16/11/2023
በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚካሄደው ዘጠነኛው "የከተሞችን ቀን" ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ
ህዳር 06/03/2016 ዓ/ም በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚካሄደው ዘጠነኛው "የከተሞችን ቀን" ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።
በከተሞች ዘላቂ ልማት እና ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚሰናዳው ሀገራዊ የከተሞችን ቀን በወላይታ ሶዶ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኘውን የወላይታ ሶዶ ከተማ በሀገር ደረጃ የሚከበረውን የከተሞች ቀን በጋራ እና በውጤት ለመፈጸም የሚያስችል ፍሪያማ ውይይት መካሄድ ነው የተገለጸው።
ለዘጠነኛ ጊዜ የሚዘጋጀው የከተሞች ቀን በወላይታ ሶዶ ፍፁም ሰላማዊ ፣ አስደሳች እና ልማትን አስቀጥሎ እንዲከበር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተሳታፊዎች አስረድተዋል።
በከተሞች መሀከል ጤናማ የውድድር መንፈስ በመፍጠር እና የከተማ ዘርፍ አመራሮችን በማቀናጀት ተፈላጊውን ልማት ለማምጣት ያስችላል ነው የተባለው።
ለነዋሪዎች ምቾት ፣ ፅዳት እና ውበት እንዲሁም የመሰረተ ልማት ተደራሽ ተሞክሮዎችን በመጋራት ከተሞች በልማት ጎዳና ለመገስገስ ዕለቱ ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተገልጿል።
በመድረኩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን ጨምሮ የሶዶ ከተማ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።