21/05/2024
በአማራ ክልል የተካሄደው የሀገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ ሙስሊሙን ያላካተተ መሆኑን ተገለፀ!
…
(ሀሩን ሚድያ ፦ግንቦት 13/2016)
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ በአማራ ክልል ለብሄራዊ ምክክር ለሚደረገዉ ሂደት የመጀመሪያ ዙር የምክክር ጉባኤ የሚሳተፉ ሰዎች ተለይተዉ ወደ ስራ እንደገቡ በመግለፅ ነገር ግን በተሳታፊ ልይታ ወቅት ሙስሊሙን ያገለለ እና የክልሉን እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባላወቀው መልኩ የተካሄደ መሆኑን አንስቷል ።
…
በክልሉ የኃይማኖት ተቋም አባል የሆነዉን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በማያዉቀዉና ሳያማክሩ የኔ የሚሉትን ብቻ በማሳተፍ የሀገሪቱ ግማሽ አካል የሆነውን ህዝበ ሙስሊሙን በማግለል የሚፈለገዉን መልካም ዉጤት ያመጣል ብሎ እንደማያምን ገልጿል፡፡
…
ስለሆነም ችግሩ ተወግዶ አሰራሩ ተሻሽለ- ከፍተኛ ምክር ቤቱ የሚሳተፉ ሰዎችን መልምሎ እንዲያቀርብና ሙስሊሙን የሚያሳትፍ ምክክር እንዲሆን እየጠየቅን አሰራሩ ሳይሻሻል ባለበት የሚቀጥል ከሆነ ለሀገራዊ ምክክሩ እዉቅና የማንሰጥና አስራሩን የምንቃወም መሆኑን በጥብቅ እናሳዉቃለን ሲል ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ላይ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
…
©ሀሩን ሚድያ