ምንጊዜም ኢትዮጵያ- Mengizem Ethiopia

ምንጊዜም ኢትዮጵያ- Mengizem Ethiopia We will promote Ethiopia to the rest of the world!

 #የአሁኗ ኢትዮጵያ !በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ምስዕሉ ሲዘዋወር ተመለከትኩ ... በትላንትናው ዕለት በጉማ አዋርድ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል የነበረዉ ፕሮግራም "ልጅ ማኛ"...
10/06/2023

#የአሁኗ ኢትዮጵያ !
በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ምስዕሉ ሲዘዋወር ተመለከትኩ ...

በትላንትናው ዕለት በጉማ አዋርድ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል የነበረዉ ፕሮግራም "ልጅ ማኛ" በሚል የምትታወቀው ቲክቶከር ባደረገችው ሜካፕ አሁን ላይ #የእስር ማዘዣ ወጥቶባታል !

ሀሳብን በነፃነት መግለፅ እንዴት ይቻል ይሁን ? በሜካፕ ብቻ ወንበር መነቅነቅ ይቻል ይሁን ? በነገራችሁ ላይ ከትላንትናዉ ፕሮግራም በኃላ የጉማ አዋርድ አዘጋጅ የሆነዉ ዮናስ ብርሃነ መዋ
"ልጅቷን አምጡ" በሚል በፀጥታ ኃይሎች ታስሮ እንደሚገኝ እየተነገረ ይገኛል..

19/03/2023

አስቂኝ የኢትዮጵያ ልጆች!!!

11ኛው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአሰላ እየተካሄደ ነው!!
01/02/2023

11ኛው ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአሰላ እየተካሄደ ነው!!

ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ !መልካም የከተራ በዓል !ጎንደር
18/01/2023

ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ !

መልካም የከተራ በዓል !
ጎንደር

ዘዳዊት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከቤተሰቦቹ ጋር
04/01/2023

ዘዳዊት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከቤተሰቦቹ ጋር

ታላቁ የጥበብ ሰው አርፏል!!የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በገጠመው ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል። አርቲስቱ ከ50 ዓመታት በላይ በሙዚቃ ሕይወት የቆየ ...
01/11/2022

ታላቁ የጥበብ ሰው አርፏል!!

የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ በገጠመው ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

አርቲስቱ ከ50 ዓመታት በላይ በሙዚቃ ሕይወት የቆየ ሲሆን ከ260 በላይ ሙዚቃዎችን ተጫውቷል።

በግንቦት ወር በ1940 ዓ.ም የተወለደው አሊ በተወለደበት ድሬዳዋ ከተማ በስሙ ፓርክ ተሰይሞለታል።

ከድሬዳዋ እና ከጅማ ዩኒቨርስቲዎች የክብር ዶክትሬት የተቀበለው አሊ ቢራ፤ ለዓመታት ባስደመጣቸው ነጻነትና ፍቅርን በሚሰብኩ ሙዚቃዎቹ ይታወቃል።

አርቲስት አሊ ቢራ በ1954 ዓ.ም የተመሰረተውን የመጀመሪያው የኦሮምኛ ቋንቋ የኪነት-ቡድን “አፍረን ቀሎ”ን በመቀላቀል ነበር የሙዚቃ ስራውን የጀመረው።

ድምጻዊ አሊ ከኦሮምኛ በተጨማሪ፣ በሱማሊኛ፣ በአፋርኛ፡ በሐረሪ፣ በአማርኛና በሱዳን ቋንቋዎች በርካታ ዘፈኖችን መጫወት ችሏል።

ነፍስ ይማር እንላለን!!

ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ  ምን ምን ነገሮችን ይዟል ?በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገ...
04/10/2022

ኢትዮጵያ ዛሬ የምታስመርቀው የሳይንስ ሙዚየም በውስጡ ምን ምን ነገሮችን ይዟል ?

በመዲናችን አዲስ አበባ አስደናቂ የቀለበት ቅርጽ ያለው ህንጻ እና ማራኪ የጉልላት ቅርጽ ያለው ተደርጎ የተገነባው ማዕከል በአይነቱ አዲስ የሆነው የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም በዛሬው እለት ይመረቃል ::

ሙዚየሙ በ7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በኪነ-ህንጻ ንድፍ ውስጥ ያካተተው ክብ ቅርጽም በማያቋርጥ እድገት ውስጥ ያለን እድገትና የሰው ልጆችን ጥበብ የሚያመለክት ነው።

በተጓዳኝም ኢትዮጵያ በአስገራሚ ፍጥነት በማደግ ላይ ካለው ቴክኖሎጂ ጋር ለመጣመር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይም ነው።

የስነ ጥበብና የሳይንስ ሙዚየሙን አስደናቂ የሚያደርገው ምንድነው ?

👉 ሁለት ግዙፍ ህንጻዎችን በተንጣለለ ስፍራ ላይ ቢያሳርፍም 80 በመቶ የሚሆነው ክፍሉ ከ4ሺህ በላይ በሆኑ ሀገር በቀል ዛፎች፣ እጽዋትና ባሸበረቁ አበቦች የተሸፈነ ስፍራ በመሆኑ አረንጓዴነቱ ጎልቶ ይታያል።

👉 ሙዚየሙ በጥንቃቄ የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያዎች በተጨማሪ በዙሪያው ካሉ የከተማችን ፓርኮች ጋር የሚያገናኘው ውብ የእግረኛ መንገዶች ያሉት ነው።

👉 የአትክልት ስፍራዎቹ ጎብኚዎች አረፍ ብለው ንፋስ የሚቀበሉባቸው ምቹ መቀመጫዎችን እንዲሁም በጥበብ ስራዎች የሚዝናኑባቸውን የስነ ጥበብና የመዝናኛ ቦታዎችን የያዙ ናቸው።

👉 ትልቁ ህንጻ ከ15ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፍ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

👉 ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ በሆነ መንገድ ሃይል ከሚያመነጩ የውሃ ግድቦቻችን እንዲሁም በጣሪያው ላይ ከተገጠሙ የጸሀይ ብርሃን ሰብሳቢ መሣሪያዎች የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ አቅርቦት የሚያገኘው ይህ ሙዚየም ተፈጥሮአዊ የሃይል ማስተላለፊያዎችንና ሃይል ቆጣቢ የተፈጥሮ ብርሃንን የሚጠቀም ነው።

ይህ የስነጥበብና የሳይንስ ሙዚየም ትላንታችንን፣ ዛሬያችንን እና ነገአችንን በአንድ ላይ አሰናስኖ ሳይንስን ጥበባዊ በሆነ መንገድ፤ ጥበብን ደግሞ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያስቃኝ በመሆኑ አስደማሚ ተሞክሮዎችና አዳዲስ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ነው።
(FM ADDIS 97.1)

እባክዎ ሁሌም ቢሆን በማስተዋል እና በእርጋታ ያሽከርክሩ
03/10/2022

እባክዎ ሁሌም ቢሆን በማስተዋል እና በእርጋታ ያሽከርክሩ

የማዲንጎ እህት ትግስት አፈወርቅ እያለቀሰች ያስተላለፈችው መልዕክት "ወንድሜን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ንጉስ በክብር ቀበረልኝ። የክብር ሞት ነው የሞተው። የኢትዮጵያ ሕዝብም ብድሩን መልሶለታ...
02/10/2022

የማዲንጎ እህት ትግስት አፈወርቅ እያለቀሰች ያስተላለፈችው መልዕክት

"ወንድሜን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ንጉስ በክብር ቀበረልኝ። የክብር ሞት ነው የሞተው። የኢትዮጵያ ሕዝብም ብድሩን መልሶለታል። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ። ኢትዮጵያን ሰላም ያድርጋት።
እኔ አንድ የሚያመኝ ነገር ወንድሜ እንደንጉስ ተከብሮ ተቀብሮ እንዲህ አንጀቴ የተቆረጠ በማያውቀው የሚያልቀው ህዝብ፣ ደጉ ባላገሩ፣ ሚስኪኑ ህዝብ ሞትስ?
ሞት ሊቆም ይገባል። እባካችሁ ኢትዮጵያ ላይ ሞት ይቁም አምላክን እግዚአብሔርን እንፍራ። ወደፍቅር እንምጣ።"

ያለም ዘርፍ የኋላው የለንደን ማራቶንን አሸነፈች።
02/10/2022

ያለም ዘርፍ የኋላው የለንደን ማራቶንን አሸነፈች።

01/10/2022

Cultural Night in Bahir Dar!

Happy Irreechaa to all Ethiopians celebrating today and tomorrow.

10,000 ሲኒ 35 ሜትር ጠረንጴዛ 100 ቡና አፋይዎች 100 ኪሎ ግራም ቡና
01/10/2022

10,000 ሲኒ
35 ሜትር ጠረንጴዛ
100 ቡና አፋይዎች
100 ኪሎ ግራም ቡና

የግሸን ደብረ ከርቤ የንግሥ በዓል እየተከበረ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።በዘንድሮው ክብረ-በዓ...
01/10/2022

የግሸን ደብረ ከርቤ የንግሥ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።

በዘንድሮው ክብረ-በዓል 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ጎብኚዎች መታደማቸውን በደቡብ ወሎ ዞን የአምባሰል ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ገልጿል፡፡

የንግስ በዓሉን የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እያከበሩ ነው ተብሏል፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች በዓሉ ላይ ለመታደም የመጡት ምዕመናን÷በዓሉን ያለምንም ችግር እያከበሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ህዝበ ክርስቲያኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት በቅንጅት የሚያከናውኑት ተግባር ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የሚመጡ ጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ የቅርስ ማስቀመጫ ሙዚየም መስከረም 17 ቀን 2012 ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ከአምባሰል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

“ፊደል ተሳስተሃል” ብሎ ተማሪውን የገደለው መምህርአዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ME) በሀገረ ሕንድ “ፊደል (ስፔሊንግ) ተሳስተሃል” በሚል ምክንያት መምህር ተማሪውን መግደሉ ተሰማ...
27/09/2022

“ፊደል ተሳስተሃል” ብሎ ተማሪውን የገደለው መምህር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ME) በሀገረ ሕንድ “ፊደል (ስፔሊንግ) ተሳስተሃል” በሚል ምክንያት መምህር ተማሪውን መግደሉ ተሰማ፡፡

የሕንድ ፖሊስ÷ “ሶሻል (social) የሚለውን ቃል ፊደላት በትክክል አልፃፍክም” በሚል ታዳጊ ተማሪውን በመደብደብ ገድሏል የተባለውን መምህር በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡

የ15 ዓመቱ ታዳጊ ኒኪል ዶህሪ በዚህ ወር መጀመሪያ ፈተና ላይ “social” የሚለውን ቃል ሲጽፍ ፊደላትን በመሳሳቱ÷ ራሱን ስቶ እስከሚወድቅ ድረስ በአስተማሪው ድብደባ እንደተፈጸመበት የሟች አባት ለፖሊስ ተናግረዋል፡፡

ታዳጊው በመምህሩ በደረሰበት ድብደባ በሰሜናዊ ዑታር ፕራዴሽ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል በህክምና ላይ እያለ ሕይወቱ ማለፉ ተዘግቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ተከሳሹ ከአካባቢው መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል ሲል ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል፡፡

የሕንድ ፖሊስ እንደገለጸው ተጠርጣሪው ለጊዜ ከአካባቢው ቢሰወርም በቅርቡ በቁጥጥር መዋሉ እንደማይቀር ገልጿል፡፡

ክስተቱ በሀገሪቱ ተቃውሞ ብሎም ሁከት እና ብጥብጥ ማስነሳቱ ነው የተጠቆመው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- share

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ?- ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው።- ማዲንጎ አፈወርቅ ያ...
27/09/2022



ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ማንነበር ?

- ማዲንጎ የተወለደው ጎንደር አዘዞ ሲሆን ልክ በ3 ወሩ ወላጆቹ ደብረ ታቦር መግባታቸውን ተከትሎ በደ/ታቦር ነው ያደገው።

- ማዲንጎ አፈወርቅ ያደገው በጦር ቤት ውስጥ ነው፤ እናት እና አባቱ "ተገኔ" /የኔ ጠበቃ/ ነበር የሚሉት፤ ወላጆቹ ያወጡለት ስም "ተገኔ" ነው። ማዲንጎ የሚለውን ስም ያገኘው በወታደር ቤት ውስጥ እየሰራ እያለ ነው፤ ከዛ በኃላ መጠሪያው ሆኖ ቀጥሏል።

- በልጅነቱ የሙዚቃ ፍቅር ያደረገበት ማዲንጎ ከደብረ ታቦር ወደ አዘዞ በተመለሰበት ወቅት በ7ኛ ክፍለ ጦር ካምፕ ውስጥ በ603ኛ ኮር ውስጥ ያለ የሙዚቃ ቡድን ልምምድ ሲያደርግ በመግባት ዘፈን እንደሚችል በመግለፅ እድል እንዲሰጠው ይጠይቃል፤በኃላም እድል ተሰጥቶ የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ ከተጫወተ በኃላ አድናቆት በማግኘቱ ተቀባይነት አግኝቶ በዛው ሊቀጥል ችሏል።

- ማዲንጎ ከጦሩ ከወጣ በኃላ በ1982 ዓ/ም አካባቢ ገና በ12 ዓመቱ በባህር ዳር የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ አንድም ድምፃዊ የመሆን ህልሙን መስመር ያስያዘበት በሌላ በኩል ገቢ በማግኘት እራሱንና ቤተሰቦቹን ማገዝ የቻለበትን ሁኔታ መፍጠር ችሏል።

- ማዲንጎ ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኃላ በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች የተለያዩ አንጋፋ ድምፃዊያንን ስራዎች ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን በኃላም የራሱን ስራዎች (ነጠላና የአልበም ስራዎች) ለአድናቂዎቹ አቅርቧል።

- ማዲንጎን በስራዎቹ የሚያውቁት ወዳጆቹ ዜማ በመያዝ ችሎታ፣ ሙዚቃን አሳምሮ በመጫወትና የአድናቂዎቹን ቀልብ በመሳብ የተካነ በማህበራዊ ህይወቱም ተግባቢ፣ ቅንና ተጫዋች እንደሆነ ይመሰክሩለታል።

(ከጨዋታ እንግዳ ፕሮግራም/ከቅርብ ወዳጆቹ የተገኘ መረጃ)

ተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ።  ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል። በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦ...
27/09/2022

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አረፈ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል። በድምጻዊው ህልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፡ ለአድናቂዎቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ይመኛል።

ነብስ ይማር

13/08/2022

የአቡበከር ናስር ጎል 🔥

የዋልያዎቹ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር በማሜሎዲ ሰንዳውንስ መለያ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል ።

አቡበከር በሀገሪቱ ትልቁ የደርቢ ጨዋታ ካይዘር ቺፍስ ላይ አራተኛውን ግብ ተቀይሮ በመግባት አስቆጥሯል ።

የአቡበከር ናስር ጎል ከላይ ተያይዟል ።

Video Credit: SuperSport

የዲባባ ቤተሰብ ልዩ ናችሁ የኢትዮጵያ ባለውለታዎች
29/07/2022

የዲባባ ቤተሰብ ልዩ ናችሁ የኢትዮጵያ ባለውለታዎች

የSrilanka ዜጎች መንግስትን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ሰልፉ እየሰፋ መጥቶ የፕሬዝዳንቱን መኖርያ ቤት ከተቆጣጠሩ በኋላ እንደምታዩት እስኪበቃቸው እየተዝናኑበት ነው 🤣 እኛም ከዚህ እንማር ...
10/07/2022

የSrilanka ዜጎች መንግስትን ለመቃወም ሰልፍ ወጥተው ሰልፉ እየሰፋ መጥቶ የፕሬዝዳንቱን መኖርያ ቤት ከተቆጣጠሩ በኋላ እንደምታዩት እስኪበቃቸው እየተዝናኑበት ነው 🤣

እኛም ከዚህ እንማር አመፅ በተነሳ ቁጥር ሆቴሎችን እና መኖርያ ቤቶችን ከማቃጠል እንዲህ ዘና ማለቱ የተሻለ ነው። ❤

ከቅዳሜው ጭፍጨፋ የተረፉት ዜጎች ድጋፍ ይሻሉ! በስልክ ለማሰባሰብ የቻልኩት መረጃ እንደሚጠቁመው ከዘግናኝ ግድያዎቹ በተጨማሪ በርካቶች ቤታቸው ከነንብረታቸው ወድሞባቸዋል፣ የሚበላ እንኳን የሌ...
24/06/2022

ከቅዳሜው ጭፍጨፋ የተረፉት ዜጎች ድጋፍ ይሻሉ!

በስልክ ለማሰባሰብ የቻልኩት መረጃ እንደሚጠቁመው ከዘግናኝ ግድያዎቹ በተጨማሪ በርካቶች ቤታቸው ከነንብረታቸው ወድሞባቸዋል፣ የሚበላ እንኳን የሌላቸው ብዙዎች ናቸው። በአካባቢው ደግሞ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ነው።

ትናንት በአንድ አይሱዙ 30 ኩንታል ስንዴ አካባቢው ቢደርስም ለ10ሺህ ገደማ ህዝብ በቂ እንዳልሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች አሳውቀውኛል። በተጨማሪም ቤታቸው ለወደመባቸው ድንኳኖች፣ ብርድ ልብሶች እና ፍራሾች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ኧረ ጎበዝ፣ ስንት መከራ አይተው አሁን ደግሞ በርሀብ፣ በመጠለያ እጦት እና በእርዛት ሲሰቃዩ ማየት የለብንም።

የመንግስት አካላት እባካችሁ፣ እባካችሁ ትኩረት። እኛ ደግሞ የቻልነውን በአይነት እና በገንዘብ ማሰባሰብ እንድንችል በዚህ ዙርያ የምትሰሩ ወይም ልምዱ ያላችሁ ግለሰቦችም ሆነ ተቋማት አሳውቁን።

Via Elias Meseret

  Fake Image Alert የሀሰተኛ ምስል ማሳሰቢያ! ‘gemechu geleta’ በሚል ስም የተከፈተና ከ27,600 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (...
24/06/2022

Fake Image Alert

የሀሰተኛ ምስል ማሳሰቢያ!

‘gemechu geleta’ በሚል ስም የተከፈተና ከ27,600 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ባለቤት አምለሰት ሙጬ ክላሽንኮቭ በመባል የሚታወቀን የጦር መሳሪያ ይዛ ይታያል ያለውን ምስል አጋርቶ ነበር።

ይህ ትዊት በርካታ መውደዶችን (like) እና መጋራት (retweet) ያገኘ ሲሆን ቁጥራቸው በዛ ያለ ሰዎችም አስተያየት ሰጥተውበታል።

ሆኖም ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ያጋራው ፎቶ የተነካካ (doctored) መሆኑን አረጋግጧል።

ትክክለኛው ፎቶ አመለሰት ሙጬ የልጇን እጅ ስትስም የሚያሳይ ሲሆን እ.አ.አ ሚያዚያ 6/2019 ዓ.ም ከ893 ሺህ በላይ ተከታዮች ባሉት የፌስቡክ ገጿ የተጋራ ነበር፣ ፎቶውን ኮራ ኢሜጅ እንዳነሳው የሚገልጽ መልዕክትም አብሮ ይታያል።

አሳሳች፣ ከአውድ ውጭ የሚቀርቡ እና የተነካኩ ምስሎችን ባለማጋራት ለሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መቀነስ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

የቴዲ አፍሮ ( Teddy Afro )   #ናዕት (እያመመው 2) የተሰኘው አዲሱ ነጠላ ዜማ በዓለማችን ላይ በዩትዩብ በመታየት ላይ ካሉት የሙዚቃ ስራዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ በርካታ ተመልካች ...
24/06/2022

የቴዲ አፍሮ ( Teddy Afro ) #ናዕት (እያመመው 2) የተሰኘው አዲሱ ነጠላ ዜማ በዓለማችን ላይ በዩትዩብ በመታየት ላይ ካሉት የሙዚቃ ስራዎች በ24 ሰዓታት ውስጥ በርካታ ተመልካች በማግኘት በ52ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሙዚቃው ከተቀቀ ጀምሮ እስካሁን ከ2 ሚሊዮን 800ሺህ በላይ ተመልካች አግኝቷል። የሌላኛው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሙዚቀኛ ዘዊኬንድ (አቤል ተስፋዬ) Save your tears የተሰኘው ስራ በ54ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
https://m.youtube.com/watch?v=1hMVeENjVew

ቂምን ሻረውና ወይ ፍቅርን አንግሰው
ሁለት ሆኖ አያውቅም አንድ ነው አንድ ሰው
ከሐገርም ይሰፋል ያ የፍቅር ገዳም
መጠሪያው ሰው እንጂ ዘር አይደለም አዳም

Via:- Petros Ashenafi Kebede

 ? በምትሰጡት comment ላይ ከፍተኛ like ያገኘ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው የ200 ብር የስልክ ካርድ ተሸላሚ ይሆናል፡፡ ለማሸነፍ 24 ሰአት ጊዜ አላችሁ።ማሳሰቢያ፦ የማህበራዊ ...
22/06/2022

?

በምትሰጡት comment ላይ ከፍተኛ like ያገኘ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው የ200 ብር የስልክ ካርድ ተሸላሚ ይሆናል፡፡ ለማሸነፍ 24 ሰአት ጊዜ አላችሁ።

ማሳሰቢያ፦ የማህበራዊ ሚዲያ ስነ ምግባር ደንብ የሚፃረሩ comments ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።

ከየትኛውም ዘርና ሃይማኖት ሳትወግን ስለ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ት ብቻና ስለ ፍቅር አንድነት በመዝፈን ኢትዮጵያን ባንተ ልክ ያከበራት የለም ! እናመሰግናለን! Teddy Afro
21/06/2022

ከየትኛውም ዘርና ሃይማኖት ሳትወግን ስለ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዊ ነ ት ብቻና ስለ ፍቅር አንድነት በመዝፈን ኢትዮጵያን ባንተ ልክ ያከበራት የለም ! እናመሰግናለን! Teddy Afro

21/06/2022

"ዶፍ ቢዘንብ እሳት፣ ሀገሬን ላልረሳት
ቃል አለኝ ኖሬ፣ ሞቼም ልክሳት"

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በአዲሱ ነጠላ ዜማ

https://youtu.be/1hMVeENjVew

ናዕት: [ነገር ስም] ሳይቦካ ተለውሶ በቂጣነት የሚጋገር ማለት ሲሆን እስራኤላውያን በግብፅ ሳሉ በሚያዝያ ወር የፋሲካ በዐልን በቂጣ እንጀራ ስላከበሩ በዐለ ናዕት ተባለ።ምንጭ: የአማርኛ መዝ...
21/06/2022

ናዕት: [ነገር ስም] ሳይቦካ ተለውሶ በቂጣነት የሚጋገር ማለት ሲሆን እስራኤላውያን በግብፅ ሳሉ በሚያዝያ ወር የፋሲካ በዐልን በቂጣ እንጀራ ስላከበሩ በዐለ ናዕት ተባለ።

ምንጭ: የአማርኛ መዝገበ ቃላት ከሣቴ ብርሃን ተሰማ
Via: Addisu F.

የአደም ልጆች የተከበሩ ናቸው:: ክብረቱ ፣ ዘሩ ፣ ብሔሩ ፣ ኃይማኖቱ ፣ ቀለሙ ፣ ፆታ ፣ ቁመት ፣ ክብደትና ውፍረት ከግምት ሳይገቡ ነው:: የአደም ልጅ በመሆናቸው ብቻ የሚጎናጸፉት መብት ...
21/06/2022

የአደም ልጆች የተከበሩ ናቸው:: ክብረቱ ፣ ዘሩ ፣ ብሔሩ ፣ ኃይማኖቱ ፣ ቀለሙ ፣ ፆታ ፣ ቁመት ፣ ክብደትና ውፍረት ከግምት ሳይገቡ ነው:: የአደም ልጅ በመሆናቸው ብቻ የሚጎናጸፉት መብት ነው:: ሰው ሰውን ሊገድል ቀርቶ እራሱንም እንዲገድል መብት አልተሰጠውም:: ክልክል ነው:: አላህ እስኪገድለው ነው የሚጠብቀው !

"... እስካሁን በደረሰን መረጃ በቶሌ ወረዳ ከ400 በላይ ህዝብ አልቋል። ነገሩን የጠና የሚያደርገው ደግሞ ሠዎች ከቤታቸው ሸሽተው መስጅድ በተደበቁበት መጨፍጨፋቸው ነው። ይሄ ጉዳይ ለመንግስት ብቻ ተሠጥቶ የሚቀመጥ አይደለም፣ ህዝቡም ሊገደው ይገባል... ሞት ትክክል የሚሆነው የፈጠረን አላህ ፍጡሩን ሲወስድ ብቻ ነው..."

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ዛሬ ካስላለፉት መግለጫ የተወሰደ !

"የእንትና ግዜ የት ነበርክ" 🤔አንድ በጣም የሚያሳስበኝ ጉዳይ ቢኖር፣ ኦርቶዶክስ ተጠቃ ስትል፣ ሙስሊሙ "የእኛ" ጊዜ የት ነበርክ ይልሀል፤ መስጅድ ተቃጠለ ስትል፣ ቤተ ክርስቲያን የባሰ ግፍ...
20/06/2022

"የእንትና ግዜ የት ነበርክ" 🤔

አንድ በጣም የሚያሳስበኝ ጉዳይ ቢኖር፣ ኦርቶዶክስ ተጠቃ ስትል፣ ሙስሊሙ "የእኛ" ጊዜ የት ነበርክ ይልሀል፤ መስጅድ ተቃጠለ ስትል፣ ቤተ ክርስቲያን የባሰ ግፍ ደርሶባታል ትባላለህ፤ ኦሮሚያ ላይ ሰው ሞተ ስትል፣ አማራ ላይ ወንጀል ሲሰራ የት ነበርክ ትባላለህ፤ አማራ ላይ እልቂት ደርሷል ስትል፤ የኦሮሚያውን የረሳን መሰለህ ወይ ትባላለህ። የሆነ የህመም ፉክክር ያለብን ነው የምንመስለው - የእኔ ህመም ከሌላው ህመም ይበልጥ የከፋ ነው የሚል አይነት። ግፍ በበዛበት ሀገር፣ ሰዎች የትኛው ሐዘን ውስጣቸው ጠልቆ እንደሚገባ ልንወስንላቸው አይገባም፣ አንችልምም። ሌሎች ሲያዝኑ እንደ "ግብዝ" መቁጠር፣ እኛን የተሻልን የመብት ተቆርቋሪዎች አያደርገንም። ይልቁኑ የአንዱ ህመም የሁላችንም ህመም እንዲሆን ከተፈለገ፣ በደል በደረሰ ጊዜ፣ የእንትን ጊዜ የት ነበርክ ብሎ ሌላ ሰው ላይ ጣት ከመቀሰር በፊት፣ ተጠቂው ማንም ይሁን ማን፣ እኔ ራሴ በደሉን እያወገዝኩ መሆኔን መፈተሽ መልካም ነው። ምናልባት ያኔ በሐዘን ጊዜ ሂሳብ ለማወራረድ መሞከሩ ይቆምና አብረን ግፍን ማውገዝና ማዘን እንጀምራለን። ሀዘን ሐዘን ነው፤ በደል በደል ነው። የማንም ሐዘን ከማንም ሊበልጥም፣ ሊያንስም አይችልም። ማስተዋሉን ይስጠን። መልካም ሰንበት ለሁላችን ይሁን።

Alemayehu Gemeda

የሰው ልጅ የክብር ጉዞ የኔና ያንተ ክብር ነው! የሰው ልጅ የውርደት እሽቁልቁሊት የኔና ያንተ ውርደት ነው። ከመኪና እያወረዱ የረሸኑን እኔና አንተን ነው፤  ረሻኞችም እኛው ነን።በወለጋ የተ...
19/06/2022

የሰው ልጅ የክብር ጉዞ የኔና ያንተ ክብር ነው! የሰው ልጅ የውርደት እሽቁልቁሊት የኔና ያንተ ውርደት ነው። ከመኪና እያወረዱ የረሸኑን እኔና አንተን ነው፤ ረሻኞችም እኛው ነን።
በወለጋ የተጨፈጨፍነው እኔና አንተ ነን። ጨፍጫፊዎቹም እኛው ነን።

የትም ቦታ የሚደርስ ኢ-ሰብአዊነት ከሰውነት ተርታ የሚያስወጣን እኛኑ ነው። ከሰውነት ክብር መውረድ ማለት ወደ እንስሳነት ደረጃ ዝቅ ማለት ነው። እንስሳነት ሲያይል በንፁሃን ደም የሚፎክርና ነውሩ ክብሩ የሆነ ሰው በማህበረሰብ ውስጥ ይበቅላል።

ወንድሜ፣
"ማን ተገደለ?" ብለህ አትጠይቅ፤
የሞትነው እኔና አንተ ነን።
"ማን ገደለ?" ብለህም አትጠይቅ፤ የጨፈጨፍነው እኔና አንተ ነን።
"ማን ያስቁመው?" ካልከኝ ራሱን "ሰው" ብሎ የሚጠራ ማንኛውም ሰው ሁሉ እልሃለሁ።
ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች...

አላህ ሆይ! በቃ በለን! የእውነት "ሰው" እንሆን ዘንድ እርዳን።

አስታዝ በድሩ ሁሴን

ጠሚ ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ካስተዋቁት አስከፊ ልማዶች አንዱ፣ የንጹሀን ዜጎችን ግድያ ራሳቸው ለምደው ሌሎች ኢትዮጵያውያንም እንዲለማመዱት ማድረግ ነው። ከዚህ አሳዛኝ አገራዊ ድብርት (de...
19/06/2022

ጠሚ ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ካስተዋቁት አስከፊ ልማዶች አንዱ፣ የንጹሀን ዜጎችን ግድያ ራሳቸው ለምደው ሌሎች ኢትዮጵያውያንም እንዲለማመዱት ማድረግ ነው። ከዚህ አሳዛኝ አገራዊ ድብርት (depression) ውስጥ በቀላሉ የምንወጣ አይመስለኝም።

Via Alemayehu Gemeda

እንዲህ አይነት ታጋይ አይተንም ሰምተንም አናቅም። ጭራቁ አይኤስ ጨፍጫፊውቦኮሃራም፣ የፊሊብኑ ዳርሽታም እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ ሲፈፅሙ አለም አሸባሪ ብሎ ስም ሰቶ እየተዋጋቸው ነው። ፖለቲካዊ...
19/06/2022

እንዲህ አይነት ታጋይ አይተንም ሰምተንም አናቅም። ጭራቁ አይኤስ ጨፍጫፊው
ቦኮሃራም፣ የፊሊብኑ ዳርሽታም እንዲህ አይነት ጭፍጨፋ ሲፈፅሙ አለም አሸባሪ ብሎ ስም ሰቶ እየተዋጋቸው ነው። ፖለቲካዊ ትርጉሙን እንለፈውና። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ምንም የማያቅን አንድን ገበሬ
በዚች ዳስ ቤት ውስጥ እየኖረ በጁ ቆፍሮ የሚበላን በአመት አንድ ጊዜ ልብሱን መቀየር የማይችል በአካባቢው የፖለቲካ ውክልና የለለውን፣ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማነው፣ አፈ ጉባኤው ማነው፣ ኢታማዦር ሹሙ ማነው ስላተ የሚናገርልህ የህዝብ እንደራሲህ ማነው ቢባል ማንም የለኝም የሚልን ህዝብ እንዴት በቁም ትጨፈጭፈዋለሁ።

የሚዋጋህ የመንግስት ወታደር እንጅ አርሶ የሚባለ ገበሬ አይደለም። እንዴት አንተ ላይ አንድ ጥይት መተኮ የማይችል የቲም ገበሬ ገለህ ታጋይና አታጋይ ልትሆን ትችላለህ።

አምኖህ የሚኖርን ሴትና ልጅ ይዞ ለአንጀቱ አርሶ የሚጎርስን ገበሬ ወንድ ሆነህ የጥይትህን ባሩድን አውቶማቲክ ላይ አድርገህ ስተኩስተበት እንዴት አስቻለህ። የሮሂጋ ሙስሊሞች ሲጨፈጨፉ
ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተብሎ በግልፅ የአሜሪካ ምክርቤት አውግዞታል። የዳርፉርን ጥቁሮች ሲገደሉ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ተብሎ በስሙ ጠሮቶ የሰላም አስከባሪ ተልኮለታል።

የወለጋው ግን ስም አልባ ፍጅት ደምፅ አልባ የዘር ማጥፋት ተግባር ነው። ነገ ሞት አለብኝ የሚል ሰው አማኝ ነው ብሎ የሚያምን ሰው ይሄንን ዘግናኝ ጭፍጨፋ በስሙ ጠርቶ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ወስዶ አረመኔውን ሰው በላ ቡድን ልክ እንዲያስገባው በድጋሚ መጠየቅ አለብን።
መውጫ የሀይማኖት ተቋማቶች በግፍ ስለተገደሉት ንፁሀኖች በግልፅ ማውገዝና ብሔራዊ የሀዘን ቀን ልታውጁላቸው ይገባሎ። የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች የማህበረሰብ አንቂ አክቲቪስቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለተጎዱት ህዝቦች ድምፃቸሁን ማሰማት አለባችሁ። የሰው ነፍ እንዲህ እንደ ደሮ ጭንቅላት ማነስ የለበትም። የወሎ ሰው በፍጹም ይሄ አይገባውም። አምስት አመት መሉ እንዲህ አይነት የለየለት ጭፍጨፋ በላዩ ላይ ሲደረግ መኖሩን መታወስ አለበት።

የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ200 በላይ መድረሱን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ሱሌማን አብደላ

በደቡብ ወሎ ዞኖን ያሉ ቀበሌዎች ሀዘን ተቀምጠዋል። ዛሬ ላይ በየቀበሌው ውስጥ የሀዘን ድንኳን ተጥሎ ዘመድ  አልቅሶና ቆፍሮ ያልቀበረው ወገኑ ሞት እየከነከነው ማልቀስና መቆጨት ይዟል።በስራ ...
19/06/2022

በደቡብ ወሎ ዞኖን ያሉ ቀበሌዎች ሀዘን ተቀምጠዋል። ዛሬ ላይ በየቀበሌው ውስጥ የሀዘን ድንኳን ተጥሎ ዘመድ አልቅሶና ቆፍሮ ያልቀበረው ወገኑ ሞት እየከነከነው ማልቀስና መቆጨት ይዟል።

በስራ ምክኒያት የማቀው ጎደኛየ ብቻ ሦስት የወንድሞቹን ልጆች ተረድቶ በስልክ ደውየ አፅናንቻለሁ። በነሱ ቀበሌ ብቻ 24 ሰው በግፍ ተጨፍጭፈዋል። ከወሎ ተሰደው ወለጋ በሰፈሩ ኖሪዎች ላይ ብቻ ባነጣጠረ ጥቃት ከ80 በላይ ሰዎች በግፍ መጨፍጨፋቸውን ነው የነገሩኝ። ትናትና ከመኪና ላይ እያወረዱ እየሳቁ በባሩድ የሰውን ልጅ ሂዎት በግፍ ሲጨፈጭፉ አይቼ እጅግ በጣም አሳዝኖኝና ትልቅ የስነ ልቦና ተፅዕኖ አሳድሮብኝ አምሽቶ፣ ከዚህ አስከፊ ምስል ትዝታ ሳንላቀቅ ወለጋ ላይ በግፍ የተጨፈጨፉ የዘመድና የጎደኛ ቤተሰቦችን ሮይታና ለቅሶ ሰማን።

ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ። የሞቱንም አላህ ጀነትን ይወፍቃቸው።

መንግስት በየ ቀበሌው በነፃ አውጭ ስም የተደራጁ ነብሰ በላዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠል አለበት። ጠንካራ የሆነ መንግስታዊ መዋቅርና ጠንካራ የሆነ የኢንተለጀንስ አደረጃጀቶችን አዋቅሮ የጅምላ ግድያ የሚፈፀምባቸው አካባቢዎች ሰላማዊ ቀጠና ማድረግ አለበት።

Via ሱሌማን አብደላ

አትሌት ዳዊት ስዩም... ጀግኒት! ማምሻውን በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ዳዊት ስዩም አንደኛ በመሆን ስታጠናቅቅ ሀዊ ፈይሳ ሁለተኛ፣ ፋንቱ ወርቁ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ ይ...
18/06/2022

አትሌት ዳዊት ስዩም... ጀግኒት!

ማምሻውን በሴቶች 5 ሺህ ሜትር የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ ዳዊት ስዩም አንደኛ በመሆን ስታጠናቅቅ ሀዊ ፈይሳ ሁለተኛ፣ ፋንቱ ወርቁ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀዋል።

እንኳን ቀናችሁ!

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ፈረንሳይ ላይ በተደረገው 5 ሺህ ሜትር ውድድር አሸናፊ ሆኗል::
18/06/2022

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ፈረንሳይ ላይ በተደረገው 5 ሺህ ሜትር ውድድር አሸናፊ ሆኗል::

ግብፅ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኟን አሰናበተችአዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2014 | የግብፅ እግር ኳስ ማህበር የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ኢሀብ ጋላልን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ።ግብጽ የዛሬ ሳምን...
16/06/2022

ግብፅ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኟን አሰናበተች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2014 | የግብፅ እግር ኳስ ማህበር የብሄራዊ ቡድኑን አሰልጣኝ ኢሀብ ጋላልን ከአሰልጣኝነት አሰናበተ።

ግብጽ የዛሬ ሳምንት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታዋን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 ለ 0 መሸነፏ ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈም በወዳጅነት ጨዋታ ከትናንት በስትያ በደቡብ ኮሪያ የ4 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዳለች።

ከደቂቃዎች በፊት ይፋ በሆነው መረጃ መሰረት ደግሞ የሀገሪቱ የእግር ኳስ ማኅበር የብሔራዊ ቡድኑን አሠልጣኝ ከመንበሩ ማንሳቱን ይጠቁማል።

የ54 ዓመቱ አሠልጣኝ ቡድኑን ከተረከቡ 2 ወር ያልሞላቸው ቢሆንም በኢትዮጵያ የደረሰባቸው ሽንፈት መንበራቸው እንዲንገጫገጭ ማድረጉን ሶከር ኢትዮጵያ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

"Hailesilassie"  newly launched Kenyan Expressway interchange ❤❤ Thank You Kenya!!
16/06/2022

"Hailesilassie" newly launched Kenyan Expressway interchange ❤❤ Thank You Kenya!!

ድምፃዊ ዳዊት ነጋ (ዘዊደሮ) በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።ለወዳጅ ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ መጽናናትን ይስጥልን ።ነብስ ይማር !
12/06/2022

ድምፃዊ ዳዊት ነጋ (ዘዊደሮ) በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ለወዳጅ ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ መጽናናትን ይስጥልን ።

ነብስ ይማር !

የኢትዮጵያችን እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በጣም ጥሩ ተጫውታችሁ በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ:: እኛም ደስ ብሎናል::Congratulations to our Ethiopian national fo...
09/06/2022

የኢትዮጵያችን እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች በጣም ጥሩ ተጫውታችሁ በማሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ:: እኛም ደስ ብሎናል::
Congratulations to our Ethiopian national football team for wining todays match!

Ethiopia 🇪🇹 is on the lead now!
09/06/2022

Ethiopia 🇪🇹 is on the lead now!

ተረመረመችግብፅ በኢትዮጵያ ተረመረመች፤ ተሸነፈች!🇪🇹ኢትዮጵያ 2-0 ግብፅ🇪🇬⚽⚽ ጎል   | ትናንት፣ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አጥቂው ሽመልስ በቀለ እንዲህ ብለው ነበር👉”የሳላ መኖር እና ...
09/06/2022

ተረመረመች

ግብፅ በኢትዮጵያ ተረመረመች፤ ተሸነፈች!

🇪🇹ኢትዮጵያ 2-0 ግብፅ🇪🇬
⚽⚽ ጎል

| ትናንት፣ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና አጥቂው ሽመልስ በቀለ እንዲህ ብለው ነበር

👉”የሳላ መኖር እና አለመኖር የእኛ እቅድ ላይ ምንም ተፅዕኖ አያደርግም” ውበቱ አባተ

👉”ከምድባችን ለማለፍ በምናደርገው ጉዞ የነገው ጨዋታ ወሳኝ ነው” ውበቱ አባተ

👉”እኔም ሆነ ጓደኞቼ የትኛውንም ቡድን አግዝፈን አናይም” ሽመልስ በቀለ

ፈረኦኖቹን በዋልያዎቹ ተረመረሙ።

የጀግኖቹን የክብር ሰላምታ ከማላዊ ይድረስዎ😘

ይህንን ሕዝባዊ፣ አገራዊ ድል ሼር በማድረግ ለኢትዮጵያ ልጆች (ምስጋና እና ክብር) ይግለጡ 😘

Address

Victoria Station
London
SW1V1JU

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ምንጊዜም ኢትዮጵያ- Mengizem Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ምንጊዜም ኢትዮጵያ- Mengizem Ethiopia:

Share

Nearby media companies


Other News & Media Websites in London

Show All