Harari Mass Media Agency

Harari Mass Media Agency Harari Mass Media Agency is a public media operating in Harar, Ethiopia.
ገፃችንን በመከተል ትኩስ ዜና እና መረጃዎችን ያገኛሉ።

25/12/2025

በሐረር ከተማ የተጀመረ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በቀን ብቻ ከመስራት ባለፈ በምሽት ጭምር የመስራቱ ባህል እየጨመረ መቷል።

25/12/2025

በአቦከር ወረዳ እየተሰራ ላለው የውስጥ ለውስጥ ኮሪደር ልማት የአከባቢውን ነዋሪ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ነው፦ ሱልጣን ሳኒ

የአቦከር ወረዳ አስተዳዳሪ

ትህነግ ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ህዝብ ላይ እያሳየ ነው ******የትህነግ ቡድን ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀ...
25/12/2025

ትህነግ ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ህዝብ ላይ እያሳየ ነው
******

የትህነግ ቡድን ሕዝብን በርሃብ በመቅጣት ለፖለቲካ መሳሪያነት የመጠቀም ተግባሩን ዳግም በትግራይ ሕዝብ ላይ እያሳየ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) ተናገሩ።

የትህነግ ቡድን የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል በመጠለያ ማዕከላትና በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የሚያቀርበውን ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈለገው ዓላማ እንዳይውል እያደረገ እንደሚገኝም የሰሞኑ የህፃፅ መጠለያ ጣቢያ ማስረጃ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የትህነግ ቡድን ህገወጥ ቡድን የትግራይን ሕዝብ መሠረታዊ ፍላጎቶችና ሰብዓዊ ቀውሶች ለፖለቲካ ዓላማ የመጠቀም ልማድ አዲስ ክስተት ሳይሆን የቀደመ ታሪኩና መገለጫው ነው።

የትህነግ ቡድን የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ በትግራይ ክልል በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች የሚቀርብን ሰብዓዊ ድጋፍ በመንጠቅ ድራማዊ ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ መሆኑንም አስረድተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም የፌደራል መንግስት በግልጽ መረጃና ማስረጃ የሚልከው ሰብዓዊ ድጋፍ የት እንደገባ መጠየቅ እንዳለበት እና በቡድኑ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መደናገር እንደሌለበትም አንስተዋል።

የትህነግ ቡድን ሰብዓዊ ድጋፍ ለፖለቲካ ዓላማ ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት ሁሉም ሊገነዘበው እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

የፌደራል መንግስትም በትግራይ ክልል አስተማማኝና ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በዚህም በትግራይ ክልል ከባለፈው ጥር 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታኅሳስ ወር 2018 ዓ.ም ድረስ ሁለት ሚሊየን ኩንታል በገንዘብ ሲተምን 32 ቢሊዮን ብር የሚገመት ሰብዓዊ ድጋፍ መሰራጨቱን አስታውቀዋል።

ይህም የፌደራል መንግስት ዜጎች ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ያለውን ጠንካራ አቋም በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

የትህነግ ቡድን በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፉ ተደራሽ እንዳይሆን በማስተጓጎል፤ ድጋፉን ከችግረኛ ዜጎች በመንጠቅ ዳግም የሕዝብ ጠላትነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ቡድኑ ይህ አልበቃ ብሎት ለእያንዳንዱ ድጋፍ ፈላጊ ዜጋ ከሚሰጥ የፍጆታ ድርሻ ላይ መዋጮ እንደሚሰበስብም ነው የተናገሩት።

ትህነግ በሰብዓዊ ድጋፍ ስም በዜጎች ላይ የሚፈጽመው አስነዋሪ ድርጊት ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ያለውን የተላላኪነት ጥግ በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ የድጋፍ ጥሪ ባላቀረበበት ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በቡድንም ሆነ በተናጠል የሚደረጉ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻ የአሰራር ስርዓትን የጣሱ ህገ-ወጥ አካሄዶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህም የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሰብዓዊ ድጋፍ በማሰባሰብ ላልተገባ ዓላማ እያዋሉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ኢዜአ

16/4/2018

ደም በመለገስ ሰብአዊ ተግባር ላይ ሁሉም በንቃት ሊሳተፍ ይገባል፦አቶ ሙክታር ሳሊህ********የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ተገልጋዮች "ደም እየለገስ...
25/12/2025

ደም በመለገስ ሰብአዊ ተግባር ላይ ሁሉም በንቃት ሊሳተፍ ይገባል፦አቶ ሙክታር ሳሊህ
********

የሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ተገልጋዮች "ደም እየለገስን አገልግሎት እንሰጣለን አገልግሎት እየሰጠን ደም እንለግሳለን" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በደም ልገሳ መርሐ ግብር አካሂደዋል።

በደም ልገሳ መርሐ ግብሩ ላይ የተሳተፉት በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ ደም መስጠትም ሆነ መቀበል ሰጪውንም ሆነ ተቀባዩን የማይጎዳ ሰብአዊ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።

ደም መለገስ ልትቋረጥ የነበረችን ሕይወት እንደገና ተስፋዋን የማለምለም ሰብአዊ አገልግሎት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ሙክታር ደም በመለገስ በተለይም በተለያዩ አደጋዎች ከፍተኛ ደም ለፈሰሳቸው ሕሙማንና በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ ደም ለሚፈሳቸው እናቶች አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ይህንን በመገንዘብ የቢሮው አመራሮች፣ ሰራተኞችና ተገልጋዮች "ደም እየለገስን አገልግሎት እንሰጣለን አገልግሎት እየሰጠን ደም እንለግሳለን" በማለት በዛሬው እለት በደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ መሳተፋቸውን ገልፀዋል።

ደም በመለገስ ሰብአዊ ተግባር ላይ ሁሉም በንቃት ሊሳተፍ ይገባል ያሉት አቶ ሙክታር መሰል በጎ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።

16/04/18

የአንደኛ መንገድ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በይፋ ተጀመረ**********የአንደኛ መንገድ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በይፋ መጀመሩን የሀረሪ ክልል ክራይ ቤቶች ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመ...
25/12/2025

የአንደኛ መንገድ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በይፋ ተጀመረ
**********
የአንደኛ መንገድ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በይፋ መጀመሩን የሀረሪ ክልል ክራይ ቤቶች ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ አስታወቁ።

የአለም አቀፉ የጁገል ቅርስ አካል የሆነውን የአንደኛ መንገድ ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ የኮሪደር መልሶ ልማት ስራውን በአንድ ወር ለማከናወን እንደሚሰራ ነው ሀላፊው የገለፁት።

የኮሪደር ልማቱ አካባቢውን ጽዱ እና ውብ ከማድረግ ባሻገር ዘመናዊ መሰረተ ያለውና ኢኮኖሚውን ሊያነቃቃ የሚችል እንዲሆን ተደርጎ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

16/4/2018

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አትክልት ና ፍራፍሬ ምርት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በሀረሪ ክልል የኤረር ወረዳ አስታወቀ። ************************የምግብ ዋስትናን ለማረጋገ...
25/12/2025

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አትክልት ና ፍራፍሬ ምርት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በሀረሪ ክልል የኤረር ወረዳ አስታወቀ።
************************

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የአትክልት ና ፍራፍሬ ምርት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በሀረሪ ክልል የኤረር ወረዳ አስታውቋል

የኤረር ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ናስር ሙመድ እንደገለፁት በወረዳው ቀደም ሲል ፍራፍሬ በስፋት ይመረት የነበረ መሆኑን ገልፀው ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች የቀነሰውን ምርት ለመመለስ በተለይ ብርቱካን ምርት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በበጋ መስኖ መስክ የተገኙ ስኬቶችን የበለጠ ለማስፋት በፍራፍሬ ልማት ላይ ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳው የብርቱካን ምርት በ6 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ እንደሚገኝ ገልፀው በዚህም በሄክታር 250 ኩንታል ምርት እንደሚገኝ ገልፀዋል

የኤረር ወረዳ የግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ረመዳን ኢድሪስ በበኩላቸው ወረዳው ቀደም ሲል በፍራፍሬ ልማት ይታወቅ የነበረ መሆኑን ተናግረው ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ምርቱ ቀንሰዋል ብለዋል።

አሁን ለዘርፉ በተሰጠ ትኩረት በወረዳው ብርቱካን ልማት ላይ ከፍተኛ ውጤት እየታየ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ረመዳን አክለውም የብርቱካን ልማትን በማስፋት እና በአንድ ወቅት ውጤታማ የነበረውን የኤረር ፍራፍሬ ወደ ነበረበት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የወረዳው የመስኖ ልማት ባለሙያ አቶ መሃመድ ሳቢት፤ ብርቱካንን በዘመናዊ መንገድ አባዝተው እያከፋፈሉ መሆናቸውን እና ለአርሶ አደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

የወረዳው አርሶ አደሮች በበኩላቸው ከሌላ አካባቢ በቀሰሙት ተሞክሮ ወደ ብርቱካን ልማት የገቡ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ በስፋት አምርተው ተጠቃሚ እየሆኑ መሆኑን ገልፀዋል።

የወረዳው አርሶ አደሮች ፍራፍሬ ልማት ላይ ውጤታማ ና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ወረዳው በትኩረት የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል ።

ዘጋቢ:- ሙያዲን ሙክታር
16/4/18

ተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/

ዩቲዩብ :
https://www.youtube.com/

ቴሌግራም:
https://t.me/hararimassmediaagency

ሀረር ወርጊቢት 29ታኝ ዓመት ሒልቂ 16 ታሕሳስ 16/2018
25/12/2025

ሀረር ወርጊቢት 29ታኝ ዓመት ሒልቂ 16 ታሕሳስ 16/2018

Gaazeexaa Harar Waggaa 29ffaa lakko 16 Mudee 16/2018
25/12/2025

Gaazeexaa Harar Waggaa 29ffaa lakko 16 Mudee 16/2018

ሀረር ጋዜጣ 29ኛ ዓመት ቁጥር 16 ታሕሳስ 16/2018 ዓ.ም
25/12/2025

ሀረር ጋዜጣ 29ኛ ዓመት ቁጥር 16 ታሕሳስ 16/2018 ዓ.ም

24/12/2025

በመርሕ የተመራ የዛሬንና የወደፊቱን ታሳቢ በማድረግ የተገነባው ፕላዛ

የሞርኮው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተቶች************በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአምስተኛ ቀን ውሎው አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደውበታል።በውድድሩ የአም...
24/12/2025

የሞርኮው የአፍሪካ ዋንጫ ክስተቶች
************
በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአምስተኛ ቀን ውሎው አዳዲስ ክስተቶች ተስተናግደውበታል።

በውድድሩ የአምስተኛ ቀን ውሎ የመጀመሪያ ቀይ ካርዶች ተመዝዘዋል።

የተመዘዙት ቀይ ካርዶች በተመሳሳይ ምድብ በሚገኙ ቡድኖች ተጫዋቾች ሆኗል።

የኢኳቶሪያል ጊኒው ባስልዮ ንዳንግ እና የሱዳኑ ሳዲል የቀይ ካርዱ ሰለባ ተጫዋቾች ናቸው።

ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጄሪያ በአፍሪካ ዋንጫው 1000 ጎሎችን ማስቆጠር የቻለች ሰባተኛዋ ሀገር መሆን ችላለች።

ሪያድ ማህሬዝ በአፍሪካ ዋንጫው ለሀገሩ አልጄሪያ 7 ጎሎችን በማስቆጠር በውድድሩ የአልጄሪያ ከፍተኛ ግብ አግቢ መሆን ችሏል።

ሪያድ ማሀሬዝ ሱዳን ላይ ያስቆጠራት ጎል የውድድሩ ፈጣን ግብ በመሆን ተመዝግባለች።

የሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ከ 16 ሺ 115 በላይ ተመልካቾች ስታዲየም ተገኝተው ተከታትለውታል።

ይህም ከሞሮኮ የመክፈቻ ጨዋታ ቀጥሎ ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።

በጨዋታው ዚነዲን ዚዳን ለአልጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የተመረጠውን ግብ ጠባቂ ልጁን ሉካስ ዚዳንን ለመመለክት በንጉስ ሞላይ ሐሰን ስታዲየም ተገኝቷል፡፡

14/05/18

ተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/

ዩቲዩብ :
https://www.youtube.com/

ቴሌግራም:
https://t.me/hararimassmediaagency

መንግሥት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ  ለሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል :-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት *******መንግሥት የሀገር ግንባታ ሂደቱን ለማጽናት ...
24/12/2025

መንግሥት ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ለሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል :-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

*******
መንግሥት የሀገር ግንባታ ሂደቱን ለማጽናት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ለሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ዲሞክራሲን መገንባት፣ ተቋማትን ማጠናከርና ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት የተሰጣቸው መሆኑን ገልጿል፡፡

እነዚህ ሦስቱ ምሰሶዎች ሀገራዊ አንድነትን፣ሰላምና ብልጽግናን፣ እንዲሁም ዜጎች በመተማመን እና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ የጋራ ራዕይ እንዲኖራቸዉ የሚያደርጉ ቁልፍ መሰረቶች ናቸው፡፡

ዲሞክራሲን የመገንባት ሂደት ለአንድ ሀገር ወሳኝ ተግባር ሲሆን፣ በዋናነት ነፃ፣ ገለልተኛ እና ብቁ ተቋማትን ማቋቋም ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ፡፡ተቋማቱ የሚመሩባቸዉ ህጎችና የአሰራር ሥርዓቶች፣የተቋማቱ አወቃቀርና አደረጃጀት፣ እንዲሁም ለህዝብ ያላቸዉን ተዓማኒነትን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራበት ይገኛል፡፡

ጠንካራ የዲሞክራሲ ባህልና ሥርዓት የሚገነባው ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማት ሲፈጠሩና ሲጠናከሩ መሆኑን መንግሥት በጽኑ የሚገነዘበው ጉዳይ ነዉ፡፡በዚህም ኢትዮጵያ ባለፉት 7 ዓመታት በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ሂደት ውስጥ ሁለተናዊ ሪፎርም ሥራዎችን ስታከናውን ቆይታለች፡፡

እነዚህ ሪፎርሞች የሀገሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑትን የዲሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ እና ጠንካራ አድርጎ ለመገንባት መንግሥት ምን ያህል ቁርጠኛ እንደሆነ ያሳየባቸው ናቸው፡፡

የእነዚህ ተቋማት መጠናከር በአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ እንደ ዋንኛ ምሰሶ የሚወሰድ ነው፡፡

በተለይም ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በዲሞክራሲ ተቋማት ላይ የታዩ ተጨባጭ ለውጦች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለመጠበቅ፣ እንዲሁም የሕዝቡን ዕምነት ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ መንግሥት በተለይ ተቋማዊ ዐቅምን በማሳደግ እና ነፃነትን በማረጋገጥ፣ የዲሞክራሲ ምህዳርን እንዲሰፋ ለማደረግ የሚጠበቅበት ግዴታ ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲ የሚያብብበትን አስቻይ ዐውድና ማዕቀፍ ለመፍጠር ዓለማው አድረጓል፡፡

ይሄንን ከግብ ለማድረስ በተለይ የፀጥታ፣ የፍትሕ፣ የሲቪልና የሚዲያ ተቋማት፣ እንዲሁም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝብን ማዕከል አድርገው እንዲሰሩ መንግሥት በቁርጠኝነት በመደገፉ እንደ ሀገር ገለልተኛ ተቋማት እንዲፈጠሩ በማደርረግ ተጨባጭ ዉጤቶች እንዲመዘገቡ አስችሏል፡፡

ሌላው መንግስት በትኩረት እየሰራበት ያለው ጉዳይ እንደ ሀገር ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ነዉ፡፡

ይህ ሂደት ዋና ዓለማ ያደረገው መላዉ ሕዝብ፣ ተቋማት፣ አመራርና ሠራተኛዉ በሀገራዊ ራዕይ ላይ በተለያዩ ድምጾች የጋራ እድገትን በመገንባት ሀገራዊ ህለውና እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ እንዲሁም በዜጎች መካከል መተማመን እና ሀገራዊ አንድነትን እንዲፈጠር ማድርግ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ የብዙሃን ድምጽ የሚሰማበት የፖለቲካ ዐዉድ ለመፍጠር አያሌ የፖለቲካ ማሻሻያዎችን አድርጋለች፡፡

በዚህም እስከዛሬ በነበሩ መንግሥታት ያለተሞከረውን ጫፍ ወጥተው የሚታዩ ተቃርኖ ሀሳቦችን ለማጥበብና ለማቀራረብ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም፣ ሀገራዊ የውይይት መድረክ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡

በዚህም ገና ከወዲሁ በርካታ ለዉጦች እየታዩ ሲሆን ውሳኔው ለምንመኛት የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን መሆን የማዕዘን ድንጋይ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡

በአጠቃላይ መንግሥት መልአተ ሕዝቡን በማስተባበር ጠንካራና ብልጽግናዋን በልጆቿ ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እያደረገ ባለው ዘርፈ ብዙ ጥረት ዲሞክራሲን መገንባት፣ ተቋማትን ማጠናከርና ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠርን ጉዳይ በልዩ ትኩረት የሚሰራበት ዋንኛው አጀንዳው ሆኖ ይቀጠላል፡፡

#የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
15/ 01/18

Address

Red Cross Street
Harar
1331

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Mass Media Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Harari Mass Media Agency:

Share