Jimma Apostolic Church Students Union

Jimma Apostolic Church Students Union ወንድማማችነት!

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅንሽ!በመልካም ፀባይ ፣ ትህትና ፣ ለአገልግሎት ባላት ፍቅርና ተጨዋችነቷ የሚትታወቀዉ እህታችን እህት ፅዮን ካሳ ነገ ትሞሸራለች። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስ...
18/11/2023

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅንሽ!
በመልካም ፀባይ ፣ ትህትና ፣ ለአገልግሎት ባላት ፍቅርና ተጨዋችነቷ የሚትታወቀዉ እህታችን እህት ፅዮን ካሳ ነገ ትሞሸራለች።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ለእህት ፅዮንና ወንድም ግርማ አማዶ መልካም የትዳር ዘመን እንዲሆንላችሁ ይመኛል።

እንኳን ደስ አለሽ!በጅማ ዩኒቨርስቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በመልካም ፀባይ ፣ ትህትና ፣ በትጉ አገልግሎቷ እና በማስተባበር የምትታወቀው እህታችን እህት ዮሃና ታደሰ ነገ ...
11/11/2023

እንኳን ደስ አለሽ!
በጅማ ዩኒቨርስቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በመልካም ፀባይ ፣ ትህትና ፣ በትጉ አገልግሎቷ እና በማስተባበር የምትታወቀው እህታችን እህት ዮሃና ታደሰ ነገ ትሞሸራለች።
የተማሪዎች ህብረት ሙሽሮቹን ወ/ካሌብን እና እህት ዮሃናን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸዉን እንኳን ደስ ያላችሁ ልላችሁ ይወዳል።
የተባረከ የትዳር ዘመን ይሁንላችሁ።

ከ1995 - 2014 ዓ/ም ድረስ የተመረቁትን ያገናኘ ድንቅ ፕሮግራም!የቀድሞ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ምሩቃንን (ከ1995 - 2014) እና አሁን በመማር ላ...
15/06/2023

ከ1995 - 2014 ዓ/ም ድረስ የተመረቁትን ያገናኘ ድንቅ ፕሮግራም!
የቀድሞ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ምሩቃንን (ከ1995 - 2014) እና አሁን በመማር ላይ ያሉትን ተማሪዎች ያገናኘዉ Grand GetTogther በከፍል ይህን ይመስል ነበር።

ደረሰ!Ready?Misganaw Michael    Misganaw Belete
23/05/2023

ደረሰ!
Ready?
Misganaw Michael
Misganaw Belete

Grand GetTogether!🔵 ልገናኙ ነዉ! 🔵በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሩ የቀድሞ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የተማሪዎች ህብረት ወንድሞች ከረጅም ጊዜ በኋላ እነሆ ልገናኙ ነዉ።...
10/05/2023

Grand GetTogether!
🔵 ልገናኙ ነዉ! 🔵
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተማሩ የቀድሞ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የተማሪዎች ህብረት ወንድሞች ከረጅም ጊዜ በኋላ እነሆ ልገናኙ ነዉ።
ቀን ተቆረጠ! ግንቦት 25&26, 2015 ዓ.ም በጅማ እናት አጥቢያ እንገናኝ።

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ!በጅማ ዩኒቨርስቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በመልካም እና አስተማሪ ህይወቱ ለብዙዎች ምሳሌ የነበረው ወንድማችን  #ወንድም ብስራት ጉድሶ Bísr...
20/01/2023

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ!
በጅማ ዩኒቨርስቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት በመልካም እና አስተማሪ ህይወቱ ለብዙዎች ምሳሌ የነበረው ወንድማችን #ወንድም ብስራት ጉድሶ Bísrê Gùúd እነሆ ልሞሸር ነዉ!

ወ/ብስራት በቅንነት ያገለገልከዉ አምላክ የትዳር ዘመንህን በዘርፈ ብዙ በረከት ይባርክ!

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት መልካም የትዳር ዘመን እንዲሆንልህ ይመኛል!

15/01/2023
💥በዓይነቱ ልዩ ኮንፈረንስ በጅማ አጥቢያ!💥በዚህ ታላቅ ኮንፈረንስ ተገኝተው እንዲባረኩ በአክብሮት ተጋብዘዋል!እርሶም ለሚወዱት ሰዉ ይህን ልዩ ግብዣ ይጋብዙ!
31/12/2022

💥በዓይነቱ ልዩ ኮንፈረንስ በጅማ አጥቢያ!💥
በዚህ ታላቅ ኮንፈረንስ ተገኝተው እንዲባረኩ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
እርሶም ለሚወዱት ሰዉ ይህን ልዩ ግብዣ ይጋብዙ!

18/09/2022

መርካቶ ሳሌም አጥቢያ የመዝሙር ፌስቲቫል

07/07/2022

Live from Yoseph

26/06/2022

2014/2022 GC STUDENTS GOOD-BYE (Well-Go)

 #ክፍል-2እኚህ ታላቅ ሰው በአሜርካን ሀገር የሚገኘው Christian life college የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ተሸልሟል። በ1993 ዓ.ምበካናዳ ሀገር ከሚገኘው ከጄነስስ ኢንስቲትዩት የ...
24/06/2022

#ክፍል-2

እኚህ ታላቅ ሰው በአሜርካን ሀገር የሚገኘው Christian life college የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ተሸልሟል። በ1993 ዓ.ም
በካናዳ ሀገር ከሚገኘው ከጄነስስ ኢንስቲትዩት የስነመለኮት ትምህርት ተከታትሎ ሦስተኛ ድግሪውን The mystery of God revealed እና mentally arrested by the myth of psychotherapy በተባሉ ርዕሶች የምርምር ጽሑፉን በማቅረብ
በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ አድናቆትን ተችሯቸዋል።(ምንጭ:የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን መክሊት የመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት 4-6ኛ የምረቃ መጽሔት በገጹ ሽፋን ላይ) በኢትዮጵያ ምድር የሐዋርያት ወንጌል እንዲስፋፋ ያደረገው ትግል እንዲህ በጥቂት ገጾች ተጽፎ የሚበቃ አይደለምና ክብር ይገባቸዋል ታሪካቸው ከቤተክርስቲያን ታሪክ ጋር በእሳቸው የተሰራው የኢየሱስ ሥራ ሲወሳ ይኖራል።
“የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? ” ዘካ 4፥10 ከእሳቸው ጋር መንፈሳቸውን ደግፈው ከተነሱ በጣት በሚቆጠሩ አባቶች
የተጀመረው ይሄው እንቅስቃሴ ዛሬ ከ7 ሚሊዮን በላይ የአንድ
አምላክ ልጆችን ከአለም ዙሪያ አስተሳስሯል ዛሬም ተቀጣጥሎ
ቀጥሏል፡፡

ዶክተር ቢሾፕ ተክለማሪያም አንድ ወቅት ጣሊያን አገር ለህክምና በሄደቡት ሀክሙ ፕሮፌር "ተክሌ እረፍት ማድረግ አለብህ " ስሏቸው እሳቸው ስመልሱለት "እኔ የማርፈው ወደኢየሱስ ስሄድ ብቻ ነው " እንዳሉ በተወለዱ በ85 ዓመታቸው በወርኃ ሰኔ 15ቀን 2014 ዓ.ም በክብር ከሥጋ ድካም አረፈው ወደ ኢየሱስ ተሰብስበዋል፡፡

ዶክተር ቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኸኝ በውድ ባለቤታቸውና የወንጌል ሥራ ባልደረባቸው በእህት እርቅነሽ ሰጋሮ መካነመቃብራቸው ላይ ያሰፈሩትን የግጥም ማስታውሻውን ከአዋሳ ከተማ እናት አጥቢያ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ቅጥር ግብ ውስጥ ከሚገኘው በስልኬ ካሜራ ካነሳሁት በመጻፍ ልጨርስ

ስምሽ ከመቃብር በላይ ነው

እርቅነሽ ሕያው ነሽ
አልሞትሽም በህይወት ትኖሪያለሽ
መስከረም 15 ቀን 87 ከሥጋ ድካም ተለየሽ
አንቺስ እንደተመቸኘሽ አረፍሽ
ለ47 ዓመት ዕድሜሽ
የ25 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ሩጫሽ
መቶ ዓመት የማያልቅ ተግባር ፈጸምሽ
ለትቀን ያለእረፍት ለፋሽ
ውጭ ደምሽ አልቆ ሥጋም ከዳሽ
ድካምሽ በዝቶ አደቀቀሽ
የሁሉ እናት ስንቱን አዘልሽ
ሁሉን ረዳሽ ሁሉን ባረክሽ
የማይሞት ነው የአንቺ ሥራ
ሕያው ፍሬሽ ባለም በራ
ነቢይት ነበርሽ እንደህልዳና
ነቀፋ የሌለብሽ እንደሐና
ከአምላክሽ የመጡ ትንቢቶችሽ
ተፈጸሙ እንጂ እያየሽ
እርቅነሽ አንቺ መቼ ሞትሽ
ሕያው ናቸው ሥራዎችሽ
እኔም አለብኝ ውለታሽ
በሕልፈት የማልረሳው ትዝታሽ
መልካም ነበርሽ ለነፍስ ለሥጋዬ
የምወድሽ የማከብርሽ ባልንጀራዬ
ላይሽ እመጣለሁ
ይናፍቀኛል ጥሪሽ
ቄስ ተክለማርያም ገ.

🖌ተጻፈ በወ/ም ሕዝቅኤል ጴ.

 #ጥቂት ስለ ዶ/ር ቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኸኝ (ክፍል 1)ላይሽ እመጣለሁ ይናፍቀኛል ጥሪሽ(ከቄስ ተክለማርያም ገ. )ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው...
24/06/2022

#ጥቂት ስለ ዶ/ር ቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኸኝ (ክፍል 1)
ላይሽ እመጣለሁ
ይናፍቀኛል ጥሪሽ(ከቄስ ተክለማርያም ገ. )

ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?” ኢዮብ 9፥12

ዶክተር ቢሾፕ ተክለማሪያም ገዛኝ የተወለዱት በአድዋ አውራጃ በአምባሰይነይቲ ወረዳ ልዩ ቦታ ጮማ እምኒ ሚያዝያ 11 በ1929 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በልጅነታቸው ብዙ የሕይወት
ውጣውረድ ያጋጠማቸው ሲሆን በዘመድ ቤት ሆነው በአድዋጨከተማ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወር 15ብር ከመንግሥት እየተከፈላቸው ተከታትለው በከፍተኛ ማዕረግ አጠናቅቀዋል።
ቀሪውን ሕይወቱን በሙሉ እግዚአብሔርን የመፈለግ ጥሪው ገና በ14 ዓመት ዕድሜው የመጣለት በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት አንገቱን ወደመንፈሳዊ አዙሮ አንድ ወጣት ጓደኛው እሱንና መጽሐፍ ቅዱስን አስተዋወቀው መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ 2 የጥንቷ ቤተክርስቲያን ክርስቲያኖች እንደተሞሉ ነገረው ተክሌም ጥማት አደረበት ፍለጋውን ይቀጥልና ከብዙ ምኞትና ፍለጋ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ተሞሉ። በ1960 ዓ.ም በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በጥልቅ ውኃ ተጠምቀ (ትምህርተ መለኮት ገጽ 33) በመቀሌ በወሎ በወልዲያ በሰሜኑ ክፍል አንድ ብሎ የጀመረው የወንጌል እንቅስቃሴ ወደኤርትራ ተሻግሮ የእስራት ገፈትም ገና ቅምሻ የጀመረባቸው ከመጀመሪዎች አከባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው። ጥቅምት 5 ቀን በ1957 ዓ.ም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ በኅዳር 5 ቀን የመጀመሪያውን በኢየሱስ ስም ጠርቶ ተአምራት
ድንቅ አየ:: በሉተራን መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ለአራት ዓመታት ቲዮሎጂን ተከታትለዋል። ቀጥሎም በናዝሬት (አዳማ )በሚገኘው በሜኖናይት መጽሐፍ ቅዱስ አካዳሚ ተከታታይ ሁለት ዓመታት የክረምት ትምህርት ተምረዋል። ግማሽ ምዕተ-ዓመት የሚጠጋ ዓመታትን ቤተክርስቲያንን ከኢየሱስ እጅ በታች የበላይ ጠባቂ በመሆን መርቷል። ደርዘን(12)
የስነመለኮት መጽሐፍትን ለትውልድና ለቤተክርስቲያን አበርክቷል። በርካቶች በእንግሊዝኛ በአማርኛ በኦሮሚኛና በትግሪኛ ትርጉም የእሱ ሥራዎች ለአንባቢያን በቅቷል።

1.መለኮታዊ ኃይል በ1961

2.እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል ?

3.ጥያቄዎቻችሁና መልሶቻቸው

4.ትምህርተ-መለኮት

5.አዲስ ልደት

6.መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለጀማሪዎች

7.መጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊያን ስነመለኮት(Bible writers
theology )

8.ኢየሱስን ማን ይሉታል

9.ቃሉ ይናገር

10.የመልዕክቶች አጠቃላይ ትምህርት

11.በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ በ1974

12.አንድ መንጋ የተሰኙ ድንቅ የስነመለኮት ጥናት የተካተተባቸውን መጽሐፍ ለትውልድ አበርከትዋል፡፡ የአንድ አምላክ ትምህርትና የስሙ ጥምቀት በአጥንታችን ሰርጎ እስኪገባ በደማችን እስክዋሄድ ዕድመልካቸው ሲናገሩ ኖረዋል። የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ናቸው ዘማሪ ናቸው የስነመለኮትፐአስተማሪና ተመራማሪ ናቸው የተዋጣለት ሰባኪ ናቸው ጸሐፊ ናቸው ቤተክርስቲያንን በዓለም አቀፉ ይዘት የመሩ መሪም ናቸው ፡፡ እኚህ ሰው ሁለገብ አገልግሎታቸው እንዲሁ በሰው ጥበብ የተገኘ ተስጥኦ ብለን መዋሸት አንችልም ከሰማይ አምላክ የተሰጠ ጸጋ ነው እንጂ። የጥንቱ መሰረት ዳግም በአንድ ሰው ልብ ተጸንሶ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ምሪት በግለሰብ ቤት የተጀመረውን የሐዋርያትን ትምህርት ሰንሰለት ከ82 በላይ በዓለም አገራት እንዲስፋፋ የራሳቸውን ጥረት አድርገው ለእግዚአብሔር ፍቃድ ተገዢ ሆነዋል።
ዶክተር ቢሾፕ ተክሌ የብዙ ሚሊዮኖች መንፈሳዊ አባት ለመሆን የበቁና በሥጋዊውም ከወንጌል አርበኛዋ ከእህት እርቅነሽ ሰጋሮ ጋር ለ25 ዓመታት በዘለቀው ትዳራቸው የ6 ልጆች አባት ለመሆንም በቅቷል። በሐዋሳ ከተማ አንድ ገበያ ላይ ባደረጉት ብርቱ በወንጌል ምስክርነት ምክንያት በቅናት የተሞሉ ሌሎች ቤተእምነት በእርቅነሽ እቅፍ የነበረውን ሕጻን ሙሴ ተክለማርያምን ደብድበውት ሕይወቱ አልፏል እናቲቱ እህት እርቅነሽም ጭንቅላቷን በዱላ ስለተመታች ደም ወደውስጥ ፈስሶ በራስ ምታት ለብዙ ጊዜ ታምማ በጸሎት የከፋ ጉዳት ሳይደርስባት ተርፋለች። መስከረም 15 ቀን 1987 ዓ.ም ተሰብስባለች ( #ይቀጥላል)

“ከሰማይም፦ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፦ አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ።”  — ራእይ 14፥13...
24/06/2022

“ከሰማይም፦ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፦ አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ።”
— ራእይ 14፥13
አዎ የትጋት ተምሳሌት ፣ የዋህ ፣ የእምነት አርበኛ ፣ ብዙዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ በር ፣ የእዉነተኛ ወንጌል መምህርና መሪ ዶ/ር ቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኸኝ እንወዶታለን! የሁልጊዜ ናፍቆቶ ወደሆነውና ከዚህ በእጅጉ ወደ ተሻለው ሀገር መሄዶ ያፅናናናል😭😭።
ለመላው የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን መፅናናትን እየተመኘን ቢሾፕ ተክሌ ህይወታቸውን በመስጠት በዉስጣችሁ ያኖሩትን ያልተቀየጠዉን የእዉነት ወንጌል ለሌሎች በማዳረስ እንድናስታውሳቸዉ ለማሳሰብ እንወዳለን።

08/06/2022

እንኳን ደስ ያለሽ እህት ፀጋ!በእግዚአብሔር ቤት አድገሽ ለዚህ ትልቅ ክብር ስለበቃሽና በህይወትሽ እግዚአብሔርን በማክበርሽ የተሰማንን ጥልቅ ደስታ በጅማ ዩኒቨርስቲ ሐዋርያዊት ተማሪዎች ህብረ...
14/05/2022

እንኳን ደስ ያለሽ እህት ፀጋ!

በእግዚአብሔር ቤት አድገሽ ለዚህ ትልቅ ክብር ስለበቃሽና በህይወትሽ እግዚአብሔርን በማክበርሽ የተሰማንን ጥልቅ ደስታ በጅማ ዩኒቨርስቲ ሐዋርያዊት ተማሪዎች ህብረት ስም ልንገልፅልሽ እንወዳለን። ቀሪው የትዳር ዘመንሽ የበረከት እንድሆን እንመኛለን።
እህት ፀጋ ጌንሣ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ ትምህርቷን በጅማ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተማረችና በፌሎ ቆይታዋም ለብዙ እህቶች እና ወንድሞች አርዓያ የሆነች እህት ናት።

እንኳን ደስ አለሽ!

ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥሪ👇
04/05/2022

ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥሪ👇

 #ጠቃሚ መረጃ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ አድስ ለተመደባችሁ የሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ተማሪዎች ጅማ ዩኒቨርሲቲ በስሩ 4 ካምፓሶች ያሉት ሲሆን እነርሱም፦1. ዋናው ግቢ (main campus )2...
27/04/2022

#ጠቃሚ መረጃ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ አድስ ለተመደባችሁ የሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ተማሪዎች

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በስሩ 4 ካምፓሶች ያሉት ሲሆን እነርሱም፦
1. ዋናው ግቢ (main campus )
2. የቢዝነስ እና ኤኮኖሚክስ ካምፓስ (BECO)
3. የግብርና እና እንስሳት ህክምና ካምፓስ (Agri )
4. የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ካምፓስ ናቸው። (Techno)

main campus እና BECO በአንድ ስፍራ የሚገኙና በድልድይ የተገናኙ ሲሆን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የግብርና ካምፓስ ደግሞ በአንድ አከባቢ በቅርብ ርቀት የሚገኙ ካምፓሶች ናቸው።
በኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን የጅማ ከተማ እናት አጥቢያ በBECO ካምፓስ ዉስጥ ልባል በሚችል ደረጃ ከBECO ካምፓስ አጠገብ ይገኛል።
ቴክኖ እና አግሪ ካምፓስ ከእናት አጥቢያው ከ4 እስከ 5 ኪ.ሜ ርቀት ውስጥ ሲገኝ በመሃል ከተማ ዉስጥ በመሆኑ የትራንስፖርት (Taxi) ችግር የለም።
ከእናት አጥቢያ በተጨማሪ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና አግሪ ካምፓስ አከባቢም ሰፋ ያለ ግቢ ያለዉ የአምልኮ ጣቢያም ይገኛል። በዚህ የአምልኮ ጣቢያ የቴክኖ እና አግሪ ካምፓስ ተማሪዎች በሳምንት ለአንድ ቀን የአምልኮ ግዜ ያካሄዳሉ።

ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፤ ሰፊው የጅማ እናት አጥቢያ እንዲሁም የተደራጀ የተማሪዎች ፌሎሽፕ እናንተን ለመቀበል ሁሌም ዝግጁ መሆኑን እናበስራለን።

ስለ ካምፓሶቹ ሆነ ስለ ጅማ እናት አጥቢያ መገኘ የሚከተለውን የgoogle map መስፈንጠሪያ በመጫን እንድትመለከቱ እናሳስባለን።

Apostolic Church of Jimma.
https://maps.app.goo.gl/sGc7xJNVDF1oaFEAA

ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!የጅማ አጥቢያ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አስተባባሪዎችን ለማግኘት የሚከተሉ...
27/04/2022

ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ-ክርስቲያን ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

የጅማ አጥቢያ ሐዋርያት ቤተክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት አስተባባሪዎችን ለማግኘት የሚከተሉ የስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም የሚያስፈልጋችሁን መረጃ በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ የሚትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።
+251913791509 (ወ/ ደረጄ)
+251916396011 (ወ/ ጥጋቡ)

03/04/2022

በጅማ ሰበካ የጊንቦ አጥቢያ ኮንፈረንስ

03/04/2022

ጊምቦ ኮንፈረንስ

16/01/2022

ወ/ደረጄ ከበደ

16/01/2022

የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም

15/01/2022

የገባራ ጎባ ንዑስ ሰበካ መዘምራን

15/01/2022

የከሰዓት ፕሮግራም

15/01/2022

ጅማ ኮንፈረንስ

Address

Ajip
Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jimma Apostolic Church Students Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Jimma Apostolic Church Students Union:

Videos

Share

Category


Other Podcasts in Jimma

Show All