Nejashi Social ኢስላሚዊ ድህረ ገፅ

Nejashi Social ኢስላሚዊ ድህረ ገፅ የደጋጎቹ ስፍራ

"እኛም የአላህ፣ወደሱ ተመላሾችም ነን"💔😭ለኛ ከየትኛውም ሰው ሞት በላይ የሷሊሆች፣የዓሪፎች፣የወሊዮች ህይወት ማለፍ በከባዱ ያሰጋናል፤ካለንበት ተጨባጭ ሁናቴ ላይ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደ...
14/08/2024

"እኛም የአላህ፣ወደሱ ተመላሾችም ነን"
💔😭
ለኛ ከየትኛውም ሰው ሞት በላይ የሷሊሆች፣የዓሪፎች፣የወሊዮች ህይወት ማለፍ በከባዱ ያሰጋናል፤ካለንበት ተጨባጭ ሁናቴ ላይ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆንብናል፤ከነምናምናችን እስካሁን የተዘገየነው በደጋግ የአላህ ባሪያዎች በረከትና ፀሎት መሆኑ ለማንም የማይሰወር እውነታ ነው!!!
የአንድ ዓሊም ወደ ቀጣዩ ህይወት መሸጋገር በቁም ለሞተው ድርብ ሀዘን ነው፤በመኖራቸው ሰበብ የደፈኑትን ክፍተት፣የመለሱትን መቅሰፍት፣ያቆዩትን ሰላም በየጊዜው በሄዱ ቁጥር ያስተዋለ ይታዘበዋል!!!
#አላህ ይኹነን 🤲
_____
ሰዪድ ሚቅባስ ዐለይኩም ረሐማቱላ፟ህ 💔

  _የጁን   መካ ሐረም ላይ ያየ ለልጃቸው ይደውልአሰላሙ አለይኩም ስሜ መዲና አሕመድ እባላለሁ በሐሙስ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት በመካ ሀረም ወስጥ አባቴ ሸይኽ አህመድ መሐመድ ያሲን(ሸይኽ አህመ...
10/03/2024

_የጁን
መካ ሐረም ላይ ያየ ለልጃቸው ይደውል
አሰላሙ አለይኩም ስሜ መዲና አሕመድ እባላለሁ በሐሙስ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት በመካ ሀረም ወስጥ አባቴ ሸይኽ አህመድ መሐመድ ያሲን(ሸይኽ አህመድ የጁ) ጠፍተዉብኛል ።

አባቴን ያየ ሠዉ ወይም በሌላ የፌስ ቡክ ገጵ ላይ ያየ በዚህ ስልክ ቁጥር ደዉለዉ ይተባበሩኝ
0534054286 መዲና አሕመድ
ወይም 0505479565 ልጅ ።

  😥የልህቀት ማዕከል የኾነው ዳና ሸይኽ የኾኑት ጀማሉዲን አንይ አራተኛ ትውልድ ሸይኽ ሹዐይብ ሸይኽ ሑሰይን ሸይኽ ዐብዱሰመድ ኢብኑ ሸይኽ ጀማሉዲን አንይ በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ተ...
05/03/2024

😥
የልህቀት ማዕከል የኾነው ዳና ሸይኽ የኾኑት ጀማሉዲን አንይ አራተኛ ትውልድ ሸይኽ ሹዐይብ ሸይኽ ሑሰይን ሸይኽ ዐብዱሰመድ ኢብኑ ሸይኽ ጀማሉዲን አንይ በትላንትናው ዕለት ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደክፍለ ሐገር እየተጓዙ ሳለ በደረሰባቸው የተሽከርካሪ አደጋ ወደአኼራ ተሻግረዋል ።

እኛ ከአሏህ ነን ። ወደእርሱም ተመላሾች ነን ።

04/03/2024

👌
በዑስታዝ አብዱል ሀሚድ part 1

  19-12-2015ይሄንን አይቶ የማይደሰት ?
25/08/2023




19-12-2015
ይሄንን አይቶ የማይደሰት ?

"እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን"በደወይ ሃረዋ ወረዳ የቡራቅሳ ሐሪማ ተቀዳሚ መውላና ሸይኽ ሑሰይን ዓብዱሏህ ከ30 አመታት በላይ ዒልም በማቅራትም ሆነ የተለያዩ ዒባዳዎችን ዘክሮ...
20/08/2023

"እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን"
በደወይ ሃረዋ ወረዳ የቡራቅሳ ሐሪማ ተቀዳሚ መውላና ሸይኽ ሑሰይን ዓብዱሏህ ከ30 አመታት በላይ ዒልም በማቅራትም ሆነ የተለያዩ ዒባዳዎችን ዘክሮ በማስዘከር ኡማውን ሲያገለግሉ የነበሩ ታላቅ ሸይኽ እነሆ ወደማይቀረው አለም አኺራ ተሻገሩ።
إنا لله وإنا إليه راجعون
لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُقْبَضَ الْعِلْمُ
"የትንሳኤ ቀን አትደርስም ዒልም እስካልተነሳ ድረስ" የዒልም ምንጮቹ ደግሞ ኡለሞች ናቸውና ሁላችንም ዱዓ እናድርግ አሏህ ቀብራቸውን ሰፊ መኖሪያቸውን ጀነት ከነብያቶች፤ ከወልያቶች እና ከሸሂዶች ጋር ያድርገው። ሁላችንም ፋቲሓ እንቅራላችው።
*****

 #መውሊድ  እንደቀጠለ ነው #ነቀምት ፈትህ መስጂድ በዚህ መልኩ ጀምረዋል
18/08/2023

#መውሊድ

እንደቀጠለ ነው

#ነቀምት ፈትህ መስጂድ በዚህ መልኩ ጀምረዋል

 #አሁን | የመውሊዱ ብስራት በወርሃ ሷፈር አንደኛው ቀን
18/08/2023

#አሁን | የመውሊዱ ብስራት
በወርሃ ሷፈር አንደኛው ቀን

 #አስቸኳይ ❗️❗️❗️ እባካችሁ Share በማድረግ ተባበሩን ዛሬ 24 አካባቢ አንድ ባለ ራይድ(ፈረስ) ሹፌር የእጅ ቦርሳዬን ይዞብኝ ጠፍቷል ።በቦርሳዬ ዉስጥ በገንዘብ 130ሺ ብር በተጨማሪ...
04/08/2023

#አስቸኳይ ❗️❗️❗️
እባካችሁ Share በማድረግ ተባበሩን
ዛሬ 24 አካባቢ አንድ ባለ ራይድ(ፈረስ) ሹፌር የእጅ ቦርሳዬን ይዞብኝ ጠፍቷል ።
በቦርሳዬ ዉስጥ በገንዘብ 130ሺ ብር በተጨማሪ ለቅርብ ቀን በረራ ቪዛ የተመታበት ፓስፖርቴን ጨምሮ መንጃ ፈቃዴንና መታወቂያዬ በቦርሳዉ ዉስጥ ይገኝበታል ።

እና እባካችሁ ሌባዉ ብሩን ከወሰደ በኋላ ፓስፖርቱን በመንገድ ሊጥለዉ ይችላልና ካያችሁ ወይንም ካገኛችሁ አሳዉቁኝ 🤲

ለጥቆማ
0912470406
0929365029

  😥===============ራህማ ሀሩና ምስኪን የ19 ዓመት ወጣት ናት። ያለ እጅና እግር ተወልዳለች። ምክንያቱ ባልታወቀና ባልተለመደ ሁኔታ እጅና እግሮቿ ሰውነቷ ላይ አልታዩም። ከዛ ይልቅ...
20/07/2023

😥
===============
ራህማ ሀሩና ምስኪን የ19 ዓመት ወጣት ናት። ያለ እጅና እግር ተወልዳለች። ምክንያቱ ባልታወቀና ባልተለመደ ሁኔታ እጅና እግሮቿ ሰውነቷ ላይ አልታዩም። ከዛ ይልቅ ተከታታይ የሆነ ከባድ ህመምን እያስተናገደች ነው። የ19 ዓመቷ ወጣት በካኖ፣ ናይጄሪያ ህይወቷን እየገፋች ትገኛለች።

ራህማ ህይወቷን በሙሉ ከምትመለከቱት ፕላስቲክ መዘፍዘፊያ ውጪ ወጥታ ኖራ አታውቅም። ታዲያ በዚህ ሁሉ ህመምና ስቃይ ውስጥ ሆናብሩህና ደስተኛ ናት። ጌታችንን ደጋግማ " #አልሀምዱሊላህ" እያለች ታመሰግናለች።

እኛስ ጌታችንን ላለማመስገን ምክንያት ይኖረን ይሆን?😭😭😭
#አልሀምዱሊላህ!

وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

20/07/2023

የይቅርታ ሚዛን በሸይኽ ዓብዱልዐዚዝ ሙሀመድ

የተከበረችው የመልእክተኛው እና የሷሂቦቻቸው ጉዞ.....ሒጅሪያ 👉👉(ከ መከተል ሙከረማህ እስከ መድነቱል ሙነወራህ)ጦለዓል በድሩ ዓለይና የተባለለት ኑር ጨረቃ ዛቱ ለመዲና ነዋሪዎች ብቻ አይደ...
19/07/2023

የተከበረችው የመልእክተኛው እና የሷሂቦቻቸው ጉዞ.....
ሒጅሪያ 👉👉(ከ መከተል ሙከረማህ እስከ መድነቱል ሙነወራህ)

ጦለዓል በድሩ ዓለይና የተባለለት ኑር ጨረቃ ዛቱ ለመዲና ነዋሪዎች ብቻ አይደለም የወጣው። ለዓለሙ ቢገለጥ ይበቃል። ወቀመሩላሂ፣ ሸምሱ ሸምሱላሂ፣ ኑሩ ኑሪላሂ! ምድር ምጥ በተያዘችበት፣ በቀትር በጨለመችበት ኑር ሆኖ መጣና ከውኑን አበራው! ሲራጀን ሙኒር!
ያ ፊቱ ከጨረቃ የሚያበራው የሁለት ሐገር ነጋሴ ወደ መዲና ዘለቀ። ሰማይ እና መሬቱን በብርሃን ሞልቶ ደመቀ። በመዲና ያንን ክስተት ያስተዋለ የአስር ዓመት ልጅ "መዲና በሙሉ ብርሃን ተሞልታ ዋለች" ሲል ተናገረ። ከዓይኖቻቸው ይልቅ ልቦቻቸው ተመለከቱ። በሩህ ሰለሉ። ውስጠታቸው ያንን ውበት አስተዋለ። ባላሰቡት ባልተዘጋጁበት የድንገቴ "ጦለዓ" እያሉ ተቀኙ። ወጣት አዛውንቱ፣ ሴቱ ወንዱ ከቴምሩ ዛፍ እኩል እየተወዘወዘ አዜመለት። ያንን "የቁድሲያ" ብርሃን ተመልክተው ሁሉም ሰለሙ። قد جأكم من الله نور እንዳለው ብርሃኑ ፈነጠቀ። በመካ ሐረም ተረግዘው በመዲና ሐረም ተምጠው እንደተወለዱ ሆነ። ኑሩ ጀለጀላሉሁ ከመዲና ሰዎች ዓይን እና ልብ ላይ የአጝያሩን ሒጃብ ገልጦ የአቅማሩን አንዋር አፈሰሰባቸው። ተመልክተው እንዲጠግቡ አወጀበባቸው። አይተው እንዲረኩ ፈቀደላቸው። አስተውለው እንዲብሰከሰኩ ወሰነባቸው።

ጀማላው እንደ ጦር ተወርውሮ በእያንዳንዱ ቀልብ ላይ ተሰካ። ያማ ሶሀብይ
رآيت الهلال ووجه النبي وكان هلالين عند النظر فلولا التورد في الوجنتين وما لاح لي سواد من الشعار لكنت اظن الهلال وجه النبي ووجه اللنبي القمر
እያለ የፈይዱን ቡን አፈላው። ደንግጦ ኖሯል። በስካር ብዛት ጥቁሩ ፀጉሩ ሊነጣ ደረሰ። ዓይኑ እየተጥበረበረ ሁለት ጨረቃ ያያል። እንዲያው ነቢ ባያዝኑለትማ ኖሮ ዓይኑ በነቢ ኑር ተይዞ ይቀር ነበረ። ሐድረተል ጀላላው ገለጥ ያለ ጊዜ ለነፍስ ፋታ አይሰጥም። ወጀላሉላሂ፣ ወጀማሉላሂ፣ ወከማሉላሂ፣ ወሒጃቡላሂ አሏቸው‘ኮ አቦ። በገላጣዋ የፀሀይ ብርሃን ውስጥ ሩሖች ያንን የጨረቃ ብርሀን ያስተውሉ ዘንድ አላህ ልዩ ተአምር አድርጎ ሠራቸው። ሙሐመድዩን ኑራኒዩን የፈጠራቸው ጊዜ ኑሩ ተወርውሮ ይህቺን ከውን ደበሰቃት። ለዛም "ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃን መጣችሁ" ተሰኙ። ዓይኑ የተገለጠለት ሰው እየሰለለ እስከ ሩሑ ይዘልቅበታል ያን የጀማል ኑር። ሰይድ ዑመር ኑሩ ተንቧልቆባቸው ነበረ። ያንን የተቅዋ ኑር ይዘው "ጦለዓ" ያሰኘውን፣ ነብዬ ከሲዲቁ ጋር የሃብሉላህን ገመድ አጥብቀው ያሰሩበትን፣ "ዓልይም በቦታው ተኛለት ሊሞት" ያስባለውን የሒጅራ ቀን ይዘው የኢስላምን ቀን መቁጠሪያ አድርገው ቀመቀሙት። ከቃፍ እስከ ቃፍ ሙስሊሙ በዚህ የኑር ቁጥር ይቆጥራል። ያ ኑር መዲና የዘለቀበት ቀን የሰው ልጅ ሕይወት የተቀየረበት፣ የሙስሊም ሐገራት አመራር የተቃናበት፣ የኢስላም ጁንድ የተበራታበት ቀን ሆነ። ያ ብርሃን ልብን እና ሰውነትን፣ ህግን እና አስተዳደርን አዳረሰ። ቤት እና ቤተ መንግስት፣ መስጂድ እና ገበያን አጣጥሞ አፀና። የትልቁ ሠው ስደት በፈትሕ፣ ሀዘኑ በሳቅ ነው የተደመደመው። ለኛም የጭንቅ መፍፈረጃ የኸይራቱ ሁላ መከፈቻ ዓመት ያድርግልን። ቀልባችንም ዳኢም ወደ መዲና ተጓዥ ይሁንልን። አሚን

እንኳን አደረሰን!💚💚💚

  🙏 👌50 ፖኪስታን ጀለብያ እና ኮፎያ ኒዛም ፋሽን ዲዛይን ለመቄዶንያ አባቶችና ወንድሞች በስጦታ አበርክተናል   በገነንዘብ ሲተመን 2000 ሽ የሚሆንም ነውኒዛሙ ጃሚኡድ ዲዛይንለአባ 50 ...
27/06/2023

🙏 👌
50 ፖኪስታን ጀለብያ እና ኮፎያ ኒዛም ፋሽን ዲዛይን ለመቄዶንያ አባቶችና ወንድሞች በስጦታ አበርክተናል
በገነንዘብ ሲተመን 2000 ሽ የሚሆንም ነው
ኒዛሙ ጃሚኡድ ዲዛይን
ለአባ 50 ፖኪስታን ጀለብያ ሰርቸ ወስጀ ጀባሁና ዱዓ ተቀበልኩኝ ከዛም መቄዶንያ ውስጥ ያሉ ሰወች ሙስሊሞቹ የሡና እና የመስገጃ ልብስ ክርስቲያኖቹ በባአላቸው እለት የሚለብሱት ልብስ እንደሚያስፈልጋቸው ተረድቻለሁና
ለጊዜው ዒድ አረፋን በተመለከተ 50ውን ሰተን ለወደፊት ሁሉንም ለማልበስ ህዝቡን እንጣራለን
ከዛም እኔ ለጊዜው የምወጣባት ሀጃ አለብኝ ብለው ሀጃቸውን ነገረው ፈገግ አስባሉኝና ወኪል ሰጡኝ
ወኪሎች
ሸህ አህመድ አወሉ አደም በዳኔ ኢማም
ሸህ አህመድ የሱፍ
ሸህ አሊን ሰጡኝ ከዛም ቀጠሮ ደርሶ ሁለቱ በሀጃ ምክኒያት ሲቀሩ ሸህ አህመድ አወሉጋ መቄዶንያ ሄደን

በአባ (ሙፍቲህ)ን የውክልና ንግግር ሸህ አህመድ በመናገር የኒዛም ዲዛይንን ስጦታ አደረስን
መቄዶንያን እንዘይር ዱዓ እንቀበል

ሳውዲ 🇸🇦❤️በዚህ ዓመት ከዓለም የተሰባሰቡ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የእስልምናን እምነት ተከታዮችሁሉም አንድ አይነት (ነጭ) ልብስ ለብሰውሀጅ ለማድረግ በአንድ ላይ ተሰብሰብዋል አላህ ...
26/06/2023

ሳውዲ 🇸🇦❤️

በዚህ ዓመት ከዓለም የተሰባሰቡ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የእስልምናን እምነት ተከታዮች

ሁሉም አንድ አይነት (ነጭ) ልብስ ለብሰው

ሀጅ ለማድረግ በአንድ ላይ ተሰብሰብዋል

አላህ ሀጃቸውን ይቀበላቸው❤️🙏

2.5 ሚሊዮን ህዝብ

ሸይኽ ሙሀመድ ረታ ይባላሉ፤ የሚኖሩት በዳና ሀሪማ አቅራቢያ ነው። እንደ እርሳቸው አቅማቸው ደከም ያሉ ባልተቤት ያለቻቸው ሲሆን የሁለታቸውን ኑሮ ለመደጎም ሲሉ የሰዎችን እርዳታ ሲጠይቁ የሚያ...
23/06/2023

ሸይኽ ሙሀመድ ረታ ይባላሉ፤ የሚኖሩት በዳና ሀሪማ አቅራቢያ ነው።

እንደ እርሳቸው አቅማቸው ደከም ያሉ ባልተቤት ያለቻቸው ሲሆን የሁለታቸውን ኑሮ ለመደጎም ሲሉ የሰዎችን እርዳታ ሲጠይቁ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቆ ብዙዎች አይተነው አዝነናል።

ሀራ የሚገኘው ወንድም Abdi Abdi የተለቀቀውን ቪዲዮ ተመልክቶ መረጃውን ና የተወሰነም ብንደግፋቸው በሚል የተነሳውን ሀሳብ ለመደገፍ በሚል የባንክ አካውታቸውን ልኮልናል።

አባት ናቸው 💔
ከታች በተቀመጠው አካውንት የቻላችሁትን ያክል በማስገባት የኸይር ስራው አካል እንድትሆኑ ጋብዣችኋለሁ።

1000 497 555 087

RReyan ReyanRReyan Reyan

አላህ የጀነት ያርጋቸው  😭😭😭🇺🇸 በአሜሪካ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለሰርግ ስነስርዓት ሲሰናዱ በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ::😭በሰሜን አሜሪካ ሚኒሶታ የ...
19/06/2023

አላህ የጀነት ያርጋቸው 😭😭😭

🇺🇸

በአሜሪካ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ለሰርግ ስነስርዓት ሲሰናዱ በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ::😭

በሰሜን አሜሪካ ሚኒሶታ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አምስት ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ባሳለፍነዉ አርብ በመኪና አደጋ ህይወታቸዉ ማለፉ ተሰምቷል።

ኢትዮጵያዊያኑ ቅዳሜ ለሚካሄድዉ የሰርግ ስነስርዓት ቁሳቁሶችን ሸምተዉ ወደ መኖሪያቸው ሲመለሱ አደጋዉ ማጋጠሙ ተዘግቧል።

* ሁለት የ 20 እና
* ሁለት የ 19 አመት ወጣቶች
* እንዲሁም አንድ የ 17 አመት ታዳጊ ህይወታቸዉን በአደጋው ማጣታቸዉን ብስራት ራዲዮ በአሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰምቷል።

በመኪና አደጋዉ ከሌላ መስመር በከፍተኛ ፍጥነት ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር በተከሰተ ግጭት ህይወታቸዉ አልፏል።

አሽከርካሪዉ አደጋዉን ካደረሰ በኋላ ከመኪናዉ በመዉጣት ሮጦ ለማምለጥ ሞክሯል።

በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ጥቆማ መሰረት ግለሰቡን የሚኒያፖሊስ የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር አዉለዉታል ተብሏል።

በተደረገለት ምርመራም ግለሰቡ አልኮልና አደንዛዥ እፅ ተጠቅሞ ሲያሽከረክር እንደነበረ ተረጋግጧል።

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሶማሌ ተወላጆች በከፍተኛ ሀዘን ዉስጥ መሆናቸዉንም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ማህበረሰቡም ለተጎጂ ቤተሰቦች እስካሁን 300 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ማሰባሰቡም ተገልጿል።

Via ዳጉ_ጆርናል

የኛ አባት 😭በአዲስ አበባ ፖሊሶች የተደበደቡት ጋሽ ዲኖ ጋሽ ዲኖ :- የሙስሊሞ ኮፍያ ስላደረኩኝ ነው እንደዛ የተደበደብኩትጀርባዬ ና ወገባዬ ጋር ተጎድቻለው* ቅጥቅጥ ነው አሉኝ* ልጆቼ ህክ...
13/06/2023

የኛ አባት 😭

በአዲስ አበባ ፖሊሶች የተደበደቡት ጋሽ ዲኖ

ጋሽ ዲኖ :- የሙስሊሞ ኮፍያ ስላደረኩኝ ነው እንደዛ የተደበደብኩት

ጀርባዬ ና ወገባዬ ጋር ተጎድቻለው

* ቅጥቅጥ ነው አሉኝ

* ልጆቼ ህክምናም በደንብ አልታየውም

* ህክምና በደንብ መታያት እፍልጋለው

ጋሽ ዲኖን ለመደገፍ ለምትፈልጉ

ንግድ ባንክ አካውንት

* 1000502116383

ስልክ

*00251923121637

ስራም አቁሜለው

ለሸሂድ ቤተሰቦች አማናውን አድርሰናል🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀በሁለተኛ ጁመዓ መስጅዴን አታፍርሱብኝ በማለታቸው ብቻ በፀጥታ አካላት የተሰዉ ሶስት ወንድሞቻችን ኢብራሂም ደንበል፣ አንዋር ሱሩር ፣ ...
11/06/2023

ለሸሂድ ቤተሰቦች አማናውን አድርሰናል
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

በሁለተኛ ጁመዓ መስጅዴን አታፍርሱብኝ በማለታቸው ብቻ በፀጥታ አካላት የተሰዉ ሶስት ወንድሞቻችን ኢብራሂም ደንበል፣ አንዋር ሱሩር ፣ ዙበይር ሙደሲር እና በመጀመሪያ ጁመዓ በጥይት ሆድ እቃውን ተመቶ የተሰዋው ጀሚል ሪድዋን በድምሩ ለአራቱ የመስጅድ ሹሀዳዎች በኮልፌ መካነ መቃብር በተገኙ ምዕመናን 245,154 ብር ተሰብስቧል።

ለአራቱ የመስጅድ ሹሀዳዎች የተሰበሰበውን ብር ከሶስት ቀናት በፊት ከኡስታዝ ናስር (አወሊያ) ጋር በመሆን ቤት ለቤት በመሄድ አድርሰናል።

✨ ለኢብራሂም ደንበል (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰብ (አየር ጤና) አሳዳጊው ለሆነችው እህታችን ኑሪት 61,288.50 ብር አስረክበናል።

✨ ለዙበይር ሙደሲር (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰብ (ሎሚ ሜዳ ) ለወላጅ አባቱ ሙደሲር 61,288.50 ብር አድርሰናል።

✨ለጀሚል ሪድዋን (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰብ (7ተኛ ወረድ ብሎ) ለወላጅ እናቱ ሳዲያ ሙስጠፋ 61,288.50 ብር ሰጥተናል።

✨አንዋር ሱሩር (አላህ ከሸሂዶች፣ከነብያቶች፣ እና ከደጋጎች ባሮቹ ተርታ ይመድብህ) ቤተሰቡን በመዘየር እናቱን በመጠየቅ ለወንድሙ ጀሚል 61,288.50 ብር አድርሰናል።

በሁለቱ ቀን ጉዞ ከኡስታዝ ናስር (አወሊያ) ጋር አራቱም ቤት በመዘየር ያደረስን ሲሆን ቤተሰቦች መዘየርና ማገዝ ከጎናቸው መቆም መስጅዴን አታፍርሱብኝ የምንል ሁላ ድርሻ ነው።

ለመስጅዶቻችን ክብር ለተሰዉ ነፍሶች የአላህ ሰላምና እዝነት ምህረት ይስፈን!

Address

Belfast

Telephone

+251949494749

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nejashi Social ኢስላሚዊ ድህረ ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Nejashi Social ኢስላሚዊ ድህረ ገፅ:

Videos

Share