Ethio Muslim

Ethio Muslim በሽገር ከተማ ስም የሚፈርሱ መስዶችን እቃወማለዉ መስጂድ ፈርሶየሚገነባ ከተማ የለም🇸🇦🇸🇦🇸🇦🇪🇹🇪🇹🇪🇹

  እናት እንዴት ደስ ይላት ይሆንእናቴ ለትምህርት ቤቱ  ካርድ ላይ ይህን ፅፋ (ከስር ምትመለከቱት ወረቀት)ደረቴ ላይ ታንጠለጥል ነበር "አብራሪ ስትሆን በአውሮፕላንህ ወደ  #መካ 🕋 ውሰደኝ...
26/12/2024

እናት እንዴት ደስ ይላት ይሆን

እናቴ ለትምህርት ቤቱ ካርድ ላይ ይህን ፅፋ (ከስር ምትመለከቱት ወረቀት)ደረቴ ላይ ታንጠለጥል ነበር

"አብራሪ ስትሆን በአውሮፕላንህ ወደ #መካ 🕋 ውሰደኝ" ትለኝ ነበር
ዛሬ እናቴ ወደ ተከበረው ቤት መካ 🕋 ከተጓዦች አንዷ ነች የበረራው ፓይለት(አብራሪ ) ደሞ እኔ ነኝ 💖.💖💖

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አቅራቢያ ለሚገነባው ለባምዛ አል-ረህማን መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በነገው ዕለት በአቡ ሁረይራ መስጂድ እንደሚካሄድ ተገለፀ!- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ...
20/12/2024

በኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ አቅራቢያ ለሚገነባው ለባምዛ አል-ረህማን መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር በነገው ዕለት በአቡ ሁረይራ መስጂድ እንደሚካሄድ ተገለፀ!

- ሀሩን ሚድያ፣ ታህሳስ 10/2017

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አቅራቢያ በተመሰረተችው ባምዛ ከተማ ላይ 'አል-ረህማን' በሚል ስያሜ እየተገነባ ለሚገኘው መስጂድ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ልዩ ቦታው ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው አቡ ሁረይራ መስጂድ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር እንደሚካሄድ አስተባባሪ ኮሚቴው ለሀሩን ሚድያ ገልጿል።

በአዲስ አበባ ወደ ቦሌ መሄጃ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው በአቡሁረይራ መስጂድ የጁመአ ሰላትን በመስገድ ለመስጂዱ ግንባታ የበኩላችንን እንድንወጣ አስተባባሪ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ኘሬዝዳንት ሸይኽ ኢብራሂም ሲራጅ በመስጂዱ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ መርሀግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አካባቢው ላይ ያለው ማህበረሰብ የመስጂድ እጦት የተቸገረና አካባቢው የመዝናኝ ከተማ እየሆነ ስለሆነ መስጂዱን በአፋጣኝ እንዲሰራ መጠየቃቸው ይታወሳል።

© ሀሩን ሚድያ

ምን አይነት አስፈሪ ክስተት ነው 🥹🥺 © እዝህ ሰፈር የተገኘ ነው ሳነበው ጥሩ መልክት አለው ላካፍላችሁ ብዬ ነው እስከ መጨረሻው አንብቡት‼️ማክሰኞ በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ የ Merc...
03/12/2024

ምን አይነት አስፈሪ ክስተት ነው 🥹🥺

© እዝህ ሰፈር የተገኘ ነው ሳነበው ጥሩ መልክት አለው ላካፍላችሁ ብዬ ነው እስከ መጨረሻው አንብቡት‼️

ማክሰኞ በሪያድ ከተማ የተከሰተው አደጋ

የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊት ተጋጭተው ነበር..

"አምቡላንስ አየሁ ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ፣

አንድ ወጣትን ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየው፡፡

ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል አካላቱ ተቆርጠዋል፣ እግሩም ጭምር ተቆርጧል እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል

"መሞት አልፈልግም፣በጣም ፈርቻለሁ ፣ እሳት ነው ምገባው እኮ" ይለዋል

እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔኮ አልሰግድም ነበር ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም፣ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል

ሰወችም ተሰበሰቡ፣ እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ፣ በጣምም ፈርቻለሁ፡፡

በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል

የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ ጩኸቱም _ ቀጠለ ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ፡፡

ሊያድኑት ግን አልቻሉም

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሀዳ በል ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም

አላሁ አክበር፣ በጣም ፈርቶ ነበር፣ ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ

ግን....ግን ሸሀዳውን ማለት አልቻለም ነበር

ከዚያም አልተንቀሳቀሰም፣ ሰውነቱም ደርቆ ቀረ

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት

ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት፡፡

ዘጋቢውም ይለናል፦" በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው፣ ሰላታችሁን ግን ጠብቁ፣ በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡

የመጨረሻ ቀናችሁ መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም እኔም ከዚህ ክስተት ቡሃላ መተኛት አልቻልኩም እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...” እሰግዳለሁ፣ ወላሂ ከዚህ ቡሃላ እሰግዳለሁ፣ መሞት ግን አልፈልግም..….”🥹🥹

ያ አላህ መጨረሻችንን አሳምርልን ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን

አንብባችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉ ምናልባትም በዚህ ታሪክ የ1 ሰውን ህይወት ማቃናት እንችል ይሆናል፡፡

አለሁ አክበር..!!!በተላቁ መሪ ቭላድሚር ፑቲን የምትመራው ራሽያ ቁርዐንን በማ*ቃ*ጠ*ል ታላቅ ወንጀል የፈፀመን ግለሰብ የሀገሪቱ ፍርድቤት በ14 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል። ጀግ...
27/11/2024

አለሁ አክበር..!!!

በተላቁ መሪ ቭላድሚር ፑቲን የምትመራው ራሽያ ቁርዐንን በማ*ቃ*ጠ*ል ታላቅ ወንጀል የፈፀመን ግለሰብ የሀገሪቱ ፍርድቤት በ14 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል። ጀግናው መሪ እስልምናን በሽብርተኝነት ማሸማቀቅ እንዲቆም ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

እንደ ፑቲን አይነት መሪ ያብዛልን 🇷🇺🙏🙏

የሳኡዲ ዜጋ የሆነው ዶክተር ሰኢድ አልቃህጣኒ ይባላል ለአስቸኳይ ቀዶ ጥገና ወደ ሆስፒታል እንዲመጣ ጥሪ ይደረግለታል እሱም እየተቻኮለ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል ነገር ግን የተወሰኑ ደቂቃዎች ዘግ...
27/11/2024

የሳኡዲ ዜጋ የሆነው ዶክተር ሰኢድ አልቃህጣኒ ይባላል
ለአስቸኳይ ቀዶ ጥገና ወደ ሆስፒታል እንዲመጣ ጥሪ ይደረግለታል እሱም እየተቻኮለ ወደ ሆስፒታል ይሄዳል ነገር ግን የተወሰኑ ደቂቃዎች ዘግይቶ ስለነበር ቀዶ ጥገና የሚያደርገው ልጅ አባት ዶክተሩ ላይ በሃይለኛው እየጮሀ ይሰድበው ጀመር " ልጅህ ቢሆን የታመመው አታረፍድም ነበር " እያለ ይጮህበታል
ዶክተሩም ስድብ እና ጩሀቱን ተቋቁሞ ምንም ሳይተነፍስ ቀዶ ጥገና ክፍል ይገባል ለረጅም ሰአት በተደረገ ኦፕሬሽን ታማሚውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሶ ይወጣል የታማሚው አባትም ይደሰታል ነገር ግን ዶክተሩ ቀዶ ጥገናውን ከጨረሰ በኋላ እየተቻኮለ ወደቤቱ ይመለሳል በእዚህ ጊዜ አብረውት የነበሩት የዶክተሩ ረዳቶች ለታማሚው አባት " ዶክተሩ ልጁ ሙቶበት የልጁን አስክሬን ቤት አስቀምጦ ነው ያንተን ልጅ ለማዳን የመጣው " ይሉታል :'( አንዳንዴ ሰዎች በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ሳናውቅ ለመፍረድ አንቸኩል ።

በሰላሙ ዘርፍ የኔ ምርጫ:-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የድምፃችን ይሰማ ፈርጥ የሆነው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ነው!!!--------Antex Ethiopia የተሰኘ ዓ...
24/11/2024

በሰላሙ ዘርፍ የኔ ምርጫ:-የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የድምፃችን ይሰማ ፈርጥ የሆነው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ነው!!!
--------
Antex Ethiopia የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት ከሰላምና ኢኮኖሚ አኳያ ለሀገራችን ኢትዮጵያ የራሳቸውን በጎ አሻራ ላሳረፉ ባለውለታ ስብዕናዎች እውቅና ለመስጠትና ለሁለቱም ዘርፍ ተመራጮች 10፣ 10 ሚሊየን ብር (በጥቅሉ 20 ሚሊየን ብር) ለመሸለም በዝግጅት ላይ ይገኛል። ለዚህ ክብር መመረጥ ያለበት ስብዕና ማን ነው ትላላችሁ? የእርስዎን እጩ ተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ በምትመለከቷቸው አድራሻዎች ይጠቁሙ!
ከታች የተጠቀሱትን ዘጠኝ ነጥቦች የሚያሟላና በሰላም ዘርፍ ሉሸለም የሚገባው በኔ እይታ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ሰብሳ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ነው።ምክንያቱም የተጠቀሱትን ዘጠኝ ነጥቦች የሚያሟላ ስለሆነ።ምን ትላላችሁ? ከታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች እንዴት እንደኖረው ከፁሁፎቹ፣ከእለት ተእለት መልእክቶቹና ተግባሮቹ ማሳያዎችን በገፍ እናገኛለን።እስቲ እንጥቀሳቸው!

.                     ሱራ አል-አንቢያእ          87.የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ         (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት        መኾና...
18/11/2024

. ሱራ አል-አንቢያእ

87.የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡

88.ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡

03/11/2024

‼️
የአዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች ሰሞኑን ኒቃብ ለብሶ የመማርን መብት በሰላማዊ መንገድ በመጠየቃቸው ብቻ ት/ቤቱ በመሰረተባቸው የውሸት ክስ 2 ሴት እና 3 ወንድ ተማሪዎች ታሰረዋል።
#ሼር

የቱንም ያህል ሀይለኛ እና ጀግና እንደሆንክ ብታስብም ጊዜህ የሚያልቅበት ቀን ይመጣል አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን እንጂ 🙏
03/11/2024

የቱንም ያህል ሀይለኛ እና ጀግና እንደሆንክ ብታስብም ጊዜህ የሚያልቅበት ቀን ይመጣል አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን እንጂ 🙏

01/11/2024

መልካም ስራዎች!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَن راحَ إلى مَسجدِ الجماعةِ فَخُطوةٌ تَمحو سَيِّئةً، وخُطوَةٌ تَكتَتِبُ لهُ حَسنةً، ذاهِبًا وراجِعًا﴾

“ጀምዓ ለመስገድ ወደ መስጂድ የተጓዘ በአንዱ እርምጃው ሀጢያቱ ይሰርዝለታል። በአንዱ እርምጃ ደግሞ ሀሰናት (መልካም ስራ) ተደርጎ ይመዘግብለታል። ሲሄድም ሲመለስም።”

📚 ሶሂህ አተርጊብ፡ 299

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሂጃብ እና የኒቃብ ጉዳይን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ!- ሀሩን ሚድያ ጥቅምት 21/2017"የሙስሊም ተማሪዎችን የሂጃብ እና የኒቃብ ጉዳይ ቋሚ መፍ...
31/10/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የሂጃብ እና የኒቃብ ጉዳይን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ!

- ሀሩን ሚድያ ጥቅምት 21/2017

"የሙስሊም ተማሪዎችን የሂጃብ እና የኒቃብ ጉዳይ ቋሚ መፍትሄ እንዲያገኝ መንግስት ምን እየሰራ ነው?" በሚል ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ከተከበሩ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ለቀረበው ጥያቄ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ "የአለባበስ ስርዓትን በሚመለከት ከድሮ ለውጥ አለ የቀረ ነገር ካለ በሂደት እናሻሽላለን ብለዋል።"

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር ) "በተሟላ ሁኔታ ምንም አይነት እንከን የለም ማለት አንችልም ግን የቀረ ነገር ካለ እናሻሽላለን" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

© ሀሩን ሚድያ

አቤ እና ከቤ በርሀ እያቋረጡ ነው.....😥ከቤ ፦"በዚሁ ከቀጠልን በርሀብና በውሀ ጥምመሞታችን ነው።😞ትንሽ እንደሄዱ ከርቀት አንድ መስጊድ 🕌አዩ...አቤ ፦ስማችንን ቀይረን እንግባ እኔ አህመ...
31/10/2024

አቤ እና ከቤ በርሀ እያቋረጡ ነው.....😥

ከቤ ፦"በዚሁ ከቀጠልን በርሀብና በውሀ ጥም
መሞታችን ነው።😞

ትንሽ እንደሄዱ ከርቀት አንድ መስጊድ 🕌አዩ...

አቤ ፦ስማችንን ቀይረን እንግባ እኔ አህመድ
እሆናለሁ አለ😎

ከቤ፦እኔ ስሜን አልቀይርም አለ😁

እንደደረሱ የመስጊዱ ኢማም በሰላምታ ተቀበላቸው🤗 ሀጂ አሊ እባላለሁ ማን ልበል? እናንተንስ።☺️

አቤ ፦አህመድ እባላለሁ

ከቤ ፦ ከቤ እባላለሁ

ሀጂ አሊ👳‍♂፦ልጆች ለከቤ ምግብ እና መጠጥ
አምጡለት

ወንድሜ አህመድ ጾም ስለሆነ ሰአት ሲደርስ ከኛ
ጋር ያፈጥራል።😂

አቤ ፦ፌንት🤪

🍁ምስሉ እንዲህ ይላል  ፦ስታያት ቦታ  ስጣት ፤  ካንተ ጋር የምትሽቀዳደም  ሳይሆን  የሰውን  ነፍስ  ለማዳን ከጊዜ ጋር የምትሽቀዳደም  ስለሆነች   !! የታመመን  ሁሉ  ከመድሃኒቱ  ጋር...
29/10/2024

🍁
ምስሉ እንዲህ ይላል ፦
ስታያት ቦታ ስጣት ፤ ካንተ ጋር የምትሽቀዳደም ሳይሆን የሰውን ነፍስ ለማዳን ከጊዜ ጋር የምትሽቀዳደም ስለሆነች !!
የታመመን ሁሉ ከመድሃኒቱ ጋር አሏህ ያገናኘው :'(

17/10/2024

ለአላህ የገባውን ቃል ሞልቶ አልፏል !
ፊቱን ሳያዞር ከመኖር ይልቅ በአላህ መንገድ መሰዋትነትን ናፍቆ ሂዷል!

ሸሂዶች ህያው እንጅ ሙታን አይደሉም ባለው ቃል እንፅናና እንጅ ምን እላለሁ !

ሄዝቦላህ 17 የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀየሊባኖሱ ሄዝቦላህ በዛሬው እለት ብቻ 17 የእስራኤል መታደሮችን መግደሉን በቴሌግራም ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።ሄዝቦላህ በዛሬው እ...
05/10/2024

ሄዝቦላህ 17 የእስራኤል ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በዛሬው እለት ብቻ 17 የእስራኤል መታደሮችን መግደሉን በቴሌግራም ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።

ሄዝቦላህ በዛሬው እለት ከእስራኤል ጋር ባደረገው ውጊያ በርካታ የእስራኤል ተዋጊዎቹን መግደሉን ነው ያስታወቀው።

የእስራኤል ጦር በዛሬው እለት ተገድለዋል ስለተባሉ ወታደሮቹ እስካሁን ምንም ያላለ ሲሆን፤ በትናንትናው እለት የሞቱ ወታደሮቹ ቁጥር ግን 9 ደርሰዋል ብሏል።

በጦርነቱ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ

እምባ አባሽ አጥቶ😥💔                እምባሽ አባሽ አጥቶ፣         ሀዘኑ ሰቆቃው አለቅጥ በርትቶ፣      ጋዛ ወፈለስጢን ደም እምባ ሲያነቡ፣          ለሙታኖቻቸው ላህድ ...
01/10/2024

እምባ አባሽ አጥቶ😥💔

እምባሽ አባሽ አጥቶ፣
ሀዘኑ ሰቆቃው አለቅጥ በርትቶ፣
ጋዛ ወፈለስጢን ደም እምባ ሲያነቡ፣
ለሙታኖቻቸው ላህድ ሲገነቡ፣

ዓለመል ኢስላሙ ዐረቡ አጀሙ፣
በዝምታ ድባብ አድበው ሲስማሙ፣
ማነህ ባለተራ? ተብሎ ሊበለት፣
ነገ ባለ ተራ ነገ ባለ ሳምንት፣

መሆኑን ዘንግቶ ጨል! በሩን ዘግቶ፣
በመከዳ ፍራሽ እራሱን ደብቆ፣
ሽንፈቱን አውጆ ፍፃሜውን አውቆ፣

እናት እያነባች ደም እምባ ጠብታ፣
በፈረሰ ገላ ፍርስራሽ ታግታ፣

አብሽሪ ባይ አጥታ ወድቃና ተንጋላ፤
መሆን እንኳ አቅቷት ለልጇ ከለላ፣

ዋ ኢስላማ! ማለት አሁንኮ ነበር፣
ዑመቱ ተዋርዶ አንገት ሲያቀረቅር፣
በጡብ በፍርስራሽ በቁሙ ሲቀበር፣

Jemal Dawud Muzeyin

“ይህን ሰይጣናዊ ድርጊት በልኩ አለመቃወም የተማሪዎችን አለመስገድ መደገፍ ነው “!!!———————————————————-ስሙ የተቀየረው የክብርት ሸኻ ፋጢማ አዳሪ ት/ ቤት ጉዳይ ከመሻሻል ይልቅ...
25/09/2024

“ይህን ሰይጣናዊ ድርጊት በልኩ አለመቃወም የተማሪዎችን አለመስገድ መደገፍ ነው “!!!
———————————————————-
ስሙ የተቀየረው የክብርት ሸኻ ፋጢማ አዳሪ ት/ ቤት ጉዳይ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰ ሄዷል። ሂጃብ ወደማስወለቅ እና ሂጃብ በቦርሳ እንኳን ይዞ ወደቅጥሩ መግባት ተከልክለው ወደመጡበት የተመለሱ ሴት አይነስውር ተማሪዎች እንዳሉም እየሰማን ነው።

ከፍ ሲል በሚዲያዎቻቸው መልካም እንደሰራ ስህተታቸውን እያወደሱ እያስወሩም እያስፃፉም ነው። ምንም አያመጡም ያንድ ሰሞን ጩኸት ናቸው ያሉን ይመስላል። ምን ያድርጉ ተግባችንም ቢሆን እንዲያ ይመስላል።

በመጀመርያ ሰላት ከለከሉ መስገጃ ነጠቁ
ሲቀጥሉ ሂጃብ ከለከሉ ሂጃብ ነጠቁ
ወደፊት ምናልባትም ኢስላማዊ የሆኑ ቃላት አልሃምዱሊላህ ፣ቢስሚላህ ፣ወላሂን እንደማይከለክሉ እርግጠኛ መሆን ይቻል ይሆን?

ለዚህ ሁሉ ክልከላ የሚመለከተው አካልም ይሁን ህዝበ ሙስሊሙ የሚገባውን ያህል መቃወም ለምን ማለት ለምን አልቻልንም???

ጉዳዩን ለባለ ጉዳዩቹ ለማድረስ ኢምባሲው እንኳን እርቆብናል። የተከለከለው ሰላት ነው ያውም ለአመታት እዛው እያደሩ የሚማሩ ተማሪዎችን ። ይህን ክፉ ሰይጣናዊ ስራ በሚመጥነው ልክ አለመቃወም አለመስገዳቸውን መደገፍ ነው።

ክብርት ሸይኻ ፋጢማ ሆይ “እኛ ነፃ ትምህርት የሚሰጡባቸው ተቋማት እንጂ ተጨማሪ የማክፈሪያ ማዕከላት አንፈልግም ።ገንዘባችሁ ባይጠቅመን እንዲጎዳን ግን አያድርጉ!!!”

በምትችሉት ቋንቋ ሁሉ ሼር በማድረግ ለተገቢው አካል እንዲደርስ ሰበብ ይሁኑ።
አቡሱመያ ዲኑ ዓሊ

"የህዲ መን የሻዕ ኢላ ሲራጢል ሙስተቂም" ያሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራለ።"  እኚህ አባት ለሰላሳ ዓመታት ያህል ቁርዓንን አንብበዋል በ81 ዓመታቸው ኢስላምን ተቀበሉ፣❤✌️🤲ዐለይ...
22/09/2024

"የህዲ መን የሻዕ ኢላ ሲራጢል ሙስተቂም" ያሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራለ።"

እኚህ አባት ለሰላሳ ዓመታት ያህል ቁርዓንን አንብበዋል በ81 ዓመታቸው ኢስላምን ተቀበሉ፣❤✌️🤲
ዐለይከ ረበና ቢሁስኒል ኺታሚ! ያ ረብ መጨረሻችንን አሳምርልን! የሚባለው ለዚህ ነው።

Jemal Dawud Muzeyin

Address

Riyadh

Telephone

+966536725022

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Muslim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category