Afar People's Voice - APV

Afar People's Voice - APV ይህ ፔጅ የአፋርን ህዝብ ታሪክና ባህል፣ ማህበራዊና ፖለቲካን የሚዳስስ እና ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች የሚያቀብል የእርሶ ገፅ ነው።
(8)

06/12/2024

ለሁሉም አስጎብኚ ድርጅቶች።
ወደ ሙርሲ የምታደርጉት ጉዞ ካለ ጥንቃቄ እንድታደርጉ
በጎብኚዎች እና የአስጎብኚ ሰራተኞች ላይ የደረሰ ጥ*ቃት መኖሩ ተረጋግጠዋል።

Via፦ Ethiopian Tourism

06/12/2024

ብልሃተኛዋ ሴት!!🤗
゚viralシfypシ゚viralシalシ ゚viralシ ゚ ゚viralシ2024fyp

06/12/2024

゚viralシfypシ゚viralシalシ

Best Picture
05/12/2024

Best Picture

የሰላም ሚኒስቴር ከአንድ ዓመት እስር ቆይታ በኃላ የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ  ከእስር ተለቀው መኖርያ ቤታቸዉ ገብተዋል።ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል።ትናንት አመሻሹን ከ...
05/12/2024

የሰላም ሚኒስቴር

ከአንድ ዓመት እስር ቆይታ በኃላ የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተለቀው መኖርያ ቤታቸዉ ገብተዋል።

ከቤተሰቦቻቸው ጋርም ተቀላቅለዋል።

ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ይታወሳል።

በኃልም የተወሰዱት ሜክሲኮ
የወንጀል ምርመራ እነደነበር ታውቋል።

ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ስንታየሁ " ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጠየቀ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ 7 ሰዓት ግድም መኖራቸው ቤት ደርሰዋል " ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ በፍርድ ቤት በ20 ሺህ ብር ዋስትና ክሳቸውን ከውጪ መከታተል እንዲችሉ በታዘዘው መሰረት ትናንት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቢለቀቁም ለምን ወደ ሜክሲኮ የወንጀል ምርመራ ማዕከል እንደተወሰዱ ግን ቤተሰብ እንዳልተረዳ ነው የተነገረው፡፡

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

🙏🙏🙏

03/12/2024

ትክክል‼️
-
-
-
-
-
゚viralシ ゚ ゚viralシfypシ゚viralシalシ

መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባትየቅጣት ውሳኔው በፍርድ ቤት ሲገለጽ፤ መስከረም አበራ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ተናግረዋል።በመስከረም አበራ ላ...
25/11/2024

መስከረም አበራ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባት
የቅጣት ውሳኔው በፍርድ ቤት ሲገለጽ፤ መስከረም አበራ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ተናግረዋል።
በመስከረም አበራ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች ችሎት ነው።
ፍርድ ቤቱ መስከረምን ጥፋተኛ ያላት “በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ክስ ነው።
መስከረም ጥፋተኛ የተባለችው በባለቤትነት በምታስተዳደረው ‘ኢትዮ ንቃት’ የዩቱዩብ ገጽ ላይ በተላለፉ ሁለት ፕሮግራሞች ምክንያት ነው።
ከተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮዎች በኋላ ዛሬ ሰኞ ኅዳር 16/2017 ዓ.ም የዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉን ጠበቃ ሄኖክ ገልጸዋል።
ጠበቃ ሄኖክ አክለውም “ይህ ውሳኔ የተላለፈው መስከረም አበራ ቅሬታ አለኝ ብላ ችሎት ባልቀረበችበት ሁኔታ ነው” ብለዋል።
አቶ ሄኖክ “ከዚህ ቀደም ያቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮቹ በአግባቡ ያልታዩልኝ ስለሆነ ከዚህ ችሎት ፍትህ አልጠብቅም፤ እናንተ ተገቢ ነው የምትሉትን ቅጣት ወስኑ፤ ከዚህ በኋላ በችሎት አልገኝም ብላ ገልጻለች ይሄንንም ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አሳውቃለች” ሲሉ የደንበኛቸውን ቅሬታ አስረድተዋል።
(ቢቢሲ)

የአፋር መርከበኞች በቀይ-ባህር 1910-1929
24/11/2024

የአፋር መርከበኞች በቀይ-ባህር 1910-1929

🤔
18/11/2024

🤔

በባጃጅ አሽከርካሪነት የምትተዳደረው እንስት....አበርቷት...👌.......የመንገድ በረከት ወጎችን ጀባ ልበል ብዬ.....ለስራ ጉዳይ ወጥቼ ጭፍራ ላይ ያጋኘኋት ጠንካራዋ እንስት ዚነት ኢብራ...
17/11/2024

በባጃጅ አሽከርካሪነት የምትተዳደረው እንስት....አበርቷት...👌
.......የመንገድ በረከት ወጎችን ጀባ ልበል ብዬ.....ለስራ ጉዳይ ወጥቼ ጭፍራ ላይ ያጋኘኋት ጠንካራዋ እንስት ዚነት ኢብራሂም ትባላለች።

ለሠባት ዓመታት ያህል በሳዑዲ አረቢያ ስትሰራ ቆይታ....ፊቷን ወደ አገር ቤት ከመለሠች በኋላ ደግሞ ባጃጅ በማሽከርገርና አገልግሎት በመሥጠት መተዳደሪያዋ በማድረግ ይዛለች።

በተለይ ሴት እህቶቼ ቆፍጠን ብለው መስራት እና መወጣት ይቻለዋል የምትለው ዚነት በዚህ ስራዋ ጥንካሬን እንዳዳበረች ነው የገለፀችው።

በዚሁ የመንገድ በረከት ጉዞዬ ላይ ያገኘኋት አሸከርካሪ ካንዴም ሁለቴ መጠነኛ ብልሸት አጋጥሟት ስትቆም ፣ለማሰራት ስትፍጨረጨር ጥንካሬዋን ማንበብ ችያለሁ።

ጭፍራ በተሠኘ ከተማ ላለፉት ሶስት ዓመት በዚህ ስራ ላይ ተሠማርታ ያለችው ዚነት የአንድ ልጅ እናት ስትሆን...ጠንክረው ከሰሩ የሚያቅት ነገር የለም. ብላለች።

ሴቶች ከኔ ትንሽ ተሞክሮዬ ቢማሩ ብላኛለች።

ይህቺን ጠንካራ እንስት በሐሣብም በሞራልም በርቺ በሏት.....

Solomon birhanu

 #መምህራን በምገባ መርሐግብር መታቀፋቸውን እንዴት ተመለከታችሁ??እኛጋ የምገባ ፕሮግራም ይቆይና ደመወዝ በሥነሥርዓት ወቅቱን ጠብቆ ይከፈለን የሚል ጩኼት በርክቷል።በሸገር ከተማ አስተዳደር ...
02/11/2024

#መምህራን በምገባ መርሐግብር መታቀፋቸውን እንዴት ተመለከታችሁ??

እኛጋ የምገባ ፕሮግራም ይቆይና ደመወዝ በሥነሥርዓት ወቅቱን ጠብቆ ይከፈለን የሚል ጩኼት በርክቷል።

በሸገር ከተማ አስተዳደር በሁሉም የመንግስት እና ትምህርት ቤቶች በመተግበር ላይ ይገኛል።

በዚህ ፕሮግራም የተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥን ማስወገድ የተቻለ ሲሆን መምህራንም በማስተማር እና በመማር የበለጠ እንዲተጉ አድርጓል ተብላል።

በሸገር ከተማ በሚገኙ 256 ትምህርት ቤቶች የተማሪ እና የመምህራን ምግብ ፕሮግራም እየተካሄደ ሲሆን እስካሁን ለ148,795 ተማሪዎች እና ለ3,707 መምህራን መስጠት ተችሏል።
በተክሌ ቶማ

01/11/2024

ዛሬ በአፋር ክልል አዋሽ ማምሻውን 3:55 ደቂቃ ላይ ተከስቶ ከነበረው አደገኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በተጨማሪ አሁን ከለሊቱ 6:13 ደቂቃ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከስቷል። አላህ ይጠብቀን🙏

መንግሥት ቤት ቢሰጥህ አትደሰትም ነበር?ጨበራ ኮንታ:- ባለቤቴስ? ስድስቱ ልጆቼስ? ፎቅ እንኳ ባገኝ እነርሱን አልተውም:: እዚያው የገጠሩ ማሳደስ ይሻላል:: እዚህ ቤት ባገኝ እንደገና እዚህ...
29/10/2024

መንግሥት ቤት ቢሰጥህ አትደሰትም ነበር?

ጨበራ ኮንታ:- ባለቤቴስ? ስድስቱ ልጆቼስ? ፎቅ እንኳ ባገኝ እነርሱን አልተውም:: እዚያው የገጠሩ ማሳደስ ይሻላል:: እዚህ ቤት ባገኝ እንደገና እዚህ ላገባ? ይህ ደግሞ ቃልኪዳን አለን:: ቤት ሳገኝ እንዴት እክዳታለሁ? ቤተክርስቲያን ገብታ ብታለቅስብኝ እኔም እሞታለሁ:: ቤቱም ቀረ:: እነርሱም ያዝኑብኛል:: እና ቤቱ ምን ጥቅም ይሰጠኛል:: ከባለቤቴና ከልጆቼ የሚነጥለኝን ፎቅ እንኳ አልፈልግም::

ጎባና ኮንታ 🙏

ለአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል፡፡በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ...
27/10/2024

ለአሰልጣኝ አስራት ሃይሌ የሽኝት መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በተጫዋችነትና አሰልጣኝነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለው አስራት ሃይሌ (ጎራዴው) ከትናንት በስቲያ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወቃል፡፡

በዛሬው እለትም ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሽኝት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

አሰልጣኝ አስራት ሃይሌ ውጣ ውረድን አልፎ በርካታ ድልን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት የተቀዳጀ ጠንካራ የስፖርት ሰው የነበረ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ የተለያዩ ክለቦችን በተጫዋችነትና በአሰልጣኝነት በማገልገል በርካታ ዋንጫ አንስቷል።

"የቶምቦላ ሎተሪ እጣ እድለኛ አሸናፊ ብሆንም ምንም አይነት ሽልማት እጄ ላይ አልገባም"አቶ ሸምሱ ተማምአቶ ሸምሱ ተማም በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ነዋሪ ናቸው።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳ...
22/10/2024

"የቶምቦላ ሎተሪ እጣ እድለኛ አሸናፊ ብሆንም ምንም አይነት ሽልማት እጄ ላይ አልገባም"አቶ ሸምሱ ተማም

አቶ ሸምሱ ተማም በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲወጣ ባዘጋጀው የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ የሁለተኛ ዕጣ ዕድለኛ ነኝ። ዕድለኛነቴም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተረጋግጦ ደስታዬን አብስረውኛል በማለት ለዳራሮ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ገልፀዋል፡፡

አቶ ሸምሱ ተማም ከነገ ዛሬ እስከ ምትገኝበት ከተማ እናደርሳለን ቢሉኝም ዕድለኛ የሆንኩት የ1500 ሲ.ሲ የቤት አውቶሞቢል መኪና እጄ ላይ አልደረሰም በማለት ቅሬታቸውን አጋርተውናል፡፡

አቶ ሸምሱ ተማም እድለኛነታቸው ተረጋግጦ አዲስ አበባ የብሔራዊ አስተዳደር ጽ/ቤት ተገኝተው በእጣ የደረሳቸውን የ1500 ሲ.ሲ የቤት ኦቶሞቢል ቁልፍ እጃቸውን አስዘይዘው ፎቶ አስነስተዋቸዋል። ግን ተሽከርካሪው እጄ ላይ አልደረሰም ሲሉ በምሬት ተናግረዋል፡፡

ዳራሮ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ቅሬታቸውን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት

''የቶምቦላ ሎተሪ ዕድለኞች ሽልማታቸውን እየወሰዱ ነው! አቶ ሸምሱ ተማም ይባላሉ ነዋሪነታቸው ዲላ/ወናጎ/ ሲሆን የ1500 ሲ.ሲ የቤት አውቶሞቢል ዕድለኛ በመሆን ሽልማታቸውን ከኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተረክበዋል፡፡" የሚል መረጃ ከተቋሙ ትክክለኛ ማህበራዊ መገናኛ አውታር ከሆነው የፌስቡክ ገጽ (Official page) አገኘን።

ይህን የተቋም ህጋዊ መረጃ መሰረት አድርገን የአቶ ሸምሱን ጥያቄ ያቀረብንላቸው ስማቸውንና ኃላፊነታቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባልደረባ ለዳራሮ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን በሰጡት ምላሽ አቶ ሸምሱ ተማም የቶምቦላ ሎተሪ እጣ የሁለተኛው እጣ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ወደ ተቋሙ መጥተው የኦቶሞቢሏን ቁልፍ ሲረከቡ የሚያሳይ ፎቶ መነሳታቸውንም ተናግረዋል። የመኪና ርክክቡን አስመልክቶም አቶ ሸምሱ በቶምቦላ ሎተሪው የደረሳቸውን ኦቶሞቢል አለመረከባቸውንም መስክረዋል።

እድለኛው በሚገኙበት ከተማ ኦቶሞቢሉን ለማስረከብ መታሰቡን የተናገሩት የመረጃ ምንጫችን ኦቶሞቢሉን እድለኛው እስከሚገኙበት ከተማ ለማጓጓዝ መኪናው እንዳይጎዳና ስም የማዛወር ስራው ለመዘግየቱ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል። ለእድለኛው ንብረታችውን ለማስረከብ ፕሮግራም መያዙንና ኦቴሞቢሉን የፊታችን ዓርብ ወይም ቅዳሜ ወደ ስፍራው ይጓዛል ብለዋል።

በተደጋጋሚ ቃል ተገብቶላቸው ተግባራዊ እንዳልተደረገላቸው የሚገልጹትን የአቶ ሸምሱን ቅሬታ ያቀረብንላቸው የብሔራዊ ሎተሪ የኬሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ምላሽ ሊሰጡን ፈቃደኛ አልሆኑም። በተደጋጋሚ የእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ስልካቸው ባለመነሳቱ ለዳራሮ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ጥያቄ ምላሻቸውን ማካተት አልቻልንም።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ቶምቦላ ሎተሪ ሁለተኛ ዕጣ ዕድለኛ መሆናቸው ከተገለፀውና ፎቶ ብቻ ተነስተው ንብረታቸውን ካልተረከቡት አቶ ሸምሱ ተማም ጋር ያደረግነውን የቪዲዮ ቆይታና የሰነድ ማስረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።

ዘገባው የዳራሮ ሚዲያና ኮምኒኬሽን ነው

ተመልከቱ የአንዳንድ ሰው የኢማን (የእምነት) ጫፍ ይህ በፎቶ የምትመለከቱት ሀሩን ሰኢድ የተባለ ግለሰብ ሲሆን ትላንትና በመርካቶ ሱቁ በእሳት አደጋ ጋይቷል ንብረቱ ወድሟልግን የኢማኑን ጥንካ...
22/10/2024

ተመልከቱ የአንዳንድ ሰው የኢማን (የእምነት) ጫፍ

ይህ በፎቶ የምትመለከቱት ሀሩን ሰኢድ የተባለ ግለሰብ ሲሆን ትላንትና በመርካቶ ሱቁ በእሳት አደጋ ጋይቷል ንብረቱ ወድሟል

ግን የኢማኑን ጥንካሬነት ተመልከቱ
በፈጣሪው ላይ ያለውን እምነት ተመልከቱ

እንዲህ ብሎ ፃፈ👇👇👇.....

አልሀምዱሊላህ!!!

በውሳኔህ ተሳስተህ አታውቅም !!!
ብዙ ሰተኸኝ ነበር ጥቂት ወስደህብኛል
ክብርና ልቅና ላንተ የተገባ ይሁን!!!

አሁንም ቢሆን የጉዳት መጠናችን በውል አልታወቀም ቢሆንም የብዙዎች ወንድሞቼ ንብረት በአጠቃላይ በሚባል መልኩ ወድሟል አላህ ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን የተሻለውን አላህ ይተካልን!!

@ # ሲቀጥል ብዙዎቻችሁ CBE account እየተቀባበላችሁ ልታግዙኝ እየሞከራችሁ ነው!!! በጣም አመሰግናለው !!!

ግን እኔ ከብዙ አላህ ከሰጠኝ ፀጋ በጥቂቱ ስለሆነ የነካኝ ለኔ የምታረጉትን ገቢ ለወንድሞቼ እንድታረጉ በትህትና እጠይቃለው!!! እንዲሁም የኔን የለጠፋችሁትን እንድትሰርዙት በአክብሮት እጠይቃለው!!!!

true love ❤
22/10/2024

true love ❤

Address

London
EC1A

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Afar People's Voice - APV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Nearby media companies


Other Digital creator in London

Show All