Wolaita Asaa

Wolaita Asaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolaita Asaa, Media, Gununo hamus city, Sodo.

አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ቃለ-መሀላ ፈጸሙWolaita Asaa- መስከረም 27/2017 ዓ.ም  የ6ኛው ዙር ቀሪና እና ድጋሚ ምርጫ ያሸንፉ አዲስ የምክር ቤት አባላት በዛሬው ዕለት ...
07/10/2024

አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ቃለ-መሀላ ፈጸሙ

Wolaita Asaa- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

የ6ኛው ዙር ቀሪና እና ድጋሚ ምርጫ ያሸንፉ አዲስ የምክር ቤት አባላት በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል፡፡

አባላቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም.፤ በተካሄደው ምርጫ የተመረጡ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ታገሰ ጫፎና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው ቃለ-መሀላ የፈጸሙት፡፡

በዕለቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ቃለ-መሃላውን ያስፈጸሙ ሲሆን አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላትም ስራቸውን በሚጀምሩበት ወቅት በሕገ-መንግስቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እንዲሁም ህግና ሥርዓትን መሰረት በማድረግ ስራቸውን ለመወጣት ቃል መግባታቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወላይታ, ኢትዮጵያ🇩🇪🇩🇪🇩🇪
05/10/2024

ወላይታ, ኢትዮጵያ🇩🇪🇩🇪🇩🇪

በሴሰኝነት የሰከሩት የሳሙኤል ፎላና የጥላሁን ከበዴ ቡድን፣ አቅምና አቋም ያላቸው ሰዎችን ከዎላይታ ፖለቲካ ስያገልሉ ማየት ያሳዝናል። ወ/ሮ መስከረም ደገፉ የክልል ምክር ቤት አባል ሆና የተ...
30/09/2024

በሴሰኝነት የሰከሩት የሳሙኤል ፎላና የጥላሁን ከበዴ ቡድን፣ አቅምና አቋም ያላቸው ሰዎችን ከዎላይታ ፖለቲካ ስያገልሉ ማየት ያሳዝናል። ወ/ሮ መስከረም ደገፉ የክልል ምክር ቤት አባል ሆና የተመረጠችው በሕዝብ ይሁንታና እምነት ነው። የሕዝቡን ይሁንታና እምነት ወደ ውጤት ለመቀየር ያላትን አቋምና አቅም በሚገባ ተጠቅማለች። ነገር ግን በሴሰኞቹ ሳሙኤል ፎላና ጥላሁን ከበዴ ወጥመድ ላለመጠመድ ባደረገችው ብርቱ ትግል የቡድኑ አባል እንዳለመሆኗ ሁሉ ሕዝቡን ለማገልገል የሰነቀችውን ተስፋ ከመንገድ አስቀርተዋል። ወ/ሮ መስከረም ደገፉ እድሉን ካገኘች ዞኑንም ሆነ ክልሉን ማስተዳደር የሚትችልበት አቋምና አቅም ያላት ድንቅ ሴት ናት። አቶ ገብረመስቀል ጫላ እና አቶ ጴጥሮስ ወልደማሪያም የወ/ሮ መስከረም ደገፉን እምቅ አቅምና ጠንካራ አቋም መጠቀም የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር አለባቸው።

 #እንድታውቁት🚨 የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡ መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መ...
28/09/2024

#እንድታውቁት🚨

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ' ሻይንፋርም ' በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

ምንጭ:-

ኢትዮጵያና ሞሮኮ ተፈራርመዋልግብፅን ያሳበደው  የኢትዮጵያ ከሞሮኮ ጋር የተደረገ ድንቅ ወታደራዊ  ስምምነት ።  ግብፅን ለምን አስደነገጠ ? ኢትዮጵያ ለምን ሞሮኮ ሄደች? ሞሮኮስ ለምን ኢትዮ...
22/09/2024

ኢትዮጵያና ሞሮኮ ተፈራርመዋል

ግብፅን ያሳበደው የኢትዮጵያ ከሞሮኮ ጋር የተደረገ ድንቅ ወታደራዊ ስምምነት ።

ግብፅን ለምን አስደነገጠ ? ኢትዮጵያ ለምን ሞሮኮ ሄደች? ሞሮኮስ ለምን ኢትዮጵያን መረጠች ? የሚለውን የኢትዮጵያን ብዙዎችን ያስገረመ የጂኦ-ፖለቲካዊ ድል አጠር ባለ መልኩ እንመልከት ።

ግብፅ ከስልጣን አልባው የበናዲሩ ሞቃዲሾ መሪ ሀሰን ሼይክ መሀመድ ጋር ያደረገችው የወታራዊ ስምምነት ብዙ የተወራለት ነገር ግን ሁለቱንም መንግስታት ባላሰቡት መንገድ ቅርቃር ውስጥ የከተተ ሆኖ መጥቷል።

ግብፅና ሞቃዲሾ ከተፈራረሙት የጦር ስምምነት እንደሚታወቀው በቀጥታ ኢትዮጵያን ለናጥቃትና ወደ ኤደንና ቀይ ባህር እንዳትወጣ ያለመ ነው። ታዲያ ከስምምነታቸው አንዱ የሆነው ኢትዮጵያን በባህር የምታደርጋቸውን ከንግድ እስከ የባህር ሀይሏ የሚኖሩትን እንቅስቃሴዎች... ግብፅ የአለማችን ወሳች የመርከቦች መተላለፊያ የሆነውን የሲዊዝ ቦይን ኢትዮጵያ ላይ በመዝጋት ፣ ሞቃዲሾ የኢትዮጵያ መርከቦች ወደ ጅቡቲና በርበራ እንዳያልፉ በማገት ኢትዮጵያ ከምግብ እስከ ጦር መሳሪያ ወደ ሀገሯ እንዳታስገባ በመከርቸም ማስገደድ ነው። ( በመሀል ኤርትራም ያለች ሲሆን ለግዜው እንዝለላት)

ታዲያ ይህችን የ129ሚሊየን ህዝብ እናት የሆነች ታላቅ ሀገር ወደ ባህር እንዳትወጣ የተሸረበው ሴራ ሳያንስ እህልና ነዳጅ እንኳን እንዳታስገባ የተሸረበውን ቀመር የተረዳችው ኢትዮጵያ በቀጥታ ያመራችው ቀድማ ወደ አዘጋጀቻት የሰሜን አፍሪካ ወደጅ ሀገር ሞሮኮ (አል-መግሪቢ) ጋር ነበር።

ሞሮኮ በአለማችን ላይ ስትራተጂካዊ የጂኦፖለቲክስ አቀማመጥ ላይ ከሚገኙ ሀገራት አንዷ ነች ። ሞሮኮ በአጭሩ ለማስረዳት ሌሎች አህጉርና ሀገራትን ትተን ወደ ግብፅ የሚሄዱ አብዛኛው መርከቦች መተላለፊያ የሆነው Strait of Gibraltar የባህር ወሽመጥ ባለቤት ነች ።

በዚህም የተነሳ ግብፅ ልክ ኢትዮጵያን በአባይ ምክንያት ታሪካዊ ጠላት እንዳደረገቻት ሁሉ ሞሮኮንም በተመሳሳይ መንገድ በጠላትነት ይዛት ኖራለች። ግብፅ በዚህም የተነሳ ልክ ኤርትራን ከኢትዮጵያ እንድትገነጠል እንደሰራች ሁሉ የሞሮኮን ተገንጣይ ራሳቸውን ሳህራዊ ሪፐብሊክ ብለው ሚጠሩትን ቡድኖች በመደገፍ ላይ ትገኛለች።

በመሆኑም ኢትዮጵያ በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አማካኝነት ከሌላኛዋ የግብፅ ስትራቴጂካዊ ጠላት ሜዲትራኒያንና አትላንቲክ ውቂያኖስን ከምታገናው ወሳኝ ሀገር ሞሮኮ ሊፐብሊክ ጋር እጅግ ወሳኝ የወታደራዊ ስምምነት ከቀናት በፊት ፈርማለች ። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ከግብፅ ሲዊዝ ካናል ላይ የሚደርስባት የመርከብ መታገት ካለ የግብፅ መርከብ Strait of Gibraltar እንዳያልፍ ይዘጋበታል ማለት ነው። በተመሳሳይ ኢትዮጵያም በኤደን ባህረሰላጤ ላይ አልፎ የሚወጣና የሚገባ የግብፅን መርከቦች ማነቅ ትችላለች።
ይህን ለማድረግ ኢትዮጵያ በቅርብ ኤደን ላይ ከሚሰፍረው ባህር ሀይሏ ባሻገር የመድፍ እርቀት ላይ የሚገኘውን ምድሯንም መጠቀም ትችላለች።

የሞሮኮና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ስምምነት በዚህ ብቻ አያበቃም ምናልባትም ሩቅ ባልሆነ ግዜ ሁለቱም ሀገራት ኢትዮጵያ በሜዲትራኒያን አቅራቢያ በሞሮኮ የናቫል ቤዝ ሊኖራት በተመሳሳይ ሞሮኮም በቀይ ባህር ዙሪያ የወታደር ሰፈር የሚኖራት ይሆናል።

በመጨረሻም ይህ የኢትዮጵያ አስደናቂ የወታደራዊ ዲፕሎማቲክ አካሄድ ሁለት የግብፅ ታሪካዊ ባላንጣ የሞሮኮና ኢትዮጵያ ልዩ አስተማማኝ ጥምረትን የፈጠረ ሲሆን ከፈረሰ መንግስት ጋር ኢትዮጵያ ላይ ያሴረችውን ግብፅን ምትይዝ ምትጨብጠውን አሳጥቷታል።

ታዳጊው ይበልጣል_ኤልያስ ለብሔራዊ ቡድን ተመረጠ💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥በስፔኑ ባርሴሎና B1 Soccer Academy በመሰልጠን ላይ የሚገኘው ታዳጊው ኮኮብ ይበልጣል ኤልያስ በአሰልጣኝ ስዩም ከበ...
21/09/2024

ታዳጊው ይበልጣል_ኤልያስ ለብሔራዊ ቡድን ተመረጠ

💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥

በስፔኑ ባርሴሎና B1 Soccer Academy በመሰልጠን ላይ የሚገኘው ታዳጊው ኮኮብ ይበልጣል ኤልያስ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ተመርጦ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ተቀላቅሏል።

ይበልጣል ኤልያስ በላሚኒ ያማል ደረጃ ያለ የነገ ተስፋችን ነው።
አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የነገ የእግር ኳስችን ተስፋ የሆነውን ምርጡን ታዳጊ በማየትህ ልትመሰገን ይገባል።

27/08/2024

የአየር መንገዱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል በተባሉ 6 ግለሰቦች ላይ የምርመራ ማጣሪያ 14 ቀን ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በተጠረጠሩ 6 ግለሰቦች ላይ የምርመራ ማጣሪያ የ14 ቀን ፈቅዷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትናንት ከሰዓት በኋላ በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ጊዜ ቀጠሮ መዝገብ የተካተቱ 6 ግለሰቦች ላይ የፌደራል መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን የጥርጣሬ መነሻ እና በተጠርጣሪ ጠበቆች በኩል የተነሱ የመከራከሪያ ነጥቦችን መርምሮ ነው ዛሬ ተጨማሪ ምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ለፖሊስ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በማመን የ14 የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ የፈቀደው።

በዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ፣ ኤልያስ ድሪባ ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ነው ምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ የተፈቀደው።

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሰራር በመጣስ፣ የአየር መንገዱን ደህንነት አደጋ ላይ ለመጣል፣ የደህንነት ባለሙያዎችን በተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረጽ አየር መንገዱ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ማቅረቡ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በተጠርጣሪ ጠበቆች በኩል ደንበኞቻቸው በዕለቱ ለጉዞ ወደ መቐለ ለመሄድ በተዘጋጁበት ወቅት በረራው በመዝግየቱ ተበሳጭተው የተፈጠረ አለመግባባት እንጂ የሽብር ተልኮ ይዘው አይደለም የሚልና ፖሊስ ያቀረበው የጥርጣሬ መነሻ የሽብር ተግባሩን የማያሟላ እና የፍትሕ ፖሊስንና የወንጀል መርሕን ያልተከተለ ነው የሚል የመከራከሪያ ነጥብ አቅርበው ነበር።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ጅምር የፖሊስ የምርመራ መዝገብን በማስቀረብና በመመልከት እንዲሁም ተጠርጣሪዎቹ ቅዳሜ ዕለት በመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ምድብ በተመሳሳይ ቀርበው የ20 ሺህ ብር ዋስ ስለመፈቀዱ የሚገልጽ ማረጋገጫ በጠበቆች እንዲቀርብ በማለት ማረጋገጫውን ተመልክቶ ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት መዝገብ መቅረባቸው እንጂ በሽብር ወንጀል በፌደራል ፖሊስ በኩል ያልቀረቡ መሆኑን አረጋግጧል።

በዚህም ፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎች ላይ ለተጀመረው ምርመራ ማጣሪያ ጊዜ መስጠት እንደሚያስፈልግ በማመን የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

በታሪክ አዱኛ

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ===============አድስ አቡባ ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ቢሮ በስሩ በሚገኙ ጤና ተቋማት ለ712 ጤና ባለሙያዎች አድስ የሥራ ማስታወቂያ አውጥቷል።በጤናው ዘ...
27/08/2024

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
===============
አድስ አቡባ ከተማ አስተዳደር ጤና አጠባበቅ ቢሮ በስሩ በሚገኙ ጤና ተቋማት ለ712 ጤና ባለሙያዎች አድስ የሥራ ማስታወቂያ አውጥቷል።
በጤናው ዘርፍ የተመረቃችሁት ዕድሉን ተጠቀሙ።

 ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሰርኩላር አስተላልፏል።በዚህም ...
20/08/2024



ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትን በተመለከተ የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሰርኩላር አስተላልፏል።

በዚህም ሰርኩላር ፥ መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ባደረገው የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ምንዛሬ በገበያው አማካኝነት እንዲወስን ማድረጉ እና ይኸው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ መደረጉን አስታውሷል።

ማሻሻያው የገቢ ንግዱን በይበልጥ እንዲያሳልጥ ወደ አገር እንዳይገቡ በሕግ ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች፣ የነዳጅ አውቶሞቢሎች እና ከፀጥታና ከደህንነት ዕቃዎች ውጪ ሌሎች ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ አገር እንዲገቡ በመንግሥት የተወሰነ መሆኑና ይኸው ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስቧል።

 🚨ከተ.መ.ድ የጤና ኤጀንሲ እንደተገኘው መረጃ በቅርቡ ኤምፖክስ (Mpox) ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ፦- በጎረቤታችን ኬንያ ፣ - በቡሩንዲ ፣ - በሩዋንዳ - በ...
15/08/2024

🚨

ከተ.መ.ድ የጤና ኤጀንሲ እንደተገኘው መረጃ በቅርቡ ኤምፖክስ (Mpox) ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ፦
- በጎረቤታችን ኬንያ ፣
- በቡሩንዲ ፣
- በሩዋንዳ
- በኡጋንዳ ተገኝቷል። ሀገራቱም ሪፖርት አድርገዋል። በነዚህ ሀገራት ውስጥ የታየው በሽታ በኮንጎ ካለው ጋር የተገናኘ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Mpox በሽታ የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት ነው።

ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት/ መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።

አሁን ላይ #ዋነኛዎቹ ናቸው የሚባሉት ሁለቱ የቫይረሱ ዝርያዎች Clade 1 - በማእከላዊ አፍሪካ ውስጥ ያለ ፤ Clade 1b - እጅግ በጣም አደገኛ የሆነው አዲስ የቫይረሱ ዝርያ ነው።

የመረጃ ምንጫችን:-

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
05/08/2024

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ😭

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

05/08/2024
ዛሬ የሚደረጉ የኢትዮጵያዊያን አትሌቲክስ ውድድሮች !    ⏰ ማታ 02:02የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያተወዳዳሪዎች - አትሌት ጌትነት ዋለ ፣ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው እና አትሌት ለ...
05/08/2024

ዛሬ የሚደረጉ የኢትዮጵያዊያን አትሌቲክስ ውድድሮች !

⏰ ማታ 02:02

የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ

ተወዳዳሪዎች - አትሌት ጌትነት ዋለ ፣ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው እና አትሌት ለሜቻ ግርማ

⏰ ማታ 04:10

የሴቶች 5000 ሜትር ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች - አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ፣ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና አትሌት መዲና ኢሳ

⏰ ማታ 04:45

የሴቶች 800 ሜትር ፍፃሜ

ተወዳዳሪዎች - አትሌት ወርቅነሽ መሰለ እና አትሌት ፅጌ ድጉማ

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን ! 🇪🇹❤️

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ አትሌት ፅጌ ዱጉማ እና አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ወደ ፍፃሜ ማለፍ ችለዋል::አሰልጣኟ ወደ ኢትዮጵያ የተባረረባት  አትሌት ፅጌ ዱጉማ ውድድሯን1:57:47...
04/08/2024

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ አትሌት ፅጌ ዱጉማ እና አትሌት ወርቅነሽ መሰለ ወደ ፍፃሜ ማለፍ ችለዋል::
አሰልጣኟ ወደ ኢትዮጵያ የተባረረባት አትሌት ፅጌ ዱጉማ ውድድሯን1:57:47 በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት በመግባት በድንቅ ብቃት ለፍፃሜ አልፋለች ።

የ800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:45 የሚደረግ ይሆናል።

KAWO            የኢትዮጵያ ልጅ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
04/08/2024

KAWO
የኢትዮጵያ ልጅ🇪🇹🇪🇹🇪🇹

04/08/2024
04/08/2024
ቢኒ💚💚
02/08/2024

ቢኒ💚💚

02/08/2024

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

የአፍሪካ ሻፒዮኗ ቤቴል ወልዴ ትሞሸራለች💚💚💚እንኳን ደስ አለሽ እህታችን🇩🇪🇪🇹🇩🇪🇪🇹🇩🇪
01/08/2024

የአፍሪካ ሻፒዮኗ ቤቴል ወልዴ ትሞሸራለች💚💚💚
እንኳን ደስ አለሽ እህታችን🇩🇪🇪🇹🇩🇪🇪🇹🇩🇪

ከሰላዲን ሰይድ ፣ ሽመልስ በቀለ ፣ ዑመድ ኡኩሪ፣ ጋቶች ፓኖም እና አቤል ያለው በመቀጠል በግብፅ ሊግ የሚጫወት ስድስተኛ ተጫዋች የወላይታ ድቻው ወጣቱ አጥቂ ቢኒያም ፍቅሬ ሆኗል 👌ቢኒያም ፍ...
30/07/2024

ከሰላዲን ሰይድ ፣ ሽመልስ በቀለ ፣ ዑመድ ኡኩሪ፣ ጋቶች ፓኖም እና አቤል ያለው በመቀጠል በግብፅ ሊግ የሚጫወት ስድስተኛ ተጫዋች የወላይታ ድቻው ወጣቱ አጥቂ ቢኒያም ፍቅሬ ሆኗል 👌

ቢኒያም ፍቅሬ 🤝 እሰማኤሊ

© Soccer Ethiopia

ጌድኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በወቴ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ  አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል😭😭😭  እሁድ 21/2016 በገዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በወቴ ቀበሌ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በ...
28/07/2024

ጌድኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ በወቴ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል😭😭😭

እሁድ 21/2016 በገዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በወቴ ቀበሌ በደረሰው የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

የትራፊክ አደጋ የደረሰው ከጠዋቱ 3:30 አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር 30552 ኢ ት የሆነ ተሳቢ ከሞያሌ የአፈር ባዳበርያ ጭኖ እየተጓዘ ሳለ ሁለት እግረኞችን ገጭቶ ወደ ገደል ውስጥ የወደቀ ሲሆን የሾፌሩም ህይወት ወዲያው ልያልፍ ችሏል።

ፈጣሪ በምህረቱ ይጠብቀን፣ ይቅርም ይበለን!😭🙏

 #8091 ኢትዮ ቴሌኮም ከጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና  ዝግጁነት ጋር በመተባበር በተከሰተወሰ የመሬት ናዳ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጊያ ይፋ ያደረገው ቁጥር ነው
24/07/2024

#8091

ኢትዮ ቴሌኮም ከጎፋ ዞን አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጋር በመተባበር በተከሰተወሰ የመሬት ናዳ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጊያ ይፋ ያደረገው ቁጥር ነው

Address

Gununo Hamus City
S**o

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Asaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category