New Africa Amharic

New Africa Amharic ኒው አፍርካ ቲቪ የሰላም የእድገትና የብልጽግና ጥሪ
(3)

የታላቁ መስጅድ ኢማም የነበሩት ሼኽ አድል አል-ካልባኒ ከአል-ሂላል ስታርስ፣ አል ናስር እና የፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ግጥሚያ በኋላ ከተጫዋቹ   #ሜሲ ና  #አሽረፍ ሃኪሚ ጋር የመታሰቢያ ፎቶ...
21/01/2023

የታላቁ መስጅድ ኢማም የነበሩት ሼኽ አድል አል-ካልባኒ ከአል-ሂላል ስታርስ፣ አል ናስር እና የፓሪስ ሴንት ጀርሜይን ግጥሚያ በኋላ ከተጫዋቹ #ሜሲ ና #አሽረፍ ሃኪሚ ጋር የመታሰቢያ ፎቶግራፍ ሲነሱ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እየሰራቸው ላሉት ስራዎች አጋዥ ይሆን ዘንድ በተለያዩ  ዘርፍ ላይ ያሉ ምሁራንን እና ኡስታዞችን በአማካሪ ቦርድነት መርጦ ሰይሟል::ጠቅላይ ምክ...
23/12/2022

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እየሰራቸው ላሉት ስራዎች አጋዥ ይሆን ዘንድ በተለያዩ ዘርፍ ላይ ያሉ ምሁራንን እና ኡስታዞችን በአማካሪ ቦርድነት መርጦ ሰይሟል::

ጠቅላይ ምክር ቤቱ የአማካሪ ቦርድ አባል እንዲሆኑ የመረጣቸው አባላት ካላቸው ሰፊ የስራ ልምድ ፣ብቃት እና እውቀት በመነሳት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙን የሚመጥን ስራ መስራት ይችል ዘንድ የማማከር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል::

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የመረጣቸው የአማካሪዎች ቦርድ አባላት ሙሉ ስም እንደሚከተለው ይቀርባል:-

1.ሼይኽ መሐመድ ሐሚዲን

2. ሐጅ ሙሐመድኑር ሐጂ ሳኒ ሐቢብ

3.ሼይኽ መሐመድ ሲራጅ

4 .ዶ/ር ሰሚር የሱፍ

5.ዶ/ር መሐመድ ሐኪም

6. ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ

7.ሐጅ አደም ቢዶሮ

8.ኡስታዝ አህመዲን ጀበል

9.አቶ አህመድ በዳሶ

10.ኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ

11.አቶ አብድልቃድር ማሂ

12.ኢብራሂም ሙሉሸዋ

13. ወ/ሮ አዲስ መሐመድ

14.ወ/ሮ ሰአዳ ኸድር

15.ዑስታዛ ፋጡማ መሐመድ

16.ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ እና

17 ወ/ሮ ራዲያ ስዑድ ናቸው::

የተመረጡ አባላትም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት ይወጡ ዘንድ የጠቅላይ ምክር ቤታችን ፕሬዝደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለተመረጡት አባላት የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::
መረጃው የኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ነው
የመጅሊሱ የሶሻል ሚዲያ አድራሻ
ይከታተሉን | Follow us፡

የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በአርጀንቲና እና በፈረንሳይ መካከል  ዛሬ ይካሄዳል፡፡በፈረንጆቹ አቆጣጠር ህዳር 20 በኳታር መካሄድ የጀመረው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ፍፃሜውን ...
18/12/2022

የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በአርጀንቲና እና በፈረንሳይ መካከል ዛሬ ይካሄዳል፡፡

በፈረንጆቹ አቆጣጠር ህዳር 20 በኳታር መካሄድ የጀመረው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ፍፃሜውን ያደርጋል፡፡

በዓለም ዋንጫው 32 ሀገራት ተሳትፈዋል፤ሴኔጋል ፣ጋና፣ ካሜሮን፣ ቱኒዚያና ሞሮኮ ደግሞ አፍሪካን የወከሉ ሀገራት ሲሆኑ÷ ሞሮኮ እስከ ግማሽ ፍፃሜው በመጓዝ ብርቱ ተፋላሚም መሆን ችላለች፡፡

ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ብትችልም በፈረንሳይ 2 ለ 0 ተሸንፋ ለፍጻሜው ሳታልፍ ቀርታለች፡፡

በዚህም ሞሮኮ ትናንት በተካሄደ የደረጃ ጨዋታ በክሮሺያ 2 ለ 1 ተሸንፋ አራተኛ ደረጃን በመያዝ የዓለም ዋንጫውን አጠናቃለች፡፡

አርጀንቲና እና ፈረንሳይ ለፍፃሜው የደረሱ ሀገራት ሲሆኑ÷ ምሽት 12 ሰዓት ዋንጫውን ለማንሳት የሚያደርጉት ብርቱ ፉክክር በጉጉት ይጠበቃል፡፡

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነውበጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ ጉመር ማዞሪያ ላይ የተገነባው አል-ሒዳያ እስላማዊ ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። አካባቢው ከመቶ ዓመት በፊት ጀምሮ መ...
11/12/2022

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

በጉራጌ ዞን በጉመር ወረዳ ጉመር ማዞሪያ ላይ የተገነባው አል-ሒዳያ እስላማዊ ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። አካባቢው ከመቶ ዓመት በፊት ጀምሮ መስጅድ ሰፈር በመባል ይታወቃል። አካባቢው መስጅድ ሰፈር ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ከመቶ ዓመታት በፊት በነበሩ ቀደምት ሙስሊሞች የተሠራ መስጅድ የነበረበት ቦታ ስለኾነ ነው። ቦታው ላይ ከመቶ ዓመታት በኋላ በ1989 አሮጌው መስጅድ የተሠራ ሲኾን፣ በ2007 መስጅዱ በአዲስ መልክ መድረሳ እና እስላማዊ ዩኒቨርስቲ ያካተተ ፕሮጀክት ሆኖ ተቀርፆ በምዕራፍ አንድ 900 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መስጅድ፣ የወንዶች መድረሳ፣ የሴቶች መድረሳ፣ የኡስታዞች መኖሪያ እና የውዱዕ ቦታዎች ተገንብተው ዛሬ ተመርቀዋል። በተጨማሪም፣ በዛሬው ዕለት በምዕራፍ 2 የሚገነባው የአል-ሒዳያ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል። ይህ ልዩ የምረቃ ፕሮግራም የፌደራል፣ የአዲስ አበባ እና የክልል መጅሊስ ባለስልጣናት፣ ትልልቅ መሻኢኾች፣ ዱዓቶች፣ ምሁራን እና ባለሀብቶች በክብር በተገኙበት ተካሂዷል። በሥራ መደራረብ ምክንያት በዚህ ታሪካዊና ልዩ የምርቃት መርኃ ግብር ላይ ባለመገኘቴ ይቅርታ እየጠየኩ የአል—ሒዳያ እስላማዊ ማዕከል ራዕይ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቀርባለሁ።

አላህ ማዕከሉን ካሰብነው በላይ እንዲያሳካልና ፐሮጀክቱ እንዲሳካ ለሚሰሩ ሁሉ አላህ አጅራቸውን ያብዛላቸው በማለት ዱዓ አደርጋለሁ።

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለሚገነባው ሂክማ ኢስላማዊ  ዩኒቨረስቲ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የግምባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም  እየተካሄደ ይገኛል።በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል መጅሊስ ከፍተኛ  አመራሮ...
10/12/2022

በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለሚገነባው ሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨረስቲ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የግምባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፌዴራል መጅሊስ ከፍተኛ አመራሮች ናየአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች አመራሮች የስልጤ ዞን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የአከባቢው ማህበረሰቦች ሌሎች በርካታ ኡለማዎች በተገኙበት የሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የግንባታ ማስጀመሪያ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በድምቀት እየተካሄደ ነው።

ከ15 ዓመታት በፊት ሊገነባ ታቅዶ የነበረው የሂክማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የዘገየ ቢሆንም በዛሬው ዕለት የግንባታ ማስጀመሪያና የገቢ ማሰባሰቢያ ኘሮግራም እየተካሄደ ይገኛል።

የሂክማ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ መገንባት የሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ ሀላፊነት በመሆኑ ሁሉም ወገን በተቻለው መጠን ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስቴር ለኦሮሚያ ክልል 900 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ አደረገ፡፡የውኃ መሳቢያ ፓምፖቹን የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ለኦሮሚያ  ክልል ርዕሰ መስተ...
07/12/2022

የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስቴር ለኦሮሚያ ክልል 900 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች ድጋፍ አደረገ፡፡

የውኃ መሳቢያ ፓምፖቹን የመስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡

በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጃፓን ከሚገኙ 13 ኩባንያዎች ሃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ መክረዋል፡፡በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ጃፓን ረጅም ዘ...
05/12/2022

በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ጃፓን ከሚገኙ 13 ኩባንያዎች ሃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ጃፓን ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በቀጣይም ሀገራቱ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት እና ትብብር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ነው ያስረዱት፡፡

አምባሳደር ተፈራ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እምቅ እና ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ህግ፣ ማበረታቻዎች፣ በአየር ጸባይ ፣ በመሰረት ልማት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይም ገላጻ አድርገዋል፡፡

አምባሳደሩ የጃፓን ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ሰፊ እና ጠቃሚ መረጃ ማግኘታቸውን ጠቅሰው÷በቀጣይ ኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲስ መልኩ እንዲዋቀር የተደረገ ሲሆን በነገዉ እለትም ርክክብ ይደረጋል።▬▬▬▬▬▬▬▬▬ህዳር 25/ 2015የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ...
04/12/2022

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአዲስ መልኩ እንዲዋቀር የተደረገ ሲሆን በነገዉ እለትም ርክክብ ይደረጋል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ህዳር 25/ 2015

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ቤት በአዲስ መልኩ ለማዋቀር የምስረታ ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ በክልሉ መዲና በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።

ይህን የሪፎርም ስራም የተሳካ እንዲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።

በጉባኤው ላይ በአማራ ክልል ከሁሉም ዞኖች የተውጣጡ ተወካዮች የታደሙ ሲሆን ከመንግስት በኩል በታዛቢነት የጠቅላይ ሚኒስተር ፅ/ ቤት ተወካዮች፣ የክልሉ መስተዳደር እና የክልሉ ፀጥታ እና ደህንነት ቢሮ ተወካዮች ታድመውበታል።

በአማራ ክልል ሁሉንም ህዝበ ሙስሊም ሊወክሉ በሚችል መልኩ 29 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት የተመረጡ ሲሆን 11የሚሆኑት ለስራ አስፈፃሚነት ተመርጠዋል።

እጅግ ሰላማዊ እና መግባባት በሰፈነበት ጉባኤ ህዝበ ሙስሊሙን በቅንነት እና በታማኝነት ያለምንም ልዩነት ለማገልገል ይችላሉ የተባሉ ኡለሞች እና አመራሮች የተመረጡ ሲሆን አመራሮቹም በጉባኤው ፊት ቃለ መሀላ በመፈፀም ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

በነገው እለት ሰኞ ጠዋት 4 ሰዓት ላይም የኀላፊነት ርክክብ እና ለቀድሞ አመራሮች የምስጋና እና የሽኝት ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል።

የዛሬው የባህር ዳሩ ጉባኤ በተሳካ እና በመግባባት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድጋፍ ላደረገው የክልሉ ህዝበ ሙስሊም እንዲሁም ከመንግስት የሚጠበቀውን ድጋፍ በማድረግ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ለተወጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ፣ ለክልሉ መንግስት አመራሮች እና የፀጥታ ክፍል ሃላፊዎች ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህዝበ ሙስሊሙን በሚመጥን ቁመና ላይ እንዲገኝ የክልል መጅሊሶች መጠናከር ወሳኝ በመሆኑ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሪፎርሙን ወደ ክልሎች በማወረድ የተሳካ ስራዎችን በመስራት ላይ ይgenyaል

የሳውዲአረቢያ ተጫዋቾች ውዱን መኪና  ተሸለሙ ። በትናንትናዉ እለት ሳይጠበቅ አርጀንቲናን ሁለት ለአንድ ለረቱት የሳዉዲአረቢያ ብሔራዊ ቡድን ለእያንዳንዳቸዉ ከአለማችን ዉድ መኪናዎች በቀዳሚነ...
23/11/2022

የሳውዲአረቢያ ተጫዋቾች ውዱን መኪና ተሸለሙ ።
በትናንትናዉ እለት ሳይጠበቅ አርጀንቲናን ሁለት ለአንድ ለረቱት የሳዉዲአረቢያ ብሔራዊ ቡድን ለእያንዳንዳቸዉ ከአለማችን ዉድ መኪናዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሰዉን Rolls-Royce መኪና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ከዛ በተጨማሪ ደግሞ የትናንትናዉን እለት እንደታሪካዊ ቀን በመዘከር በየአመቱ የእረፍት ቀን እንደሚያደርጉት መናገራቸዉም ይታወሳል።

22ኛው የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት በድምቀት ተካሂዷል፡፡የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ የተካሔደው በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታ እያስተናገደ በሚገኘው እና 60 ሺህ ተመልካቾችን በሚያስተናግ...
21/11/2022

22ኛው የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት በድምቀት ተካሂዷል፡፡

የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ የተካሔደው በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታ እያስተናገደ በሚገኘው እና 60 ሺህ ተመልካቾችን በሚያስተናግደው አል ባይት እስታዲየም ነው፡፡

በመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ላይ የውድድሩ ሳውንድ ትራክ ተብሎ በፊፋ ዕውቅና የተሰጠው “ሃያ ሃያ” (አብሮነት ይሻላል) የሚለው ቀርቧል፡፡

አስተናጋጇ ኳታር ከደቡብ አሜሪካዋ ኢኳዶር ጋር የመክፈቻ ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው፡፡

ኳታር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ፈረንጆቹ ታህሳስ 18 ቀን 2022 ድረስ ለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ስምንት ስታዲየሞች መርሐግብሮቻቸውን ለማከናወን ተሰናድተዋል፡

ከሁለት ቀን በኋላ የሚጀመረው እና ኳታር ስለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ  ዝግጅት አስገራሚ እውነታዎች ፡-• የዓለም ዋንጫውን ካዘጋጁ አገራት ኳታር በጣም ትንሿ አገር ያደርጋታል።• ...
19/11/2022

ከሁለት ቀን በኋላ የሚጀመረው እና ኳታር ስለምታስተናግደው 22ኛው የዓለም ዋንጫ ዝግጅት አስገራሚ እውነታዎች ፡-

• የዓለም ዋንጫውን ካዘጋጁ አገራት ኳታር በጣም ትንሿ አገር ያደርጋታል።

• በአረብ ሃገር የተዘጋጀ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ነው።

• በዓለም ዋንጫው ታሪክ ኳታር ካወጣችው ወጪ አንፃር እጅግ ውዱ የዓለም ዋንጫ ያደርገዋል።

• ኳታር ለዓለም ዋንጫው በአጠቃላይ 220 ቢሊዮን ዩሮ በማውጣት ላለፉት 35 ዓመታት የተካሄዱ ተመሳሳይ7 የዓለም ዋንጫ ዝግጅቶች ከወጣው ወጪ ጋር ተቀራራቢ መሆኑ አነጋጋሪ ነው ።

• ለዓለም ዋንጫው ሙቀትን የሚያቀዘቅዝ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው 6 ቅንጡ ስቴዲየሞችን ገንብታ ዝግጁ አድርጋለች።

• ከዓለም ዋንጫው በኋላ የሚፈርሰው ከ974 ከንቴይነሮች የተገነባው ስታዲዬም 40ሺ ተመልካች በመያዝ በዓይነቱ ለየት ያለ ክስተት ሆኗል።

• ለዓለም ዋንጫው 3.2 ሚሊዮን ትኬቶች ተዘጋጅተዋል።

• 5 ሚሊየን ታዳሚዎች የዓለም ዋንጫን ለመታደም ኳታር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል

• የኳታሩ ዓለም ዋንጫ የመጀመሪያው በበጋ የሚከናወን የዓለም ዋንጫ ነው።

• በእግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑ የአየር ሁኔታ ማስተካከያ የተገጠመላቸው ስቴድየሞች (air-conditioned stadiums) ኳታር ለዚህ ዓለም ዋንጫ አዘጋጅታለች።

• በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ዳኞች ዋና ዳኛ ሆነው በኳታር የዓለም ዋንጫ የምንመለከት ይሆናል።

• አፍሪካን የሚወክሉት 5ቱም ቡድኖች ለመጀመሪያ ጊዜ በአገራቸው አሰልጣኞች ይመራሉ ።

• በዚህ የዓለም ዋንጫ የሚሳተፈው በእድሜ ትንሹ ተጫዋች የጀርመኑ የሱፋ ሙኮኮ ሲሆን በእድሜ ትልቁ ደሞ የሜክሲኮው አልፌርዶ ታላቬራ ነው።

ምንጭ፡- ፍራንስ 24

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታይለር ቤክለማን ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የ...
18/11/2022

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታይለር ቤክለማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ መንግስት ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን እና በአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሴን ጆንስ ተሳትፈዋል፡፡

በውይይታቸውም በክልሉ በተደጋጋሚ ለሚከሰተው ድርቅ ዘላቂ መፍትሔ በማምጣት የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ÷ በክልሉ የሚከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የሚሰጠውን ዕርዳታ በማጠናከር የህብረተሰቡን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል ከአጋር አካላት ጋር በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን በበኩላቸው÷ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በተለይም በሶማሌ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ በማቅረብ የምናደርገውን ተሳትፎና ትብብር አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትየጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ያለበትን ደረጃ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡በውይይቱ የፌደራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተ...
18/11/2022

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትየጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ያለበትን ደረጃ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ የፌደራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ አጠቃላይ ገጽታ የሚያሳይ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑን የኢዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል÷ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከተጀመረ ወዲህ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ጥሩ ውጤት መታየት ጀምሯል ብለዋል።

በዚህም ወደ ዘርፉ በርካታ ኢንቨስትመንት መሳብና የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች እንዲያመርቱ ማድረግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

ሳዑዲ አረቢያ  #ላዛሪኒ በአምስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ " #ፓንጊዮስ" ተብሎ የሚጠራውን የዓለማችን ትልቁን ጀልባ ለመክፈት በዝግጅት ላይ ናት።በኤሊ ቅርጽ ያለው ይህ ጀልባ 60,000...
16/11/2022

ሳዑዲ አረቢያ #ላዛሪኒ በአምስት ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ " #ፓንጊዮስ" ተብሎ የሚጠራውን የዓለማችን ትልቁን ጀልባ ለመክፈት በዝግጅት ላይ ናት።

በኤሊ ቅርጽ ያለው ይህ ጀልባ 60,000 ሰዎችን ያስተናግዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የባህር ዳርቻ ፣ቪላዎች፣ የገበያ ማዕከሎች እና ዘጠኝ የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ያካተተ ተንሳፋፊ ከተማ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ እንደምታጋራ እና የመፍትሔ አንድ አካል ለመሆን ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብጽ እየተካሄደ...
07/11/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ እንደምታጋራ እና የመፍትሔ አንድ አካል ለመሆን ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግብጽ እየተካሄደ ካለው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ስልታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከዚህ ባለፈም ከአህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋር በጋራ የትኩረት ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ነው የገለጹት።

በዚህ ወቅትም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ሥጋትና እሳቤ እንደምትጋራ እና የመፍትሔዎች አንድ አካል ለመሆን ቁርጠኛ መሆኗን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ለ15 የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች የድህረ ምረቃ ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠች፡፡በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከኢትዮጵያ መንግስት በተሰጠው የነፃ ትምህርት...
04/11/2022

ኢትዮጵያ ለ15 የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች የድህረ ምረቃ ነፃ የትምህርት ዕድል ሰጠች፡፡

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከኢትዮጵያ መንግስት በተሰጠው የነፃ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለሚሆኑ ተማሪዎችን በትናንትናው ዕለት ሽኝት አድርጓል፡፡

የነጻ ትምህርት እድል ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግስት የደቡብ ሱዳንን የሰው ሀይል ልማትን ለማጠናከር እና የተቋማትን አቅም ግንባታ ለማሳደግ ካለው ቁርጠኝነት የተነሳ መሆኑ ተገልጿል።

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ ተማሪዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ወደ ሁለተኛ ቤታቸው እየሄዱ እንዳሉ ነግረዋቸዋል።

ዕድሉ በያዝነው ወር መጀመሪያ ወደ አዲስ አበባ ከተጓዙት ሃያ ዘጠኝ የደቡብ ሱዳን የህክምና ተማሪዎች በተጨማሪ የተሰጠ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡በውይይቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤት አፈጉባኤዎ...
04/11/2022

ከደቡብ አፍሪካው የሰላም ስምምነት መልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሰላም ሂደቱ፣ ውጤት እና አንድምታው ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ምክር ቤት አፈጉባኤዎች፣ ርዕሰ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬዲዋን ሁሴን በውይይቱ የተደረሰውን ስምምነት በተመለከተ አጠቃላይ ገለፃ መደረጉን ተናግረዋል ።

የሰላም ስምምነቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያስጠበቀና የሀገር ሉዓላዊነትን ያከበረ ነው ብለዋል።

የሰላም ስምምነቱ የባከኑ ጊዜያትን የሚክስና የተጉዱ አካባቢዎችን በመልሶ ግንባታ ለማስተካከል ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ ላይ መነሳቱን ገልጸዋል ።

በጦርነቱ የተጎዳችው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የሰላም ስምምነቱ ጥቅሙ የሁሉሞ ነው ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የስምምነቱ አተገባበር ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል፡፡

ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት  ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀ።በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሲካሄድ የ...
02/11/2022

ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ሰላማዊ እልባት ለመስጠት ሲደረግ የነበረው ንግግር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቀቀ።

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ሲቋጭ የተደረገው ስምምነት ግጭትን በዘላቂነት ማቆምን ያካተተ ነው።

በትግራይ ክልል ህገመንግስታዊ ስርዓት እንዲመለስም ከስምምነት ተደርሷል።

ስምምነቱ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችል የጠቀሰ ሲሆን፥ በዚህም መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱ ይሆናል።

በትግራይ ክልልም መሰረታዊ አገልግሎት እንዲጀመርም እንደዚሁ ከስምምነት ተደርሷል።

በኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ወልመራ ወረዳ የበጋ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ፡፡ዛሬ የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ክልል አቀፍ መሆኑ ተገልጿ...
01/11/2022

በኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ልዩ ዞን ወልመራ ወረዳ የበጋ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሄደ፡፡

ዛሬ የተጀመረው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ክልል አቀፍ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አበራ ወርቁ እንደገለጹት÷ በኦሮሚያ ልዩ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት 50 ሔክታር በበጋ መስኖ ይሸፈናል፡፡

በወልመራ ወረዳ ደግሞ 350 ሔክታር መሬት የበጋ ስንዴ በኩታገጠም ያለመ መርሐ ግብር ዛሬ በይ ፋ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

በክልል ደረጃም አንድ ሚሊየን ሔክታር በበጋ ስንዴ እንደሚሸፈን እና ከዚህም 40 ሚሊየን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

የአፍሪካን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ትክክለኛው አቅጣጫ አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት ነው ሲሉ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ፡፡እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ወጣ...
30/10/2022

የአፍሪካን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ትክክለኛው አቅጣጫ አፍሪካዊ መፍትሔ መስጠት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ፡፡

እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ወጣቶች ጉባኤ ላይ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቧል።

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በመድረኩላይ እንደገለጹት÷ አፍሪካውያን ችግሮችን ለመፍታት በሰላም ግንባታ እና በፀጥታ ጉዳዮች በርካታ አቅም አላቸው፡፡

አህጉሩን በቀጣይ የሚመሩት ወጣቶች የእርስ በእርስ ግንኘነትን በማጠናከር ለጋራ ውጤት መስራት አለባቸው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ አህጉር የምትወከለበት ስርዓት በድጋሚ መታየት እንዳለበትም ገልፀዋል።

በውይይቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ሚኒስትር ዛዲግ አብረሃ የፓን አፍሪካኒዝም እሳቤ እና ታሪክ በሚል የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እንድሪስ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ÷ በአፍሪካ ለሚፈጠሩ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ እንዲሁም ማህበራዊ ችግሮች ብቸኛው መፍትሔ አፍሪካውያን ችግሮችን የሚፈቱበት መንግድ የራሳቸው አገር በቀል እውቀት መሆን አለበት ብለዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የተወያየው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን ...
26/10/2022

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የተወያየው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡

የሀገሪቱን ወቅታዊና ዘላቂ የግብርና ልማት ፍላጎት በውጤታማ ምርምር ለማሳለጥ የሚያግዙ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማልማት፣ የግብርና ምርምር ሥርዓቱን በማስተባበር፣ በመደገፍና በማበረታታት እንዲሁም ተቋማዊ ትስስርን በማጎልበት በግብርና ምርቶች ራስን ለመቻል ብሎም የወጪ ንግድ ግብን ለማሳካት ግልጽ ተልዕኮና ኃላፊነት ያለው ተቋም ማቋቋም በማስፈለጉ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ተወያይቶ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በተጨማሪም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ወቅቱ ከደረሰበት የቴክኖሎጂ እድገት ጋር የሚራመድ፤ የዜጎችን እና የአካባቢን ደህንነትና ጤንነት ያረጋገጠ እንዲሆን እንዲሁም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች በተገቢው ወጪ፣ ጊዜ እና ጥራት መፈፀማቸውን በመቆጣጠር እና በመደገፍ የኢንዱስትሪውን ብቃትና ተወዳዳሪነት ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የባለስልጣኑን አደረጃጀት እንዲሁም ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮበሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በመጨረሻ ምክር ቤቱ የተወያየው የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደርን እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደርን ለማቋቋም በቀረቡ ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡

የተቋማቱን አሠራር እና የመፈፀም አቅም ማላቅ፤ አደረጃጀቶቻቸውን ማዘመን እና ስልጣንና ተግባሮቻቸውን ግልፅ ማድረግ በማስፈለጉ፣ በተለይም ተቋማቱ የሚሰበስቡትን የጡረታ ፈንድ ትርፋማና አዋጭ መሆናቸው በጥናት በተለዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በማዋል ሀገራቸውን አገልግለው ጡረታ ለሚወጡ ዜጎች የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ቀጣይነት እና አስተማማኝነት ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ነባሮቹን ደንቦች ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ቀን በተለያየ መርሐ ግብር እየተከበረ ነው።“የእሳት ቀለበት የህግ ማስከበር ዘመቻ ንፍቀ መዋዕል” በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ ዛሬ እየተመረቀ ነው። መጽሐፉ በዋና አዘጋጅ፣...
25/10/2022

የመከላከያ ሠራዊት ቀን በተለያየ መርሐ ግብር እየተከበረ ነው።

“የእሳት ቀለበት የህግ ማስከበር ዘመቻ ንፍቀ መዋዕል” በሚል ርዕስ የተጻፈ መጽሐፍ ዛሬ እየተመረቀ ነው።

መጽሐፉ በዋና አዘጋጅ፣ በአዘጋጅና በረዳት አዘጋጅነት የተጻፈ 360 ገጽ ያለው ነው።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የቀድሞ የኢፌዴራ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች ተገኝተዋል።

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ባደረጉት ንግግር÷ ሠራዊቱ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት በማሰብ ለዚሁ ምስጋና እያቀረብን እና ስለ ጀግንነታቸው እየዘከርን የምናሳልፈው ቀን በሠራዊቱ ስም ተሰይሟል ብለዋል፡፡

የዕድገታችን ቁልፍ በእጃችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ የተሣለጠ የሚ...
24/10/2022

የዕድገታችን ቁልፍ በእጃችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ የተሣለጠ የሚሆነው በዋናነት በውስጣዊ ዐቅማችን ላይ ከተመሠረተ ነው ብለዋል፡፡

ውስጣዊ ዐቅማችን ማለት፥ የሕዝባችን ዐቅም፣ የሀገራችን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሀብት እንዲሁም የአዲሱ ትውልድ የፈጠራ ክህሎት ናቸው ብለዋል።

በአስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ እያለፍን እንኳን ችግር ተቋቋሚ ኢኮኖሚ ሊኖረን ችሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ የዚህ ዋነኛ ምክንያቱ በመጠኑም ቢሆን ያሉንን ውስጣዊ ዐቅሞች አሟጠን ለመጠቀም መነሣታችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡


ከየትኛውም ወገን የሚሰጠን ድጋፍ በውስጣዊ ዐቅማችን ላይ ተጨማሪ እንጂ ዋና የዕድገት ምንጭ ሊሆን አይችልም ብለዋል።

ውስጣዊ ዐቅማችንን ተጠቅመን ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ ከዕንቅፋቶች የጸዳ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ሌብነትና ምርት ሥወራ ዋነኞቹ ፈተናዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በዚህም ወደ ውጭ መላክ የሚገባውን ምርት መደበቅ፣ ሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ዝውውርና መሬትን በአሻጥር መውረር በቆራጥነት ፈጣን እርምጃ ልንወስድባቸው የሚገቡ የብልጽግና ዕንቅፋቶች ናቸው ብለዋል።

በቀጣይ ፈተናዎችን የሚሻገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እንድንችል ሁለት መልክ ያሉት ትግል ያስፈልገናል። ማጥፋት እና ማልማት ነው ያሉት።

የኢኮኖሚ አሻጥሮችን፣ ሌብነትንና ምርት ሥወራን ለማጥፋት የሁሉንም ወሳኝ ትግል እንደሚፈልግ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ገቢን የመጨመርና ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ የመቀነስ የልማት ትግል ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፥ እነዚህ ሁለቱ የትግል መስኮች በራሳችን ፖሊሲና በራሳችን ዐቅም ማደግ እንድንችል ያስችሉናል፤ የዕድገታችን ቁልፍ በእጃችን ነውና ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለትጋታችን በምላሹ የለምነቷን ፍሬ እንደምታጠግበን አይተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ በሩዝ የለማ ማሳን ጎ...
23/10/2022

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለትጋታችን በምላሹ የለምነቷን ፍሬ እንደምታጠግበን አይተናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን ሸቤ ሶምቦ ወረዳ በሩዝ የለማ ማሳን ጎብኝተዋል።

በጅማ ዞን፣ በሦስት ወረዳዎች ላይ ከተንሰራፋው የኪሼ ኩታ ገጠም የሩዝ ልማት፣ በሸቤ ሶኖ ወረዳ በኩል የሚገኘውን የሩዝ ምርት ማየታቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

አክለውም ፥ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለትጋታችን በምላሹ የለምነቷን ፍሬ እንደምታጠግበን ያየንበት ነውም ብለዋል።

በተጨማሪም በጅማ ከተማ በ10 ሄክታር ላይ ያረፈ ጥምር ግብርናን መጎብኘታቸውን አንስተው ፥ በወጣት ትኩስ ጉልበት፣ መሬትን በውጤታማነት መጠቀምን በተገበረ ሁኔታ አትክልትና ፍራፍሬን ያመርታልም ነው ያሉት፡፡

በዚህም የአሣ እርባታን ይከውናል፣ የንብ ማነቢያንም አካትቷል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ጠንክረው ሠርተው ለሌሎችም የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ወጣቶች ለሀገር ኩራት እና ለብዙዎች አርዓያ እንደሚሆኑም ነው ያሰፈሩት።

በያለንበት ዘርፍ በርትተን እንትጋ ሲሉም ጥያቄ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዞኑ በዚህ ዓመት ከ27 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሩዝ ተሸፍኗል ።

በ2013/2014 የምርት ዘመን በዞኑ ሩዝ ተዘርቶ የነበረው ከ2 ሺህ ሄክታር በማይበልጥ መሬት ላይ ነበር።

በዚህ አመት ስራው በመስፋፋቱ ከጅማ ዞን ብቻ ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሩዝ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

አርሶ አደሮች ሩዝን በኩታ ገጠም ነው የዘሩት ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በጎበኙት ሸቤ ሶምቦ ወረዳ ኪሼ ክላስተር 3 ሺህ 500 ሄክታር መሬት ማሳ በሩዝ ለምቷል።

የሩዝ ምርቱ ከተነሳ በኋላ ስንዴ ለመዝራት መዘጋጀታቸውንም አርሶ አደሮቹ ገልጸዋል ።

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ጋር ውይይት አደረጉ።አምባሳደር ዘነበ ከኮሚሽነር...
21/10/2022

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዘነበ ከበደ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ቢሮ ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ተርክ ጋር ውይይት አደረጉ።

አምባሳደር ዘነበ ከኮሚሽነር ተርክ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ሁኔታ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

ሁለቱ አካላት ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን በጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በተመድ የስደተኞች አገልግሎት ረዳት ከፍተኛ ኮሚሽነር በመሆን ያገለገሉት ኦስትሪያዊ የሕግ ባለሙያ ቮልከር ተርክ በሚሼል ባቺሌት ቦታ መተካታቸው ይታወቃል።

ሐረር ኢማሙ አህመድ እስታዲየም የታላቁን ሼክ ኣደም ቱላ የቀብር ሽኝት ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጣ  በርካታ ህዝብ ተገኝቷል።
19/10/2022

ሐረር ኢማሙ አህመድ እስታዲየም የታላቁን ሼክ ኣደም ቱላ የቀብር ሽኝት ላይ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጣ በርካታ ህዝብ ተገኝቷል።

إنا لله وإنا إليه راجعون                ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴የሽኮች ሼክ የሆኑት ታላቁ ዓሊም ሼክ አደም ቱላ ወደ አኪራ ሄደዋል። አላህ ...
18/10/2022

إنا لله وإنا إليه راجعون

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴

የሽኮች ሼክ የሆኑት ታላቁ ዓሊም ሼክ አደም ቱላ ወደ አኪራ ሄደዋል። አላህ በጀነቱል ፍርደውስ ይቀበላቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን፣  #የገበታለሀገር አንድ አካል የሆነውን የጎርጎራ የልማት ፕሮጀክትን የሥራ ክንውን ጎብኝተዋል።
17/10/2022

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ጋር በመሆን፣ #የገበታለሀገር አንድ አካል የሆነውን የጎርጎራ የልማት ፕሮጀክትን የሥራ ክንውን ጎብኝተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት፤ ሕወሐት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሙሉ ዐቅሙ የከፈተውን ጥቃ...
17/10/2022

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የመከላከል ርምጃ በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረው ግጭት፤ ሕወሐት ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በሙሉ ዐቅሙ የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ የመጣ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። ይህም የኢትዮጵያ መንግሥት በሚያዝያ ወር ያወጀውን በሰብአዊነት ላይ የተመሠረተ የተኩስ አቁም የጣሰ ነው። የመንግሥት ጥረት ምንም ዋጋ ስላልተሰጠው፣ ሕወሐት በሁለት ዓመት ውስጥ ሀገሪቱን ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ግጭት አስገብቷታል።

ሕወሐት ሦስተኛውን ግጭት የከፈተው በአፍሪካ ኅብረት በኩል በሚደረገው የሰላም ንግግር፣ ያለ ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ላይ ለመነጋገር የኢትዮጵያ መንግሥት ዝግጅነቱን ከገለጠ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለልዩ መልእክተኞችና መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ ዲፕሎማቶች ጥቃት ለመሠንዘር ሕወሐት ያለውን ዝግጁነት አመልክቶ ነበር። ሕወሐት ለተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት በበተነው ደብዳቤ ላይ ይሄንን ጥቃት የመክፈት ፍላጎቱን በግልጽ አመልክቷል። በመሆኑም አሁን ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ብቸኛ ተጠያቂው ሕወሐት መሆኑ የተረጋገጠ ነው። ጊዜና ቦታ ከተሰጠውም ሌላ ዙር ግጭት እንደሚፈጥር ከሰሞኑ መግለጫዎቹ ለመረዳት ይቻላል።

ሕወሐት በሙሉ ዐቅሙ ጥቃት ከመክፈቱ በፊት የኢትዮጵያን የአየር ክልል ደጋፊዎቹ በሆኑ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ሲያስደፍር ቆይቷል። በዚህም የተነሣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል። የኢትዮጵያመንግሥት የሚወስዳቸውርምጃዎች የግድ አስፈላጊ የሆኑት በሕወሐት ተደጋጋሚ ጥቃት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋርተቀናጅቶ በሚፈጽማቸውተግባራት ምክንያት ጭምር ነው። ስለሆነም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግሥት የአውሮፕላን ማረፊያዎችን፣ የፌዴራል ተቋማትንና ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የግድ መጠበቅ አለበት ማለት ነው። ይህም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በተለይም የአየር ክልልን በሚገባ ከማስከበር አንጻር መጠበቅን የግድ አድርጎታል።

እነዚህ ተግባራት መፈጸሙ መንግሥት ሰብአዊ ርዳታን ለተረጂዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲያሣልጥ የሚረዳው ይሆናል። በአንድ በኩል እነዚህን ዓላማዎች እያስፈጸመ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄደውየሰላምውይይት ዝግጁመሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ያረጋግጣል። ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁለንተናዊና በንግግር ላይ የተመሠረተ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ያምናል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አግባብነት ባላቸዉ አሠራሮችና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎች በጽኑ የሚገዛ መሆኑን መንግሥት ግልጽ ለማድረግ ይፈልጋል። ንጹሐን እንዳይጎዱ ለመከላከል እንዲቻል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ በከተሞች ውስጥ እንዳይደረግ ጥንቃቄ እያደረገ ይገኛል። ይሄንን በጽኑ ለመፈጸም እንዲቻልም ለሁሉም ተዋጊ አሐዶች ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል።

ከዚህም ባሻገር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆኑ አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ በተሻለ መንገድ መቅረብ እንዲችልና የርዳታ ሠራተኞች ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን መንግሥት ከርዳታ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነው። ሕወሐት ንጹሐንን እንደ ጦር መከላከያ የመጠቀምና ሲቪል ተቋማትን ለወታደራዊ ሠፈርነት የመጠቀም የቆየ ልማድ አለው። ስለሆነም ሕዝቡና የርዳታ ሠራተኞች ራሳቸውን ከሕወሐት ወታደራዊ ተቋማት እንዲያርቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል። የርዳታ ሠራተኞችን ጨምሮ በሲቪሎችን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት መንግሥት ኀዘኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልጣል። እውነቱን ለማወቅና ያልተገደበ የርዳታ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ጉዳቶች ከተከሠቱ የሚያጣራ ይሆናል።

በመጨረሻም፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ዜጎቹን ደኅንነት ለመጠበቅ በሕግ የተሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን ለመወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ዝግጁነት በዚሁ አጋጣሚ ያረጋግጣል።
ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ።ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባህር ዳር ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ...
15/10/2022

የሱዳን የሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ለጣና ፎረም ባህር ዳር ገቡ።

ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባህር ዳር ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን፥ ከጥቅምት 4 እስከ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡

ፎረሙ ትናንት የቀድሞውን የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኬኔት ካውንዳን በማሰብ በቅድመ ጉባኤ ደረጃ ተካሂዷል።

በፎረሙ ላይ ለመካፈል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የአሁን እና የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ከተለያዩ የአፍሪካ ክፍል የመጡ ተመራማሪዎች እና ፖለቲከኞች ባህር ዳር ገብተዋል።

Address

New Africa Amharic
Khartoum
12345

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Africa Amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share


Other Broadcasting & media production in Khartoum

Show All