02/09/2024
የቲክቶክ ጊፍት በአሜሪካ የሀበሾችን ትዳር አፈረሰ
ስማቸው ያልተጠቀሰ ሀበሻ ባለትዳሮች ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ሀገር ነው። በጋራ የሚጠቀሙበት የካፒታል ዋን የባንክ አካውንት አላቸው ከሰባት ወር በኋላ ባል ወደ ባንክ በአጋጣሚ ሲሄድ እሱ የማያውቀው 50ሺ ዶላር ወጪ መሆኑን ይመለከታል ይላል ፋስት መረጃ ከታዲያስ አዲስ የሰማው ዘገባ፣ ከዛ የባንኩን ኃላፊዎች ሲያናግር 50ሺ ዶላሩ ለቲክቶክ አፕሊኬሽን ወጪ እንደሆነ ይነገረዋል።
ባል ወደ ቤት በመግባት ባለቤቱን ሲጠይቅ "ስራ ስለሌለኝ ለመደበሪያ ብዬ ነው ቲክቶክ ስጠቀም ለጊፍት ያወጣውት" የሚል ምላሽ ከሚስቱ ያገኛል፣ ባል እሺ በማለት ነገሩን ተቀብሎ ከቆይታ በኋላ 50ሺ ዶላሩ ለአንድ ወንድ ቲክቶከር ብቻ ወጪ እንደሆነ ይደርስበታል።
ጉዳዩ ወደ ፀብ ተቀይሮ በመሃል ሽማግሌ ገብቶ ትዳሩ መቀጠል ሳይችል በፍቺ ተጠናቋል።
የጊፍተር ትዳር ተበተነ።