22/07/2024
ዘመኑን የሚመጥን የትራፊክ ፖሊስ እንዲኖረን እንፈልጋለን
ሰብአዊ መብት መጣስ አመኔታ ማጣትና የግል ጥቅምን ማሳደድ መሸነፍ ነው።
የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን።
ሀምሌ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ለትራፊክ ፖሊስ አባላትና አመራር በስነምግባርና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በሰጡት ስልጠና ላይ የተናገሩት ንግግር ነበር።
የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንደ ገለፁት የስልጠናው ዋና አላማ ትራፊክ ፖሊሶች በሚሰጡት አገልግሎት በየወቅቱ አቅማቸውን ማጎልበትና ህብረተስቡን በታማኝነት በቅንነት እንዲያገለግሉ በማሰብ ነው ሌላው
ሞያዊ ግዴታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የስራ ላይ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አክለው ገልፀዋል።
ኮሚሽነር ረምዚ የስነ ምግባር መረሆች እና መሠረቶች ለትራፊክ ፖሊሶች እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በቅንነት ማገልገል ለሙያ ክብር መስጠት ከአድሎና ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ ሐላፊነታቸውን መወጣ እንደሚገባቸው በስልጠናው ግንዛቤ እንዲፈጠር አድርገዋል።
ትራፊክ ፖሊሶች በራሳቸው የሚተማመኑ ለተገልጋይ አክብሮት በመስጠት በትህትና ማገልገል እንዳለባቸውም ጠቅሰዋል።
የዚህ ሰልጠና ዋና አላማ የሚታዩ ችግሮችን የትራፊኩን ክህሎት በማሳደግ መቅረፍ ስራን በእውቀትና በብቃት ለመምራት እና ከራስ ጋር እያገናዘቡ የማረም ስራዎችን እንዲሰሩ ነው ብለዋል።
ማንም ሰው በራስ መተማመንን የሚያጣው አንዱ በእውቀት ችግር የሙያ ብቃት ማነስ ሊሆን ይችላል ሌላው ከአመለካከትና ጥቅምን ከመፈለግ ጋር የተያያዘ ሲሆን ነው ብለዋል
ከሚሽነር ረምዚ በሰጡት ማብራሪያ አስደሳች ማራኪ ሁኔታ መፍጠር ነው ይሄውም በከባድ አየር ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ለህዝብ ጥቅም መስራት ፍተሀዊ ሆኖ በህግ አግባብ ብቻ መስራት ሲሆን ። መጥፎ አጋጣሚን በመቀነስ ህዝብና ፖሊስ መልካም ግኑኝነት እንዲኖረው መስራት ብልሹ አሰራሮችን ማስወገድና
በመልካም አጋጣሚ እንዲተኩ መስራት ይገባል ብለዋል።
ከትራፊክ ደንብ ጋር በተያያዘ አመልካችና ማመልከቻ ጠቋሚ ምልክቶች በአግባቡ ህጉ ሳይሸራረፍ መከበር እንዳለበትም ተገልጿል።
በመጨረሻም ከተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመነሳት የሐረሪ ክልል ትራፊክ ፖሊስ ዘመኑን የሚመጥን በእውቀትና በብቃት የሚሰራ በህግ የበላይነት ብቻ ፍትህ የሚሰጥ የህዝብ አገልጋይ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራም ኮሚሽነር ረምዚ ተናግረዋል።
ዘገባ
ጣሰው ቻለው