሚደረግና ሚልዮን ብሮችን በሚያሸልም ውድድር ላይ በሰላም ዘርፍ ተሳታፊ እንደሚሆን ተገልጾ ነበር። አሁን ደግሞ "ጩኸት ስለበረከተ ከግለሰቦች ጋር መወዳደር አይመጥነኝምና አልወዳደርም ብሎ እግሩን ሰበሰበ" መባሉን ሰማን! እናም ትዝብት አዘል ጥያቄዎቻችንን እንድናነሳ ተገደድን!
ለመሆኑ :-
🔴- ይህ ደብዛው እንዲጠፋ ተደርጎ የነበረው ድምጻችን ይሰማ እንዴት የሚልዬን ብሮች ሽልማት የሚያስገኝ ውድድር አለ ሲባል ከተሸሸገበት ብቅ ሊል ቻለ?

🔴- ውድድሩ የሚሊዬን ብሮች መሆኑ ቀርቶ የመቶ ብሮች ቢሆን፣ አልያም ብር የማያሸልም ነገር ግን እውቅና የሚያስገኝ ታላቅ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ መድረክ ቢገኝ ስሙን ለማደስና ለማስጠበቅ ሲባል ከግለሰቦች ጋርም ቢሆን እየተጋፋና "አለሁ ፣ልዘከር እንጂ ልረሳ አይገባም!" እያለ እንዲወዳደር ይደረግ ነበርን?

🔴 እውን በአሁኑ ሰአት ድምጻችን ይሰማ ነኝ የሚለው አካል ማን ነው? የሚወከለውስ በማን ነው?

🔴- ድምጻችን ይሰማ ነኝ ያለው አካል ውድድሩን ሊሳተፍ ሲወስን በንቅናቄው መስዋእትነትን ለከፈለው የትግሉ ባለቤት ተናግሯልን?

🔴- ለመሆኑ ድምጻችን ይሰማን ከጣለበት አንስቶ፣ አቧራውን አራግፎ የሚልዬን ብሮች ሽልማት ወደሚያስገኘው የሰላም ዘርፍ ውድድር ያመጣው በዃላም የኦንላይን ጩኸት ሲበዛበት ከውድድሩ እንዲወጣ ያደረገው አካል ሁለቱ ውሳኔዎች ላይ የደረሰው በውይይትና በፍጭት ነው ወይንስ በግለሰቦች ግብታዊና የመሻት ውሳኔ ?

🔴 -ለመሆኑ የድምጻችን ይሰማን ድምጽ እንዳይሰማ አፍነው የያዙት አካላት ሲያሻቸው ይለቁታል ማለት ነውን?

🔴- የህዝብ የነበረው የድምጻችን ይሰማ ትግልን ከኪሱ እያወጣ ሲሻው የሚጠቀምበት አካል ማን ነው?

🔴- ድምጻችን ይሰማ አሁን ተቋም ነው ወይንስ ግለሰብ?

🔴-ተቋም ካልሆነ ውድድሩን ፈልጎ መልሶ ጩኸት ሲበዛበት የሰረዘው ማን ነው?

🔴- ውድድሩን ቢያሸንፍስ ሽልማቱን የሚቀበለውና የሚያስተናብረው ማን ነበር?

🔴- ሽልማቱስ የትኛው የድምጻችን ይሰማ ጉዳይ ላይ ይውል ነበር?
በነዚህ ጉዳዬችስ ዙርያ ማብራርያ ያልተሰጠው ስለምን ነው?

🔴- ድምጻችን ይሰማ ከነበረበት ሀገራዊና አለምአቀፋዊ እድገቱ አውርዶና ስሙ እንዳይወሳ፣እንዳይጠና፣እንዳይዘከር አድርጎ ሲያበቃ የግለሰቦች ንብረት እንዲሆን ያደረገው ማን ነው?

- ሌላም ሌላም!!!
ህዝብ ዝም ቢልም ይታዘባል! ስለ ከፈለውም ዋጋ ያገባዋል! ለማለት ነው።
ይሄው ነው!!

🚩በጋዛ ዙርያ - ሊቀ ፓፓሱና የእስራኤል መንግስት ተናቆሩ!~~~~~~~~~~~~~~~~                        _______________________👉"እስራኤል በህጻናት ላይ የፈጸ...
22/12/2024

🚩በጋዛ ዙርያ - ሊቀ ፓፓሱና የእስራኤል መንግስት ተናቆሩ!
~~~~~~~~~~~~~~~~

_______________________

👉"እስራኤል በህጻናት ላይ የፈጸመችው ጭካኔ ነው ! ይህ ጦርነት አይደለም" ፖፕ ፍራንሲስ
👉"ፓፓሱ ስለ ታገቱብን ከ100 በላይ ዜጎች መናገር አይፈልጉም" የእስራኤል የዉጭ ጉዳይ መ/ቤት
_______________________
.
ወደ 1.4 ቢልዮን ገደማ የሚጠጋ የአለም ካቶሎክ እምነት ተከታይን በበላይነት የሚመሩትና መቀመጫቸዉን በቫቲካን ያደረጉት ፓፓስ ፍራንሲስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እስራኤል በጋዛ ዉስጥ የምታደርገዉን ወረራና ግድያ ሲተቹ መስማት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ለወትሮው በዚህ ጉዳይ ብዙም ሲናገሩ የማይደመጡት እኚህ ፓፓስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አልፎ አልፎ እያነሱ ያሉት የተቃዉሞ ሃሳብ በምላሹ የእስራኤል ባለስልጣናት ቁጣና ትችት እያስከተለ ይገኛል፡፡
ፓፓሱ በትላንትናው ቅዳሜ እንደፈረንጆቹ ዲሴምበር 21/2024 ተከታዩን የገና በአል አስመልክቶ ለፓፓሶችና የተለያዩ የእምነቱ መምህራን ባደረጉት ንግግር
እስራኤል በሰሜን ጋዛ ህጻናትን ጨምሮ ከአንድ ቤተሰብ ብቻ 10 ሰዎች በአንዴ የተገደሉበትን የሰሞኑን የእስራኤል ጥቃት በማንሳት "እስራኤል የምታካሂደው ጦርነት ሳይሆን ጭካኔ ነው!" ሲሉ ተችተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፈው ወር በታተመ መፅሃፍ ዉስጥ "በጋዛ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር አንዳንድ አለም አቀፍ ባለሙያዎች የዘር ማጥፋት ባህሪ አለው ብለዋል" የሚል ሃሳብ ማካተታቸው ሌላው የእስራኤልን ባለስልጣናት ያስቆጣና ለምላሽ የጋበዘ ጉዳይ ሆኗል፡፡
ፓፓሱ አያይዘዉም ገናን አስመልክቶ የእየሩሳሌም ፓትርያርክ ወደ ጋዛ ለመግባትና የእምነቱን ተከታዮች ለማግኘት ቢጠይቁም በእስራኤል መከልከላቸዉን አጥብቀው ኮንነዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " እስራኤል እየታገለችና ራስዋን እየተከላከለች ያለችው የእስራኤልን ልጆች ከሚገድሉ፣ ከህጻናት ጀርባ ከሚደበቁ፣ እንዲሁም ከ 100 በላይ ታጋቾችን በመያዝ እና በማንገላታት ላይ ካሉት ከሀማስ አሸባሪዎች ጋር ነው፡፡ ጭካኔ ከተባለም ይህ የሃማስ ስራ ነው ጭካኔ፣ ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ እነዚህን የሃማስ ወንጀሎች ሁሉ ከመናገር ችላ ማለትን መርጠዋል” ሲል ሊቀ ፓፓሱን ወቅሷል፡፡
በፍልስጤም በተለይም በጋዛ የሚገኙ የካቶሊክና ሌሎች ክርስትያኖች እንደ ሙስሊም ወንድሞቻቸው ሁሉ በራሳቸዉና በልጆቻቸው ላይ ቤቶችን በቦምብ እያፈረሱባቸዉና እየተገደሉ ከመሆኑም በላይ ታሪካዊ ቤተ እምነቶቻቸዉም ሆን ተብሎ ኢላማ ስለመደረጋቸው ሲናገሩ ይደመጣል፡፡
እየሱስ የተወለደበት ነው የሚባለው የፍልስጤም ምድር ቤተልሄም ዉስጥ እንኳ ከአለፈው አመት ጀምሮ በእስራኤል የጋዛ ዘመቻ ምክንያት የገናን በአል ለሁለተኛ ጊዜ ማክበር እንዳልቻሉ የካቶሊክና የኢቫንጄሊካል ቤተ እምነቶች ተወካዮች ለተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ተናግረዋል፡፡

-----
*** በጋዛ ዙርያ ዘገባችን ምክንያት ፌስቡክ ተከታታዮቻችን ኖቲፊኬሽን እንዳይደርሳቸው ስላደረገ እርሶ ሼር ያድርጉን ! የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive

🚩ኢስላም ጠሉ ግለሰብ በጀርመን የገና ገበያ የፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል አነጋጋሪ ሆኗል! ~~~~~~~~~~~~~~~~"ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ጸረ ኢስላም እንደሆነ እናውቃለን..."  የሀገር ዉስ...
21/12/2024

🚩ኢስላም ጠሉ ግለሰብ በጀርመን የገና ገበያ የፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል አነጋጋሪ ሆኗል!
~~~~~~~~~~~~~~~~
"ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ጸረ ኢስላም እንደሆነ እናውቃለን..." የሀገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስቴር

በጀርመን ማግድቡርግ ከተማ በገና በዓል መገበያያ ስፍራ በነበሩ በርካታ ሰዎች ላይ አንድ ግለሰብ መኪናውን በከፍተኛ ፍጥነት በማሽከርከር በፈጸመው ጥቃት 5 ሰዎች ሲሞቱ ወደ 400 ገደማ ሰዎች ቆስለዋል። በጥቃቱ የተጠረጠረ አንድ በሙያው ሐኪም የሆነ የ 50 አመት እድሜ ያለዉ የሳውዲ አረቢያ ዜጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል።
ጀርመኖች የገና በዓል ቀደም ብለውና በከፍተኛ ቁጥር በየገና ገበያው እንደሚያሳልፉ ይታወቃል፤ ይህንኑ ተከትሎ በዚሁ የገና ወቅት ከ 8 አመት በፊት አንድ የጭነት መኪና የያዘ ግለሰብ በህዝቡ መሃል ገብቶ አደጋ እንዳደረሰ የሚታወቅ በመሆኑ ዘንድሮም አደጋ ሊደርስ እንደሚችል የጀርመን ፖሊስ ማሳሰብያ ሰጥቶ እንደነበር ተነግሯል፡፡
እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነበር ከበርሊን አቅራብያ ባለችው ማግደምቡርግ በምትባለው ከተማ ጀርመኖች በብዛት በገና ገበያ ላይ በተሰባሰቡበት ወቅት ከላይ የተገለጸው ግለሰብ በተከራየው መኪና ሰዎቹ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት በማሽከርከር እስካሁን ድረስ 5 ሟችና ከ 400 በላይ ቁስለኛ ያደረጋቸው ነው የተባለው፡፡
የሃገሪቱ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ በቦታው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በድርጊቱ እጅግ ማዘናቸዉንና ህጉ የሚፈቅድላቸዉን ተከትለው ሁሉንም ነገር እንደሚያደርጉ፣ በተርፈ ጥላቻን ማስፋፋት መልካም አለመሆኑን ለህዝባቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም ወቅት ከከተማው ነዋሪ "እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል?" በሚል የቁጣና የቅሬታ ተቃዉሞን አስተናግደዋል፡፡
ከእሳቸው ጋር አብረው ከነበሩት የተለያዩ ፓርቲ አባላትና ባለስልጣናት መካከል የሳክሶኒ አንሃልት የሃገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ ተጠርጣሪው ከ 1990 ዎቹ ጀምሮ እስልምናን የለቀቀ መሆኑንና በ 2006 በጀርመን ጥገኝነት ጠይቆ ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ያገኘ መሆኑን አዉስተዋል፡፡
እንደ ታገስ ሻው፣ WDR እና NDR የተሰኙ ሚድያዎች በምርመራ ዘገባዎቻቸው እንዳሳወቁት ግለሰቡ ከ 1990 ዎቹ ጀምሮ ከእስልምና የወጣና በ 2006 በጀርመን ሃገር በሃይማኖትና በአጠቃላይ ሳዉዲ ባለው የፖለቲካና የመናገር ነጻነት እጦት ሰበብ ጥገኝነት ጠይቆ ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ እንደተሰጠው ፣ ከዛ በኋላ በግል ገጾቹ ላይ ጸረ እስልምና ጥላቻ ሲያራምድ እንደቆየ ዘግበዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም የሳዉዲ መንግስት በጀርመኗ ማግድቡርግ ከተማ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ እንዳዘነና ሃገራቸዉና መንግስታቸው ድርጊቱንም እንደሚያወግዙ በዉጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በኩል መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡
ቪድዮዉን ለማየት የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ተቀላቀሉን t.me/RNZeroFive


-----

🚨 “ የሚላስ የሚቀመስ የለም ” - የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ🔴 “ ችግር እንዳለ ይታወቃል ” - የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽንበአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግ...
21/12/2024

🚨 “ የሚላስ የሚቀመስ የለም ” - የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

🔴 “ ችግር እንዳለ ይታወቃል ” - የአማራ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ሳቢያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደተጎዱ፣ በተለይ ጨቅላ ህፃናት የከፋ ስቃይ ላይ እንደሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

“ ጉዳዩ በጣም አሳዛኝ ነው። በእኛ ቦታው ያልሆነ ሰው አይገባውም ” ሲሉም የሁነቱን አስከፊነት አስረድተዋል።

ስሜ ከመነገር ይቆይ ያሉ የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፣ “ በቡግና ወረዳ ጉልሃ ቀበሌ አንድ ህፃን በምግብ እጥረት ሞቷል ” ብለዋል።

የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል አለሙ በበኩላቸው፣ በክልሉ ባለው ግጭትና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅና ለምግብ እጥረት በመጋለጡ ህፃናትን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን ሰሞኑንን ለቢቢሲ አማርኛ መናገራቸው አይዘነጋም።

በወረዳው በተከሰተ የምግብ እጥረት በተለይ ጨቅላ ህፃናት ስለተጎዱ ነዋሪዎቹ የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸውን በመግለጽ ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቀው የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ “ እኛ ጋር ስራ የለም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥቷል።

ጽሕፈት ቤቱ፣ “ እውቅናው የለኝም ” ያለ ሲሆን፣ ጉዳዩን እንደሚያውቁት ነዋሪዎች መናገራቸውን ብንገልጽለትም፣ “ እስካሁም ምንም አይነት በሪፓርትም የመጣ ነገር የለም ” ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቡግና ወረዳ በተጨማሪም ለአማራ ክልል ስጋት አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ችግሩ መኖሩን አምኗል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌ በሰጡን ቃል፣ “ ጉዳዩ በኛ ቁጥጥር ውስጥ ነው። ከእኛ አቅም ውጪ የሆነ ነገር የለም ” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም፣ “ ችግር እንዳለ ይታወቃል። ድጋፍ እየቀረበ ነው። ምንም የተለዬ ነገር የለም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ የአምናውን ድርቅ ችግር ተቋቁመናል አሁን እንዲያውም ጥሩ ነው ምርት አምርተዋል ” ሲሉ ተናግረዋል።

ድጋፍ እየተደረገላቸው ከሆነ ምን ያክል ድጋፍ ተደርጓል ? ሰሞኑን ያደረጋችሁት ድጋፍ ነበር ? በተለይ ሰሞኑን ህፃናቱን የሚመግቡት እንደተቸገሩ ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፣ ስንል ለወ/ሮ ፍቅሬ ተጨማሪ ጥያቄ አቅርበናል።

እሳቸውም በምላሻቸው፣ “ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው በተለመደው አግባብ (ድጋፉ የሚሰጥበት ቀመር አለው) ድጋፍ እየደረሳቸው ነው ” ከማለት ውጪ የችግሩን አስከፊነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ነዋሪዎቹ የላኳቸው ፎቶዎች ህፃናቱ በምግብ እጥረት እንደተጎዱ የሚመሰክሩ እንደሆኑ ገልጸን፣ ድጋፍ ካለ ጉዳዩ እንዴት በዚህ ልክ ጉዳት እንዳደረሰ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ኃላፊዋን ጠይቋል።

በዚህም፣ “ ይለካል እኮ ማልኑውትሬሽን፣ ሞዴሬት የሆኑት እየተለካ ምግብ ሁሉ ይሰጣቸዋል ለእናቶች፣ ለህፃናት ” የሚል ምላሽ ሰጠተዋል።

“ ለዩኒሴፍም ይቀርባል። ለአዋቂዎች ደግሞ እህል ይቀርባል። የገንዘብ ደጋፍም ይሰጣልና ክትልትል እየተደረገ ነው ” ያሉት ወ/ሮ ፍቅሬ፣ “ በመሀል ደግሞ በህመምም በምንም ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል ” ነው ያሉት።

የቡግና ወረዳ ኮሚዩኒኬሽንና ኮሚሽኑ ይህን ይበሉ እንጂ የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ግን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጠው ቃል፣ “ ማህበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን ባግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው አድርጓል ” ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የሰሜን ወሎ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር ዛሬ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል " አካባቢው በፋኖ ታጣቂዎች ስር በመሆኑ ለተከሰተው የምግብ እጥረት መንግሥት በቶሎ ምላሽ መስጠት አልቻለም " ብለዋል።

የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች በአደረጉት ጥረትም አሁን ላይ የርዳታ እህል ወደ ስፍራው እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቀዋል።

የወረዳው ነዋሪ ያለበትን የምግብና የጤና ችግር ለፋኖ ታጣቂዎችና ለመንግሥት አካላት ለማስረዳት ከተመረጡት 18 ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበርኩ ያሉት ቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዝናቤ ይርዳው " በአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናትና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተደረሰው ስምምነት መድኃኒቶችንና አልሚ ምግቦች ወደ ወረዳው እየገቡ ነው " ብለዋል።

የኤሪካ ኤምባሲ ደግሞ ፤ የምግብ እጥረት ቀውስ ሰለመኖሩ የወጡ ሪፖርቶችን እየተከታተለ እንደሆነ አመልክቷል።

ቀውሱ መወገዱን ለማረጋገጥ እንደሚሠራም ጠቅሷል።

ኤምባሲው ቀውሱን በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን አላካተተም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመደገፍ ፣ አጋሮቹ በአሁኑ ሰዓት በችግሩ በተጠቁት አብዛኞቹ ስፍራዎች የምግብ እና አልሚ ንጥረ ምግቦች ስርጭትን ያጠናከሩ መሆናቸውን አክሏል።

ዘገባው የ Tikvah ነው

Adress

Stockholm

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när RN05 postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Videor

Dela