Gondar Men Ale?

Gondar Men Ale? This page is design to give more information about the city of gondar and give a lot of information

16/03/2021

በጎንደር ዘመነ መንግሥት

| የነገስታት ስምና የነገሱባቸው ጊዚያት፦፦

1.አፄ ሰርፀ ድንግል ከ1555___1589ዓ.ም

2.አፄ ያዕቆብ ከ1589___1594 ዓ.ም

3.አፄ ዘድንግል ከ1594____1596 ዓ.ም

4.አፄ ሱስንዮስ ከ1596____1624 ዓ.ም

5.አፄ ፋሲል ከ1624____1659 ዓ.ም

6.አፄ ዮሀንስ 1ኛ ከ1659____1674 ዓ.ም

7.አፄ ኢያሱ ( አድያም ሰገድ) ከ1674____1698 ዓ.ም

8.አፄ ተ/ሀይማኖት(ልዑል ሰገድ) ከ1698____1700 ዓ.ም

9.አፄ ቴዎፍሎስ ከ1700____1703 ዓ.ም

10. አፄ ዮስጦስ(ፀሐይ ሰገድ) ከ1703____1708 ዓ.ም

11.አፄ ዳዊት (አድባር ሰገድ ከ1708____1713 ዓ.ም

12.አፄ በካፋ (መሲ ሰገድ) ከ1713___1723 ዓ.ም

13.አፄ ኢያሱ 2ኛ(ብርሃን ሰገድ) ከ1723___1748 ዓ.ም

14.አፄ ኢዮአስ ከ1748___1762 ዓ.ም

15.አፄ ዮሀንስ 2ኛ (አድማስ ሰገድ) ከ1762___1763 ዓ.ም

16. አፄ ተ/ሀይማኖት 2ኛ (ኃያል ሰገድ) ከ1763___1770 ዓ.ም

17.አፄ ሰለሞን (ጥበብ ሰገድ)ከ1770____ 1772 ዓ.ም

18.አፄ ተ/ጊዮርጊስ (ፍቁር ሰገድ) ከ1772____1777 ዓ.ም

# ማስታወሻ ፦አመተ ምህረቶች የተፃፉት በኢትዮጵያን አቆጣጠር ነዉ፡፡

(ጎንደር የመማፀኛ ከተማ መፅሐፍ ቁጥር 1 የተወሰደ)

12/03/2021
12/03/2021

በጎንደር ዘመነ መንግስት የነገስታት ስምና የነገሱባቸው ጊዚያት፦፦
1.አፄ ሰርፀ ድንግል ከ1555___1589ዓ.ም
2.አፄ ያዕቆብ ከ1589___1594 ዓ.ም
3.አፄ ዘድንግል ከ1594____1596 ዓ.ም
4.አፄ ሱስንዮስ ከ1596____1624 ዓ.ም
5.አፄ ፋሲል ከ1624____1659 ዓ.ም
6.አፄ ዮሀንስ 1ኛ ከ1659____1674 ዓ.ም
7.አፄ ኢያሱ ( አድያም ሰገድ) ከ1674____1698 ዓ.ም
8.አፄ ተ/ሀይማኖት(ልዑል ሰገድ) ከ1698____1700 ዓ.ም
9.አፄ ቴዎፍሎስ ከ1700____1703 ዓ.ም
10. አፄ ዮስጦስ(ፀሐይ ሰገድ) ከ1703____1708 ዓ.ም
11.አፄ ዳዊት (አድባር ሰገድ ከ1708____1713 ዓ.ም
12.አፄ በካፋ (መሲ ሰገድ) ከ1713___1723 ዓ.ም
13.አፄ ኢያሱ 2ኛ(ብርሃን ሰገድ) ከ1723___1748 ዓ.ም
14.አፄ ኢዮአስ ከ1748___1762 ዓ.ም
15.አፄ ዮሀንስ 2ኛ (አድማስ ሰገድ) ከ1762___1763 ዓ.ም
16. አፄ ተ/ሀይማኖት 2ኛ (ኃያል ሰገድ) ከ1763___1770 ዓ.ም
17.አፄ ሰለሞን (ጥበብ ሰገድ)ከ1770____ 1772 ዓ.ም
18.አፄ ተ/ጊዮርጊስ (ፍቁር ሰገድ) ከ1772____1777 ዓ.ም
# ማስታወሻ ፦አመተ ምህረቶች የተፃፉት በኢትዮጵያን አቆጣጠር ነዉ፡፡
(ጎንደር የመማፀኛ ከተማ መፅሐፍ ቁጥር 1 የተወሰደ)

10/03/2021

የጎንደር ከተማ ተራሮች በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ ለአልሚዎች ሊሰጡ መሆኑ ተገለጸ።

ባሕር ዳር: የካቲት 30/2013 ዓ.ም (አብመድ)
የጎንደር ከተማን የከበቡ ተራሮችን በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ ለአልሚ ባለሀብቶች እንደሚሰጡ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ አስታወቁ፡፡

አቶ ሞላ እንዳስታወቁት፣ ከተማዋን የከበቡትን ተራሮች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በመስጠት ከተማዋን የበለጠ የቱሪስት መስህብ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው።

ተራራን ማልማት ከባድ እንደሆነ የሚገልፁት ከንቲባው፣ የጎንደር ተራሮችን ልክ እንደ እንጦጦ ፓርክ ጥቅም ላይ ለማዋል የተራራ ልማት ፕሮጀክት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ከንቲባው፣ የዲዛይን ስራውን የኢትዮጵያ ዲዛይን ድርጅት እንዲያካሂደው በአምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ስምምነት መፈረሙን ጠቁመዋል፡፡

በፕሮጀክት ለመሰመራት ባለሀብቶች እየመጡ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባው፣ አንድ የዱባይ ባለሃብት የኩሪፍቱ ሪዞርት ቅርንጫፍን በጎንደር ለመክፈት ጥያቄ ማቅረቡን አስታውቀዋል፡፡

በጎንደር ከተማ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በተለይም በገንፎ ቁጭ፤ በአንገረብና መገጭ ተራሮች ዙሪያ ከተማዋን ለማልማት የሚያስችሉ ሰፋፊ የዲዛን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ በሎጂ ሥራ መሰማራት ከሚፈልግ ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ በመድረሱ የመሬት ርክክብ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እንደሆነ መናገራቸውን የዘገበው ኢትዮ ፕረስ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

09/03/2021

የጎንደር ከተማ ተራሮች በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ ለአልሚዎች ሊሰጡ መሆኑ ተገለጸ።

ጎንደር: የካቲት 30/2013 ዓ.ም (ጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን )
የጎንደር ከተማን የከበቡ ተራሮችን በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ ለአልሚ ባለሀብቶች እንደሚሰጡ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ አስታወቁ፡፡

አቶ ሞላ እንዳስታወቁት፣ ከተማዋን የከበቡትን ተራሮች በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በመስጠት ከተማዋን የበለጠ የቱሪስት መስህብ እንድትሆን ለማድረግ እየተሰራ ነው።

ተራራን ማልማት ከባድ እንደሆነ የሚገልፁት ከንቲባው፣ የጎንደር ተራሮችን ልክ እንደ እንጦጦ ፓርክ ጥቅም ላይ ለማዋል የተራራ ልማት ፕሮጀክት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ከንቲባው፣ የዲዛይን ስራውን የኢትዮጵያ ዲዛይን ድርጅት እንዲያካሂደው በአምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ስምምነት መፈረሙን ጠቁመዋል፡፡

በፕሮጀክት ለመሰመራት ባለሀብቶች እየመጡ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባው፣ አንድ የዱባይ ባለሃብት የኩሪፍቱ ሪዞርት ቅርንጫፍን በጎንደር ለመክፈት ጥያቄ ማቅረቡን አስታውቀዋል፡፡

በጎንደር ከተማ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በተለይም በገንፎ ቁጭ፤ በአንገረብና መገጭ ተራሮች ዙሪያ ከተማዋን ለማልማት የሚያስችሉ ሰፋፊ የዲዛን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ በሎጂ ሥራ መሰማራት ከሚፈልግ ድርጅት ጋር ስምምነት ላይ በመድረሱ የመሬት ርክክብ ለመፈፀም በዝግጅት ላይ እንደሆነ መናገራቸውን የዘገበው ኢትዮ ፕረስ ነው ።

09/03/2021

በጎንደር አብያተ መንግሥታት ዉሽባ መኖሩን ያውቃሉ ?
ውሸባ ግንብ /እንፋሎት መታጠቢያ /
ኢትዮጵያዊን ከጥንት ጀምሮ በእንፋሎት እየታጠቡ ( እየታጠኑ) ለዉበት መጠቀሚያ ከማዋላቸዉ በላይ በእንፋሎት መታጠብ(መታጠን) የሰዉነት መርዛማ ነገሮችን በማስወገድ ለጤና ፍቱን መሆኑን ቀድመው ያዉቁ ነበር ።ከዚህ የተነሳ የእንፋሎት መታጠቢያ አዘጋጅተው ይጠቀሙ ነበር ።
በአፄ ፋሲል ቤተመንግሥት ግቢም ከተገነቡ ግንቦች መካከል ዉሽባ ግንቦች ይጠቀሳሉ ።አፄ ፋሲለደስ ያሰሩት የመጀመሪያ የእንፋሎት መታጠቢያ ሲሆን ከእሳቸው በተጨማሪ ከአፄ ዳዊት ግንብ ትንሽ እልፍ ብሎ የሚገኘው በልጅ ልጃቸው በአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ በ1690 የተሰራው ወሽባ ግንብ አንዱ ነው ።ይህ የወሽባ ግንብ 5 የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጎ ተገንብቷል ።
ከዋናው የእንፋሎት መታጠቢያ ክፍል በተጨማሪ አንድ መቆያ ክፍል ፣አንድ የልብስ መቀየሪያና ጌጣጌጦች ማስቀመጫ ክፍል እንዲሁም በእንፋሎት ከታጠቡ በኃላ ተጠቃሚዎቹ ሰዉነታቸዉን የሚያቀዘቅዙባቸዉ ሁለት ክፍሎች ይገኙበታል ።
ዋናው የእንፋሎት መታጠቢያ ክፍል ከዉስጥ ሲሆን እንፋሎትም ሲጠቀሙ ጎድጓዳ በሆነ ቦታ ላይ መጠኑ ትልቅ የሆነ የባዛልት ድንጋይ አድርገው ድንጋዩን በታች ባለው ክፍት ቦታ እሳት እያነደዱ በማጋል በጋለዉ ድንጋይ ላይ በግድግዳው በኩል በተከፈተው ቀዳዳ ዉሃ በማፍሰስና እንፋሎት እንዲፈጠር በማድረግ ሲጠቀሙ ፣ እንፋሎቱ በዝቶ እንዳያፍናቸዉ ከላይ በኩል የእንፋሎት ማስተንፈሻ (ችሚኒ) አሰርተው እንፋሎቱን በማስተንፈስ ሌሎች ከላይ ባለው ክፍል እንዲጠቀሙ ያደርጉ ነበር ።
ምንጭ ፦ ድብ አንበሳ መጽሐፍ የተወሰደ

01/03/2021
25/02/2021

ሸህ አሊ ጎንደር
ሸህ አሊጎንደር በዘመነ መሳፋንት መጨረሻና በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ የነበሩት ታላቅ ወልይ ናቸው ።
የተወለዱትም በወሎ በወረይሉና ኮሬብ መካከል በምትገኝ አምቦ ፈረስ በሚባል አካባቢ እንደነበር ይነገራል ።
ሺህ አሊ ጎንደር ታላቅ እዉቀት የነበራቸው ትምህርታቸውንም ከኢትዮጵያ አልፎ በግብፅ ካይሮ የተማሩ በርካታ ሙህራንን ያፈሩ ሲሆኑ ብዙ አለማትን የጎበኙ ናቸው ።ከሄዱባቸዉ ቦታዎች ዉስጥ ግብፅ ፣ የመንና ህንድ በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ።
ሸህ አሊ ጎንደር ኢትዮጵያ አገራችን ከአረብ ሀገራት ጋር በነበራት የንግድ ትስስርና የዲፕሎማሲ ግንኑነት ከፍተኛና ታላቅ አስተዋጽኦ ለሀገራችን አበርክተዋል ።በአዲስ አለም በየዓመቱ ሚያዚያ 2 ቀን ታላቅ የዝየራና የመውሊድ ስርዓት ይደረጋል ። ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰዎች እየመጡ ይዘየራሉ።
(ምንጭ :-ድብ አንበሳ መፅሐፍ የተወሰደ)

24/02/2021

የአድዋ ድል በዓል በጎንደር ከተማ ይካቲት 23 እስከ 24 በድምቀት ይከበራል ። ስለሆነም በታሪካዊቷ ከተማ በቦታው ተገኝታችሁ የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ ተጋብዛችኋል ።

22/02/2021
22/02/2021

የማህበረ ስላሴ አንድነት ገዳም
የማህበረ ስላሴ አንድነት ገዳም ከጎንደር ወደ መተማ በሚወስደው ዋና መስመር 121 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ደረቅ አባይ ቀበሌ ተነስተው በስተደቡብ የ3 ስዓት የእግር ጉዞ ካደረጉ በኃላ የሚያገኙት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም ነው፡፡
ገዳሙ ማራኪ በሆነ የተፈጥሯዊ የመሬት አቀማመጥ ባለው ለአይን በሚማርክ ጥቅጥቅ ባለ ደን በተሸፈነ ተራራማ ቦታ ላይ የተመሠረተ ሲሆን በ4ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በአብርሃና አጽብሃ ዘመነ መንግሥት የተመሰረተ በኢትየጵያ ቀደምትነትና ትልቅ ታሪክ ያለው ገዳም እንደሆነ የገዳሙ አባቶች ይናገራሉ፡፡ ይህ ገዳም አፄ ሱስንዩስን ከበሽታ የፈወሰ፣ የተለያዩ የሀገራችን የሃይማኖት አባቶችና መሪዎችን አፄ ቴዎድሮስ ጨምሮ እንዲሁም ሌሎች ምዕመናን ትምህርታቸውን የተከታተሉበት ትልቅ ታሪክ ያለው ገዳም ሲሆን በውስጡም በርካታ ታሪካዊ ቅርሶች ይገኙበተል፡፡
በዚህ ገዳም ውስጥ መኖር የሚፈቀደላቸው ወንድ ምዕመናን ብቻ ሲሆኑ በገዳሙ ህግና ደንብ መሠረትም ሌሎች ከገዳሙ ተራራ ግርጌ ወይም “ ግዝት በር “ እየተባለ ከሚጠራው የገዳሙ ክልል አልፎ መግባት ፈጽሞ የተከተለከለ ነው፡፡
የማህበረ ስላሴ አንድነት ገዳም በየዓመቱ የካቲት 27 ቀን እጅግ በደመቀ ሥነ ሥርዓት የሚከበር ሲሆን የመድሃኒዓለም ታቦት በገዳሙ የሃይማኖት አባቶችና ቀሳውስት በጥንቃቄ ተይዞና በዝማሬ ታጅቦ ከተራራው ግርጌና ግዝት በር እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ላይ ያርፋል፡፡ በእለቱም ምዕመናን ያላቸውን ሃይማኖታዊ ክብር በእልልታ፣ በሆታ ይገልጻሉ በማግስቱ መመንኮስ ለሚፈልግ ሥርዓተ ምንኩስና፣ ለሚቆርቡ ደግሞ ሥርዓተ ቁርባን ይፈፀምላቸውና ምዕመናን ተባብረው ታቦቱ ወደ ቤተክርስቲያኑ በዝማሬና በእልልታ ታጅቦ ይገባል፡፡
(ምንጭ፡-የጎንደር ከተማና በድሮዉ መጠሪያ ሰሜን ጎንደር የቱሪስት መፅሄት የተወሰደ፡፡)

21/02/2021
19/02/2021

የጎንደር ከተማ አስተዳደር “በተኩስ ደስታችንን እንገልፃለን” የሚሉ አካላትን ለሕግ እንደሚያቀርብ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ አስተዳደር “በተኩስ እሩምታ ደስታቸውን የሚገልፁ አካላት” ባላቸው ላይ የሕግ የበላይነትን እንደሚያስከብር ገለፀ፡፡

በሕግ ማስከበሩ ሂደት የተገኙ ድሎችን ምክንያት በማድረግ “ደስታቸውን በተኩስ እሩምታ የሚገልጹ አካላት” የነዋሪውን ህዝብ ተረጋግቶ በሰላም መኖር እና የጎብኚዎችን ደህንነት የሚረብሽ ተግባር እየፈፀሙ መሆናቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በሕግ ማስከበሩ ዘመቻ ከተገኘው ድል ጋር በተያያዘ ያለውን የአሸናፊነት ስሜት በመረዳትና “በተኩስ ደስታን መግለፅ” ይቆማል በሚል በማስጠንቀቂያ ማለፉን አስታውሷል፡፡

ሆኖም ግን ይህ ሕገወጥ ድርጊት፣ የከተማዋን ገፅታ የሚጎዳ፣ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ጎብኚዎችንና ፍጹም ሰላማዊ ሕዝቦችን የሚረብሽ በመሆኑ የጎንደር ከተማ አስተዳደርና የፀጥታ ኃይል ከአሁን በኋላ የሕግ የበላይነትን የሚያስከብር፣ ድርጊቱን በሚፈፅሙ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህን ሕገወጥ ድርጊት ሽፋን በማድረግም ወንጀል ለመስራት የሚጥሩ አካላት እንደሚኖሩ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚገነዘብም ነው የገለፀው፡፡

በመሆኑም ደስታን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለጽ ሲቻል፣ በጥይት ተኩስ እንገልፃለን የሚሉ አካላትን ለሕግ ለማቅረብ እሰራለሁ ብሏል የከተማ አስተዳደሩ፡፡

ነዋሪውም ይህንን አውቆ በሕገወጥ ተግባራቸው ከተማዋን እየጎዱ ያሉ አካላትን ስርዓት ለማስያዝ መንግሥት በሚያደርገው ህግን የማስከበር ዘመቻ ከጎኑ እንዲቆም ጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Address

Gondar
Gondar
41

Telephone

0918734637

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Men Ale? posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share