20/09/2023
ከአሳሳች ገለጻዎች ተጠበቁ!
ከተስፋዬ ሮበሌ
ነጋዴውን "ሁለትና ሁለት ስንት ነው?" ቢሉት "ሲያተርፍ አምስት ሲያከስር ሦስት ነው" ብሏል የሚል የአገራችን ጫወታ አለ! ከሥር ያለውን ሥዕል ይመለከቶአል!
(1) "እውነት ነባራዊ ሳይሆን አንጻራዊ (እንደየሰዉ አተያይ) ነው" የሚሉ ሰዎች የሚጠቀሙበት ምሳሌ ነው! ይህ ድኅረ ዘመናዊ ዐስተሳሰብ ነው!
(2) እውነት ነባራዊ እንጂ አንጻራዊ አይደለም! አንተ ስድስት ብር ቢኖርህ እኔ ዘጠኝ ብር ቢኖረኝ አተያያችን የብሩን መጠን አይለውጥም!
(3) ባይሆን ከዚህ ምሳሌ የምንማረው አንድን ነገር እንዲህ ነው ወይም እንዲያ ነው ከማለታችን በፊት ጉዳዩን አገላብጦ ማየት እንደሚያስፈልግ ነው!
(4) ውሸት ውሸት ነው! እውነትም እውነት ነው! የእንግሊዝኛው ገለጻ "just because you are right, doesn’t mean I am wrong.” ይላል!
በሥነ አመክንዮ ሦስት መሠረታውያን ሕግጋት አሉ! እነዚህ ሕግጋት ለሳይንስ! ልፍልስፍና...ሁለ መሠረቶች ናቸው:-
(ሀ) The law of non-contradiction states that it is not possible for a statement to be true and false at the same time in the exact same manner.
(ለ) the law of the excluded middle says that a statement has to be either true or false.
(ሐ) the law of identity states that each thing is identical with itself.
በዐጭሩ የአመለካከት ("opinion “) መለያየት የእውነት መለያየትን አያሳይም! የሥነ ምግባር መርሖ የሚለው መጽሐፌ ይህን ጉዳይ በስፋት ይሞግታል!