Hawassa tube ሀዋሳ ቲዩብ

Hawassa tube ሀዋሳ ቲዩብ ታርክ ሰርተን ነው እንጅ ሌላው በሰራው ታርክ አንጓራደድም

31/01/2025

إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تسليماً )

ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በመጪው እሁድ ጥር 25 በአዲስ አበባ እስታዲየም እንዲገኝ ጥሪ አቀረቡ።
29/01/2025

ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በመጪው እሁድ ጥር 25 በአዲስ አበባ እስታዲየም እንዲገኝ ጥሪ አቀረቡ።

በአክሱም ት/ቤቶች ዛሬ የመጀመሪያ ሴሚስተር የማጠቃለያ ፈተና (Final Exam) ተጀምሯል። እህቶቻችን ከዩኒፎርማቸው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሒጃብ ለብሰው ቢሄዱም፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ተመልሰዋል...
27/01/2025

በአክሱም ት/ቤቶች ዛሬ የመጀመሪያ ሴሚስተር የማጠቃለያ ፈተና (Final Exam) ተጀምሯል። እህቶቻችን ከዩኒፎርማቸው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሒጃብ ለብሰው ቢሄዱም፤ በሚያሳዝን ሁኔታ ተመልሰዋል።

ጥር 17፣ 2017 ዓ.ል |  ረጀብ 26፣ 1446 ዓ.ሒبِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ                  •••••••••••••••••••••••••••••...
25/01/2025

ጥር 17፣ 2017 ዓ.ል | ረጀብ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የስራ አስፈፃሚ አባላት ልዑክ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር ተወያየ::
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ወላይታ ሶዶ

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ አባል ና የክልል፣ የሰላምና ዲያስፖራ ዘርፍ ተጠሪ ሀጅ ሙስጠፋ ናስር የሚመራው ልዑክ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

ውይይቱ በኡስታዝ ቢላል ማይዶ ክስ እና ከኢስላማዊ አልባሳት ጋር ተያይዞ የመማር መብት በተነፈጉ ሙስሊም ሴቶች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ተጠሪና የልዑኩ አባል ሸይህ ሁሴን ሀሰን፣ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ በቀለ ሎኮርማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ አባላት በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን የተፈጠሩት ችግሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ከተለያዩ መዋቅር ለተውጣጡ ለክልሉ ወጣቶች ለ4 ቀን የሚቆይ ስልጠና መሰጠት ጀመረ !የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል  በጠቅ...
22/01/2025

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ከተለያዩ መዋቅር ለተውጣጡ ለክልሉ ወጣቶች ለ4 ቀን የሚቆይ ስልጠና መሰጠት ጀመረ !

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በጠቅላይ ም/ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ዘርፍ አዘጋጅነትና በካውንስሉ አስተባባሪነት የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የወጣቶች የስራ አመራርና ስራ ፈጠራ ስልጠና የመክፈቻ ፕሮግራምና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ክፍተኛ ምክር ቤት ፕረዚዳንት ሼክ አብዱሹኩር አብድልቃድር አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመዘዋወር ከተለያዩ መዋቅር ውስጥ ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር የውይይት እና ስልጠና መርሃግብር ለማካሄድ እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ ቀደም በወራቤ ከተማ በትላንትናው ዕለት ደግሞ በሻሸመኔ ከተማ የውይይት እና የስልጠና መርኅ ግብር ማካሄዱ ተገልጿል።

- ጥር 14/2017 ዓ.ል
ሀዋሳ -ሲዳማ

በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ አሁን በዚች ስዓት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል::* ሂጃባ ውበቷ ነው:...
21/01/2025

በትግራይ ክልል በመቐለ ከተማ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ አሁን በዚች ስዓት ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄደ ይገኛል::

* ሂጃባ ውበቷ ነው::
* ሂጃብ ከትምህቷ በላይ ነው::
* ሂጃባ የፈጣሪዋ ትእዛዝ ነው::

#ሂጃቧንም ትለብሳለች
ትምህርቷም ትማራለች::

እያሉ በጭዋነት እና ስነስርዓት ባለው መንግድ ድምፃቸውን እያሰሙ ይገኛል::

🙏🙏🙏

06/01/2025
https://vt.tiktok.com/ZS6yN6MUA/
03/01/2025

https://vt.tiktok.com/ZS6yN6MUA/

303 likes, 79 comments. “ #ሀበሻ🇪🇹🇪🇹🇪🇹tiktok 🇬🇲🇬🇲🇬🇲 -Media Mubarek Abent Official”

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሒጃብ የመብት ጥሰት ጉዳይ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል። ምክር ቤቱ በመግለጫው ሒጃቧንም ታደርጋለች ትም...
03/01/2025

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሒጃብ የመብት ጥሰት ጉዳይ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል። ምክር ቤቱ በመግለጫው ሒጃቧንም ታደርጋለች ትምህርቷንም ትማራለች በሚል መፈክር አስተጋብቷል። አክሎም በአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘው የሒጃብ ክልከላ እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል። (ሚንበር ቲቪ)

(በዚህ ዜና ላይ ከቆይታ በኋላ ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን)

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
01/01/2025

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

31/12/2024

ታህሳስ 20/04/2017 ዓ.ም በሲዳማ ክልል በምስራቅ ሲዳማ ዞን ቦና ዙርያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰ በመኪና አደጋ የ66 ስዎች ህይወት በማለፉ መራራ ሀዘን ተሰምቶኛል😭😭

30/12/2024

1000668851391
ቦና ለተጎዱ ቤተሰብ ድጋፍ በማህበረሰቡ በጎ ፈቃደኞች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከፈተ የባንክ ሂሳብ ነው። ለወገን ደራሽ ወገን ነውና የአቅማችንን እንረባረብ።

በትራፊክ አደጋ ከ69 በላይ የሰው ሕይወት ተቀጠፈ*************************ሀዋሳ፣ ታህሳስ 20፣ 2017 (ኤስቢሲ) በሲዳማ ክልል በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ከአንድ ገጠር...
29/12/2024

በትራፊክ አደጋ ከ69 በላይ የሰው ሕይወት ተቀጠፈ
*************************

ሀዋሳ፣ ታህሳስ 20፣ 2017 (ኤስቢሲ) በሲዳማ ክልል በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ ከአንድ ገጠር ቀበሌ ሰርግ ለማጀብ በአይሱዙ ተጭነው ስጓዙ በገላና ድልድይ ላይ ተገልብጠው ከ69 በላይ ነፍስ መጥፋቱን ተገልጿል።

የዞኑ አስተዳዳሪ ዶ/ር ማቴ መንገሻ ለኤስ ቢ ሲ እንደገለጹት ይህ ዘግናኝ እልቂት የተፈጠረው በአይሱዙ የጭነት መኪና ላይ ተጭነው ደስታቸውን በሚገልጹበት በተፈጠረ የመገልበጥ አደጋ ነው።

የነፍስ አድን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት አስተዳዳሪው ለሟች ቤተሰቦችና ዘመድ አዝማድ መፅናናትን ተመኝተዋል።

በይስሃቅ ፍቅሩ

24/12/2024



Sasuri Noosi Manchi Iimaanu Coommilli Noosiho

fans Harun media ሃሩን ሚዲያ Voice of Sidaama የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ Mujib Amino

22/12/2024

በሲዳማ ክልል ሙስሊም ወገኖቻችንን በግድ ሀይማኖታቸውን ለማስለወጥ የሚደረገው ዘመቻ ይቁም !

Address

Buraydah

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa tube ሀዋሳ ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hawassa tube ሀዋሳ ቲዩብ:

Videos

Share