Woldia Online

Woldia Online Woldia Online is news and entertainment website!!

04/01/2025

ኢትዮጵያ በቀን እስከ 10 ጊዜ እየተንቀጠቀጠች ነው በመሬት መንቀጥቀጥ የሚል አፕ አውርዳችሁ አለም ላይ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ የ 24 ሰዓት ሪፖርት ማየት ትችላላችሁ
እንደ አፑ ሪፖርት ከሆነ አሜሪካ ሳትንቀጠቀት አትውልም!!

😘
02/01/2025

😘

በወልዲያ ደብረ ሲና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የታላቁ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ የልደት በዓል አከባበር በከፊል። (ታኅሣሥ 24/2017 ዓም)📸 Muller M M...
02/01/2025

በወልዲያ ደብረ ሲና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን የታላቁ ኢትዮጵያዊ ሐዋርያ አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ የልደት በዓል አከባበር በከፊል። (ታኅሣሥ 24/2017 ዓም)

📸 Muller M Mhss

Via Solomon Ayalew

02/01/2025

የአሁኑ መናሃሪያ ስራ ከጀመረ 32 ዓመት ሆነው!
ወልድያ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመናሃሪያ ሲያገለግል የነበረው ሰፈር ሙጋድ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ደብረገሊላ/ፒያሳ እንደመናሃሪያ ሲያገለግል ቆይቷል በደርግ ጊዜ ለአቢዮት አደባባይነት ሲያገለግል የነበረው የአሁኑ መናሃሪያ ከ1985 ዓም ታህሳስ 24 /ቀኑ አርብ ቀን ነበር የዋለው ይባላል/ ለመናሃሪያ ስራ ጠረጋ የተጀመረበት ቀን ነበር...
ቀኑን ያስታወሰኝን ጓደኛየን አመሰግናለሁ!!

😘
01/01/2025

😘

01/01/2025

😘

01/01/2025
01/01/2025

የወልዲያ ጠቅላላ  ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኦክስጅን ማምረት ጀመረ ወልዲያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህክምና አገልግሎት የሚውል ኦክስጅን ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።የኦክስጅን ማምረቻ ማሽ...
31/12/2024

የወልዲያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኦክስጅን ማምረት ጀመረ

ወልዲያ ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህክምና አገልግሎት የሚውል ኦክስጅን ማምረት መጀመሩን አስታወቀ።

የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኑ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተመልክቷል።

በሆስፒታሉ የሚታየውን የኦክስጅን ምርት እጥረት ለመፍታት የሚያስችል ኦክስጅን የሙከራ ማምረት የጀመረው ዛሬ መሆኑን በሆስፒታሉ የባዮ ሜዲካል ባለሙያ አቶ ዮሴፍ ምህረቴ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ሆስፒታሉ ለህክምና የሚያስፈልገውን ኦክስጅን ከደሴ እና የግል ሆስፒታሎች በማስመጣት ሲጠቀም መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህም በተፈለገው መጠንና ጊዜ ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኖ በህክምና አገልግሎት ዘርፉ ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ጠቅሰዋል።

ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል የኦክስጅን ማምረቻ ማሽን በመትከል ዛሬ ማምረት መጀመሩን ጠቅሰው፥ ማሽኑ በቀን እስከ 200 ሲሊንደር የማምረት አቅም አለው ብለዋል።

ኦክስጅኑን አምርቶ መጠቀም መጀመሩ የተሟላ ህክምና ለመስጠት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በሰሜን ወሎና በወልዲያ ከተማ ለሚገኙ ጤና ተቋማት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቱን እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በወልዲያ ከተማ የቀበሌ 01 ነዋሪ አቶ አለባቸው አዳሙ በሰጡት አስተያየት፤ ከ6 ወር በፊት በተሽከርካሪ አደጋ የተጎዳ ልጃቸው በኦክስጅን እጥረት ምክንያት ወደ ደሴ " ሪፈር " መባላቸውን አስታውሰዋል።

በዚህም ለአላስፈላጊ ወጪና መጉላላት መዳረጋቸውን አንስተው፥ አሁን ላይ ሆስፒታሉ በራሱ አቅም ኦክስጅን ማምረት መቻሉ የህብረተሰቡን ችግር እንደሚያቃልል ገልጸዋል።

የኦክስጅን ማምረቻ ማሽኑ 70 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን፤ ይህም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ትብብር እንደተከናወነ ተመልክቷል።
ዘገባው የኢዜአ ነው

ቀይ ባህር ግን በሱማሊያ በኩል አለ እንዴ?የኤደን ባህረ ሰላጤ እና ህንድ ውቂያኖስ እንዳለ ነው የማቀው ሰሞኑን የማያቸው ዜናዎች ግራ ስላጋቡኝ ነውእስኪ የገባው ?
31/12/2024

ቀይ ባህር ግን በሱማሊያ በኩል አለ እንዴ?
የኤደን ባህረ ሰላጤ እና ህንድ ውቂያኖስ እንዳለ ነው የማቀው ሰሞኑን የማያቸው ዜናዎች ግራ ስላጋቡኝ ነው
እስኪ የገባው ?

31/12/2024
30/12/2024

በቅሎየ ስገሪ እንድንገባ ሰኞ
ቤቷም ወልድያ ነው ገበያው ማክሰኞ!

Address

Riyadh

Telephone

+251920212121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woldia Online posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Woldia Online:

Videos

Share