04/04/2021
ኢሰመጉ ሪፖርት እንዳደረገው በአጣዬና አካባቢው 108 ሰወች ተገለዋል!! ዝርዝር ሪፖርቱ እንደሚከተለው ቀርቧል:: ውብሸት ሙላት !!
1. ኤፍራታና ግድም ወረዳ- በኦነግ ሸኔ
◾️አጣዬ -የተገደሉ- 46
◾️አለላ ቀ/ገ/ማ - የተገደሉ - 6
◾️ብርቂቱ ቀ/ገ/ማ- የተገደሉ- 9
◾️ደረሃ ቀ/ገ/ማ - የተገደሉ - 1
◾️ በጥይት የቆሰሉ - 50
◾️ የተቃጠሉ መኖሪያ ቤቶች - 21
◾️የተቃጠሉ ሆቴልና ሱቅ- 9
◾️የተቃጠሉ ሚኒባሶች - 5
◾️የተቃጠሉ ባጃጆች - 2
◾️የተፈናቀሉ ሰዎች - 19,200
2. ማጀቴ- በኦነግ ሸኔ
◾️ የተገደሉ - 2
◾️ በጥይት የቆሰሉ - 53
◾️ የተፈናቀሉ - 111
3. ጀውሃ- በኦነግ ሸኔ
◾️ የተገደሉ - 20
◾️የተቃጠሉ - አንድ ቤተ ክርስቲያንና አንድ ት/ቤት
◾️የተፈናቀሉ - ከ 5,000 በላይ
4. ቀወትና ሸዋሮቢት - በኦነግ ሸኔ
ሸዋሮቢት ከተማ
◾️ የተገደሉ - 16
◾️ በጥይት የቆሰሉ - 24
◾️ የተቃጠሉ መኖሪያ ቤቶች - 15
በቀወት (ሸዋሮቢት ዙሪያ)
◾️የተገደሉ - 8
◾️የተቃጠሉ የገበሬ መኖሪያ ቤቶች - 30
◾️ከሸዋሮቢትና ቀወት የተፈናቀሉ - 16,100
ሌላ ሁለት ቤተ ክርስቲያኖችም ተቃጥለዋል። ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።
~የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ይሄን ያህል ጉዳት ያደረሰ ኦነግ ሸኔ ቡድን ደግፎ ነው በወቅቱ መግለጫ ያወጣው። በዚያ ፍጥነት የአማራ ክልል መንግሥትን ዘልፎና ኦነግ ሸኔን በድርጊቱ እንደለሌበት መግለጫ ማውጣት የሚያመለክተው ከድርጊቱ ጀርባ አብሮ መሳተፍን ነው።
~ ሁለቱ የፓርላማ አባላት ይህን ሁሉ የሽብር ጥቃት የፈፀመ ቡድን ደግፈውና ተከላክለው ጥብቅና ቁመው ይህንን አሳዛኝና አስነዋሪ የሽብር ጥቃት ከለላ ለመስጠት በፓርላማ የተከራከሩት።
~ በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የሚገኙ ወረዳዎች የኮምኒኮሽን ጽ/ቤቶች ይህንን የኦነግ ሸኔ የግዲያና የንብረት ማውደም የሽብር ተግባር በደገፍና ከለላ ለመስጠት በተደጋጋሚ መግለጫ ሲያወጡ የሰነበቱት።
~ በተቀናጀ መልኩ ኦሮሞ አክቲቪስቶች በሐሰት የወሎ ኦሮሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ጥቃት አደረሰ በሚል የተነዛው የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የሚያሳየው ኦነግ ሸኔ፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ አክቲቪስቶቹ፣ ፓርላማ ላይ በሐሰት የተናገሩት አባላት እና በዞኑ የሚገኙ አመራሮችም (ቢያንስ የኮምኒኬሽን ጽ/ቤቶቹ በተደጋጋ ካወጡት መግለጫ አንጻር) አቋም አንጻር ሲታይ በጋራ ፣በተቀናጀና በተናበበ መልኩ አልተፈጸመም ማለት አይቻልም።
ይህ ሁሉ የተፈጸመው አማራ ክልል ውስጥ ነው። በክልሉ ውስጥ የሚኖረው አማራ የክልሉ መንግሥት ጥበቃ ባለማድረጉ የጸጥታ ሁኔታውን በተገቢው መንገድ መረጃ በመሰብሰብ አስቀድሞ ባለመከላከሉ በዚህ መጠን ጥቃትና ጉዳት ከደረሰበት፣ በዚህ መጠን ለሞትና ለመፈናቀል ከተጋለጠ፣ ለአካል መጉደልና ለንብረት ውድመት ሰለባ ከሆነ .... ሌላ ቦታ የሚኖረው አማራ ምን ዓይነት ተስፋ ሊኖረው ይችላል??
የአማራ ክልል መንግሥት አሁንም በፍጥነት ነገር ግን ጥንቃቄ የተሞላበት ተግባራዊ እርምጃ ሊወስድባቸው የሚገባ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ግልጽ ነው!!! ከላይ በተገለጹት አካባቢዎች ሌላ (3ኛ) ዙር ጭፍጨፋ ላለመከሠቱ ምንም ዋስትና የለም።