ቱሪናፋ

ቱሪናፋ collect all of you guys have to do something about the new album and the other side.

 #የጥልቁ  #አገልጋዮችቃል ኪን የሚባል ቀደም ሲል በጌታ የነበረ አሁን ደግሞ በዘፋኝነት ሉሲፈር የቀባው ወጣት በሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ቀርቦ ቃለ ምልልስ ሲደረግለት ተመለከትኩ። በቅርቡ ...
17/05/2022

#የጥልቁ #አገልጋዮች

ቃል ኪን የሚባል ቀደም ሲል በጌታ የነበረ አሁን ደግሞ በዘፋኝነት ሉሲፈር የቀባው ወጣት በሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ቀርቦ ቃለ ምልልስ ሲደረግለት ተመለከትኩ። በቅርቡ ታዋቂ እንዲሆን ምክንያት የሆነው የዘፈን ክሊፕም በዘጠኝ ቀናት ውስጥ በዩቲዩብ ከሁለት ሚልዮን በላይ ተመልካቾችን ስላተረፈለትም ለቃለ ምልልስ የክብር እንግዳ ሆኖ ቀረቦም ከተናገራቸው መካከል በጣም ያስገርመኝንና ልጁ የነፍስ ሽያጭ ከሉሲፈር ጋር እንዳደረገ የሚያሳዩ ቁልፍ አነጋገሮች ነበሩ። "አሁን ባለሁበት ሁኔታ ምንም ቅሬታ የለኝም በጣም ደስተኛ ነኝ"፣ "ማንም ሰው ሲያድግ የሕይወቱን አቅጣጫ ይመራልና እኔ ደግሞ የመረጥኩት መንገድ ይኼ ነው"፣ " በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እርሻ ለመማር ሄጄ ታምሜ ተመለስኩ ደግሞም የምወደው ትምህርት አልነበረም። ያልሞከርኩት የስራ ዘርፍ የለም አካውንታት ለመሆን ጭምር ሞክሬአለሁ ግን አልተሳካም የተሳካልኝ ሙዚቃ ነው" በሚል ሲናገር ሰይፉ "ይኼ የነፍስ ጥሪህ ነው" በማለት ሁለት ጊዜ ሲኔገረው ልጁም በአጽንዖት "አዎን ትክክል ነው" ሲል መልሶአል።
ይኽ የ 27 ዓመት ዕድሜ ያለው ወጣት ቀደም ሲል በጌታ ቤት ውስጥ እንዳደገ፣ ይዘምር እንደነበረና ከዚያም አልፎ በትምህርት ቤት ውስጥ የክርስቲያን ተማሪዎች ኅብረት (Christian Fellowship) ላይም የአመራር ኃላፊነት እንደነበረው ጭምጭምታ ሰምቼአለሁ። ስለ ዝማሬ አገልግሎቱም በርስ አንደበት ልጅ ሆኖ ይዘምር እንደነበር ቢናገርም ብዙ ዝርዝር ከመናገር ይልቅ አሁን ስላለበት የጨለማ ሕይወት አስደሳችነት ሊናገር ችሎአል።
ቃል ኪን የሚለው ደስታ በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ገንዘብ በማግኘት፣ በዝና፣ ምድራዊ ስኬት ያለበትን እነዚህን ደግሞ በማምጣት የሚጠፋ ደስታ ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ልጆቹ ለሆኑት ከሚሰጠው ደስታ ጋር ሰማይና ምድር የሚለያይም ነው። ጌታ ኢየሱስ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ዓለም እንደሚሰጣችሁ አየደለም እንዳለው ዓይነት ነው። ከውስጥ የሆነና በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ማግኘት ቢሆን ማጣት፣ መከራ ቢሆን ተድላ፣ ረሃብ ቢሆን ጥጋብ፣ በሽታ ቢሆን ጤና ምንም የማይበግረው ደስታና ሰላም ነው።
ቃል ኪን ምድራዊና ጊዜያዊ እንደውም ውጭያዊ ደስታን የሚሰጠው ሕይወቱ የዘፈን ስራው፣ የሕዝብ ጭብጨባና ገንዘብ ሲሆን ይኽንን ሁሉ ደግሞ የዚህ ዓለም ገዢ ለመንግስት ሰራተኞች የሚሰጡው ሽልማት ነው። ሉሲፈር ደግሞ ሲክዱት ነጥቆ አፈር ከድሜ የሚያስግጥ ነው።
ዘፈን ኃጢአት ነው ስንል የጨባጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ አለን። የዮሐንስን አንገት ያስቀላው የመልካም ልደት በዓል ጭፈራ (Happy Birthday Party) ዘፈን ነው። ዘፈን ለተቃራኒ ጾታ፣ ለአገር በአጠቃላይ ለፈጣሪ ሳይሆን ለፍጡር የሚቀርብ አምልኮ ነው። ዘፈን፣ ስካርና፣ ዝሙትን፣ አመጻን፣ ቅንዐትን፣ ድብድብን፣ ጭንቀትን፣ ክፋትን ሌላም በርካታ የአማጻ ስራዎችን የያዘ ነው።
ለአብነት ያህል ማይክል ጃክሰን ስለነበረው የነፍስ ሽያጭ ኮንትራት ሲኔገርና ያም ሲቁዋረጥ ሕይወቱን ሉሲፈር እንደቀጠፈው ይታወቃል። ሌላም ገና በአስራዎቹ ዕድሜ ያለ ### Tentacion የተባለ ዘፋኝ ይዘፍናቸው የነበሩ ዘፈኖች በርካታ ወጣቶች ለአእምሮ ሕመም እንዲዳረጉና ራሳቸውን እንዲያጠፉ ምክንያት ሆኖአል። ዘፈኖቹም "ሕመም፣ ጭንቀትና ተስፋ መቁረጥ፣ ጭንቀት ጉዋደኛዬ ሲዖል መኖርያዬ የሚል መልእክት ይላቸውና ትውልዱን ለአጋንንት እስራት ያጩ ናቸው።
(ስለቴንታሲዮን ከወራት በኁዋላ በሚታተመው መጽሐፌ ላይ በመጠኑ ገልጩዋለሁ)
ሉሲፈርን አናገርኩት የሚለውን ይኽንን ዘፋኝ ገና በ 19 ዓመቱ ገደማ ሉሲፈር በሞት መስዋዕት አድርጎታል።
ታዲያ ዛሬ ዘፋኞች መድረክ ላይ እየወጡ ፈታኝ ወድቃችሁ ብትሰግዱልኝ ይኽንን ሁሉ እሰጣችኁዋለሁ ብሎ ዓለምን ያሳያቸውን የጨለማው ገዢ ያደረገላቸውን ተዓምራት ሊነግሩን መድረኩን ይይዛሉ።
ከእነዚህም መካከል ቃል ኪን አንዱ ነው። ብንቀብልም ባንቀበልም ስማቸውን ራሱ የሚሰይመው የጨለማው ገዢ ነው። በውስጣቸው የስያሜ ሃሳብ እንዲቀመጥ ያደርጋል ወይም በማኅበረሰቡ ይኽንን ቅጥል ስያሜ በስማቸው ላይ ታኮ አድርጎ ያስገባል።
ሉሲፈር መንግስቱ እንዲሰፋ ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ዘፈን ስለሆነ ለራሱም ክብርን እየተቀበለ ሌሎችንም በዘፈን ወደ ነፍሳቸው ይደርሳል። ለታሰዙት ዘፋኞች ደግሞ በየደረጃው ከፍ ያደርጋቸዋል።
ዛሬ ሉሲፈርን እንደ ጌታቸውና ንጉሳቸው ከተቀበሉት መካካል ሕዝብን ወደ ሲዖል የሚነዱለት ዘፋኞች በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ።
በተለይ ደግሞ እንደ ቃል ኪን ጌታን አውቀው የተዉት በእግዚአብሔር መንግስት ላይ ለማመጽ ቀድሞውንም ጌታን ከማያዉቁት ይብሳሉ።
አሁንም ቢሆን አብ ያልተከለው ይነቀላል። በአሸዋ ላይ የተሰራ ቤትም ይፈርሳል።
ወዮ ለይሁዳ ምንም ቢሆን ጴጥሮስን መሆን ይሻላልና ቃል ኪን ቃልኪዳንህን ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አድስ። የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ክቡር ነው። ረግጠኽው የሄድከው የእግዚአብሔርን ልጅ ደም ነውና ንስሃ ግባ። ውስጤ በቁጣ እንድገስጽህ እንጂ በመለላለስ እንድ ምክር አልነገረኝም። ድካም ነው ለሚሉ ክህደት ድካም ሊሆን አይችልም ሰይፉ እንዳለው የነፍስ ጥሪ እንጂ። ጴጥሮስን መሆን ይሻልሃል አሊያም ነፍስ ግን ያስገዛህለት ሉሲፈር ነፍስህን ለሲዖል እንዳጨህ በጊዜውም ወደ ገሃነም ያደርስሃል።
"እሺ ከዛስ" ብለህ ቪድዮህን እንደሰይምከው ከዚያማ ሲዖልና ገሀነም ነው ወይም ገነትና መንግስት ሰማያት ነው።

ርቱዕ የሆነውን የወንጌል መረዳት ይዘናል የሚሉ ክርስትያኖች (Reformed) እውነቱን የሚያስፋፉበት መንገድ ምንድነው? በየዘመኑ የሚመጡትን ማናቸውንም የቴክኖሎጂ መንገዶች አሟጦ መጠቀም ተገ...
16/05/2022

ርቱዕ የሆነውን የወንጌል መረዳት ይዘናል የሚሉ ክርስትያኖች (Reformed) እውነቱን የሚያስፋፉበት መንገድ ምንድነው? በየዘመኑ የሚመጡትን ማናቸውንም የቴክኖሎጂ መንገዶች አሟጦ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ከነዚህ መንገዶች በላይ አስፈላጊ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን መንገድ የዘነጉ ይኖራሉ፡፡ ስለዚህም ሪፎርምድ ክርስትና ሀይማኖት ያላቸው አንዳንዶች ምናልባትም ብዙዎች ባለንበት ቤተ ክርስትያን ለውጥ እንዲመጣ መስራት እንጂ ጥሎ መውጣት ስህተት ነው ይላሉ፡፡ የዚህን አመለካከት ችግሮች በጥቂቱ እንመልከት፡- 1) ሊሳካ የማይችል አላማ ይዘዋል፡፡ ባለፉት በርካታ አመታት በዚህ አካሄድ የተሳካለት አለመኖሩ ብቻ ሳይሆን የራሱንም አቋም ያለዘብ ብዙ ነው፡፡ የዚህ አካሄድ ያስገኘው ውጤት ካለ ማሳያው መቅረብ አለበት፡፡ እንዲህ ሲባል ግን ሙሉ ለሙሉ የሰባኪነቱ ሀላፊነት የያዘ ከሆነ ምናልባት ሊሳካ ቢችልም ከአጥቢያ አያልፍም፡፡ ይህን እድል ያገኘ ሰበኪ ሊጠቀመው ይገባል፡፡ 2) አለመታዘዝ ውስጥ ናቸው፡፡ ትክክለኛ ትምህርትና አካሄድ የሌላቸውን ልንለያቸው እንደሚገባ 2 ቆሮንቶስ 6፡14 ያዛል እንጂ በውስጥ ሆኖ ለመለወጥ የተሰጠ ተልዕኮ የለም፡፡ ይህ የውስጥ ለውስጥ አካሄድ ክርስትያናዊ ሳይሆን የፖለቲከኞች ይመስላል፡፡ 3) ከበረከት ያጎድላል፡፡ መዝሙር 133 የወንድሞች ስብሰባ ያለውን በረከት ይናገራል፡፡ ጤናማ ያልሆነ ቤተ ክርስትያን መቆየት ከበረከት ያጎድላል፤ ስብሰባው በእውነተኛ መንፈሳዊ ወንድማማችነት ላይ አልተመሠረተምና፡፡ ስለዚህ የሪፎርምድ ሀይማኖት ተከታዮች በያሉበት በመሰባሰብ ቤተ ክርስትያኖችን በማብዛት ርቱዕ የሆነውን የወንጌል ትምህርትና አካሄድ መደገፍ አለባቸው፡፡

🙏🙏🙏🙏🙏 🙏🙏🙏🙏🙏 #አሜሪካ ውስጥ የ15 አመት ታዳጊ ሱቅ ሲሰርቅ ከዛም ሊያመልጥ ሲል አንዱን መደርደሪያ ሰበረ ይህ ፍትሃዊ ዳኛ የሰጠው ፍርድ!!ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ...
16/05/2022

🙏🙏🙏🙏🙏 🙏🙏🙏🙏🙏
#አሜሪካ ውስጥ የ15 አመት ታዳጊ ሱቅ ሲሰርቅ ከዛም ሊያመልጥ ሲል አንዱን መደርደሪያ ሰበረ ይህ ፍትሃዊ ዳኛ የሰጠው ፍርድ!!
ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰማ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው።
"በእርግጥ የሆነ ነገር ሰረቅክ? ዳቦና አይብ ሰርቀህ መደርደሪያ ሰባበርክ?"
ልጁም አንገቱን ደፍቶ በአፍረት መለሰ፡-
አዎ.
ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?"
ታዲጊው ልጅ: በጣም ፈልጌው ነው
ዳኛ፡ ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር?
ልጅ፡ ምንም ገንዘብ አልነበረኝም።
ዳኛ፡ ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ ትችላለህ።
ልጅ፡ እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናቴን ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ።
ዳኛ፡ እና አንተ… ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም?
ልጅ፡- የመኪና ማጠቢያ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ ለዚህም ነው ያባረሩኝ።
ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡-
“ሌብነት በተለይም #ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አለ።
በመቀጠልም ሁሉም ተሰብሳቢዎች አሥር ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም. ዳኛው ከኪሱ የ10 ዶላር ቢል አንሥቶ እስክሪብቶ አወጣና እንዲህ ብሎ መጻፍ ጀመረ።
"በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1,000 ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እና ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል."
በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ለልጁ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት። ዳኛው እንባውን ለመደበቅ እየሞከረ ከችሎቱ ወጣ። ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ።
ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና ህብረተሰብ ሊያፍር ይገባል” ሲሉም አክለዋል።

ዘማሪ ተመስገን ማርቆስ እና ባለቤቱ ሲሳይ እንኳን ለ 10ኛ የጋብቻ በዓላችሁ አደረሳችሁ “ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀ...
14/05/2022

ዘማሪ ተመስገን ማርቆስ እና ባለቤቱ ሲሳይ እንኳን ለ 10ኛ የጋብቻ በዓላችሁ አደረሳችሁ
“ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።”
— ዘፍጥረት 29፥20

እባካቹእግዚአብሔር የማያይ አይምሰለን🏥     ለሌሎች እንድደርስ ሸር ያድርጉት🇪🇹🇪🇷                     እስከመቼ እንታገስ    የሌላውን  ቤተሰብ  እየበተንክ  የሌሎችን  ቤት ...
28/04/2022

እባካቹእግዚአብሔር የማያይ አይምሰለን🏥
ለሌሎች እንድደርስ ሸር ያድርጉት🇪🇹🇪🇷
እስከመቼ እንታገስ
የሌላውን ቤተሰብ እየበተንክ የሌሎችን ቤት እያራቆትክ የሌላውን ልጅ እያቀጨጭክ አንተም እግዚአብሔርን እንደሚያውቅ ሰው "ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው" ስትል ትንሽ አታፍርም በየቦታው ወልደህ የተውካቸው ልጆችህስ ?
የስንቱን ቤት እና ትዳር ያፈረስክበት ክፉ ስራህስ ?
ልጆቼ የምትላቸውንስ በሜያውቁት ነገር የምታበላቸው እና የምታቀናጣቸው የደም ገንዘብ እና እርም አስበህበት ታውቃለህ ?
ለነገሩ ያንተን ልብ በደንብ እናውቀዋለን "እኔ ከሞቱኩ ሰርዶ አይብቀል" እንዳለችው አህያ በልተህ ለመሞት የተፈጠርክ ሆዳም እና ሀሸተኛ ሰው እንዴት አንተ ይሄንን ቃል መናገር ወይንም መስበክ ትችላለህ ?
የዕውር ድንብር ይሉሀል እንዲህ ነው ።
አይቀርም እግዚአብሔር የደሆችን እምባ ቆጥሮ በአደባባይ ያዋርድሀል ።

በ ቱሪናፋ ሕዝቡ እስከመቼ ይጭበረበራል።
ሀሳባችሁን ስጡበት ።
ስለዝህ ቱሪናፋ ብዙ ያልተሰሙ ያልተባሉ ሚስጥሮችን ወደ እናንተ በስፋት ያደርሳል ከእናንተ የሚጠበቀው follow ,like, comment and share ማድረግ ብቻ ነው። እናመሰግናለን !!

 #እግዚአብሔር ለወንጌል አገልግሎት ረጅም ጫማ እንድለብስ አዞኛል ያለው አወዛጋቢውን  #የቶጎ ፓስተር እያነጋገረ ነው።😂😄🙄🤔 የእነርሱ አምላክ ብዙ ነገር  ይላል፡፡ #እግዚአብሔር ግን እንደ...
26/04/2022

#እግዚአብሔር ለወንጌል አገልግሎት ረጅም ጫማ እንድለብስ አዞኛል ያለው አወዛጋቢውን #የቶጎ ፓስተር እያነጋገረ ነው።😂😄🙄🤔
የእነርሱ አምላክ ብዙ ነገር ይላል፡፡

#እግዚአብሔር ግን እንደዚህ አይልም፡፡
እንኳን ለአገልግሎት ሴቶችን እንኳን ብትጠይቋቸው ለብዙ ሰዓት አይጠቀሙትም ምቾት የለውም ያማል፡፡

#የእኔ ሀሳብ ይሄ ልምምድ የነገ ነገ እኛም መንደር እንዳይገባ ነው ልምምድ ሁሉ አይቀዳም እኛ ሀገር ያሉ አንዳንዶች ሁሉንም እንዳለ እንደመለኮት ድምፅ እየቀዱ ስለሚወስዱ ነው

#እንደተረቱ ማለት ነው፦ ህፃን ልጅን ከነ..... እንደሚባለው ናቸው
ሁሉ አይወሰድም፡፡
ሀሳባችሁን ስጡበት ።
ስለዝህ ቱሪናፋ ብዙ ያልተሰሙ ያልተባሉ ሚስጥሮችን ወደ እናንተ በስፋት ያደርሳል ከእናንተ የሚጠበቀው follow ,like, comment and share ማድረግ ብቻ ነው። እናመሰግናለን !!

አንተ  በገስት  ሀውስ  የገባውን  ሁሉ  ፋይል  እና  ፕሮፋይል  እየሰበሰብክ  በየ  አጥቢያው  የመረጃ  ሰብሰቢ  ልጆች  አደራጅተህ  ነው  የምታገለግለው  አንተ  እኮ  ገስት  የገቡ ...
26/04/2022

አንተ በገስት ሀውስ የገባውን ሁሉ ፋይል እና ፕሮፋይል እየሰበሰብክ በየ አጥቢያው የመረጃ ሰብሰቢ ልጆች አደራጅተህ ነው የምታገለግለው አንተ እኮ ገስት የገቡ ሰዎች ለመረጃ ካልተመቹክ ዘይት ብቻ ቀብተህ ነው የምትልካቸው ብቻ ግን አንዳዶቹን የምትሸውድበት እስተዬል ተመችቶኛል ።
ወንዱንም ሴቷንም ነብይ ነሽ ትላለህ
ወንዱንም ሴቷንም መንፈሳዊ አባትሽ ነኝ ትላለህ
አሮጊት እና ሽማግሌውን ሁሉ መንፈሳዊ ልጄ ትላለህ
በተለያየ ጥያቄ የሚመጡትን የውሸት የማታደርገውን ቃል ትገባ እና መረጃቸውን ገስት ሀውስ ከተቀበልክ በኋላ ቆይ ቸርች ነው የምፀልይላቹ እያልክ ትጫወትባቸዋለህ ።
ለምሳሌ :- የኔ የጓደኛዬ እህት መስከረም 27 ገስት ብትገባ ሁሉንም ሰው እየሸኘ እሷን ግን 4 ቀን አስቀምጧት ቀስ እያለ ፀሎት ክፍል እያስገባ የውሸት ጨዋታ እያስመሰለ በየዋህነት ብዙ መረጃ ከተቀበላት በኋላ በማግስቱ በራሱ መኪና ቸርች ልኳት ስለቤተሰቦቿ ስለ እህት ወንድሞቿ ስም ስለባለቤቷ ስም ባለቤቷ ስላለበት ችግር ሁሉ በነገረችው መሠረት ጌታ እንደነገረው አድርጎ ይሄንን ነውር ፈጸመ ።
በዚያ ላይ ገና በጌታ ሁለት አመቷ ነው ባለቤቷ አሁንም በጌታ አይደለም 2 ልጅ አላቸው ስራ ተበላሽቶባቸው ብዙ እዳ ውስጥ እንደገቡ እና ያለባቸው እዳ ቤታቸውን ሊያሸጣቸው እንደሆነ ነግራው ነበረና በጉባኤ ፊት ትንቢት ብሎ ከቀለደባት በኋላ መጨረሻ ላይ አፏን ይዛ አሜን ብላ እንድትሄድ ቀስ ብሎ በጆሮዋ እዳውን እኔ እከፍልልሻለው ብሎ በጩኸት እና በለቅሶ አሳብዷት ሚዲያውን እና ጉባኤውን አሞቀበት ከዚያ በኋላ ግን ብዙ ተመላለሰች ጋርዶቹ ብዙ ናቸው ልታገኘው አልቻለችም ።
በጣም የሚያሳዝነው የጋብቻ ቀለበቷን ሸጣ እሱን ለማግኘት ገስት ስትገባ ሌላ ውሸት ዋሽቶ ሸኛት ከዚያ በኋላ ግን ተስፋ ቆርጣ ቤት ቀርታ በለቅሶ እያለች ሌባው ሀሰተኛው ጌታ ተናገረኝ እያለ በቴሌቪዥኑ ሲያስተላልፍ ገበናዋን የተመለከቱ ሁሉ ምን ጉድ ነው የባለቤትሽን ይህን ሁሉ ጉድ ተሸክመሽ እያሏት አሳቀቋት
ባለቤቷ ደግሞ ይሄንን ነገሩት እና አይንሽን እንዳላይብሏት ጥሏት ትዳሩንም በትኖ ይኸው 3 ወር የት እንደገባ አይታወቅም እንግዲህ ለነብያቶች ሁሉ ነብይ ነኝ የሚለው ነብይ እስራኤል በአጭሩ እንዲህ አይነት ነጋዴ ነው ።
ወገኖቼ በዚህ አይነት የስንቱ ቤት ትዳር ኑሮ እንደፈረሰ ልብ በሉ መቼም እኔ እዚያው አፍንጫቸው ስር ስላለሁ ገና ብዙ ጉድ አስነብባችኋለው ።
በ ቱሪናፋ ሕዝቡ እስከመቼ ይጭበረበራል።
ሀሳባችሁን ስጡበት ።
ስለዝህ ቱሪናፋ ብዙ ያልተሰሙ ያልተባሉ ሚስጥሮችን ወደ እናንተ በስፋት ያደርሳል ከእናንተ የሚጠበቀው follow like comment and share ማድረግ ብቻ ነው። እናመሰግናለን !!

ግልጽ ደብዳቤ ለወይዘሮ ሃና:-ይደርስ በጌታ ለተወደድሽው እህቴ ሃና (ሃኒቾ)፣የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛልሽ።ከሰላምታዬ ቀጥዬ የማሳስብሽ ነገር ቢኖር ባለቤትሽ ሐዋርያ እስራኤል ዳንሳ በግሪጎርያ...
18/04/2022

ግልጽ ደብዳቤ ለወይዘሮ ሃና:-

ይደርስ በጌታ ለተወደድሽው እህቴ ሃና (ሃኒቾ)፣

የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛልሽ።
ከሰላምታዬ ቀጥዬ የማሳስብሽ ነገር ቢኖር ባለቤትሽ ሐዋርያ እስራኤል ዳንሳ በግሪጎርያን አቆጣጠር በ2016 ለአገልግሎት በድንገት የቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ከተከሰተበት ዕለት አንስቶ ለብዙዎች ግራ መጋባትን እየፈጠረ በመገኘቱና በእግዚአብሔር ስም በድፍረት የሃሰት ትንቢትን ተዓምራትን አደርጋለሁ እያለ ሕዝብን እያደናበረ በመሆኑ በምክርና በተግሳጽ ልምምዶቹን ለማስቆም እንድትሞክሪ ለመንገር ነው።
በአሜሪካን አገር በ2017 ከኦክቶበር እስከ ዲሴምበር በነበረው የአገልግሎት ቆይታ ወቅት ባለቤትሽ ባዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ የመካፈል ዕድሉ ነበረኝ። በተደጋጋሚም ባዘጋጃቸው ፕሮግራሞች ላይ ተሳትፌአለሁ። አንድ አብሮት የነበረ አገልጋይ አንድም ቀን ሲጸልይ እንዳላየውና "ለምን አትጸልይም?" ብሎ ሲጠይቀው "የእኔ ትንቢትና አገልግሎት በጸሎት አይሰራም" የሚል ምላሽ እንደ ሰጠው ነግሮኝ "ምን ሲሰራ ነው የሚያድረው? ስለው እንቅልፍ እንደሌለው ስልክ ላይ እንደሚያሳልፍ ሲነግረኝ መረጃ ስብሰባ እንደሚሆን ባላረጋግጥም ገምቼ ነበር።
በአንዱ ፕሮግራሙ ላይ ለአንዲት ሴት ብቻ ለ02:40 ሰአት ያህል የተጠና ትንቢት ሲናገር ብዙ ጥያቄ በውስጤ ያጫረ ሲሆን እንዲህ ዓይነት ልምምድ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አላነበብኩም።
በስቴዲየም አርመሪ ዲሲ ጂሰስ ወንደርፉል ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ ጉባኤ ውስጥ አነጋግሮኛል። ከዚያም ባለፈ ስልክ እንድደውልለትም ነገሮኝ ነበር እና በሌላ ጊዜም ከሌላ ፓስተር ጋር አብረነው ስታርባክስ ቡና እየጠጣን ስለ አገልግሎቱ ተወያይተናል። እርግጥ ቅንነት፣ የዋህነትና ደግነትን ተመልክቼበታለሁ ንገር ግን አንዳንድ እንግዳ የሆኑ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ግራ እንድጋባ አድርገውኝ ነበር። ሆኖም ግን ገና ከዓለም እንደመጣና ቀድሞ የነበረው የጭፈራ ቤት ባህርይ ሊሆን ይችላል በሚል በመጠኑ ለመገሰጽ ብሞክርም የሚሰማ ሰው ሆኖ አላገኘሁትም ነበር። ከዚያም በመቀጠል አሜሪካን አገር ውስጥ በሶስት ወራት ውስጥ አምስት ቦታ ቤተ ክርስቲያን ቢተክልም ከስመዋል። ለምን? የሚለውን እንተወውና በበርካታ ሰዎች ዘንድ ተጭበረበርን፣ የሃሰት ትንቢት አመጣልን፣ ቦርሳችንን ከፍቶ በወረቀት ላይ የጻፍነውን የጸሎት ርእስ አንበበና የውሸት ትንቢት አመጣልን የሚሉ በርካቶች ናቸው።
ኢትዮጵያ ውስጥም ገስት ሃውስ በከፍተኛ ደረጃ የመረጃ ሰብሳቢዎቹ የሰዎችን መኝታ ቤት እየከፈቱ "ፓስፖርትና መታወቂያ የተለያዩ መረጃዎችንም ይወስዳሉ" የሚል አቤቱታ ለአመታት ባለማቁዋረጥ ይጎርፋል። ሰነዶች በስልኩ እንደሚያስተላልፍ ያለፈ ሁኔታን በፎቶና በቪድዮ እንደሚያነሳ ሌላም ብዙ ሃሰተኛ ልምምዶች እንዳሉት አይተናል። ያገኝውን ሰው ሁሉ በጌታ ያልሆነውን ጭምር 'ነቢይ ነህ" በማለት ዘይት ሰዎች ላይ በማፍሰሰ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ ያለ ልምድ ያለው ስለ ዘይት እንክዋን የማያውቅ ሰው ነው።
ነገር ግን በድርጊቱ ግራ በመጋባት "ሃሰተኛ ነው" ብለው ቀድመው የነቁ ቢኖሩም በርካቶቻችን "ይኽ ሰው ከጌታ ዘንድ ጥሪ አለው" ብለን በማመንም ብዙዎቻችን ተቀበልነው "በጊዜ ሂደትም ሕይወቱና አገልግሎቱ ይስተካከላል" በሚል ብዙዎቻችን ጠበቅን ወጀብ በተነሳበት ጊዜ "መጥፎ ድርጊት ፈጽሞአል" ብለን ላለማመን ጆሮአችንን ዘግተን "ምን ዓይነት ሰፊ ትከሻ አለው?!" ብለን አዘንለት። እነዚያ ከሳሾቹ ከእርሱ ጋር በጥቅም ትስስር ስለነበራቸው ተአማኒነታቸው በግምት 70/30 ያክል ነበር።
በስርቆትና በዝሙት ልምምዱም በርካቶች ይተቹታል። በየኔታ ቲዩብ በርካታ ቀድመውት ያገለግሉ ሰዎችም በእርሱ ላይ ብዙ መስክረዋል። ከዳይመንድ ስርቆት እስከ ቤትና ካርታ ዘረፋ፣ ምን የቀረ አለ?። "ጥቅም ሲቀርባቸው በአድማ ተነስተውበት ነው" እየተባለ ሲወራ ነበር። እርግጥ እንዲህ ዓይነት የሃሰት ምስክርነቶች ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ከቅርብ ጊዜ እየታዩ ቢሆንም ጥቂቶቹ ግን የእርሱን ማንነት በትክክል አስቀመጠዋል።
ይህንን ያኽል ወጀብ አልፎበት ዳግም አኮብኩቦ ሲነሳም "እውነትም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው" ተባለ። በስደት ለዓመታት ሳያይሽ የቆየውን ባለቤቱንና አራት ልጆቹንም ለማየት ዕድለኛ ሆነ። ነገር ግን ይኽ ሰው አገልግሎቱ እንደ መሻሻል ፋንታ አሁንም ሰዎች ግራ በሚያጋባ አገልግሎት ለብዘዎች እንቅፋት ሆኖአል።
"በሕይወት ትኖራላችሁ ያላቸው ሲሞቱ፣ ሃብታም ትሆናላችሁ ያላቸው ሲደኽዩ፣ ገንዘብ እሰጣችኁዋለሁ ብሎ ቃል የገባላቸውን ሲክድ" ትንቢቱ በተቃራኒው በምውርት ሲሰራ እያየን ነው እና ይኼ ነገር ምንድን ነው?
ሃኒቾ ስለባለቤትሽ ሁሉንም ነገር ታውቂያለሽ ለማለት ባልችልም ከማንም በላይ ስለእርሱ አገልግሎት መሰል ግራ የሚያጋባ ልምምድ ግንዛቤ ይኖርሻል ብዬ እምናለሁ።
ሃኒቾ አንድ ጊዜ ቃለ ምልልስ ላይ እንዴት አንቺም በአነሳሱ ግራ ተግብተሽ እንደነበር፣ በሁኔታው መንፈስ ተሞላ ተብሎ ሲያጉዋራ በር ቀርቅረሽ ቆልፈሽበት ከቤት እንደወጣሽ ተናግረሻል።
ሃኒቾ ባለቤት የሚያደርገው ልምምድ ውስጥ ተሳታፊ ሁኚ አትሁኚ ለማወቅ ይከብዳል። ይኼ ሰው ግን ማንንም የማታለል ባህርይ ያለው ስለሆነ ይኽንን ሁሉ ዓመት አንቺንም አታልሎሽ ከሆነ እጅግ እገረማለሁ፣ አዝናለሁም። ግን አንቺ ከማንም በላይ ስለ እርሱ የማወቅ ዕድሉ አለሽ ብዬ አምናለሁ።
ሃኒቾ እርሱ በሃሰት አገልግሎቱ አንቺንና ልጆቹን የተንደላቀቀ ሕይወት ሊያኖር ቢችልም ሰው አለምን ሁሉ አትርፎ ነፍሱን ግን ቢያጎድልብምን ይጠቅመዋል? ሃኒቾ በጌታ ስም ተነግዶ የሚገኝ ገንዘብ መብላት እኮ እርም ነው። ሃኒቾ እናንተን ዱባይ ለማኖር ገንዘብ ከየት አመጣ? በ 45 ሚልዮን ብርስ ቤት እንዴት ሊገዛ ቻለ? ሃዋሳስ ላይ ያንን የሚያካ ግቢ ያለው ርስት ሃውስ እንዴት መግዛት ቻለ? ያንን ሁሉ ቪ8 መኪኔስ ከየት አመጣ? ሃዋሳስ ላይ የገዛው ትልቅ መሬት፣ አጠገቡ ላሉት ተባባሪዎቹ እንዳላወቀ ሰዉ የሚያስመስሉት ጋር እየበተነ ያለውስ ገንዘብ? ወላይታ ሶዶ ቃለ ሕይወት የገዛችውን ስፍራ በጨረታ በሚልዮኖች ብር ነጥቆ በፖሊስ ያስወጣቸውና ያስለቀሳቸው ሽማግሌዎችስ ጉዳይ እንዴት ነው? ለወንጌልስ እስከመሼ እንቅፋት ይሆናል?
እስኪ ይኼንን መልሽልን ሃኒቾ። ከባለቤትሽ የሚልቀው እውነተኛ ሐዋርያ ጴጥሮስ በዚህ ዘመን ቢኖር የአንቺና የባለቤትሽ ጉዳይ ምን ይመስልሻል?
ባለቤትሽ የተጠናከረ መዋቅር ያለው ዝርፊያ እየሰራ ነው? ወይስ ከጥልቁ ጋር ኅብረት አለው? ሳያውቅ እየተሳተ ነው? ወይስ የአምሮ ጤና እክል አለበት? ወይስ የሚያገለግለው ነጫት ሱስ በተከፈተ ጆሮው በሃሉሲኔሽን ነው? ልምምድ ምንድን ነው? ዘንዶ የሚያናግሩ ሰዎች ያሉበት ስፍራ የተወለደው ባለቤትሽ ምን ዓይነት መንፈስ እንዳለበትስ አረጋግጠሻልን?
ሃኒቾ እውነት አንቺ ጌታን የምትፈሪና በትክክል የምትከተይ ከሆነ ይኽንን ማውቅና መገሰጽ አለብሽ አለበለዚያ የእግዚአብሔር ክንድ በእናንተ ላይ ትከብዳለች።

ዕብራውያን 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁹ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?
³⁰ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፦ ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።
³¹ በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።

አክባሪ እህትሽ

ዜድ የክርስቶስ

10/04/2022
እውነት  ነው  ስራክ  ገና  አንገት  ብቻ  አይደለም  ነብስህንም  ያስደፋታል  የስንቱን  እንባ  እና  ደም  እንደ  መዥገር  እየመጠጥክ  ፈጣሪ  ዝም  የሚልህ  ይመስልሀል  ?እግዚአብ...
08/04/2022

እውነት ነው ስራክ ገና አንገት ብቻ አይደለም ነብስህንም ያስደፋታል የስንቱን እንባ እና ደም እንደ መዥገር እየመጠጥክ ፈጣሪ ዝም የሚልህ ይመስልሀል ?
እግዚአብሔር ዝምታው የንሰሀ ጊዜ መስጠቱ እንጂ አንተ እንደምታስበው ፈራጅ አምላክ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም እናንተ ሴሰኞች ጌታ ይገስጻቹ ።
ጉድ በል ጎንደር ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ አለ ያገሬ ሰው መቼም JW ሁሉም ከአባታቸው ከእስራኤል የተጋባባቸው የዝሙት መንፈስ አለባቸው ለዛሬ ግን ላወራቹ የፈለኩት የእፍረተ ቢሱ የኮርማው ዳዊት ዳንሳን ነው ።
ዳዊት ዳንሳ ማለት ኮርማነት ከቤታቸው ቢሆንም የሱ በጣም አይን ያወጣ ነው ታስታውሱ እነደሆን በዘጠናዎቹ አካባቢ የቤተሰብ ምጣኔን ለማስተማር ዲኬቲ ኢትዮጲያ አራርቀው ይውለዱ ይል ነበር ።
ታዲያ ዳዊት ዳንሳ ደግሞ በተቃራኒው አራርቆ ያገባል በእርግጥ የዳንሳ ልጆች በቁርጥ ሥጋ እና በጭን ስጋ አይታሙም እስራኤል ጭን ካየ በጉባኤ ቃል ይጠፋበታል ዳዊት ጭን ካየ በጎዳና መንገድ ይጠፋበታል በጣም መጥፎ ልክፍት ነው ።
አረ እንዲያው ደህና ዘመድ ኖሯቸው ጩፋ ጋር ወስደው አጋንታቸውን ባባረረላቸው አሊያም ደግሞ የሰሞኑን የመቃብር ዘበኛውን ነብይ ተብዬ ሲኦል ይሁን ገነት የሚገቡት በጠየቃችሁልኝ ።
ዳዊት ዳንሳ እና እስራኤል ዳንሳ ሹፌራቸውን ጨምሮ ዳሌ ያላትን ሴት ከአዲስ አበባ ጀምሮ በየ JW አጥቢያ ትዳር ያላት ትሁን የሌላት አግብታ የፈታች ሳትቀር ያልቀመሷት የለችም አንዳንዶቹን ተፈራርቀውባቸዋል አረ እንደውም አንድ ጊዜ ምስኪኗ ሀኒቾ እና ነብይ በረከት ሲነግሩኝ እኔ ሲምቦል ነኝ መኪና ፣ ቁርጥ እና ሴት የሚመርጥለት ማሙሽ እና ግዛው ናቸው ብላኝ ነበር መቼም እኔም ሴት ነኝ እና አዘንኩ ዳንሳ በእኔም ላይ በቂቤ ምላሱ እና በብጣሽ ቼክ የሰራኝ ይሄንን ጉድ ብልጭ አለብኝ ይህንን ስላቹ ለማመን ትቸገሩ ይሆናል እግዚአብሔር ሴትነቴን ይንሳኝ የማውቀውን ነው የምነግራቹ ባለፈው እንደነገርኳቹ ደካማ ጎኔን ተጠቅሞ እስራኤል በማይረባ ረብ የዛሬ አራት አመት ገደማ ታልዬለት ጉድ አደረገኝ በወሩ ደግሞ ወንድምየው ዳዊት ዳንሳ አይኑን በጨው ታጥቦ መጣ አንደኛው ኬብሮን ገስት ሀውስ ሁለተኛው ጋርመንት ገስት ሀውስ ጠየቀኝ የለመደች ጦጣ እንዲሉ ከቆይታ በኋላ የወንድሜ እጮኛ ለልጅ ጉዳይ ተጨንቃ ለኔም ሳትነግረኝ ከወንድሜ ተደብቃ ፉሪ ገስት ሀውስ ብትገባ 4 ቀን አሳድሯት ልጅ እንቢ አለን 3 አመታችን ነው ብትለው ቢሮውን ቆለፈ እና ነይ ብሎኝ ጨለም ወዳለ ክፍል አስገባኝ በጣም የሚያምር አልጋ አለ የክፍሉ ጠረን ያውዳል መብራቱ ደብዘዝ ያለ ነው ፊት ለፊቴ ቆሞ እንዲህ አለኝ ብር መቁጠር ሰለቸኝ አንቺ ዝም ብለሽ ቁጠሪልኝ ብሎ ከአራት ጥቁር ፌስታል መአት የታሰሩ ብሮች ዘረገፈልኝ እና እኔ ለሌሎቹ ፀልዬ እመጣለው አለና በላዬ ዘግቶ ወጣ ጨነቀኝ ፍርሀት ዋጠኝ አለችኝ እኔ ግን ጉዱን አውቀው ነበር ከዚያም ለ
ከምሽቱ 6 : 20 መጠሠ እና ከደከመሽም እዚሁ እንድትተኚ ብዬ ወደቤት ሄጄ ነበር ልክ ቤት ገብቼ ስፀልይ ጌታ ሂድ እና በአንተ ብልት ቀድሳት መንታ ትወልዳለች አለኝ አለች በቃ የቸገረው እርጉዝ ያገባል ይሉ የለ ይኸው ልጅም የለም ክብርም የለም በስነ ልቦና ከኔ የባሰ የወንድሜ ሚስት ተጎድታ ተቀምጣለች
በርግጥ ከገጠመኝ አንፃር እንዳልፈርድበት የእቃው ሸክም እራሱ አደጋ ነው እኔ እስራኤል ለ 30 ደቂቃ አግኝቶኝ ሰላሳ ቀን ነው ያስተኛኝ ይሄንን ደግሞ ከቤታቸው እንደሆነ ነግሮኛል ።
ታዲያ እንዲህ የሚግማሙት እነኚህ ሰዎች እስራኤል የ4 ህጋዊ እና በውጪ የሚቀለቡ የ 3 ልጆች በድምሩ የ 7 ልጆች አባት ነው ።
ዳዊት ዳንሳ ደግሞ ከቀድሞ ህጋዊ ሚስቱ 1 ልጅ ከአሁኗ ከረፈፍ ሚስቱ 2 ልጅ እና በየ ከተማው አራርቆ ከወለዳቸው መካከል አምኖ የተቀበላቸው 6 የካዳቸው 4 አድራሻቸው የማይታወቁ ቤት ይቁጠረው ይሄንን በራሱ አንደበት የሚያወራው ነው ።
አሁን እንኳን በቅርቡ ከዚያው ከ JW ያስቀመጣትን ቅምጥ ውለጂ አልወልድም ጭቅጭቅ ላይ እንዳሉ መረጃው አለኝ ምክንያቱም ቀድሞም ከሌላ ወልዳ ጥሎባት ስለሄደ ዳግም መውለድ አትፈልግም ሚስትህን ከፈታህ ግን እወልድልሀለው እንዳለችው ምንጮቼ ነግረውኛል ።

ጅማ  ላይ  ምን  ተፈጠረ  ?              🔥ማን ነው ገዳይ !! "እስራኤል  ዳንሳ"  በጅማ  ከተማ  በሀሰት  ትንቢት እና ቅጥረኞቹ  ባቀበሉት መረጃ  የምንወደውወንድማችንን ነብይ...
07/04/2022

ጅማ ላይ ምን ተፈጠረ ?
🔥ማን ነው ገዳይ !!
"እስራኤል ዳንሳ" በጅማ ከተማ በሀሰት ትንቢት እና ቅጥረኞቹ ባቀበሉት መረጃ የምንወደው
ወንድማችንን ነብይ ወንድዬን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፈውሼሀለው ይልሀል አንተ በጭራሽ ሞት አያይህም ነብይ ሳትሆን ሀዋሪያ ነህ ገና 700 ቸርች ይኖርሀል ጌታ ሀብታም አገልጋይ ትሆናለህ ብሎኛል ገና ገና ዓለማትን ሁሉ በወንጌል ትዞራለህ ብሎ በመድረክ ላይ አውጥቶት ቱሪ ናፋውን በመንፋት ጉባኤውን አስጩሆ እና አስጨብጭቦ በህዝብ እና በእግዚአብሔር ፊት ዋሽቶ ለፎቶ እና ለቪዲዮ መጠቀሚያ ሲያደርገው ወንድማችን ነብይ "ወንድዬ" በመረጃ መገልገሉ አልገባውም ነበርና የሚወደው እና የሚያገለግለው ጌታ የእውነትም የተናገረው መስሎት አሜን ብሎ ተቀብሎ ይህ የውሸቱ ትንቢት በተነገረው በስምንተኛው ቀን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ አሸልቧል ።
ይህ ሀሰተኛ ነብይ ነኝ ባይ ቱሪ ናፋው ሰው ከተናገራቸው እና ከተዋረደባቸው ንግግሮቹ ወይንም ውሸቶቹ ጥቂቱን ላሳያቹ :---
1ኛ . አንተ ነብይ አይደለህም ሐዋርያ ነህ ገና 700 ቸርቾችን ትተክላለህ በሀብት ትባረካለህ ያም አልበቃ ብሎት ሚስትህ ትቀባለች አብራቹ ታገለግላላቹ እያለ ቀባጠረ ።
2ኛ . እኔ ሆኜ ነው እንጂ ይሄ ትንቢት ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ ብሎ በሀሰት ትንቢቱ ሊኩራራ ቢልም በብዙዎች መቀለዱን ያየው እግዚአብሔር ግን እጅ ከፍንጅ አዋርዶታል ።
3ኛ . በጣም የባሰው አሳፋሪው ቱሪ ናፋው ለዓለም የተሾመ ሰው ጅማ ላይ ሞቶ አይቀርም እያለ ይንደቀደቅ እና ጉባዔውን ለማሳመን ፌኳ ነብይት ሀና ተብዬዋን ቁማርተኛ እንዲህ ይላት ነበር ሀኒቾ ጌታ እኮ ነው የሚለኝ እያላት ጉባዔውን ያጃጅለው ነበር ።
4ኛ . በጣም የሚያሳዝነው የሚያስቀውም ደግሞ እዚህ ጅማ ከተማ ላይ የሱ ጥያቄ ብቻ ተመልሶ ብሄድ እኔ አሸናፊ ነኝ አለ አያቹ የወንድዬም ጥያቄውም አልተመለሰም ተሸናፊነቱ እና ሌብነቱም ተጋለጠ ።
ይህ ጉዳይ የመጀመሪያው ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ጓደኞቹ ጥልቅ ሀዘን ሲሆን በጅማ ከተማ 90% ፐርሰንት አሕዛብ ባለበት ከተማ ላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ መሳለቂያ ሆኗል ................ ሕዝቤ ሆይ እባክህ ንቃ ።
🔥 እግዚአብሔር ሆይ ወይ ውረድ ወይ ፍረድ !!
ሆሴዕ ምዕ 4
6: ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
አያቹ ወገኖቼ እንዲህ አይነቱ ሀሰተኛ እና ቱሪ ናፋ ካህን ወይንም አገልጋይ መሆን አይችልም ለምን ቢባል የአምላኩን ህግ እረስቷል እና እኔም ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ እንደሚል ለልጆቹ መርገምን እና ጨለማን የሚያስቀምጥ የጨለማ ልጅ ማለት ቱሪ ናፋው እስራኤል ዳንሳ ነው ።
በ ቱሪናፋ ሕዝቡ እስከመቼ ይጭበረበራል።
ሀሳባችሁን ስጡበት ።

ቱሪናፋ  ሸንጋይ ነው ያልሆነውን ነው የሚል የሆነውን የሚክድ ሐሰተኛ የእውነት ጠላት የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ለህዝብ የማይራራ ዘራፊ ነጣቂ ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኛ የወንጀል ተባባሪ አመፀኛ ...
05/04/2022

ቱሪናፋ
ሸንጋይ ነው ያልሆነውን ነው የሚል የሆነውን የሚክድ ሐሰተኛ የእውነት ጠላት የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ ለህዝብ የማይራራ ዘራፊ ነጣቂ ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኛ የወንጀል ተባባሪ አመፀኛ ክፉ ብዙ እናቶችን ያስለቀሰ የብዙ አባቶችን ልብ የሰበረ እልፍ ወጣቶችን ያሳተ የህፃናትን አእምሮ በከንቱ ንግግር የሚሞላ በላባቸው ለፍተው ጥረው ግሮ ያከማቹ ሀብታሞችን እያጭበረበረ ከሌላቸው ድሆች ያችን ትንሿንም አራግፎ ወስዶ ባዷቸውን የሚሰዳቸው የብዙዎችን ትዳር የሚበጠብጥ እንዲሁም እግዚአብሔር የመሰረተውን ውብ ተቋም አፍራሽ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር ቱሪናፋ አማኞች ራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከዝህ ክፉ ተኩላ እንድትጠብቁ አደራችሁን እንላለን….ብቻ ውድ ተከታዮቻችን በአንድ ጀምበር መች ያልቃል ሰንቱንስ እንበላችሁ እንደው መግቢያ እንድሆነን ነው እንጂ …. ስለዝህ ቱሪናፋ ብዙ ያልተሰሙ ያልተባሉ ሚስጥሮችን ወደ እናንተ በስፋት ለማድረስ ተዘጋጅተናል ከእናንተ የሚጠበቀው follow like comment and share ማድረግ ብቻ ነው። እናመሰግናለን !!

Address

Hawassa
1245

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቱሪናፋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category

Nearby media companies


Other TV Channels in Hawassa

Show All

You may also like