13/04/2024
Welcome To Ethio Review . please leave us a comment on any that you enjoy!
ዘመቻውን ተቀላቀሉ!
ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ ዘመቻ ጀመረ
ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከአራት ወራት በፊት የታሰረው ጋዜጠኛ Belay Manaye ከእስር እንዲፈታ የሚጠይቅ ዘመቻ ጀመረ።
“የኢትዮ ኒውስ” ዩትዩብ ዜና ማሰራጫ መሥራቹ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር የዋለው ከአራት ወራት በፊት ኅዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር። ጋዜጠኛዉ በቁጥጥር ስር ከዋለ ወራቶች ቢቆጠሩም፤ እስከዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረበም፤ የታሰረበት ምክንያት አልተገለፀም፤ ምርመራም አልተደረገበትም።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ የታሰረው፤ „በአማራ ክልል ያለውን ግጭት አስመልክቶ በሠራው ዘገባ ነው ተብሎ ቢታመንም የታሰረበት ምክንያት አልተገለጸለትም“ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በአማራ ክልል ለተፈጠረው ግጭት “ሌሎች ሰባት ጋዜጠኞችን በዘፈቀደ አስሮ ጥቂቶችንም ከእስር ፈትቷል” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይፋ ባደረገዉ መግለጫ አስታዉቋል።
“የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ያሰሯቸዉን ጋዜጠኛ በላይ ማናዬን እና ሌሎች ሁለት ጋዜጠኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ” አምነስቲ ዘመቻውን አስመልክቶ በድረ ገጹ ይፋ ባደረገዉ መልዕክት አሳስቧል።
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር የተደነገገዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስታከዉ “ፕሬሱን እና ሰላማዊ ተቃውሞዎችን ለማፈን ተጠቅመውበታል” ሲል አምነስቲ ከሷል።
አምነስቲ ሰዎች በድረ ገጹ የተጋራውን የደብዳቤ ቅጂ ወይም በራሳቸው የጻፉትን ድብዳቤ ተጠቅመው ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ጠይቋል።
ጭንቅና መከራው ሲበዛ ሀገሩን ጥዬ ለመሰደድ ተገድጃለሁ !
ህዝብ ራሱን ከመንግስት የሚጠብቅበት፣ ሽሽትና ፍርሀቱም አላስጥል ብሎት በመንግስት ተገዳይና ተሳዳጅ ህዝብ ያለበት ሀገር..... ሀገረ- ኢትዮጵያ !
ሀገርንና ህዝብን አስቦ መስራት፣ ሙያና ፀጋን በተግባር ማዋል፣ ከሰከረ ፖለቲካ ውጪ በመርህ መስራት፣ ያለ ገዥው ፓርቲ ማለም፣ በግርድና ከሚያገለግሉት ተገዥ ካድሬዎች ሃሳብ መቃረን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከባድ ወንጀል ተደርጓል። ብዙ መከራና ስቃይም አምጥቷል።
በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የአመታት ቆይታዬ ስለ ተሳዳጁ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ከሚገድዳቸው ወዳጆች ጋር ብዙ ለመታገል ሞክረናል። ከወለጋ እስከ አጣዬ ከማይካድራ እስከ ቤንሻንጉል ግልፅ ጦርነቶች እስከ ስውር ደባዎቹ ብዙ ለመስራት ሞክረናል።
ነገሩ ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም። ብዙ ፈተና ብዙ ምክርና መከራ፣ ብዙ እንግልትና ወከባንም እያመጣ እሱን ማውራትም ሌላ መከራ እየደቀነ ውጠነው ኖረናል።
አሁን ግን ከአፈናና ወከባው መብዛት ባሻገር ሁኔታዎች እጅግ በመበለሻሸታቸው ሀገር ጥለን መሰደድ ምርጫ ሆነ።
በዝርዝር ጉዳዮችና በተሻለ ስራ ወደ ህዝባችን እንመለሳለን !
እንዳልካቸው አባቡ አየለ !
የአድዋ ባዶ እግር ሩጫ ተሳታፊዎች በአሁኑ ወቅት አዘጋጁ ጋዜጠኛ ብስራት መንግስቱን ጨምሮ በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎች የተካተቱበት የሩጫው ተሳታፊዎች በፀጥታ አካላት ወደ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል!!! ፕሮግራሙ ሕጋዊ ፍቃድ እንደነበረውም የሚታወቅ ሲሆን አዘጋጁም በዚሁ ዝግጅት ተደጋጋሚ ፈተናዎችን ተጋፍጧል!
Am alive
The former ETV (EBC) Jornalistas
አማራነት ወንጀል አይደለም
እኛ በግፍ የታሰርነው አማራዎች ህፃናት አላረድንም ።ነፍሰጡር እናት ሆዷን አልሰነጠቅንም ።ህዝብ አልጨፈጨፍንም ።ሴት ተማሪዎችን አግተን አልሰወርንም ።ባንክም አልዘረፍንም ። ህዝብም አላፈናቀልንም ። ወንጀላችን ህፃናትን አትረዱ ፤ነፍሰጡሯን እናት አትሰንጥቁ ፤ የአማራን ህዝብ አትጨፍጭፉ፤ያገታችኋቸውን አማራ ሴቶች ተማሪዎችን መልሱ ፤ በዳቦ ስም ባንክ አትዝረፉ ፤የአማራ ህዝብ አታፈናቅሉ ብለን ለአማራ ህዝብ ስለ እውነት በመቆማችንና አማራ ሆነን መፈጠራችን ብቻ ነው ።
አርቲስት ዬርዳኖስ አለሜ ከቂሊንጦ እስር ቤት ዛሬ ያስተላለፈው መልክት !!
!
በሰላማዊ የነፃነት ታጋዮች ላይ እየደረሰ ያለው የፍትሕ እጦት፣ የሰብዓዊ መብት ገፈፋ እና ያለ ጥፋታቸው መታሰራቸው የመብት ረገጣ መሆኑን በመግለጽ በአስቸኳይ ከግፍ እስር እንዲለቀቁ " እኔም እጠይቃለሁ ፤ ለምን ?! " የበይነ መረብ ዘመቻው ዛሬ በይፋ ተጀምሯል ፣ይቀላቀሉ !
ለዘመቻው የተዘጋጀው ፕሮፋይል ይሄ ስለሆነ ፤ ፕሮፋይል ምስልዎን በመቀየር ፣ጽሁፎችን በመጻፍ፣ ምስሎችን በማጋራት ሃሳብዎን ያንፀባርቁ !!
" እኔም እጠይቃለሁ ፤ ለምን ?! "
ማሰር መሸነፍ ነው።
ጋዜጠኛ Yehualashet Zerihun በፌደራል ፖሊሶች ተይዞ ተወሰደ
ጋዜጠኛ የኋላሸት ዘሪሁን ዛሬ ከቀኑ 7:40 ላይ ባልዳራስ ኮንዶሚኒየም ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በ7 የፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዞ ሜክሲኮ የቀድሞው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ወደሚገኘው ጊዜያዊ ማቆያ ቦታ ተወሰደ ። ባለቤቱ የታሰረበት ቦታ ሄዳ የጠየቀችው ሲሆን በምን ምክንያት እንደታሰረ እንዳላወቀና ለጥያቄም እንዳልቀረበ ገልጾላታል ።
Tewodros Teklearegay
የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !
| እኔ ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ ጳጉሜ 6 በሸራተን አዲስ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የሙዚቃ ስራዬን ለማቅረብ ተፈራርሜ የተዘጋጀሁ ቢሆንም ይህን ስራ በመሰረዜ የሚያስከፍለኝ ዋጋ ቢኖርም ከሁሉም በላይ በቃሏ የምመራላት ቤትክርስትያን ሀይማኖት አባቶቼን ትዕዛዝ በመቀበል የማቀርበውን የሙዚቃ ስራ ሰርዤአለሁ !
ለውድ አድናቂዎቼ እንዲሁም የፕሮግራሙ አዘጋጆች ይቅርታ እየጠየኩ በሌላ ዝግጅት እንደማስደስታችሁ እና እንደምንገናኝ ስገልፅላችሁ በታላቅ አክብሮት እና ምስጋና ነው!
ኩኩ ሰብስቤ
ይህቺ የOMN ዘገባ እኔን ጨምሮ አንዳንድ ሰዎች ያቀረቡትን ትችት ተከትሎ የተሰጠች የመልስ ምት ትመስላለች። ቀሽም መልስ። ይህቺው እንደመልስ ምት የተወረወረችው ዜና በራሷ ከOMN ኩሽና እንዴት ክሽን ብላ እንደተሰራች ለማወቅ የምትከብድ አይደለችም። ፈጠራ አልቆባቸዋል። ማስመሰልም ጥበብን ይጠይቃል። የብሄር ስም ለጥፈህ የመሰረትከው ሚዲያ ማንነትህንና ስራህን በሚገባ ይናገራልና ወዲህ መቧጠጥ ወዲያ መላላጥ አያስፈልግም። ጋዜጠኝነት ትወና አይደለም። ገጸባህሪ ፈጥረህ የምትጫወተው ቲያትር አይደለም። ፕሮፖጋንዳም ከሆነ ትልቅ እውነት ይዞ ትንሽ ቅመም የሚጨምሩበት ክህሎት ነው። ዝም ብሎ በደረቁ ውሸት መጋት ጋዜጠኝነት ሳይሆን ጋጠወጥነት ነው።
ስለእዉነት ፆምን ፍቺ አሳቦ አይከብድም ለአራጅ እና ሰዉ በላ መንግስት ለሚያደላ መከላከያ ህዝቡን ለመፍጀት ብትሉት ጥሩ ነበር
ከዚህ በታች ያለው ፅሁፍ ሰሞኑን በፀጥታ ሃይሎች የታፈነው ታዋቂው የፊልም ዳይሬክተር እና የጉማ ሽልማት መስራች ዮናስ አባት ጋሽ ብርሃነ መዋ በፌስቡክ ገፁ ላይ የከተበው ነው::
ከብርሃነ መዋ
ሰኔ 4 ቀን 2015
ዮናስ ብርሃነ መዋ የኢትዮፊልም ዋና ስራ እስፈጻሚና የጉማ ፊልም ሽልማት መስራችና ዳይሬክተር
እስር-ፍች-እስር
በጉማ ፊልም ሽልማት 7ተኛ ዙር ዝግጅት ወቅት ለኔ ለአባቱ በተደጋጋሚ በፖለቲካ ስለመታሰሬ ጉዳይ
“ በሃይለ ስላሴ ጊዜ ታሰርክ፣ በደርግ ጊዜ ታስርከ፣ በኢሃዲግ ጊዜ 2 ጊዜ ታስርክ፣ ከንግዲህ ፖለቲካ ውስጥ ብትገባ እኔው አራሴ አስርሃለሁ” ብሎኝ ነበር። ዮናስ ብርሃነ መዋ
ምክሩን ሰምቸ ብቀዘቅዝም፡ ሲታሰር ትዝ ያለኝ ይህ ነበር። አንደሱ ፖለቲካ ውስጥ የሌለም፣ ሙያውን ለማሳደግ ሲጥርም ያላግባብ ሊታሰር አንድሚችል ሳየው፡፡
የጉማ ፊልም ሽልማት የፕሮግራሙ መስራችና ዳይሬክተር በሰኔ 2 ቀን በፕሮግራሙ ማጠናቅቂያ ላይ በፖሊስ ለእስር ተዳርጓል።
ይህን ጉዳይ በሚመለከት በተለያየ መንገድ ስጋታችሁን፡ አጋርነታችሁን፡ ብሶታችሁን፣ ንዴታችሁን፣ ለገለጻችሁ፣ እንዳንድ ማብራሪያዎችን ለጠየቃችሁ ወዳጆች፣ ባለሞያዎችና ቤተሰቦች። በራሴ አና በቤተሰቡ ስም ታላቅ ምስጋናየን አቀርባለሁ። የሆነውንና ትክክለኝውን ነገር እንድትረዱት አንደሚከተለው እቅርቤዋልሁ።
እርብ ሰኔ 2 ቀን
ከምሽቱ 5፡30 ሰአት የጉማ ፕሮግራም ተጠናቀቀ
ሌሊቱ 6፡00 ሰአት ዮናስና ባለቤቱ ሳምራዊት(ሊሊ) ወደ ቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተወሰዱ
ከለሊቱ 6፡00 ሰአት ሳምራዊት(ሊሊ)ስትለቀቅ ዮናስ ታሰረ
ቅዳሜ ሰኔ 3 ቀን
ከጥዋቱ 3፡00 ሰአት ዮናስ ፍርድ ቤት ተወሰደ
ከጥዋቱ 4፡00 ሰአት ዮናስ ዳኛ ፊት ሳይቀርብ ወደ እስር ቤት ተመለሰ
ከጥዋቱ 4፡30 ሰአት ዮናስ ወደ ፍርድ ቤት አንደገና ተመለሰ
ከጥዋቱ 5፡30 ሰአት ዮናስ በ 5ሽህ ብር ዋስትና እንዲፍታ ተወሰነ
ከቀኑ 7፡15 ሰአት ዋስትና ተከፈለ የፍች ፎርማሊቲ ተሟላ
ከቀኑ 7፡20 ፍርድ ቤቱ ከእስር እንዲፈታ የሰጠውን የመፍቻ ጽሁፍ ትእዛዝ ለፖሊስ መመሪያው ደርሶ እንደሚለቀቅ ተነገረን
ከቀኑ 7፡20 እስክ 8፡15 የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ለፖሊስ ገቢ ሆኖ እንደሚለቀቅ እና የሃላፊዎች መቅረብ እንድንጠባበቅ ተነግሮን በተስፋ ስንጠባበቅ ቆየን
ከቀኑ 8፡15 ወደቤተሰብ ሊቀላቀል ሲሄድ በፖሊስ መምሪያው ሚኒ ባስ መኪና እንዲገባ ተገዶ ወዴት እንደሚሄድ ሳይነገረን ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት በተለምዶ 3ኛ ተብሎ ወደ የሚጠራው ቦታ ተወሰደ (አዲዮስ የፍርድ ቤት ትዛዝ)
ከቀኑ 9፡00 ሰአት ዮናስን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተረክቦት ታሰረ
እቃ ገባለት ሰኞ ጠዋት ፍርድ ቤት እንደሚቀርብ ተነገርን።
እኔ ብርሃነ መዋ፡ የዮናስ አባት ሃሙስ ስኔ አንድ ቀን ከአሜሪካ አዲስ አበባ ገባሁ፤ በማግሰቱ አርብ የልጀና የስራ ባልደረቦቹ ዝግጅት የሆነውን ጉማ ለመታደም። እንደ አባት ለአግሩ የሙያ እድገት ያበረከተውን ላደንቅለት፣ አገሩ ስታመሰግነው ለማዳመጥ፣ ያጋጠመኝ ግን ሲመሰገን ስይሆን ሲታስር ማየት ሆነ።
ጥፋት ያጠፋ አይቀጣ፣ ወንጅል የሰራ አይጠየቅ የሚል ግብዝነት የለኝም። እሱ ባላረገውና ሌሎች መብታችን ነው ብለው ባደረጉት ድርጊት ምክንያት ተጠርጣሪ ተደርጎ ለስር ሲዳረግ ማየት ግን ቅስም ይሰብራል ተስፋን ያጨልማል።
በ1996 በህገመንግስት ውይይት በሰነዘርኩት ሃሳብ መነሻነት ጥርስ ተነክሶብኝ የጋዜጣ ድርጅቴ እንደምክንያት ተወስዶ አዘጋጁና እኔ በባለቤትነት አንድ ወር ታስረን በዋስ ተፈታን፣ ከጣቢያው ስንወጣ ወዲያው ተገደን በሌላ መኪና ወደ ሌላ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደን ታሰርን። የቅዳሜው ክስተት በኔ የደረሰን አሮጌ አሰራር አስታወሰኝ።ባሁኑ ጊዜ ይህ መሆኑ እንዴት? የሚል ጥያቄ ጫረብኝ እንጅ አልገረመኝም።
ሁሌም በኢትዮጵያ ተስፋ አልቆርጥምና በልጀ የዮናስ ብርሃነ መዋ ጉዳይ ላይ የተጀመረው ምርምራ አግባብ አለመሆኑ ተረጋግጦ ይለቀቃል የዋስትና መብቱም ይከበርለታል ብየ ተስፋ አድርጋለሁ።
የመንግስት ባለስልጣናቱ ከህዝብ ጋር በዚህ መልኩ በቲውተር ገፃቸዉ ዘቅጠዉ ይስተዋላል ።
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው እና ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለዘሐበሻ የደረሰው መረጃ ያስረዳል።
አቤል ገብረኪዳን (Ab Bella ) በ3000 ብር ዋስ እንዲፈታ ፍ/ቤት ፈቅዶ ነበር።
ፖሊስ እንደተለመደው እና እንደሚጠበቀው ይግባኝ ጠይቋል!
5 ቀናት የት እንዳቆየ መረጃ አምጣ ቢባልም ዛሬም መረጃውን ይዞ ያልቀረበው ፖሊስ ለይግባኝ ግን ፈጥኗል። ዋስትና አስፈቅጄ ከችሎት ወጥቼ ቢሮዬ ሳልደርስ ተመለስ ይግባኝ ቀርቧል ተብያለሁ።
ከሰሞኑ ልምድ አንጻር ዋስትና ሲፈቀድም እንኳ ስራዬ ገና ሀ ብሎ እየተጀመረ እንደሆነ ይገባኛል!! እንግዲ ፖሊስ ደንበኞቻችንን ይዞ በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ መሟገት እንጂ ምን ማድረግ ይቻላል?!
ሁላችሁም ሼር አድርጉ!!!!
ጋዜጠኛ አቤል ገብረ ኪዳን በፌስቡክ ስሙ በፖሊሶች ተወስዷል። ለምን እንደተወሰደ ለምን እንደሆነ ምንም መረጃ የለም።
ይሄ ወንድማችን ቤተ ክርስቲያን ችግር ላይ በነበረችበት ጊዜ አጀንዳውን ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ስለ ቤተ ክርስቲያን ሲሟገት ሲጽፍ ሲያነቃን በርካታ ሃሳቦችን ሲያካፍለን የነበረ ሲሆን፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የድል በዓል ስለሆነው ዓድዋም የተለያዩ ሳቅ አዘል እና ኢትዮጵያዊነትን አዘል ጽሑፎችን ሲያጋራን ነበረ። እናም ለወንድማችን ድምጽ እንድንሆን አሁንም አጀንዳችን ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን አደራ ልላችሁ እወዳለሁ። ወንድማችንን ፍቱልን!!!
የአማራዉን አጀንዳ ለማስቀየር በአማራ ክልል ''ኢትዮጵያ ታምርት'' የንቅናቄ መድረክ እየተካሔደ ነው ሲል የፊንፊኔዉ ሚዲያ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በገፁ አስፍሯል ።
ከታሪክ የተጣላ መንግስት ሲመራህ ዛሬ በነፃነት እንዲቀመጥ ያረጉትን ጀግና እንኳን በሙሉ አፉ መጥራትና በፓስተሩ ማረግ ያሳፍረዋል ።
ምኒልክ ዛሬም ንጉስ ነዉ
#ሚኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነዉ
በአድዋ ላይ ውይይት ለታሪክ የሚቀመጥ ፎቶ !!
አምባሳደር ዲና ምን አስገርሟቸው ይሆን ?
በሀይማኖትና በብሄር ሽፋን የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞችን በመታገል ወጣቱ አንድነቱንና አብሮነቱን እንዲያጠናክር ያስፈልጋል ይላል ማጣፊያዉ ያጠረዉ መንግስት ወጣቶችን ሰብስቦ ፕሮፓጋንዳዉንና ስልጣኑን እንዳያጣ ለመለማመጥ ዛሬ በማዘጋጃ አዳራሽ በጠራዉ ስብሰባ ።
What is goingnon in Addis Ababa
ከጦር ሀይሎች- 22- መገናኛ- ሲኤምሲ መንገድ ዝግ ነው!!
ተፈቷል
የሃቅ አሳዳሪዋ። ለህሊናዋና ለሰውነት ቋሚ ተሰላፊ። የፍትህ አምበል! ብርቱ እንስት ጋዜጠኛ መምህርና የፓለቲካ ተንታኝ! የእኛ ሰው መስኪላታ !!!
(ሸጋ ነገር ለሰው)
ከ 80 በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን በግፍ ያባረረው Addis Media Network-AMN የስራ ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።
Be the first to know and let us send you an email when Ethio Review ኢትዮ ሪቪው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
Send a message to Ethio Review ኢትዮ ሪቪው:
Want your business to be the top-listed Media Company?