Shelarea - ሸላሬ

Shelarea - ሸላሬ Kontaktinformation, kartor och vägbeskrivningar, kontaktformulär, öppettider, tjänster, betyg, foton, videor och meddelanden från Shelarea - ሸላሬ, Medier/nyheter, Sweden �, Södertälje.

Ethiopian Orthodox ‼️
07/01/2025

Ethiopian Orthodox ‼️

ታህሳስ 5 2017 ሸላሬ መረጃካፒታል ገበያ ‼️ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የመጀመርያ ደረጃ የአክሲዮን ድርሻውን ሸጦ ለመጨረስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት ተብሏል።የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገ...
14/12/2024

ታህሳስ 5 2017

ሸላሬ መረጃ

ካፒታል ገበያ ‼️

ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የመጀመርያ ደረጃ የአክሲዮን ድርሻውን ሸጦ ለመጨረስ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት ተብሏል።

የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ጥር ወር ላይ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ግብይቱን እንደሚጀምር ም ተናግሯል።

ገበያው ቀዳሚ ስራው የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶችን ማሻሻጥ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም ከ ሳምንታት በውሀላ በሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው ላይ የአክሲዮን ድርሻዎቹን ለሽያጭ ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን፣ ለሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያው ባለፈው ሳምንት የሥራ ፍቃድ ሰጥቷል።

የካፒታል ገበያው በፍጥነት ወደ ኢኮኖሚው እየገባ ነው።

ታኅሳስ 5 2017    ሸላሬ  መረጃ ‼️ቢዝነስ ‼️የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቱርኩ ተቋራጭ የፒ መርከዚ ኩባንያ ተካሰዋል።ክሱ የአዋሽ-ወልድያ-መቀሌ የባቡር ሐዲድ ግንባታ ባለመጠ...
14/12/2024

ታኅሳስ 5 2017

ሸላሬ መረጃ ‼️

ቢዝነስ ‼️

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቱርኩ ተቋራጭ የፒ መርከዚ ኩባንያ ተካሰዋል።

ክሱ የአዋሽ-ወልድያ-መቀሌ የባቡር ሐዲድ ግንባታ ባለመጠናቀቁ ነው።

የፒ መርከዚ ፕሮጀክቱን ሳያጠናቅቅ በመውጣቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካሳ ክፈለኝ ሲል ምድር ባቡር ከሷል።

የፒ ኩባንያ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ሳቢያ ፕሮጀክቱን አቋርጦ እንዲወጣ እንደተገደደ ሪፖርተር ፅፋል።

ኮርፖሬሽኑ 1 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው በለንደኑ ዓለማቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ክስ መስረቶ እየተከራከረ ነው።

የግልግል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን በቀጣዩ ወር ይፋ ያደርጋል።



#ሸላሬ

ታህሳስ 5 2017አለም አቀፍ ‼️አሜሪካና አፕል ኩባንያ ተነጋግረዋል።47ኛው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ና ቲም ኩክ ተገናኝተዋል።ቲም ኩክ የ አፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናቸው።በአለም ...
14/12/2024

ታህሳስ 5 2017

አለም አቀፍ ‼️

አሜሪካና አፕል ኩባንያ ተነጋግረዋል።

47ኛው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ና ቲም ኩክ ተገናኝተዋል።

ቲም ኩክ የ አፕል ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናቸው።

በአለም አንቱ የተባሉ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ከ ትራምፕ ጋር በተደጋጋሚ እየተገናኙ ነው

ለ ትራምፕ ወደ ቤተመንግስት መግቢያም የሚሆን ሚሊየን ዶላር እያቀበሉ ነው።

ትራምፕ ቲክቶክን እጠረቅመዋለው እያሉ እየዛቱ ነው።

ቲክቶክና አሜሪካ ተፋጠዋል።

በቅርቡ ቲክቶክና አሜሪካ ይለይላቸዋል።



#ሸላሬ መረጃ

ቤት ‼️ማህበራዊ ‼️ታህሳስ 5፣2017በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤት ሳይሰጣቸው ቤታቸው ፈርሶባቸዋል።አካባቢው ለልማት እንደሚፈለ...
14/12/2024

ቤት ‼️

ማህበራዊ ‼️

ታህሳስ 5፣2017

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ተክለሃይማኖት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤት ሳይሰጣቸው ቤታቸው ፈርሶባቸዋል።

አካባቢው ለልማት እንደሚፈለግ ተነግሮን ነበር ብለዋል።

ምትክ ቤት እንደሚሰጣቸው ተነግራቸው ነበር ።

ነገር ግን ቤቱን እየጠበቁ እያለ ዛሬ ማለዳ ቤታቸው በላያቸው ላይ ፈርሷል።

‘ክፍለ ከተማው ምትክ ቦታ ሳይሰጣችሁ እንዳትወጡ ብሎ ነበር።

ወረዳው ግን በተኛንበት መጥቶ ቤታችን አፈረሰብን ሲሉ ለሸገር ራዲዮ ነግረዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የተክለሓይማኖት አካባቢ ነዋሪዎቹ ቦታው ለልማት እንደሚፈለግ ተነግሮን እኛም ተስማምተን፣ ምትክ ቦታ በመጠበቅ ላይ እያለን ነበር ብለዋል።

ዛሬ ማለዳ ግን ቤታችንን በድንገት አፈረሰብን ሲሉ ቅሬታቸውን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አቅርበዋል፡፡

ክፍለ ከተማው ‘’አዎ ምትክ ቤት ሳይሰጣቸው ቤታቸው እንደማይፈርስ ቃል ገብቻለሁ ነገር ግን ቤቶቹ እየፈረሱ ስለመሆኑም የማውቀው ነገር የለም’’ ብሏል፡፡

ወረዳው በበኩሉ ‘’ለነዋሪዎቹ ምትክ ቦታ እንደተሰጣቸው እና እንዳፈርስ ከክፍለ ከተማው ትዕዛዝ ስለሰጠኝ ነው ያፈረስኩት ብሏል፡፡

ምትክ ቤት መሰጠቱን ማረጋገጥ የእኔ ሃላፊነት አይደለም ሲልም ጨምሮ ተናግሯል::

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በበኩሉ ቤቶቹ እንዲፈርሱ እንዳላዘዘና ስለመፍረሳቸውም መረጃው እንደሌለው ተናግሯል፡፡



#ሸላሬ መረጃ

ህዳር 21 2017 ባንክ ‼️የ ኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንከ ሁለተኛውን የፋይናንሽያል ሪፖርት ለቀቀ።ባንኩ በ ብሔራዊ ደረጃ ከዚ ቀደም ያልነበረውን ሪፖርተ እሲያወጣ ለ ሁለተኛ ግዜ ነው።ሪፖርቱ የ...
30/11/2024

ህዳር 21 2017

ባንክ ‼️

የ ኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንከ ሁለተኛውን የፋይናንሽያል ሪፖርት ለቀቀ።

ባንኩ በ ብሔራዊ ደረጃ ከዚ ቀደም ያልነበረውን ሪፖርተ እሲያወጣ ለ ሁለተኛ ግዜ ነው።

ሪፖርቱ የባንኮች ጤና እና አጠቃላይ የፋይናንስ ስርአቱ ምን ላይ እንዳለ የሚያስረዳ ነው።

https://nbe.gov.et/fsr/



#ሸላሬ መረጃ

ህዳር 21 2017ቱሪዝም‼️ዱባይ በ አለም እግሮች ለጉብኝት የሚጣደፉባት ሀገር ነች።በ ባለፈው አመት ብቻ 17.2 ሚሊዮን አለም አቀፍ ጎብኚዎች ዱባይን እረግጠዋል።ይህ ማለት በየቀኑ 46 ሺ ...
29/11/2024

ህዳር 21 2017

ቱሪዝም‼️

ዱባይ በ አለም እግሮች ለጉብኝት የሚጣደፉባት ሀገር ነች።

በ ባለፈው አመት ብቻ 17.2 ሚሊዮን አለም አቀፍ ጎብኚዎች ዱባይን እረግጠዋል።

ይህ ማለት በየቀኑ 46 ሺ 500 ሰዎች ዱባይን ለመጎብኘት ይተማሉ።

በ የሰአቱ 1ሺ 900 አለም አቀፍ ጎብኚዎች ዱባይ ጎርፈዋል።

በዚህም ምክንያት ዱባይ ከ አለም ከሚጎበኙ ሐገሮች የ 3ተኛ ደረጃን ይዛለች።

በ አለም አቀፍ ደረጃ ከ ሚጎበኙት ቦታዎች መካከል
ዱባይ ሞልና የ ሳፋሪ በረሀ ይገኙበታል።

ለዱባይ ይህ የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ፤ የልብ ምቷ ማለት
ነው።



#ሸላሬ

ህዳር 20 2017 አፍሪካ‼️ግብፅ በ አፍሪካ ቀዳሚ ብርቱካን አምራች ሐገር ነች።በ ዓመት 3.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብርቱካን ፤ በ ናይል ውሃ አብቅላ ወደ ውጭ ትልካለች።ግብፅ የምታመርተው ...
29/11/2024

ህዳር 20 2017

አፍሪካ‼️

ግብፅ በ አፍሪካ ቀዳሚ ብርቱካን አምራች ሐገር ነች።

በ ዓመት 3.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ብርቱካን ፤ በ ናይል ውሃ አብቅላ ወደ ውጭ ትልካለች።

ግብፅ የምታመርተው የብርቱካን መጠን የ ደቡብ አፍሪካን ሁለት እጥፍ ነው።

ለ አፍሪካ ገበያ አንድ ሶስተኛውን አምርታ ትቸበችባለች።

በአለም ገበያም ስድስተኛ ደረጃን ይዛለች ።

በ ብርቱካን ምርት 1ኛ ብራዚል ፤ 2ተኛ ቻይና ፤ 3ኛ ህንድ ፤ 4ተኛ ሜክሲኮ 5ተኛ ደግሞ እስፔን የሚቀድማቸው የለም።



#ሸላሬ

ማህበራዊ‼️ልቧ የሚኮላተፍ ነው።ስሟን እንኳ አታውቀውም። ዛሬ  5 ሰዓት አካባቢ እምነት የተጣለባት ሞግዚት እምቦቃቅላዋንይዛት ተሰውራለች።የሞግዚቷ ሥም ቤዛዊት  በቀለ ነው።ወላጆች ጉልበታቸው...
16/03/2023

ማህበራዊ‼️

ልቧ የሚኮላተፍ ነው።

ስሟን እንኳ አታውቀውም።

ዛሬ 5 ሰዓት አካባቢ እምነት የተጣለባት ሞግዚት እምቦቃቅላዋንይዛት ተሰውራለች።

የሞግዚቷ ሥም ቤዛዊት በቀለ ነው።

ወላጆች ጉልበታቸው ውሀ ሆኗል።

በየትኛውም ሥፍራና ጎዳና ልጃችንን አፋልጉን እያሉ ነው።

በ 0951090999
0947365252

ህፃናቱን ሁሉ ፈጣሪ ይጠብቅ!

( የሞግዚቷ ጥርት ያለ ፎቶ ቢኖር ጥሩ ነበር)

ወላጆች የልጆቻችሁን ሞግዚት ፎቶ ግራፍ አስቀሩ!

ታሪክ‼️የንግድ ሥራ ኮሌጅን ህንፃን አውድሞ ህንፃ እገነባለሁ የሚለው ባንክ ለ ሥሙስ ቢሆን ጥሩ ነው?!ትዝታ እንዴት በየሁኔታው በየመንገዱ ይሽቀነጠራል ?! ይጣላል?!  ይወረወራል?!የፊቱን ...
24/02/2023

ታሪክ‼️

የንግድ ሥራ ኮሌጅን ህንፃን አውድሞ ህንፃ እገነባለሁ የሚለው ባንክ ለ ሥሙስ ቢሆን ጥሩ ነው?!

ትዝታ እንዴት በየሁኔታው በየመንገዱ ይሽቀነጠራል ?!
ይጣላል?! ይወረወራል?!

የፊቱን ለማሳየትና ለማስረዳት የኋላውን ካላስታወሱት እንዴት ይሆናል?!

ነበርንም ነውንም ላለማወቅ እንዴት በየመንገዱ ለልማት እየተባለ ይዳመጣል?!

ለማልማት ማጥፋት እንደማያስፈልግ እኮ ያደጉት ሐገሮች ያስረዱናል።

ከታች ያለውን ፎቶ ተመልከቱት በንፅፅርነት አምጥቼዋለሁ።

በጥቁርና ነጭ የምትመለከቱት ህንፃ የድሮ ከተማ በነበረችው በዛሬዋ መሀል ቶሮንቶ የሚገኘው gooderham ህንፃ ነው።

ይህ ህንፃ እድሜው እረጅም ነው የሐገሩን የኪነ ህንፃና እድገት አመጣጥ የሚናገር ትዝታ ያለው እድሜ ጠገብ ነው።

በዚ ቶሮንቶ ከተማ የፋይናንስ ማዕከል ለመገንባት ተፈለገ።(ልክ እንደኛው ሐገር ማይጨው አደባባይ ወይም ሜክሲኮ )

በዚሁ ሐገር ቶሮንቶ ዳውን ታውን በ 1891 የተገነባ ነው።

እድሜው ከ መቶ አመት በላይ ነው።

ልክ እንደኛ ሐገር ኮሜርስ ኮሌጅ እድሜ የጠገበ ነው።

ይህ ህንፃ በዚሁ ሐገር በቶሮንቶ ከተማ የፋይናንሻል መንደር financial center ሊገነባ ነው ተብሎ አልፈረሰም በክብር አሁንም ይገኛል።

ሌሎች ግዙፍና እረጃጅም ህንፃዎች ሲገነቡ ይህ ህንፃ አይፈለግም ተብሎ አልተሽቀነጠረም።

አርጅቷል ቦታ ይልቀቅ ተብሎ ሌሎች በቁመት የሚበልጡት ህንፃ ከኋላው ሲገነቡ ይህ ታሪካዊ ህንፃ ግን አልፈረሰም አልተነካም ቅርስ ነው።

ትዝታ ይከበራላ።

ይጎበኛል ሰዎች እየገቡ የድሮ ትዝታቸውን እየተመላለሱ ሀሳባቸውን ያሳርፉበታል።

እዚህ ከተማ ግን የፈይናንስ ማዕከል ለመገንባት እየተባለ ኮሜርስ ኮሌጅን ለማፍረስ ጥድፊያው ለጉድ ነው።

ይህን ህንፃ አፍርሶ ህንፃ የሚገነባው ባንክስ ቢሆን የሚቀርለት ታሪክ ጥሩ ነው?!

ኮሜርስን ያፈረሰው ባንክ እየተባለ ቅፅል የዳቦ ስም አይወጣለትም?!

የጠፋ ስምስ በምን ይመለሳል?!

ግዴለም ሥማችሁን ጠብቁት!

የ 80 ዓመት ዕድሜ ያለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት ኮሜርስ በፋይናንስ ማዕከሉ አካባቢ ሳይነካ ቢቆይ ውበት አይሆንም ?!

እስኪ ለህዝቡ ትዝታውን እንኳ አስቀሩለት!

ተዉለት !

አኑሩለት!

የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣንስ " ባለስልጣን " አይደለህም ወይ?!

22/02/2023

ሶሻል ሚዲያ‼️

ቀልድ ነው አታምሩ hahahaha

ሰሞኑን ሰው ሁሉ በ19 ሚሊዮን ብር ስለተገዛው አዲሱ ባስ ሲያወራ ለምን ሄጄበት አልሞክረውም ብዬ ዛሬ ከጀሞ 1 ወደ ሜክሲኮ ሄጄ ነበር።
ባስ ስቴሽኑ ጋ የደረስኩት ከጠዋቱ 12 ሰአት ሲሆን ከተደረደሩት አዲስ ባሶች ውስጥ አንዱን መርጩ ገባሁ።

በር ላይ ሚኒ ስከርት የለበሰች አስተናጋጅ በፈገግታ ተቀብላኝ ጉንጬን ከሳመችኝ በኋላ ስልኳን ሰጥታኝ ወደ ውስጥ አስገብታ ወንበር አስያዘችኝ።

በጣም ብርድ ስለነበር ከወንበሬ አጠገብ የነበረውን Heat የሚለውን በተን ክሊክ ሳደርገው ወዲያውን ከወንበሬ ዙሪያ ጠርዝ ላይ ነጭ ጋቢ ወጥቶ ሙሉ ሰውነቴን አለበሰው።

በዚህ ተገርሜ እንደምንም ከጋቢ ውስጥ እጄን አውጥቼ ፊት ለፊቴ ያለውን ስክሪን ሳበራው መኪናው ላይ ስለተገጠሙት ቴክኖሎጂዎች የሚገልፅ ፅሁፍ መጣልኝ።

ፅሁፍ ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ክረምት ክረምት መንገዶች በጎርፍ ሲሞሉ ይሄ ባስ ወዲያውን ቅርፁን ወደ ዝርግነት በመቀየር ወደ መርከብነት የሚለወጥ ሲሆን በውስጡም መለስተኛ ኳስ ሜዳ እና የባስኬት ቦል ኮርቶች እንዲሁም ለፈረስ ግልቢያ የሚሆን ሰፊ ሜዳ ይዟል።

ምናልባት ከቤቱ ተቻኮሎ ፊቱን ሳይታጠብ የመጣ ተሳፋሪ ካለ ባሱ የራሱን የፊት ሳሙና እና የጥርስ ብሩሽ ከኮልጌት ጋር እንዲሁም ከማይመለስ አንድ ፎጣ ጋር የሚያቀርብ ሲሆን ስቲም እና ሳውናም ከሾፌሩ ጀርባ ባለው ክፍል ውስጥ ዝግጁ ሆኖ ተሳፋሪዎቹን ይጠብቃል።

በተጨማሪም መንገድ በሚዘጋበት ጊዜ ከጎን እና ከጎን ክንፎቹን በመዘርጋት ልክ እንደ ዴር 33 ከራዳር እይታ ውጪ መብረር የሚችል ሲሆን ምናልባት በሰማይ ላይ እያለ የሰማይ ትራፊክ መጨናነቅ ቢያጋጥመው እንኳን ከስሩ እሳት በመፍጠር ራሱን ወደ መንኮራኩነት በመቀየር ወደ ጨረቃ የሚያምዘገዝግ የሮኬት ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል።

ለባለስልጣኖች ራሱን የቻለ መኝታ ቤት ያለው ሲሆን ለሰፊው ህዝብ ደግሞ ትኬት ሳይቆርጥ የገባን ቆርጦ ከገባው የሚለይ ሴንሰር ተገጥሞለታል።

የሚገርመው ትኬት ያልቆረጡትን ሰዎች በስም መለየት የሚችል ሲሆን አንዱ ተሳፋሪ ሳይቆርጥ ገብቶ ወዲያኑ "ደጀኔ እባክህ ወይ ቁረጥ ወይ ውረድ አትሞላፈጥ" በሚል ድምፅ ተሳፋሪውን ሲያስጠነቅቅ በጆሮዬ ሰምቻለሁ።

በመጨረሻም ሜክሲኮ ባስ ስቴሽን ደርሰን ስንወርድ ለሁላችንም የጫማ ማስጠረጊያ እና ለቀጣይ ታክሲ መሄጃ ስልሳ ስልሳ ብር የተሰጠን ሲሆን ሾፌሩን ጨምሮ ሁሉም የባሱ ሰራተኞች በእግራቸው የተወሰነ መንገድ ሸኝተውናል። በእኔ እይታ ይሄ ባስ 19 ሚሊየን ሲያንስበት እንጂ ከዚህም በላይ ይገባዋል።

Thank you አዴክስ ጭሷ!

ዳጊ ነኝ ከገፈርሳ ወንዝ ማ።))

ማህበራዊ ‼️ወደዚህ ምድር ከመጣ 6 ዓመት ብቻ ነው።ለ እናት የአይኗ ማረፍያ አንድ ለናቱ ብቸኛዋ ነው።ሐገር ቤት መታከም ስለማይችል እናቱ ተጨንቃ እየተንሰፈሰፈች ነው።ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላ...
17/02/2023

ማህበራዊ ‼️

ወደዚህ ምድር ከመጣ 6 ዓመት ብቻ ነው።

ለ እናት የአይኗ ማረፍያ አንድ ለናቱ ብቸኛዋ ነው።

ሐገር ቤት መታከም ስለማይችል እናቱ ተጨንቃ እየተንሰፈሰፈች ነው።

ልጄ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሷል ብላለች።

እየደከመብኝ ነው ብላ ትንገበገባለች።

ስሙ የአብስራ_ህይወት ነው።

ከ አመት ግድም በፊት የአብስራ በድንገት ከገር ሰውነቱ ክፋትና ደግነትን ለይተው ከማያውቁ ሰውነቱ የልጅነት ደሙ ያለማቋረጥ ፈሰሰው።

እናቱ ወዲያው ወደ ህክምና ወሰደችው።

ህክምና ቢያገኝም ሙሉ ለሙሉ መፈወስ አልቻለም።

የአጥንት መቅኔው ደም ማምረት አቆሞ።

ወደ ውጪ ሄዶ መታከም አለበት ተብሎ ተወሰነ።

3ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያስፈልግ ተረዳች።

ይህች እናት አደባባይ ወጣች።

ለነፍስም ለስጋም ይሆናችኃልና አንድ ጠጠር ወርውሩ።

ደውሎ መጠየቅ ማፅናናት ማረጋጋትም በጎ ሥራ።

ሰላማዊት አወል የዚህ አንድ ፍሬ ልጅ እናት ነች

ስልካቸው
👇
0934425413
0916078158

የዚህ አንድ ፍሬ ልጅ የ ባንክ ቁጥር
በናቱ ስም የተመዘገበ ነው
👇
cbe

1000405903516

27/01/2023

ባንክ‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ፕሬዝዳንቶችን ለመሰብሰብ ቀጠሮ ይዟል።

ማዕከላዊ ባንኩ የግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶችን ለመምከር ይሁን ለመገሰፅ አልታወቀም።

በዚያውም አዲሱ ገዢ ከፕሬዝዳንቶቹ ጋር እገረ መንገዳቸውን ይተዋወቃሉ።

ከምምክክሩ በውኃላ ከብድር ከውጪ ምንዛሪ አስተዳደርና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ጠንከር ያሉ የፋይናንስ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ልንሰማ እንችላለን።

በተቃራኒው በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር 110 ብር እንመንዝርላችሁ ይላሉ።

በግልጥ በፋይናንስ ተቋሞች አካባቢ የፈሰሱ ጥቁር መንዛሪዎች ሰዎች ብዛታቸው ለጉድ ነው ጠጠር መጣያ የለውም።

ከከርሞ በዝተዋል።

23/01/2023

ትችት‼️

የግል ቤት፤ ሪልስቴት ፤ኮንዶሚንየም ፤የቀበሌ ቤት ፤የኪራይ ቤቶች ፤ እና አጠቃላይ ቤቶች ሳይቀሩ ሊቆጠሩ ነው።

የኪራይ ቤቶች አስተዳደርም ሆነ ሌላው በአጠቃላይ ምን ያህል ቤት እንዳለው በቁጥር አያውቅም ነበር።

መንግስት ያለውን resource ቆጥሮ አያውቃቸውም።

በዚህ ሰበብ በንጉሱ ዘመን እንኳ መንግስት ሲለዋወጥ የነበሩ የመንግስት ቤቶች ፋይላቸው እየተሰረዘ እየጠፋ ለግለሰብ ተሽጠዋል።

በከተማው የተሰራው የጋራ መኖሪያ ቤት ሁለትና ሦስት መኖሪያ ቤት ላላቸው ተላልፎ ተሰጥቷል።

መንግስት ይህን መለየት አልቻለም።

ዛሬ ከረፈደ በውኃላ ያለውን ሀብት መኖሪያ ቤት ለማስተዳደር እንዲመችና ሀብቱን ለማወቅ ሶፍትዌር ገንብቻለሁ ብሎናል።

የከተማና መሰረተ ልማት መንግስት ሐብቱን ለይቶ እንደማያውቀው ነግረውናል።

አጠቃላይ መኖሪያ ቤቶች የግል ቤት ሪልስቴት ኮንዶሚንየም የቀበሌ ቤት የኪራይ ቤቶች ሳይቀሩ ሊቆጠሩ መሆኑ ተሰምቷል።

ሶፍትዌሩ ከዚህ በውኃላ ያለውን ለመለየት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የተሰራውን የውንብድና ሽያጭና ሌላውንም ለይቶ መፍትሄ ይዞ እንዲመጣ ይጠበቃል።

አንድ ሰው ምን ያህል ቤት እንዳለው መለየት የሚችል group of instruction ይጠቅማል።

ምክንያቱም በከተማው

✍️ የቀበሌ ቤት

✍️ የመንግስት የኪራይ ቤት

✍️ ኮንዶሚንየም ቤት

እና

✍️ የግል መኖሪያ ቤት አቅፎ ቁጭ ያለ አለ

ይህን ማስተካከል ለምን አልተፈለገም?!

ባንክ‼️የዛሬ ዓመት በዚህ ወር ተመሳሳይ ግዜ የሐገሪቱ ኢኮኖሚ በክፉ ተረብሾ ነበር።ማክሮ ኢኮኖሚውም ተናግቷል የተባለበት ወቅት ነበር። ወደገበያ መቅረብ ያለባቸው ምርቶች ይደበቁ ነበር (አሁ...
21/01/2023

ባንክ‼️

የዛሬ ዓመት በዚህ ወር ተመሳሳይ ግዜ የሐገሪቱ ኢኮኖሚ በክፉ ተረብሾ ነበር።

ማክሮ ኢኮኖሚውም ተናግቷል የተባለበት ወቅት ነበር።

ወደገበያ መቅረብ ያለባቸው ምርቶች ይደበቁ ነበር (አሁንም አለ በርግጥ)

የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ጦዞ ነበር ( አሁንም እዛው ነው)

የኑሮ ውድነቱም ተሰቅሎ ቆየ።(አሁንም አለ)

የባንክ የሥራ ኃላፊዎች በተለይ የ branch ማናጀር የሚሰሩት አይን ያወጣ የዶላር ሽያጭ የባሰ ሐገሪቱን አደቀቃት (አሁንም አለ)

በዚህ ግዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ ማሞ እስመ ለዓለም ምህረቱ በ ብሔራዊ ሚዲያ ብቅ አሉ ፡፡

የግዜው አማካሪ የዛሬው የ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ በህገወጥ መንገድ የውጭ ምንዛሬ የሚያደርጉትን መንግስት ያድናል ።

ወደውጭ ተልኮ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ምርትን የሚደብቁትንና ኢኮኖሚውን የሚረብሹትን ወንጀሎች አድኖ እርምጃ ለመውሰድ እየተሰራ ነው ብለውን ነበር።

እሳቸው ይህን በተናገሩ በዓመቱ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው መጥተዋል።

በዚህ አንድ አመት ግን

የሐገሪቱ inflation ........

የወጪና ገቢ ንግድ እጅግ መስፋት ............

ሐገር ቤት በሌለ የውጭ ምንዛሪ በየተ በኩል LC እየተከፈተ ሸቀጥ እንደሚራገፍ ......

የኑሮ ውድነት........

በትይዩ ገበያና በባንክ መሀል ያለው የምንዛሪ ልዩነት.........

የፋብሪካዎች ምርት ማቆም ጥሬ እቃ አጥቶ ማሽን መንቀል.........

የገንዘብ እጥበት ..........

የመሬትና ተያያዥ ውንብድና ...........

የሐብት ማሸሽ ✈️ ና ሌላውም ............እንዳለ ተሿሚው ያውቃሉ !

ይህን ማወቃቸው ለሥራቸው ያግዛቸዋል።

ከ እለታት በአንዱ ቀን አንድ ሐብታም ባለ ፀጋ አባት ፤  ቤተሰቡንና ልጁን ይዞ ከከተማ ይወጣል። በገጠር በአንድ ገበሬ መንደር አካባቢው ዋሉ ሰነበቱ። ከሰነበቱበት አካባቢ ሲመለሱ አባት " ...
20/01/2023

ከ እለታት በአንዱ ቀን አንድ ሐብታም ባለ ፀጋ አባት ፤ ቤተሰቡንና ልጁን ይዞ ከከተማ ይወጣል።

በገጠር በአንድ ገበሬ መንደር አካባቢው ዋሉ ሰነበቱ።

ከሰነበቱበት አካባቢ ሲመለሱ አባት " ጉብኝት እንዴት ነበር ? ምን ያህል የሐብታም ልጅ እንደሆንከ ተረዳህ ?" ብሎ ይጠይቀዋል።

ልጁም

“በጣም ጥሩ ነበር !” ብሎ ይመልሳል።

“በገጠር ድሆች እንዴት እንደሚኖሩ አስተዋልክ ?” ብሎ አባት ልጁን ይጠይቀዋል

“አዎ!” ልጅ ይመልሳል

አባት “ምን ተማርክ ” ይለዋል

ልጅ

“ ቤታቸው 4 ውሻ እንዳላቸው አይቻለው እኛ ቤት ግን 2 ውሻ አለ፤

"እኛ የተገደበ የውሀ መዋኛ ገንዳ አለን እነሱ ደግሞ በጣም ነጭ ፋፋቴው የሚያምር ዥረትና የማይንጠፈጠፍ ውሀ መዋኛ "

"እኛ ለመዋኛ ገንዳው መብራት ጠልፈንለታል፤ ለነሱ የሰማይ ኮከብ አድምቆላቸዋል"

"የኛ ግቢ አጥር አለው የነሱ ግን የተገደበ አይደለም በጣም ሰፊ ነው" ብሎ ልጅ ለአባቱ መለሰለት ።

አባትየው የሚናገረው ጠፋው ልጁም ለአባቱ በድጋሚ

" አባ ምን ያህል ድሀ እንደሆንን ስላስመለከትከኝ አመሰግናለሁ "

ብሎ መለሰለት ይባላል።

ከዚ ምን እንማራለን

ሁሉ ሰው ሕይወትን የሚያይበት መነፅር የተለየ ነው!

በምድር በጣም አስፈላጊ ነገሮች ምንድናቸው?!

ድህነት ወይም ባለፀግነት አንፃራዊ ነው!

20/01/2023

በሸገር ከተማ አስተዳደር ሥር የተጠቃለሉት ስድስት ከተሞች የቀለበት መንገድ ሊሰራላቸው ነው።

በቀለበት መንገድ ለማስተሳሰር ጥናት አልቆ ዲዛይን እየተሰራ መሆኑ ተሰምቷል።

ይሁን ደግ ትልቁ ነገር አሁን ያለው የአዲስ አበባ ቀለበት መንገድ ከተማይቱን ያቅፋል ቢባልም ደንቃፋ ሆኗል።

አዲስ አበባ አሁን ከጠበባት መንገድ ለመውጣት በትንሹ አምስት ቀለበት መንገድ ያስፈልጋታል።

Adress

Sweden �
Södertälje
SÖDERTÄLJE

Telefon

+46761930232

Webbplats

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när Shelarea - ሸላሬ postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Affären

Skicka ett meddelande till Shelarea - ሸላሬ:

Videor

Dela