አዲስ መዝናኛ

አዲስ መዝናኛ ሰላም በዓለም አቀፍ ዙርያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ሁሉ ኢት ቴሌግራም ይቀላቀሉ https://t.me/joinchat/iux6B4HDpgg5NGI8
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ሰላም ፈቅር ጤና አፈር ለሚበላው ጉልበት ስቀን ተጫውተን እንኑር
(15)

ብዙ አቅም ያለው ደፋርና በራሱ ዘይቤ የሚኖር ልጅ ነበረ ። ነፍሱን ይማርልን ጌታቸው 😭🙏ባቡጂ
25/08/2024

ብዙ አቅም ያለው ደፋርና በራሱ ዘይቤ የሚኖር ልጅ ነበረ ። ነፍሱን ይማርልን ጌታቸው 😭🙏ባቡጂ

ኦ እግዝዮኦ ይህ ወንጀል ሳይሆን ይህ ግፍ ሳይሆን ኦ እግዚዮኦ 😭😭😭😭ጭካኔው ጭካኔው ሰቅጣጭ ነው ።
18/08/2024

ኦ እግዝዮኦ ይህ ወንጀል ሳይሆን ይህ ግፍ ሳይሆን ኦ እግዚዮኦ
😭😭😭😭ጭካኔው ጭካኔው ሰቅጣጭ ነው ።

ስለምናከብርሽ አለመቻልሽን መናገር ፈራን ‼️አስደስተሽን ስለኖርሽ ስታሳዝኚን ለመተቸት አልፈጠንም‼️ግን ከሀገር አትበልጪምና...ጎበዝ ሯጭ እንጂ ጎበዝ መሪ አለመሆንሽን አይተናል‼️የምትመሪው...
13/08/2024

ስለምናከብርሽ አለመቻልሽን መናገር ፈራን ‼️

አስደስተሽን ስለኖርሽ ስታሳዝኚን ለመተቸት አልፈጠንም‼️

ግን ከሀገር አትበልጪምና...

ጎበዝ ሯጭ እንጂ ጎበዝ መሪ አለመሆንሽን አይተናል‼️

የምትመሪው ፌዴሬሽን ከዘረኝነት አልፎ በተራ ፆታዊ ጉዳዮች ተተብትቧል‼️

ከአትሌቶች አመራረጥ ጀምሮ የሠራሻቸው ስህተቶች ብዙ ናቸው ‼️

እንደ ታሪካዊ አትሌትነትሽ አትሌቶችን ማበረታታት ሲያሸንፉ መሣቅ ሲሸነፉ ማልቀስ ያምርብሻል። መሪነቱን ግን ተይው አልቻልሽበትም ‼️
TesfaGNeda
💚💛❤

ሶሥቱ እንቁ ህፃናት ዓይናቸዉ ማየት ቻለእልልልልልልል!!! 🙏🙏በዕለተ ሀምሌ 19/2016 ማየት እንደቻሉ እናታቸው ተናግራለች ህፃናቱ እና ጀግናዋ እናታቸዉ ትዕግስት ካሳ ቀፀላ የበኩላችሁን አ...
31/07/2024

ሶሥቱ እንቁ ህፃናት ዓይናቸዉ ማየት ቻለ
እልልልልልልል!!! 🙏🙏

በዕለተ ሀምሌ 19/2016 ማየት እንደቻሉ እናታቸው ተናግራለች

ህፃናቱ እና ጀግናዋ እናታቸዉ ትዕግስት ካሳ ቀፀላ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ ብለዋል።

እልልልልልልል 🙏

የህወሀት ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል  ከሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ ቃለምልልሱ የተጀመረው ‹‹ሁለት አመት እየሞላው ያለው የሰላም ስምም...
16/07/2024

የህወሀት ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከሬዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡

ቃለምልልሱ የተጀመረው ‹‹ሁለት አመት እየሞላው ያለው የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ምን ይመስላል?›› በሚል ነበር፡፡ ደብረፅዮን ሲመልሱ ‹‹አዎ ስምምነቱ ከተፈፀመ ሁለት አመት እየሞላው ቢሆንም አፈፃፀሙ ግን ዘግይቷል፡፡›› በማለት ጀምረዋል፡፡

ሲቀጥሉም ‹‹መጀመሪያ አካባቢ ጥሩ መሻሻሎች ነበሩ፡፡ የመንግስት ስራዎች ማለትም ቴሌኮሚኒኬሽን፣ ኤሌክሪክ ትራንስፖርትና የመንግስት ፈንድ መልሶ እንዲጀመር ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉም ሰው ደስተኛ ነበር፡፡ ቢያንስ አንድ እርምጃ ወደፊት ለመሄድ ችለናል፡፡ ዋናው ነገር ደግሞ ሌላ የተኩስ ድምፅ አልተሰማም፡፡

በእርግጥ በሁሉም የትግራይ ክፍል ሰላም ባይኖርም አብዛኛው መሬታችን ግን በመንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛል፡፡ ሌላ ውጊያ፣ ሌላ ግድያ፣ ሌላ ውድመትና ሌላ ቦምብ ፍንዳታ አለመኖሩ በእርግጥም ጥሩ ተብሎ የሚወሰድ ነበር›› ብለዋል፡፡

ዶክተር ደብረፅዮን ጨምረውም ‹‹ይሁንና እነዚህ መሻሻሎች ወደኋላ እየተቀዛቀዙ መጡ፡፡ ትልቁ ችግር የጄኖሳይድ ፈፃሚዎች በትግራይ ውስጥ መኖራቸው ነው፡፡ ለቀው አልወጡም፡፡ በፕሪቶሪያ በተደረገው ስምምነትና ከወራት በኋላ በናይሮቢ በተፈፀመው ውል መሰረት የከባድ መሳሪያ ትጥቅ መፍታት ተደርጎ እንደተጠናቀቀ ወታደሮችም ለቀው እንደሚወጡ እቅድ ነበር፡፡ ቀጥሎ ተፈናቃዮች እንደሚመለሱና ከዚያም ትክክለኛው ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚመሰረት ሁሉ ታቅዶ ነበር፡፡›› በማለት አስረድተዋል፡፡

የወታደሮቹ ከትግራይ መልቀቅና የተፈናቃዮች መመለስ ባለፈው አመት መከናወን እንደነበረበት ጠቅሰውም ከተያዘለት እቅድ አንድ አመት እንዳለፈው አስረድተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም የትግራይ ስቃይ አሁንም መቀጠሉን ገልፀው በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ያላቸው ስሜት የተደበላለቀ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ ለዶክተር ደብረፅዮን በቀጣይነት የቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹የስምምነቱ አፈፃፀም ረጅም ጊዜ ሊወስድ የቻለው ለምን ይመስልዎታል፡፡ አንዳንዶች የፖለቲካ ቁርጠኝነት ስለሌለ ነው ይላሉ›› የሚል ነበር፡፡

ሲመልሱም ‹‹በትክክል፡፡ ምክንያቱም ስምምነቱ በግለፅ እንዳስቀመጠው አብዛኛው ሀላፊነት የተጣለው በፌዴራል መንግስቱ ላይ ነው፡፡ የኤርትራና የአማራ ሀይሎችን ማስወጣት የአዲስ አበባው መንግስት ግዴታ ነው፡፡ አማራ የመንግስት አካል ነው፡፡ ኤርትራዊያን ደግሞ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ጥምረት አላቸው፡፡ ስለዚህም መንግስት ኤርትራዊያንንና አማራዎችን ውጡ ወደግዛታችሁ ሂዱ ሊላቸው ይገባል፡፡ ሀላፊነቱም ነው›› ብለዋል፡፡ የአርኤስኤፍ ጋዜጠኛው ይህንን አስታኮ ‹‹በአዲስ አበባ በኩል ይህ መዘግየት የተፈጠረው የፌዴራል መንግስቱ በትግራይ ላይ ድጋሚ ጥቃት ለማድረስ አቅዶ ነው ወይንስ የአስተዳደር ችግር ነው›› ሲልም ጠይቋቸዋል፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን በመልሳቸው በስምምነት አፈፃፃም ላይ ሁልጊዜም የአስተዳደር ችግር እንዳለ ጠቅሰው ቢሆንም ይህኛው ከልኩ ማለፉን አስረድተዋል፡፡ የፖለቲካ ምርጫ እንደሆነ ተናግረውም መልካም አስተሳሰብ ቢኖር እስካሁን መፈፀም ይቻል እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡ መዘግየቱ ያለ ቢሆንም ከአንድ አመት በላይ መቆየቱ ግን ከአስተዳደር ችግርም በላይ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ጋዜጠኛው በማስከተል ‹‹በስምምነቱ መሰረት የትግራይ ታጣቂዎች በሙሉ ትጥቃቸውን ፈተው ወደዲዲአር(ማለትም ተበትነው ወደህብረተሰቡ መቀላቀል) ውስጥ መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ግን የክልሉ ባለስልጣናት ሁለት መቶ ሀምሳ ሺ ሰዎች አሁንም ከእነትጥቃቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የተነሳ አንዳንዶች በትግራይ በኩልም መልካም ፈቃድ እንደሌለ አድርገው ያስባሉ›› በማለት ጥያቄ አንስቶላቸዋል፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ሲመልሱ ‹‹አይደለም፡፡ እኛ ትጥቅ በማስፈታት በኩል ምንም የፈቃደኝነት አጥረት የለብንም፡፡ በስምምነቱ ላይም የተቀመጠ ነው፡፡ ነገር ግን ዲዲአሩን ብቻ መገምገም የለብንም›› ብለዋል፡፡

እንደገለፁትም በመጀመሪያ ትግራይን የወረሩ ሀይሎች ለቀው መውጣት የሚኖርባቸው ሲሆን ዲዲአር ከዚህ ተከትሎ የሚመጣ ነው፡፡ ያለበለዚያ አስቀድሞ ዲዲአር እንደማይኖርም አስረድተዋል፡፡ የህወሀት ሊቀመንበሩ ማብራሪያቸውን በመቀጠል ‹‹ጦር መሳሪያን በተመለከተ እኛ ከባድ መሳሪያዎችን ፈተናል፡፡ ይህንን ያደረግነው ከሚጠበቀው ጊዜም ቀደም ብለን ነበር፡፡ እኛ በፍጥነት ይህንን ያደረግነው እነዚህን ሀይሎች የማስወጣት ስራውም በፍጥነት ይከናወናል ከሚል ተስፋ ነበር፡፡›› በማለት ጠቅሰዋል፡፡ ጨምረውም ትክክለኛው ዲዲአር ከመከናወኑ በፊት በግላቸው ታጣቂዎችን መበተናቸውን ገልፀው ያን ያህል ብዙ ታጣቂ አያስፈልገንም በሚል መቶ ሺህ ታጣቂዎችን ወደቤሰቦቻቸው ልከናል ብለዋል፡፡

ይህንንም ያደረጉት በቂ በጀት ስለሌላቸውና ያን ያህል ታጣቂ ለማስተዳደር የሚበቃ ድጋፍ ከአዲስ አበባ ስለማይሰጣቸው እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ ጋዜጠኛው በማስከተል ‹‹ስለዚህ የአማራና የኤርትራ ሀይሎች እያሉ ዲዲአር አይከናወንም ማለት ነው›› ሲል ጠይቋቸዋል፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ‹‹አዎ ሊሆን አይችልም፡›› በማለት መልሰዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹እነዚህ ሀይሎች ከወጡም በኋላ ቢሆን የተወሰነ ጊዜን ይወስዳል፡፡ ዲዲአር በአንድ ጀምበር የሚሆን ነገር አይደለም፡፡ ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ታጣቂዎችን ወደህብረተሰቡ መልሶ መቀላቀል በቢሊዮን የሚቆጠር ኢንቨስትመንት የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ ስልጠናዎችንና ሌሎችንም በርካታ ነገሮችን የሚፈልግ ነገር ነው፡፡ እኛ በዲዲአር መሰረተ ሀሳብ ላይ የተስማማን ቢሆንም ሊሆን የሚችለው ግን እነዚህ ሀይሎች ከትግራይ ከወጡ ብቻ ነው›› ብለዋል፡፡

የኤርትራ መንግስት በስምምነቱ ላይ እንዳልፈረመ የጠቀሰው ጋዜጠኛው ኤርትራዊያን እነዚህን ቦታዎች የያዙት የእኛ ነው በሚል እንደሆነ በማንሳት ጥያቄ አቅርቦም ነበር፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ሲመልሱ ‹‹እነሱ ባይፈርሙም የፌዴራል መንግስቱ አጋሮች ናቸው፡፡ የኤርትራ ወታደሮችን የጋበዛቸው የፌዴራል መንግስቱ እስከሆነ ድረስ የማስወጣት ሀላፊነቱም የአዲስ አበባው መንግስት ነው፡፡ ማእከላዊው መንግስት ውጡ የማለት ግዴታ አለበት›› ብለዋል፡፡

በመቀጠል የቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ ‹‹የጄኖሳይድ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂንና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ጥፋተኞች ለህግ መቅረብ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡ እርስዎስ መየጠቅ አለባቸው ይላሉ?›› የሚል ነው፡፡ ዶክተር ደብረፅዮን ሲመልሱ ‹‹አጥፊዎች ተጠያቂ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ተጠያቂው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ወይንም የኤርትራው ፕሬዘደንት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚወሰነው ለደረሰው ጥፋት ባለባቸው ሀላፊነት መሰረት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ የከሳሾች ስራ ይሆናል፡፡ እኔ በበኩሌ ይህን ወንጀል የፈፀመውእከሌ ነው ያንን ደግሞ እከሌ ነው አልልም፡፡ ይህንን የሚወስኑት አለም አቀፍ መርማሪዎች ናቸው፡፡›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹በግሌ ግን እነዚህ ሰዎች መሪዎች በመሆናቸውና ትእዛዝ የሰጡትም እነሱ ስለሆኑ መከከስ ይገባቸዋል የሚል አስተያየት አለኝ›› በማለት አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል የትግራይ ታጣቂዎች ማለትም ቲዲኤፍ በዚህ ምርመራ ውስጥ መካተት አይገባውም ወይ የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው ዶክተር ደብረፅዮን ‹‹በእኔ አስተያየት ቲዲኤፍ በጄኖሳይድ ተጠያቂ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ቲዲኤፍ የጄኖሳይድ ውጤት ነው፡፡ ቲዲኤፍ ከተጎጂዎች ጎን በመሆን የትግራይ ተወላጆችን ከጄኖሳይደሮች ለመጠበቅ የቆመ ነው፡፡ እኔ የእነሱ መሪ እንደመሆኔ በአማራዎችም ሆነ በሌላው ላይ ጥቃት የማድረስ ሀሳብ ይዘን አልተነሳንም፡፡›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹በእርግጥ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ ጦርነት ስናደርግ የተፈጠሩ ክስተቶችን ለመካድ አልችልም፡፡ ይሁንና እነዚህ ክስተቶች ጄኖሳይድ ሊባሉ አይችሉም፡፡ ቢሆንም ለማናቸውም አይነት ምርመራ በራችን ክፍት በመሆኑ ውጤቴን የምናየው ይሆናል›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

Best Ethiopia Musician Abrham Wolede
09/07/2024

Best Ethiopia Musician Abrham Wolede

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶስት ዓመት በፊት  በፓርላማ  ሲቀርቡ ከ40 ሺ ሰው  በላይ በቀጥታ የሚከታተላቸው ነበር። ዛሬ በፓርላማ ቆይታቸው ደግሞ አንድ ሺ   ሰው እንኳን ማግኘት አልቻሉም። ለምን...
04/07/2024

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሶስት ዓመት በፊት በፓርላማ ሲቀርቡ ከ40 ሺ ሰው በላይ በቀጥታ የሚከታተላቸው ነበር። ዛሬ በፓርላማ ቆይታቸው ደግሞ አንድ ሺ ሰው እንኳን ማግኘት አልቻሉም።

ለምን ይመስለዎታል ?

ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ

ወገን  ልብላው
03/07/2024

ወገን ልብላው

18/06/2024
05/06/2024
20/05/2024
"አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አይበላም" ክርስቲያኖ ሮናልዶ
19/05/2024

"አርሰናል የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አይበላም" ክርስቲያኖ ሮናልዶ

በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ የቆመው የቅዱስ ያሬድ ሐውልት።
19/05/2024

በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ የቆመው የቅዱስ ያሬድ ሐውልት።

ቀራኒዮ
16/05/2024

ቀራኒዮ

16/05/2024

የሞተ ሰው ባይኖርም ከባድ አደጋ ተከስቷል ሸገር ኦሮሚያ መግብያ የትራፊክ መጨናነቅ አለ ይህ መርጃ የደርሳቹ ሹፌሮች ቀራኒዮ መስመር በእርጋታ ‼️📵

ሀሳቡ የአካል ጉዳተኛ መወጣጫ ለማድረግ  ነው ። ችግሩ ግን እንኳን የአካል ጉዳተኛ ፀሀይ የመታው መንገደኛ የማይወጣው አቀበት ሰርተው አረፉት። positive thinker መሆንህ ወደ prob...
11/05/2024

ሀሳቡ የአካል ጉዳተኛ መወጣጫ ለማድረግ ነው ። ችግሩ ግን እንኳን የአካል ጉዳተኛ ፀሀይ የመታው መንገደኛ የማይወጣው አቀበት ሰርተው አረፉት።

positive thinker መሆንህ ወደ problem-solver ካላደረሰህ: ትርፉ ኪሳራ ነው ።

ኧረ መውጫው በየት ነው?

ዶሮ እንደ ንስረ መብረር ሲያምራት ተኝታ በህልሟ ከቆጠ ዘላ በፈላ ውሀ ሰመጠች 😂😂
09/05/2024

ዶሮ እንደ ንስረ መብረር ሲያምራት ተኝታ በህልሟ ከቆጠ ዘላ በፈላ ውሀ ሰመጠች 😂😂

Milano ረጀናሌ ሰንጃሎ አቴንስዮ ተሬኔ 😂ቤንች ኳትሮል 🤯🤯🤯😂😂😂
03/05/2024

Milano ረጀናሌ ሰንጃሎ አቴንስዮ ተሬኔ 😂ቤንች ኳትሮል 🤯🤯🤯😂😂😂

03/05/2024

Gare de Milan porta Garibaldi የለ ወደ ሰው መጥቶ እንገናኝ አዲስ መዝናኛ ❤️Coll me 0628046836

03/05/2024

ድሮን

እዉነት ከተባለ ይህ ስተት ነዉ 🐛
24/04/2024

እዉነት ከተባለ ይህ ስተት ነዉ 🐛

19/04/2024

መልክተኛው ፔጅ

18/04/2024

ሌሎች በሌላ አቅጣጫ አዝምተውታል

15/04/2024

ሰይፈ ፋ

ኢድ ሙባረክ 💐በመላው ዓለም የምትግኙ ኡመት በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ❤️
10/04/2024

ኢድ ሙባረክ 💐በመላው ዓለም የምትግኙ ኡመት በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ❤️

ቀለሜ
09/04/2024

ቀለሜ

ጉራጌ Pro Max 😂📷
06/04/2024

ጉራጌ Pro Max 😂📷

እንኳንም በሙሉ ጤንነት ላይ ሆኑ፤ ከላይ የምትመለከቱት በአክሱም መጋቢት 22፤2016 ተጣብቀው የተወለዱ ሴት መንትያ ህፃናቶች ናቸው ፤ይሄ በቀዶ ጥገና ሊስተካከል የሚችል የሚገጥም ክስተት ነ...
02/04/2024

እንኳንም በሙሉ ጤንነት ላይ ሆኑ፤ ከላይ የምትመለከቱት በአክሱም መጋቢት 22፤2016 ተጣብቀው የተወለዱ ሴት መንትያ ህፃናቶች ናቸው ፤ይሄ በቀዶ ጥገና ሊስተካከል የሚችል የሚገጥም ክስተት ነው። ከታች ያሉት በቀዶ ጥገና ህክምና የተለያዩ ናቸው ፈጥንው ሳይጠንክሩ ህክምና ማግኘት እሚችሉበት መንገድ መፈልግ ነው

Adresse

Il De
Bouray-sur-Juine

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque አዲስ መዝናኛ publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Contacter L'entreprise

Envoyer un message à አዲስ መዝናኛ:

Vidéos

Partager

ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን ሰላም ሚመኝ ሰው ሁሌ ሰላምን ይከተለዋል ።

Keep us laughing all the time


Autres entreprises de médias à Bouray-sur-Juine

Voir Toutes