Abadirto Alafar

Abadirto Alafar Peace for all

ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሽብር ተግባር ፈፅሟል በሚል ሲፈለግ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለሚያዝያ 28/2015 (ዋልታ) በአማራ ክልል ሕገ-መንግሥ...
06/05/2023

ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሽብር ተግባር ፈፅሟል በሚል ሲፈለግ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሚያዝያ 28/2015 (ዋልታ) በአማራ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፍረስ ከፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ተባብሮ በመሥራት የሽብር ተግባር ፈፅሟል በሚል ሲፈለግ የነበረው ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ አምልጦ ጅቡቲ ከገባ በኋላ ወደሌላ አገር ሊሻገር ሲል ከዓለም አቀፉ ፖሊስ እና ከጅቡቲ መንግሥት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውል እና ተላልፎ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ተደርጎ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ መግባቱን የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።

በአማራ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት በህቡዕ ተደራጅተው እና ተቀናጅተው በሚንቀሳቀሱ ፅንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

በዚህ መሠረትም፦

1. ሀብታሙ አያሌው፣
2. ምንአላቸው ስማቸው
3. ብሩክ ይባስ እና
4. እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ
5. ዘመድኩን በቀለ
6. ልደቱ አያሌው
7. መሳይ መኮንን
8. ጎበዜ ሲሳይ
9. ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
10. በለጠ ጋሻው እና
11. ሙሉጌታ አንበርብር የተባሉት ተጠርጣሪዎች በፈፀሙት የሽብር ተግባር እንደሚፈለጉ እና ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል ለሕግ እንደሚቀርቡ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ማሳወቁ ይታወሳል።

ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከልም ጎበዜ ሲሳይ ዘገየ የተባለው ግለሰብ፣ በአማራ ክልል ቆቦ አካባቢ የፅንፈኛ ታጣቂ ኃይሎችን በማደራጀት፣ በቅርቡም በጽንፈኞች ግድያ የተፈጸመበትን የአቶ ግርማ የሺጥላን ግድያ በማስተባበር ሚና እንደነበረው፣ በመከላከያ እና በሕዝቡ ላይ ፅንፈኞች ጥቃት እንዲያደርሱ በማደራጀት እና ቃል አቀባይ ሆኖ በማስተባበር የሽብር ተግባር ውስጥ በመሳተፍ ተጠርጣሪ በመሆን ሲፈለግ ቆይቷል።

ግለሰቡ አማራ ክልልን በማሸበር እና ሥልጣንን በኃይል በመቀማት በቀጣይም የፌዴራል መንግሥትን ለማፍረስ ሲንቀሳቀስ ከነበረ ፅንፈኛ አካል ጋር በመተባበር ሲሠራ እንደነበር በመጠርጠሩ፣ ግለሰቡን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የጋራ ግብረ ኃይሉ ከኢንተርፖል ጋር ባለ ስምምነት መሠረት ሲሠራ መቆየቱን ገልፆ ነበር።

በዚሁ መሠረትም አስፈላጊውን ፎርማሊቲ እና አግባብ ያላቸው መረጃዎችን በማደራጀት ጎበዜ ሲሳይ የተባለው ግለሰብ አምልጦ ጅቡቲ ከገባ በኋላ ወደሌላ አገር ሊሻገር ሲል ከዓለም አቀፉ ፖሊስ እና ከጅቡቲ መንግሥት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር እንዲውል እና ተላልፎ ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ተደርጎ ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብቷል።

የፀጥታ እና የጋራ ግብረ ኃይል አሁንም ኢትዮጵያ ባላት ስምምነት መሠረት ሌሎች ያልተያዙ የሽብር ቡድኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሠራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጿል።

06/05/2023
01/05/2023
01/05/2023
01/05/2023
01/05/2023
01/05/2023

Kabajamoo Dr. Lammaa Magarsaa

ልዪሀይል ይፍረስ ሲሉ የነበሩ ቡድኖች: አሁን ልዪሀይል ወደ መከላከያ እና ወደ ፓሊስ ይግቡ ሲባል ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ግን ምንድን ነው ፍላጎታቸው።
09/04/2023

ልዪሀይል ይፍረስ ሲሉ የነበሩ ቡድኖች: አሁን ልዪሀይል ወደ መከላከያ እና ወደ ፓሊስ ይግቡ ሲባል ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት ግን ምንድን ነው ፍላጎታቸው።

09/04/2023

Why does the government choose to be silent when it has power, energy and potential? Why was silence chosen when the country was shaken by such extremists? More than that, silence seems to be fear.

09/04/2023

የቀድሞ አርሰናል ተጨዋቻችን Sol Campbell ዛሬ እንዳለው

አርሰናል የዛሬውን ሊቨርፑል vs አርሰናል ጨዋታ አንፊልድ ላይ ካሸነፈ ከዚህ በሃላ ፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ለማስቆም እሚችለው ክለብ አይኖርም ብሏል !

(እኔ በግሌ ሁሉም እየተነሳ አርሰናል ያሸንፋል ይላል ,እኔ ግን የሊቨርፑል እና የአርሰናል ጨዋታ ጭንቀት ከፈጠረብኝ ዛሬ ሳምንቴ ነው )

https://instagram.com/abebe5548?igshid=YmMyMTA2M2Y= ኢንስትግራም

https://www.facebook.com/befakadu.girma.9?mibextid=LQQJ4d ፌስቡክ

https://t.me/HuleArsenal1 ቴሌግራም(ሃይ ላይት ማየት ከፈጉ ይህን ሊንክ ይሄው

ዘንድሮ ማንቸ አልተሳካለትም ከደረጃው ዝቅ ብሏል
02/04/2023

ዘንድሮ ማንቸ አልተሳካለትም ከደረጃው ዝቅ ብሏል

ዘንድሮ ዋንጫው የኛ ነዉ
02/04/2023

ዘንድሮ ዋንጫው የኛ ነዉ

02/04/2023

Full Time
Newcastle united 2 : 0 Manchester united

Address

Logya
Welo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abadirto Alafar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abadirto Alafar:

Share


Other Digital creator in Welo

Show All