16/09/2020
“በሽኸት/አብዓላ ከተማ የተፈፀመው ድርጊት አሳፋሪ፣ ሃላፊነት የጎደለውና ፍፁም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው”ሲሉ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነብዩ ስሑል ሚካኤል ገለፁ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሽኸት ከተማ የመቻቻል፣ የመፈቃቀርና የአንድነት ከተማ እንጂ የብሄር ነጋዴዎች፣ ሴረኞችና ቁማርተኞች እንደሚመኙት የመለያያና የግጭት ከተማ አይደለችም።
ቅድምያ ለሰላም፣ ለመቻቻልና ለአብሮ መኖር ይሁን፤ አጥፊዎችም በአፋጣኝ ለፍርድ ይቅረቡ።
ለሟቾች ዘለአለማዊ እረፍት፤ ለቤተሰብ ደግሞ መፅናናትን እመኛለሁ ሲሉ ሃላፊው ገለፀዋል።