![ጎንደር - የአጼ ፋሲል ግቢ 12 በሮችብዙ ጊዜ የአጼ ፋሲል ግቢ በመባል የሚታወቀው ቦታ ስፋት 70,000 ካሬ ሜትር ይሆናል፡፡ ግቢው ከ17ኛውና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪዎች ...](https://img4.medioq.com/244/425/238446412444253.jpg)
25/07/2023
ጎንደር - የአጼ ፋሲል ግቢ 12 በሮች
ብዙ ጊዜ የአጼ ፋሲል ግቢ በመባል የሚታወቀው ቦታ ስፋት 70,000 ካሬ ሜትር ይሆናል፡፡ ግቢው ከ17ኛውና 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ መሪዎች ከነበሩት መካከል የስድስቱን አብያተ መንግስታትና ሌሎች በርካታ የህንፃ ፍርስራሾችን ይዞ ይገኛል፡፡
የአፄ ፋሲል ግቢ ቀደም ብሎ አገልግሎት የሚሰጡ አስራ ሁለት በሮች ነበሩት፡፡ ከፊት በር ጀምሮ በስተቀኝ የሚገኙት ጥንታዊ በሮች ስም የሚከተለው ነው፡፡
1- ፊት በር/ጃን ተከል በር
2- ወንበር በር
3- ራስ በር
4- አዛዥ ጠቋሬ በር
5- አደናግር በር
6- ኳሊ በር
7- እምቢልታ በር
8- ባልደራስ በር
9- እርግብ በር
10- ቀጭን አሸዋ በር
11- እንኮይ በር
12- እቃ ግምጃ ቤት በር
የክረምት ጊዜዎን ጎንደርና አካባቢዋን በመጎብኘት አስደሳች ጊዜ ያሳልፉ!