21/03/2019
ጥናታዊ ጽሑፍ ለምታዘጋጁ #ተመራቂ ተማሪዎች ስለምትሠሩት Proposal እና Research ትንሽ እገዛ
------=================--------
እንዴት ናችሁ? በመጀመሪያ ደረጃ የሚመርጡት የጥናት ርዕስ መነሻውና መድረሻውን ሥነፍኖት በትክክል የተረዱትን መሆን ይገባዋል። ጥናታዊ ጽሑፍ መጨረሻ መታወቅ ያለበት ውጤቱ ነው እንጂ ሂደቱ መሆን የለበትም። ህደቱን ገና ከመጀመሪያው በትክክል እና በግልጽ (Accurately and clearly) መረዳትና ማወቅ ለውጤታማነት ተገቢ ነው። የጥናቱ ንድፈ ሀሳብ (Proposal) በሚገባ የሚመራ መንገድ መሆን አለበት። ጥናትን በተመለከተ ምሁራኑ የሚሉትን አንድ ታላቅ ገለፃ ላስታውሳችሁ "A research is as good as its propsal" -(የአንድ ጥናት ጥሩነት እንደ ንድፈ ሀሳቡ/ዕቅዱ/ ጥሩነት ይታወቃል) እንደማለት ነው። በመሆኑም የተወሰነ ምክረ ሃሳብ እገዛ ለማድረግ ጥቂት ነገር ላስታውሳችሁ። ልብ ሊባል የሚገባው ግን የግል ድጋፍ እንጂ የተቋም ይፋዊ format እያሳወቅሁ አለመሆኑን ነው።
#1ኛ. ፦ ርዕስ ለመመረጥ የመጀመሪያው ትኩረት ከሙያዎት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ያስተውሉ። ከዚህ ባለፈ ሙያዎትን ተጠቅመው በአካባቢዎ ባለው ማህበረስብ ውስጥ ያለውን ችግር በመፍታት አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉበት ቢሆን ይመረጣል። ከዚህ አንጻር "ይህንን አይነት መፍትሔ ብሠራለትስ" የሚሉትን ችግር መርጠው አጭር እና ገላጭ የሆነ የጥናት ርዕስ መምረጥ ነው። ከተቋሙ አካባቢ ወጣ ያሉ ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ርዕሶች መሆንም ይችላሉ።
# 2ኛ. # Introduction_to_your_title ፦ በዚህ ርዕስ ሥር ስለ ጥናቱ ርዕስ ምንነት ገለጻ ማድረግ ነው። በዚህ ርዕስ ሥር የሚያካትቷቸው ይዘቶች defnitions, theories, materials used, tests, methods, constructions systems, types, ..... የመሳሰሉት ቢሆኑ መልካም ነው።
#3ኛ. ፦ ይህ ደግሞ ስለሚያጠኑት ጥናት ታሪካዊ ዳራ/አመጣጥ (hisorical status) ገለጻ ማድረግ ነው። [who start investigate first, which country use, improvement (ማን ጀመርው? የት ቦታ? መቼ? በምን ተጀምሮ ወዴት ተሻሻለ all improvements፣ አሁን የት ደረሰ፣ .....) የሚሉትን የርዕሳችሁን ታሪካዊ ጉዞ አሁን እስካለበት ድረስ ብቻ የምታስቀምጡበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ እርስዎ ሊጨምሩበት ወይም ሊቀይሩት ወይም ሊያስተካክሉት የሚችሉበትንም ጎን ጠቆም ማድረፍ መልካም ነው።
#4ኛ. ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
#5ኛ. {General and Specific}፦ ጠቅላይ/ዋና ዓላማ ከአንድ ዓረፍተ ነገር ባይበልጥ ከበዛ ደግሞ ከሁለት በላይ እንዳይሆንይመከራል። በዝርዝር ዓላማ (specific objectives) የሚቀመጡት ደግሞ በዋና ዓላማ ዉስጥ የሚገኙ በጥናቱ መከናወን የሚታወቁ የተለያዩ መልሶችን ታስቀምጣላችሁ።
#6ኛ. # Scope_of_the_Research ፦ ይህ የሚገልጸው የጥናትችሁን ስፋተ-ሜዳ ነው። ምን ምን እንደሚያጠቃልል ወይም እንደሚዳስስ፣ ምን ምንን ደግሞ እንደሚተው /እንደማያጠቃልል/ ከነምክንያቱ፣ ለምን አይነት ተግባር የሚውል እንደሆነ ... በአጠቃላይ የጥናቱን መጠነ-ስፋት ወይም ይዘት የሚያስረዳ ይሆናል።
#7ኛ. # Litrature_review ፦ [በርዕሱ ዙሪያ እስካሁን የተጠኑ ጽሁፎች ምን ብለዋል?] “ማን የተባለው ሰው በየትኛው መጽሐፉ/ጥናቱ የትኛው ገጽ ላይ ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ምን ብሏል?“ የሚለውን መረጃ የያዘ ነው። በ"Litrature" ሥር የሚያካትቱት የቀደሙ ህትመቶች ማስረጃ ከእርስዎ ጥናት ጋር ተያያዥ ሀሳብ ያላቸውን ብቻ ነው። እርስዎ የማይዳሡትን ነገር በዚህ ርዕስ ሥር ማስገባት ከማንዛዛት እና ትርጉም አልባነት አያልፍም፣ ይልቁንም ሥራዎትን ውጤት (value) እና ተቀባይነት (acceptance) ሊያሳጣ ይችላል። በዚህ ሥር የሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች reference specification [books, quastionary, journals, published apers, recorded interviews, vedio evidences] መሆን አለባቸው እንጂ guide specification [oral speeking, internet notes, handouts, non published documents] ላይ ያገኙትን ነገር ባይጠቀሙ ይመከራል። የተጠቀሙትን ምንጭም ከነመገኛ ገፁ አብረው ዋቢ ማስቀመጥም ተገቢ እና ግዴታ ነው።
# 8ኛ. # METHODOLOGY ፦ ይህ ደግሞ ዋናው የጥናት ሂደት መረብ ነው። ትናቱ የሚከናወንበት አካባቢ (study area)፣ ናሙና የሚወሰድበት የናሙና አወሳሰው ሥነዘዴ - ሥነዘዴው የተመረጠበትን ማስረጃ ምክንያት ጨምሮ (sampling system)፣ ከንድፈ ሀሳብ እስከ ፍጻሜ ያለውን የሚያሳይ የጥናቱ መነሻና መድረሻ ፍሰት (research deign - ብዙ ጊዜ በ"Chart" ሊገለፅ ይችላል) መካተት አለባቸው። ከዚህ በተጨማሪ ቤተሙከራዊ ጥናት (Experimental research) ከሆነ የተለያዩ የቤተሙከራ ፍተናዎች (laboratory tests) የሚሠሩበት ስለሆነ የሚሰሩት ሙከራዎች (tests) የሚያስፈልጉ መሥሪያ ነገሪች (materials), መሥሪያ መሳሪያዎች (equipments), የሙከራ ሂደቶች (procedures to be used) የሚሉት ይዘቶች በግልፅ መታወቅ አለባቸው።
ከቤተሙከራ ውጪ ከሆነ ደግሞ አንዳንዶቹ ተግባራዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፍልስፍናዎች ስለሆኑ የሚጠቀሙትን ሂደት ማስቀመጥ ተአቢ ነው። (ምሳሌ ~ መኪና መሥራት፣ በፀሀይ ጉልበት የሚሰራ ባቡር መሥራት ሊሆን ይችላል)።
በሌላ በኩል Theoretical or statistical data analaysis ላይ የተመሰረቱ ጥናቶች ከሆኑ ደግሞ የሚጠቀሟቸው የቃለመጠይቅ ጥያቄዎች (interiview questions)፣ የሚያስሞሉት የሰነድ ጥያቄ (questionair formats for data statistics)፣ የሚጠቀሟቸው የኮምፒዉተር ፕሮግራም (softwares to be used)፣ የሚፈልጉት ስታቲካዊ መረጃ (statistic data)፣ የሚሳተፉት ባለድርሳዎች (participants /responsible bodies)፣ የጥናት ማመዛዘኛ መንገድ (analaysis statics method..) የመሳሰሉትን ማካተት ተገቢ ሲሆን ይህ "Methodology" የሚባለው ክፍል አንድ ሰው በየትኛው ሥነዘዴ እንደሠራ የክንውን ሂደቱን የሚያስቀምጥበት ክፍል ነው።
# NB ፦ እነዚህ ከላይ ያሉት በሙሉ በንድፈ ሀሳብ ሰነድ (proposal document) ላይ ጭምር መስፈር ኣለባቸው ሲሆኑ ቀጥሎ ያለው ተራ ቁጥር 9፣ 13፣ 14 ብቻ ግን ጥናቱ ከተጀመረ በኋላ የሚካተቱ ክፍሎች ናቸው።
# 9ኛ . # RESULT_AND_DISCUSSION ፦
# RESULT [ፕሮጀክቱ የሚሰራው በTEST ከሆነ የተገኘውን ዉጤት፣ theory ከሆነ የ[intrview, questionaier, system documented data, real and visual application,...] የሚያሳዩትን ዉጤት/አኳኋን ማስቀመጥ ነው
# DISCUSSION [ከተገኘው ውጤት አንጻር ለእያንዳንዱ ውጤት ሙያዊ ማብራሪያ እና የማሻሻያ ድጋፍ ሀሳብ ማስቀመጥ የሚጠበቅብዎት ክፍል ነው። [discuss weather the result implies good or bad accourding to proffesional point of view based on standards, laws, codes, contract agreement document, principles, softwares ... and put your proffesional solution for failures in the results]
# 10ኛ. # Beneficiariers_of_your_project_output {may not mandatory}፦ ጥናቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጠቃሚ አካላት እነማ ናቸው። [may be scientists, teachers, students, farmers, gevornment, contractors, or all ethiopians or world.... as per your study scope]
# 11ኛ. # Desimination_of_output [i.e. how you make available your study paper for users? May be by puting at different libraries, publishing and posting on google, by training.....]
#11ኛ. የማጥኛ ጊዜ ሰሌዳ (Schedule)
# 12ኛ. የሚያስፈልገው በጀት (Bedjet/cost)
# 13ኛ . # Conclusion
# 14ኛ . ፦ [this should be not advice rather it is the measure to be taken for problems and organaizatinal failures based on your proffesional know how!]
#15ኛ.
#16ኛ.
#ምንጭ፦
√… Research Methodology, Addis Ababa Univerity