GMN TV Ethiopia

GMN TV Ethiopia ኢትዮጵያ እንዴት ዋለች?
የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታን በየለቱ እናቀርባለን

17/11/2024

ትናንት ሄልኮፍተር በባህር ዳር አካባቢ በፋኖ ተመታ ወድቃለች

በአዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኒቃብ እንዳይለበስ የከለከሉ ሙስሊም ጠ*ል አመራሮች እነዚህ ናቸውበደምብ ሼር ይደረግ
30/10/2024

በአዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኒቃብ እንዳይለበስ የከለከሉ ሙስሊም ጠ*ል አመራሮች እነዚህ ናቸው
በደምብ ሼር ይደረግ

11/10/2024

ኡኡኡ😢😱🙄
ባህር ዳር ከተማ ላይ 2 ሊትር ቤንዚን በጥቁር ገብያ 500 ብር እየተሸጠ ነው : : ይህ ማለት ከሊትር 160 ብር ያተርፋሉ ማለት ነው ::

አንድ ማደያ አንድ ቦቴ ሲያራግፍ 45,000 ሊትር ነው 25,000 ሽጦ ቀሪውን 20,000 ሊትር ለብላክ ነጋዴዎች በሊትር 150 ብር ቢሸጥ ከአንድ ሊትር 60 ብር ያተርፋል
20000 *60 = 1,200,000 ሚሊየን ብር ያተርፋል ይህ ብር ንግዱንም ምኑንም ለማፈን በቂ ነው እንዲህ ያለ ጥቅም የሚገኝበት ሂደት ባለበት ትክክለኛ የነዳጂ ስርጭት ይኖራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል ::

ሌላው ትልልቅ ሳልባቲዮ ጭነው አውርደው ለመሸጥ የሚሰማሩ መኪኖች ዳማሶች የችግሩ አባባሾች የጥቁር ገብያው አንቀሳቃሾች ናቸው እጥረት እስኪቀረፍ የሚሰጥ ቤንዚል በሊትር መተመን ቢቻል ::

ይህንን ስንል ሀቀኞች ባለማደያወች እንዳሉ ሳንዘነጋ ነው ::

10/10/2024

ሰበር ዜና
በአማራ ክልል ተዘግቶ የነበረው መንገድ
ነገ አርብ ይከፈታል
ማለትም ከጥቅምት 01/02/2017

10/10/2024

በአማራ ክልል ተጥሎ የነበረው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እቀባ ከነገ 01/02/2017 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተነስቷል የሚል መረጃ ደርሶናል አጣሩ ::

09/10/2024

90 ብር በገባ ነዳጂ ነዳጂ ሳይሞሉ ግዳጂ የሚሉ የሞሉበት ሀገር ላይ እንዴት ተሰርቶ ይታደራል ቤተሰብስ ኑሮስ ይመራል 1 ጎማ 52 ሽህ ብር በገባበት አንድ ፉል ነዳጂ 45,000 ብር በሚቀዳበት ሀገር ያለምንም ክፍያ የግለሰብን ንብረት ግዳጂ እያሉ ማንገላታት አይከብድም ??

ቀበሌው ግዳጂ
ወረዳው ግዳጂ
ዞኑ ግዳጂ
ከተማው ግዳጂ
ክልሉ ግዳጂ
ሀገሪቱ ግዳጂ

የት ተኬዶ ይሰራ 😱😱

ጎበዝ ወደየት ሂደን ነው የምንሰራዛሬ ማለትም በ 29/011 2017 ወልደያ ላይ በእንቅስቃሴ እገዳ ምክንያት ቆመው  የነበሩ የጭነት መኪኖች ወዴትም አትወጡም በማለት የፌደራል ፖሊሶች አስቁመ...
09/10/2024

ጎበዝ ወደየት ሂደን ነው የምንሰራ
ዛሬ ማለትም በ 29/011 2017 ወልደያ ላይ በእንቅስቃሴ እገዳ ምክንያት ቆመው የነበሩ የጭነት መኪኖች ወዴትም አትወጡም በማለት የፌደራል ፖሊሶች አስቁመውናል ሰንጠይቃቸው ያስቆመህ ይምጣና ይስደድህ የሚል መልስ ሰጠውናል ሲሉ መልህክት እድርሰውናል ::

ሾፌር ክልከላ ባለባቸው ሲያሽከረክር እርምጃ ሲወሰድበት ቀርባችሁ ለማትረፍ በማትሞክሩበት ሂደት እንዴት በምን ሞራል ነው ያስቆመህ ያስለቅቅህ ልትሉስ የደፈራችሁ ?

የመኪኖቹ መቆም ካሳሰባችሁ ለምን እያጀባችሁ እንዲጓዙ ያላደረጋችሁ እናንተ የፈራችሁትን መንገድ ሾፌር በምን ድፍረቱ እንዲሄድበት ፈለጋችሁ ???

ወልድያ ያላችሁ ህግ አስከባሪዎች ሾፌሮችን አትንቀሳቀሱም የምትሉ የፌደራል ፖሊሶች ልታፍሩ ይገባል ::

የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ብቻ አይደለችም።"መሬት መንቀጥቀጡ አዲስ አበባ አይደለም ተረጋጉ ማለት ምን ማለት ነው?"***(ስናፍቅሽ አዲስ - ለድሬ ቲዩብ)የሀገሩ ሚዲያ ስለ ሀ...
07/10/2024

የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ብቻ አይደለችም።
"መሬት መንቀጥቀጡ አዲስ አበባ አይደለም ተረጋጉ ማለት ምን ማለት ነው?"
***
(ስናፍቅሽ አዲስ - ለድሬ ቲዩብ)

የሀገሩ ሚዲያ ስለ ሀገሩ ያለው አስተሳሰብ ከሚሰራቸው ዘገባዎች በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል። በትናንትናው ዕለት ተከሰተ የተባለውን የመሬት መንቀጥቀጥ የዘገቡበት መንገድ አስተሳሰባቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

እንዲህ ያለ ነገር የሰነበተ ይመስለኛል። አዲሴ አበባ መብራት ካለ ሀገሩ በርቷል። አዲስ አበባ ሰላም ካለ ሀገሩ በሙሉ ሰላም ሰፍኗል። አዲስ አበባ ቆሞ ኢትዮጵያን ከመመልከት አዲስ አበባ ሆኖ አዲስ አበባ ላይ ብቻ መወሰን የሚዲያው ባህሪ ከሆነ ከረመ።

ዜናዎቹ በይፋ በመዲናዋ የተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አይደሉም። በሚሉ አረፍተ ነገሮች የሚጀምሩ ናቸው።

የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቨዥን እራሱ የመዲናዋ ኤፍ ኤም ይመስል "ዛሬ ምሽት የተሰማው የመሬት ንዝረት ለከተማዋ ነዋሪዎች አስጊ አለመሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጂኦፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤሊያስ ሌዊ ገልፀዋል" ሲል እዚያ የእሳተ ገሞራው ፍንዳታ ጉያ ያሉ ከተሞች፣ የመሬት መንቀጥቀጡ መነሻ ስር የሚኖሩ ሰዎችስ የሌላ ፕላኔት ዜጎች ናቸው?

ባለሙያው በአዲስ አበበ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ አዋሽ ፈንታሌ አከባቢ የተከሰተ እንደሆነ ገልፀው ከፈንታሌ ተራራ ጉያ ያለው ወገን በሚሰማው ዙሪያ "ሰላም ነው ችግሩ አዲስ አበባ የተከሰተ አይደለም" ማለት ምን ማለት ነው?

የአንድ ሀገር ብሔራዊ የቴሌቨዥን ጣቢያም ሆነ ሜኒስትሪም ሚዲያ በምን ስሌት በአዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ አልተከሰተም የሆነው፤ በአፋር ፈንታሌ አከባቢ በተከታታይ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተፈጠረ የመሬት ሞገድ (ንዝረት) ስለሆነ ተረጋጉ ይላል?

እሺ ለመሬት መንቀጥቀጡ ቅርብ የሚገኙ አካባቢዎች እና በችግሩ ጉያ ያሉ ወገኖች ማን እንዴት ምን ብሎ እንዲያረጋጋቸው ነው?
አደጋው የተከሰተው ሌላ ቦታ ስለሆነ ተረጋጉ ብሎ የአዲስ አበባ ህዝብ መውሰድ ስላለበት ጥንቃቄ ያብራራው ሚዲያ አደጋው የተፈጠረበት ቦታ ያሉ ዜጎች ምን ማድረግ ይገባቸዋል የሚለውን ግን ማንሳት አልፈለገም።

አሁንም እንዲህ ያሉ አደጋዎች ከመዲናይቱ ከራቁ ትኩረት የሚነፈግበት ልማድ መቅረት አለበት። ጎርፍም እሳትም መሬት መናድም ሆነ ሌላ ችግር ሌላ ቦታ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ እስከማይመስል ድረስ ትከረት የሚነፍጉ ሚዲያዎች ከተደጋጋሚ ስህተታቸው ሊማሩ ይገባል።

 # # # # # #የኢሬቻ በዓድ አምልኮ ያመጣብን ጣጣበሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል:: መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች...
06/10/2024

# # # # # #የኢሬቻ በዓድ አምልኮ ያመጣብን ጣጣ
በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል::
መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች መካከል አንዱ ነው::

በእኛ እግር ዘወትር የምትረገጠው መሬት በጌታዋ ትዕዛዝ ትንቀጠቀጣለች:: ህዝቦች በወንጀል ሲዘፈቁ፣ ሽርክ እና ጥፋት ሲንሰራፋ፣ በምድራችን ብክለት ሲስፋፋ ጌታችን አላህ ሰዎች ከጥፋታቸው ታርመው ወደሱ ይመለሱ ዘንድ ማስጠንቀቂያዎችን ይልካል:: ከነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው::

ይህ ማስጠንቀቂያ ካለንበት የወንጀል አረንቋ በመውጣት ወደ አላህ እንድንመለስ የማንቂያ ደውል ነው::

በሀገራችን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በትንሹ ተከስቶ ያለፈ ቢሆንም ከበድ ያለ ሆኖ ቢከሰት ባለንበት የወንጀል አረንቋ እንደተዘፈቅን ወደ ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር::

ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ላይ እድል አግኝተናል:: ወደ አላህ እንመለስ:: ጌታችንን አብዝተን ምህረትን እንለምን:: አላህ እንዲታረቀን ፣በእዝነቱ እንዲያየን በዱኣ ልንበረታ ይገባል

አላህ ምህረቱን ይለግሰን!

ነገ ኢሬቻ ለመሄድ አስበሃል⁉️====================✍ ሙስሊም ሆነህ ሳለ ነገ ለሚከበረው የኢሬቻ (የዋቄፌታ ኃይማኖታዊ በዓል) ለመሄድ ዝግጅትህን አጠናቀሃል? የሚገዙ ልብሶችንና የ...
05/10/2024

ነገ ኢሬቻ ለመሄድ አስበሃል⁉️
====================
✍ ሙስሊም ሆነህ ሳለ ነገ ለሚከበረው የኢሬቻ (የዋቄፌታ ኃይማኖታዊ በዓል) ለመሄድ ዝግጅትህን አጠናቀሃል? የሚገዙ ልብሶችንና የሚያዙ ነገሮችን ሸማምተሃል?

እንግዲያውስ ሸይኽ ኣደም ቱላ (ረሒመሁ-ል'ሏህ) እንዳሉት፤ በዓሉን አክብረህ ስትመለስ ቀጥታ ወደ መስጅድ ገብተህ ከመስገድህ በፊት ሸሃዳ ያዝና ገላህን ታጥበህ ግባ።

«ኢሬቻ ላይ ሄዶ የመጣ ሙስሊም ገላውን ታጥቦ ሸሃዳ ይዞ ካልሆነ በስተቀር ወደ መስጂድ መግባት አይችልም!»
ታላቁ ዓሊም ሙፍቲ ሸይኽ አደም ቱላ (ረሒመሁ-ል'ሏህ)

*
ለማንኛውም ወንድሜ፤ መቼ እንደምትሞት አታውቅምና የጓደኞችህ ቀጠሮም ሆነ ውስወሳ ሳይሸነግልህ ለአላህ ብለህ ማክበሩን ተወው።
ብሔርህንና ማንነትህን አትጥላ። ግን ከእምነትህ ጋር የሚጋጭን ከማንነትና ብሔር ጋር የተያያዘን ነገር ተው።

ለአላህ ብለህ ከተውከው ውዱ ነቢይ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
( إنك لن تدع شيئاً لله عز وجل إلا بدلك الله به ما هو خير لك منه )
«አንተ ላቅና ከፍ ላለው አላህ ብለህ አንድን ነገር አትተውም፤ ለአንተ በርሱ ከርሱ የበለጠ የተሻለን የቀየረልህ ቢሆን እንጂ!»
[አሕመድ: 21996]
*
በል! እንግዲያስ የተሻለን ነገር አላህ እንዲለውጥልህ ከፈለግክ የስሜትን ውስወሳና ሞቅታ ተወውና ከዲንህ ጋር ከሚጋጭ ነገር ራቅ።
«እኔ እዛ ሂጀ አላከብርም!» ብለህ አትሸንግል።
እዚያ መሄድ የምትችለው አቅሙ ካለህ ሰዎችን ለማስተማር እንጂ ባትተገብርም ለመታደም አይደለም።
አላህ ያግራልህ።


ስለ ኢሬቻ በዝርዝር ማንበብ የፈለገ ይህን በዚህ አስፈንጣሪ ያገኛል።
https://t.me/MuradTadesse/31980

||
t.me/MuradTadesse

የአላህ የአላህ😭ኒቃብ የፈጣሪዋን ትዛዝ የጠበቅችን ሴትልጅ እንደዚህ መሬት ላይ እስከመዘረር የሚያደርስ ምት መምታት ከአንድ ህብረተሰብን አገለግላለው ከሚል ፓሊስ አይጠበቅምምንም ጥፋት አጥፍታ...
10/09/2024

የአላህ
የአላህ

😭

ኒቃብ

የፈጣሪዋን ትዛዝ የጠበቅችን

ሴትልጅ እንደዚህ መሬት ላይ እስከመዘረር የሚያደርስ ምት መምታት ከአንድ ህብረተሰብን አገለግላለው ከሚል ፓሊስ አይጠበቅም

ምንም ጥፋት አጥፍታ ከሆነ በህግ ና በህግ አግባብ መዳኘት ሲገባት

በአፋን ኦሮሞ አውጪ አውጪ እያሉ የፈጣሪዋን ትእዛዝ የምትጠብቅን ሴት መምታት ነውር ና ብልግናም ነው::

* የፌዴራል ፓሊስ ይፍርድልን

* ፓሊሶም ተፈልጎ ይታሰርልን

ያረብ ፍርዱ ላንተ ይሁንልን 😭

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

ግብፅ inbox ጉርሻ የኢትዮጵያውን የድረሱልን ጥሪ………ትላንትና ዛሬ በግብፅ መአዲ የምባል ሰፈር በከፍተኛ ሁኔታ ሰው እየታፈሰ ነው የዋለው በወረቀት ሰበብ አድርገው ብዙ ኢትዮጵያውያን እየታ...
09/09/2024

ግብፅ

inbox ጉርሻ

የኢትዮጵያውን የድረሱልን ጥሪ………

ትላንትና ዛሬ በግብፅ መአዲ የምባል ሰፈር በከፍተኛ ሁኔታ ሰው እየታፈሰ ነው የዋለው በወረቀት ሰበብ አድርገው ብዙ ኢትዮጵያውያን እየታፈሱ ነው የዋሉት

በየቤቱ እየገቡ ቤት እየፈተሹ

* ብር
* የተለያዩ ላፕቶፕ ካገኙ እየወሰዱ ነው

* የታጠቁ እና
* ስቭል የለበሱ ቤት ውስጥ ስፈትሹ

የታጠቁት ቤር ላይ ይቆማሉ እና በከፍተኛ ደረጃ ሀበሻዎች ላይ ከፍተኛ ዝርፍያ የምመስል በግብፅ ፖሊሶች መአዲ ላይ ቀኑን ሙሉ ቤት ለቤት ስፈትሹ ነው የዋሉት

የምንጠይቀው ሰውም የለም በሀገራችን ህጋዊ መፈተሻ ከለሌ አይገቡም እዚህ ግን እንደዛ የምባል ነገር የለም ።

አሁንም በከፍተኛ ጥንቃቄ እንድያደርግ ህዝቡ ያስተላልፉልን እኔ ጽፈላችሁ ቶሎ ነው የማጠፋው ስልከ ስፈተሽ እንዳይገኝብኝ መረጃዎች ።

በጣም ነው ተጨንቀን ያለነው መአዲ አከባቢ የምንኖር ወረቀት አድስ ያለውንም ለማጣራት ብለው ያስራሉ

* ከ15/20 ቀን አሰቃይተው ይለቃሉ

ገንዘብ ያለው ድንገት ከተገኝ የተወሰነ ብር ተቀባብለውት መንገድ ላይ ይለቁታል ዩኤንም አስተማማኝ አይደለም ።

😭😭😭

🌴🌴🌴

እእእ😎😎😎The Goat Lifeይህን ፊልም ጉርሻዎች ቅዳሜ እለት ምን ተፈጥሮ ነው ብለው 2 ስአት ከፈጀ በኃላ ጨረስነው::ሳውዲዎችን ያስቆጣ እንዲሁም ብዙ ሀረቦች ያስቆጣል እንደሆነ ታውቋል ...
02/09/2024

እእእ

😎😎😎

The Goat Life

ይህን ፊልም ጉርሻዎች ቅዳሜ እለት ምን ተፈጥሮ ነው ብለው 2 ስአት ከፈጀ በኃላ ጨረስነው::

ሳውዲዎችን ያስቆጣ እንዲሁም ብዙ
ሀረቦች ያስቆጣል እንደሆነ ታውቋል

ይህን ፊልም ለመተንትን ሀረብ ሀገር ብዙ
ዓመት መኖር ይጠይቃል

ኢትዮጵያ ውስጥ ቁጭ ብለህ ወይንም ብለሽ :-

* ሀረብ እንዲህ ነው
* ሀረብ ጨ ካ ኝ ነው ብትል ሰው ሲቅብሀል

ፊልም የግሀድ ዓለም ነፀብራቅ ነው ቢባልም
ይህ ፊልም ግን በጣም ተጋኗል

ሳውዲ :-

* ለብዙ ህንዳውያን መኖር ትርጉም የሆነች
* ለብዙ ኢትዮጵያውያን መቀየር ትርጉም የሆነች
* ለብዙ ኢትዮጵያውያን ሞት ተጠያቂ የሆነች
* ለብዙ ኢትዮጵያውያን መፈናቀል ተጠይቂ የሆነች

ብትሆንም ?

ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ከብዙ ዓመት በፊት ጀምሮ ምን አደረጉ ስትል ደሞ :-

እውነታው :-

* ሀሸሽ በመሸጠት
* መጠጥ በመሸጠት
* ሀገሪቱን ወሰክ (ቆሻሻ) አድርገዋት

የሩሱል ሀገር የሆነችው ሳውዲ ና ብዙ ሚሊዮን ህዝብ በዓለም በዓመት ውስጥ የሚጎበኛት ሳውዲ በምእራባውያን ምክንያት የዓለም ህዝብ እንዲጠላት በዚህ ፊልም እየተደረገ ቢሆንም እሷ ግን እኛን አይወክልም እኛ እንዲህ አይደለም እያለች ትገኛለች::

ኢትዮጵያውያን አንድ ነገር መገንዘብ ያለብን :

* ሀረብ ሁሉ ክፉ አይደለም

* ሀረብ ሁሉ መጥፎ አይደለም

* ሀረብ ሁሉ ጨ ካ ኝ አይደለም

* ስንት ፈጣሪን የሚፈሩ
* ስንት መልካም ነገር የሚስሩ
* ስንት ሚሊዮን ህዝብ የሚረዱ
* ስንት እርዳታ ያደረጉ
* ስንት መልካም ነገር የሰሩ

ሀረቦች አሉ::

እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ሀረቦችን የመኮነንም ሆነ የመተቸት መብታ ያላቸው አይመስለንም

በዚህ በ6 ና በ7 ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ተካሄደ

* ሰው በቁሙ
* ሰው ከቀዬው
* እርጉዝ ሴት
* ሰው በማንነቱ

ስንት ጉድ ተሰርቶ ሀረቦች መኮነን ትንሽ አይከብድም
እኔ ምን ስስራ ነበር ብላችሁ ወደኃላ ሀስቡ

እንደውም ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈፀመው በፊልም ቢሰራ ዓለም ጉድስ አይልም::

ፃድቅ ፃድቅ የምናጫወተውስ ? ? ?

ሳውድ ግን ለብዙ ለዓለም ሰዎች

* ፍፁም ሰላም
* ፍፁም እረፍት
* ፍፁም ፍቅር

የሚነፍስባት ሀገር መሆኗን አትዘንጉ::

The Goat life ፊልም ተጋኗል::

😎😎😎

🌴🌴🌴

 #ቻግኒ #ከተሞቻችንቻግኒ ከተማ በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ በ1842 ዓ.ም እንደተቆረቆረች ይነገራል፡፡ ቻግኒ የሚለው የከተማዋ ስያሜ የአገውኛ ቋንቋ ሲሆን ...
27/08/2024

#ቻግኒ
#ከተሞቻችን

ቻግኒ ከተማ በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ ዞን ውስጥ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ በ1842 ዓ.ም እንደተቆረቆረች ይነገራል፡፡ ቻግኒ የሚለው የከተማዋ ስያሜ የአገውኛ ቋንቋ ሲሆን "ቻ" ማለት ነገ የሚል ትርጉም ሲኖረው፣ "ኒ" ማለት ደግሞ ቤት ማለት ነው፡፡ በዚህም "የነገ ቤት" የሚል የአማርኛ ፍቺ አለው።

ከባህር ጠለል በላይ 1 ሺሕ 538 ሜትር ከፍታ ላይ የከተመችው ቻግኒ ከተማ ቆላማ የአየር ንብረት አላት፡፡ ከመዲናችን አዲስ አበባ 495 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ቻግኒ ለኑሮ የምትመች ከተማ ናት፡፡

ከተማዋ በአምስት የከተማ እና የገጠር ቀበሌዎች የተዋቀረች ስትሆን ልዩ ልዩ የሰፈር ስያሜዎች አሏት፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ቴክኒክ፣ ጂጂ፣ መድሀኒያለም፣ ቦሌ፣ አባሙሳ፣ ሽሮ ሜዳ የሚባሉ የሰፈር ስሞች ይጠቀሳሉ።

በቻግኒ ሕዳሴ ቻግኒ 2ኛ ደረጃ፣ መሰረት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ፣ ቻግኒ 2ኛ ደረጃ፣ ሂባ አካዳሚ፣ ቻግኒ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ እና ሌሎች የትምህርት ተቋማት ይገኛሉ፡፡

ከቻግኒ ከተማ በደቡብ አቅጣጫ 1 ኪ.ሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው "ዶንዶር ፏፏቴ" ልዩ የከተማዋ ተፈጥሯዊ መስህብ ሥፍራ ነው።

ከ35 ሜትር ከፍታ ላይ ቁልቁል እየተወነጨፈ ከሚወርደው ፏፏቴ የሚወጣው የውሃው ጭስ ለቻግኒና ለአካባቢዋ ድንቅ የተፈጥሮ ውበትን አላብሶታል፡፡ በፏፏቴው ዙሪያም እዕዋፋትን ጨምሮ የተለያዩ የዱር እንስሳት ይገኛሉ፡፡

ቻግኒ የሀገር ባለውለታ የሆኑ ታላላቅ ሰዎችን፣ ሙዚቀኞችንና ጋዜጠኞችን ያፈራች ከተማ ነች።

በዚህች ውብ ከተማ ተወልዳችሁ ያደጋችሁ እንዲሁም በተለያየ አጋጣሚ አይታችኋት ልዩ ትዝታን ያተረፋችሁ ትዝታችሁን አጋሩን።
መልካም ሳምንት!

በአዲስዓለም ግደይ

👏👏👏5 ሊትር ዘይት በ400 ብር ደሴ ከተማ‼በደሴ ከተማ አላግባብ ዘይትን የደበቁ ባለሀብቶችን መጋዘናቸውን በማሸግ ለህብረተሠቡ በዝቅተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ተደርጓልበአራዳ ክፍለከተማ አላግባብ ዘ...
04/08/2024

👏👏👏

5 ሊትር ዘይት በ400 ብር

ደሴ ከተማ‼

በደሴ ከተማ አላግባብ ዘይትን የደበቁ ባለሀብቶችን መጋዘናቸውን በማሸግ ለህብረተሠቡ በዝቅተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ተደርጓል

በአራዳ ክፍለከተማ አላግባብ ዘይትን የደበቁ ባለሀብቶችን የዘይት አቅራቢ ድርጅቶችም ሳይደብቁና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ለህብረተሠቡ እንዲሸጡ ምክርና ማስጠንቀቂያ ቢሠጣቸውም ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸውና በመደበቃቸው የክፍለ ከተማው አመራሮች የዘይት መጋዘኑን በማሸግ ለህብረተሠቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸጥ አድርገዋል።

የተያዘውን ዘይትም ዛሬ ከሰአት ቡሀላ ጀምሮ

400 ባለ5ሊትር ዘይት ለህብረተሠቡ

5ሊትሩን የተለያዩ ስያሜ ያላቸውን ፈሳሽ

የምግብ ዘይት በ980 ብር ሂሳብ ኡመር ዘይትን በ1100 ብር ፒያሳ አደባባይ ጊዜያዊ መሸጫ በማቋቋም ለማህበረሰቡ እንዲሸጥ አድርገዋል።

የምግብ ዘይትና የተለያዩ ሸቀጦችን በየሠፈሩ የከዘኑ፣ ምርቱን የደበቁና ያላግባብ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ህብረተሠቡ ለሚመለከተው አካል ጥቅማ እንዲሰጡ ማሳሰቡን ከከተማው ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ መረጃው ያሳያል

ደሴ 👏👏👏

🙏🙏🙏

🌴🌴🌴

አንድ ባስ ሙሉ መንገደኞች መታገታቸው ተነገረ ከባህር ዳር አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በፍቼ እና በገርበጉ...
03/08/2024

አንድ ባስ ሙሉ መንገደኞች መታገታቸው ተነገረ

ከባህር ዳር አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በፍቼ እና በገርበጉራቻ መካከል ልዩ ስሙ ደገም በምትባል አነስተኛ ከተማ ሲደርሱ ታጣቂዎች መኪናውን አስቁመው ብዛት ያላቸው ተሳፋሪዎቹን አግተው እንደወሰዷቸው ተሰምቷል።የመኪናው ሾፌርና አንድ ሌላ ተሳፋሪ በአጋቾቹ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ተነግሯል።አካባቢው ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ እገታ የሚፈፀምበት ነው።ይህ እየታወቀ ስለምን የፀጥታ ሀይሎች የሉም?
===================================
ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ 👇
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ጥቆማና ማስታወቂያ👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

02/08/2024

የአውቶቡሱ ሾፌር በጥይት ተገሏል
በኦሮሚያ ክልል ከፍቸ ደብረ ጉራቻ መሀከል ዛሬ በ26/11/2016 ተሳፋሪዎች በወንበዴ ዘራፊዎች ታፍነው መታገታቸው ይታወቃል በዚሁ ሰአት የ3 ልጆች አባት የሆነው የአውቶብሱ ሾፌር መገደሉን መረጃ ደርሶናል :: ሾፌር ወንበዴ እየበደለ እየገደለው እስከመቸ ነው የሚቀጥለው ለሚለው ጥያቄ መልሱ የአንዳችን ጉዳት ለአንዳችን ጉዳት ሆኖ ሲሰማን ለመብታችን በአንድነት መነሳት ስንችል ብቻ ነው ::

ነፍስ ይማርልን

የኢትዮጵያ መንግስት 1,500 ብር የሚከፈላቸው ሰራተኞችን ደመወዝ በ300 እጥፍ ሊጨምር ነውየኢትዮጵያ መንግስት ለደመወዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ እንደመደበ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አ...
02/08/2024

የኢትዮጵያ መንግስት 1,500 ብር የሚከፈላቸው ሰራተኞችን ደመወዝ በ300 እጥፍ ሊጨምር ነው

የኢትዮጵያ መንግስት ለደመወዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ እንደመደበ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚቀርበው ተጨማሪ በጀት የሚካተተው የደመወዝ ጭማሪ በዋናነት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን የሚመለከት እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ተሿሚዎች ብዙ ላያገኙ ይችላሉ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን ጉዳይ ያነሱት፤ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ነው። ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀው ውይይት፤ የኢትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ቢሆንም በገበያ ላይ ወደ ተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት የተደረገው ሽግግር ዋነኛ ትኩረት አግኝቷል።

አብይ በትላንቱ ገለጻቸው መንግስታቸው በተገበረው የኢኮኖሚ ማሻሻያ “የሚጎዱ ሰዎች” መኖራቸውን አምነዋል። የኢኮኖሚ ማሻሻያው “በትሩን የሚያሳርፍባቸው” ካሏቸው መካከል የመንግስት ሰራተኞች እና ገበሬዎች ይገኙበታል። ተጽዕኖውን ለመቋቋም መንግስታቸው ለሚያደርገው የደመወዝ ጭማሪ 90 ቢሊዮን ብር እንዳስፈለገውም ጠቅሰዋል።

በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ “በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በወር 1,500 ብር የሚከፈላቸው የመንግስት ሰራተኞች “300 እጥፍ” የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከ25 ሺህ ብር በላይ ወርሃዊ ደመወዝ የሚከፈላቸውን የመንግስት ሰራተኞች “ለጊዜው ታገሰን አልነው” ሲሉም ተደምጠዋል። የደመወዝ ጭማሪው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ባገኘው ብድር እና እርዳታ የሚሸፈን ነው።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦

ዜና የኢትዮጵያ መንግስት 1,500 ብር የሚከፈላቸው ሰራተኞችን ደመወዝ በ300 እጥፍ ሊጨምር ነው August 2, 2024 FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailCopy URL የኢትዮጵያ መንግስት ለደመወዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን ብር በላ....

Address

Jeddah

Telephone

+966583516623

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GMN TV Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GMN TV Ethiopia:

Videos

Share