Guang Intercept ጓንግ ኢንተርሴፕት

Guang Intercept ጓንግ ኢንተርሴፕት Media

04/11/2022

መቀሌ

አሳዛኝ ዜና ታዋቂው ባለሀብት እና የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ባለቤት በባቡር አደጋ አረፋ።
25/09/2022

አሳዛኝ ዜና
ታዋቂው ባለሀብት እና የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ባለቤት በባቡር አደጋ አረፋ።

የባህር ዳር ከተማ በሃያ አራት ሚሊዮን ብር ወጪ በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ የመንገድ ላይ መብራቶችን ግንባታ ስራ እየሰራ ነው።
25/09/2022

የባህር ዳር ከተማ በሃያ አራት ሚሊዮን ብር ወጪ በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ የመንገድ ላይ መብራቶችን ግንባታ ስራ እየሰራ ነው።

 የወገን ደራሽ ጥሪ  በ ጋምቤላ ክልል ቴዶ ቀበሌ የውሃ   ሙሊት አስከፊ ጉዳት አድርሷል። ለህዝቡ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋል።
25/09/2022


የወገን ደራሽ ጥሪ
በ ጋምቤላ ክልል ቴዶ ቀበሌ የውሃ ሙሊት አስከፊ ጉዳት አድርሷል። ለህዝቡ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋል።

ፈንቅል ተከስተ ሀጎስ የሽራሮ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።
25/09/2022

ፈንቅል ተከስተ ሀጎስ የሽራሮ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።

ሰበር ዜናአቶ ግርማ የሽጥላ ከሌሊቱ 10:30 በመኖሪያ ቤታችው ላይ በደረሰ የቦንብ ጥቃት ተሰው። ጓንግ ኢንተርሴፕት ለቤተሰባቸው እና ለድርጅታቸው መፅናናትን ይመኛል።
25/09/2022

ሰበር ዜና
አቶ ግርማ የሽጥላ ከሌሊቱ 10:30 በመኖሪያ ቤታችው ላይ በደረሰ የቦንብ ጥቃት ተሰው። ጓንግ ኢንተርሴፕት ለቤተሰባቸው እና ለድርጅታቸው መፅናናትን ይመኛል።

ሰብልዬ ስራዋን ልትጀምር ተሰናድታለች!                                                                                                ...
24/09/2022

ሰብልዬ ስራዋን ልትጀምር ተሰናድታለች! በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን የሚመራው ጥምር ጦሩ እያጠራ፣ የትግራይን ህዝብም ለነፃነቱ አብሮት እያሰለፈ ወደ መቐሌ በመገስገስ ላይ ነው! ሰብልዬም ስራዋን ልትጀምር ተሰናድታለች! ከምንም በላይ የሚያስደስተው እና የሚያረካው ነገር የትግራይ ህዝብም በቃኝ ማለቱና ለነፃነቱ መነሳቱ ነው! እንደ ቀደመው ሁሉ የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያዊነት ዋልታና ማገር ይሆናል! የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ማህደር ውስጥ በደማቁ ተፅፎ ያለ ኩሩ ህዝብ ነው! ያሁኑ የትግራይ ትውልድም ይሄን ያስቀጥላል! ወንጀለኛውንም ሰብልዬ ሰብሉካ፣ አርገው ነካ ነካ ለህግ ታቀርብልናለች!
በትግራይ ምድርም ኢትዮጵያዊነት ደምቆ ያብባል!

በጎንደር ዩኒቨርስቲ  ህግ ት/ ቤት  "የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ እና የተገልጋዮች እርካታ" በሚል ርዕስ ሲጠና  የቆየው ክልል አቀፍ የዳሰሳ ጥናት  ለህትመት በቃ****...
24/09/2022

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ህግ ት/ ቤት "የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ እና የተገልጋዮች እርካታ" በሚል ርዕስ ሲጠና የቆየው ክልል አቀፍ የዳሰሳ ጥናት ለህትመት በቃ
***********************************************
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ት/ቤት ከUSAID Feteh (Justice) Activity in Ethiopia በወሰደው የፕሮጀክት ውል መሰረት "የአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ እና የተገልጋዮች እርካታ" በሚል ርዕስ ክልል አቀፍ የዳሰሳ ጥናት አከናውኗል። የዚህ ጥናት ውጤት ለህትመት የበቃ ሲሆን ፣ መስከረም 13/2015 ዓ/ም በተዘጋጀው መድረክ ህትመቱን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማስረከብ ስነ ስርዓት ተካሂዷል። ዩኒቨርሲቲያችንም ስራውን በአግባቡ ሰርተው ላጠናቀቁ የህግ ት/ቤት የጥናት ቡድን አባላትና በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።
*******************************************
ለልህቀት እንተጋለን !
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
መስከረም 14/2015 ዓ/ም
መረጃው የባህርዳር ኮሙኒኬሽን ነው

የአርበኛ ዘመነ ካሴን መታሰር አስመልክቶ ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ!አማራ ወገኑን የሚወድ፣ ከወገኖቹ ጋር የሚጋራው የነፃነትና የተጋድሎ ታሪኩ፣የሀገሩ አንድነትና የሰንደቅ አላማው ክ...
24/09/2022

የአርበኛ ዘመነ ካሴን መታሰር አስመልክቶ ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ!

አማራ ወገኑን የሚወድ፣ ከወገኖቹ ጋር የሚጋራው የነፃነትና የተጋድሎ ታሪኩ፣የሀገሩ አንድነትና የሰንደቅ አላማው ክብር ሲነካ ፈፅሞ የማይታገስ ኩሩ ህዝብ ነው። አማራ ለዚህ አቋሙ፣ይህም ለሚጠይቀው መስዋዕትነትና ተጋድሎ የተለየ ዋጋና ክብር የማይጠይቅ ቢሆንም ይህ አቋሙ በፀላኤ ኢትዮጵያ ኃይሎች እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ለአስርት አመታት የቀጠለ አማራ ጠል ፕሮፓጋንዳ፣መቆሚያ ያጣ የግፍ ጭፍጨፋና መፈናቀል፣የግፍ ወረራና ዝርፊያ ኢላማ አድርጎታል።

ይህ አማራ-ጠል ጭፍጨፋና መፈናቀል፣ወረራና ዝርፊያ ነው የፋኖ ንቅናቄን እንዲያንሰራራና እንዲጎለብት ያደረገው። ይህ ንቅናቄ በተለይ የአማራ-ጠል ትርክት ደራሲና አቀንቃኝ፣አማራን መጨፍጨፍ፣መዝረፍና ማፈናቀልን ለቢጤዎቹ ያስተማረው፣መሬት ላይ እውን ሆኖ የግፍ ጭፍጨፋን እንዲወልድ ያደረገው የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግምባር (ትህነግ) በአማራ ምድር ተደጋጋሚ ወረራ ከፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።

ትህነግ ሦስተኛ ዙር ወረራ አካሂዶ የሀገራችንን አንድነት እየፈተነ፣አማራን እንደ ህዝብ በመውረር እየጨፈጨፈ፣ እያፈናቀለና እየዘረፈ ባለበት፣በአንፃሩ የመከላከያ ሰራዊቱ፣የአማራ ልዩ ኃይል፣ፋኖና ሚሊሻው ደጀኑን ህዝብ ከጎኑ አሰልፎ ከእዚህ እኩይ ኃይል ጋር በሚፋለምበትና መስዋዕትነት በሚከፍልበት በእዚህ ወቅት ትኩረትን ቅድሚያ መሰራት ካለበት ሥራ የሚያናጥቡ ተሻሚ አጀንዳዎች መፈጠር አይኖርባቸውም።

የምስራቅ አማራ ፋኖ በሀገርና በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ብቻ ሳይሆን የህዝብ የተጋድሎ ታሪክ አሁናዊ ምዕራፍ አንድ አካል ሆኖ በሥሩ በአሰባሰባቸው ፋኖዎች ቀጣይ መስዋትነት የደመቀ ታሪክ እየሰራ ያለ፣ ፋኖነት በግብር ለመጭው ትውልድ ለማሻገር በነፍሳቸው የቆረጡና በአገር ፍቅር የሰከሩ የአማራ ልጆች የተሰባሰቡበት የአርበኞች ጎራ ሆኖ ቀጥሏል።

ለዚህም ነው ጠላት ሁሉንም አቅሙን ተጠቅሞ፣ የውስጥ እና የውጭ ግብረ-አበሮቹን አስተባብሮ አገር እና ሥርዐት ለመበተን እየሠራ ባለበት በዚህ ሰአት ከዚህ ቀዳሚ አጀንዳ ይነስም ይብዛ ትኩረትን በማናጠብ ወገንን ጉልበት የሚነሳ ማናቸውም የውስጥ አለመግባባትም ሆነ መገፋፋት በእጅጉ የሚያሳስበው።

የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር እና አባላት አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ላይ የተፈፀመውን እስር በጥሞናና በቅርበት ስንከታተለው ይቆየን ሲሆን እስካሁን ባለን ግንዛቤ፣ ህዝባችን እና ቀጠናው ካለበት ሁኔታ አንፃር ጭምር ስናየው አግባብ ነው ለማለት አንደፍርም። አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲና እኩልነት እንዲሰፍን ከትህነግ መራሹ መንግስት ጋር በግምባር ቀደምትነት የታገለና መስዋዕትነት የከፈለ ብቻ ሳይሆን በመሪነት ያታገለ ጀግናና አርበኛ ነው።

አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ትህነግ መራሹ ግፈኛ ሥርአት በህዝብ ትግል ከተወገደ በኋላም ቢሆን መልኩን ቀይሮና ተባብሶ የቀጠለውን አማራ ጠልነት፣አማራን በግፍና በገፍ የመጨፍጨፍ ተደጋጋሚ ተግባር፣ በኃይል ወሮ የማንበርከክ ጥረት በግምባር ቀደምትነት የታገለና ያታገለ የአማራ ልጅ ነው። ይህንና መሰል ተጋድሎውንና የከፈለውን መስዋዕትነት ስናስብ መያዙና መታሰሩ እጅግ አሳስቦናል።

በመሆኑም፡

▪️1. የህግና ፍትህ አካላት በፋኖ ዘመነ ካሴ አያያዝ ዙሪያ ለህዝብ ግልፅና ተአማኒነት ያለው መረጃ እንዲሰጡና ውዥምብሩ እንዲጠራ!

▪️2. የፍትህ ሂደቱ ግልፅና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ጥሪያችንን እያሰማን የአርበኛ ወንድማችንን አጠቃላይ ሁኔታ በንቃት የምንከታተል መሆናችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

▪️3.የተፈጠረውን አሳዛኝ ሁኔታ በማባባስ የአማራን ህዝብን ለማተራመስና ሰላም ለመንሳት፣ክልሉ ያለበት ሁለንተናዊ ችግር ሳያንስ የሁከት ቀጠና ሆኖ እንዲቀጥል የሚፈልጉ ጎራ ለይተው የሚናከሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ ህዝባችንም ይህንን ነቅቶ እንዲጠብቅ፣ አንድነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልና ከህልውና ትግሉ ላይ አይኑን እንዳያነሳ በአፅንኦት እናሳስባለን፡፡

"ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው፡፡"

የምስራቅ አማራ ፋኖ

አሁን ከአባ ሳሙኤል እስር ቤት መመለሴ ነው። በትግል ሂደትም በመርህ ደረጃም ከምለያየው ወንድሜ አሳየ ደርቤን ጠይቄ መመለሴ ነው! ዛሬ ከሰዓት ወይንም ነገ ለመጠየቅ የምትሄዱ ሰዎች ካላችሁ ...
24/09/2022

አሁን ከአባ ሳሙኤል እስር ቤት መመለሴ ነው።

በትግል ሂደትም በመርህ ደረጃም ከምለያየው ወንድሜ አሳየ ደርቤን ጠይቄ መመለሴ ነው! ዛሬ ከሰዓት ወይንም ነገ ለመጠየቅ የምትሄዱ ሰዎች ካላችሁ የመፅሃፍ ችግር እንደለባቸው ከጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ ጋር ገልፆልኛል! የምትችሉ ካላችሁ መፅሃፎችን ይዛችሁ ሂዱ! ይሄው ነው።
Written via solomon Alameins.

ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴን በጠዋት ሰባታሚት ተገኝተን ጎበኘነው። ከሁሉም አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች አርበኛውን ለመጠየቅ ወረፋ ተሰድረዋል። ፍተሻውን አልፈን ወደ ውስጥ ስንገባ አርበኛ...
24/09/2022

ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴን በጠዋት ሰባታሚት ተገኝተን ጎበኘነው። ከሁሉም አካባቢዎች የተሰባሰቡ ወጣቶች አርበኛውን ለመጠየቅ ወረፋ ተሰድረዋል። ፍተሻውን አልፈን ወደ ውስጥ ስንገባ አርበኛው ልክ እንደባለቅኔ ቀደምቶቹ ወንበር ዘርግቶ ጠያቂዎቹን ፈገግታ እየመገበ ወኔ ያስዘርፋል።

የአርበኝነት መዓዛውን ታጥነው የሚወጡ ውርዝው ሁሉ ፊታቸው ወዝቶ ሲወጡ ተመልክተናል። ስንገባ እንደሁልጊዜው በፈገግታ ተቀበለን። በርቱ ብሎን በርትተን ተመለስን። ከወጣን በኋላ አንድ ወቅት ለእንዲህ ዓይነት «ደግ ቀን» የከተብናትን አስታውሰን ፈገግ አልን። አብረን ፈገግ እንበል😃

የሚስቅ ሰው…
ብፁዕ ነው፣
እግዜር የቀደሰው፣
ጥርሱ ያከበረው፡፡
በድቅድቅ ጨለማ…
ሳቁን እየሞቀ፣
ብሶቱን ያመቀ፡፡
በመከራ መሀል…
በፈገግታ ምሽግ፣
ሀዘኑን ‘ሚሸሽግ፡፡
በፈተና ጊዜ…
በጥርሱ ብልጭታ፣
ክፉን ድል ሚመታ፡፡
የሚስቅ ሰው…
ፃድቅ ነው!

መልካም ቅዳሜ!
ክርስቲያን ታደለ

የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነትን የሚዘክር ሀውልት ተመረቀ።የጋሞ አባቶች እርጥብ ሳር ይዘው ሰላም ያወረዱበትን የሠላም እሴት  የሚዘክር ሀውልት ምርቃት ተከናውኗል።በወጣቱ ቀራፂ ዋሲሁን ለ...
24/09/2022

የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌትነትን የሚዘክር ሀውልት ተመረቀ።
የጋሞ አባቶች እርጥብ ሳር ይዘው ሰላም ያወረዱበትን የሠላም እሴት የሚዘክር ሀውልት ምርቃት ተከናውኗል።
በወጣቱ ቀራፂ ዋሲሁን ለገሰ የተሰራው ሀውልት 4 ሜትር ከ70 ሴንቲሜትር ርዝማኔ ሲኖረው ሙሉ በሙሉ በፋይበር ግላስ መሰራቱ ተገልጿል።

አጠቃላይ ስራውን ለማጠናቀቅ አራት ወራት የፈጀ ሲሆን በምረቃ በዓሉ የፌዴራል ፣የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የሐገር ሽማግሌዎች ተገኝተውበታል።

24/09/2022
"የነቁ እና ለአማራ ህዝብ መኖር የጀመሩ በሙሉ የዘመነ ካሴ አይነት ፈተና እንደሚገጥማቸው የታወቀ ነው" ጌትነት ይርሳው በዛሬው ዕለት ባህርዳር ከሚገኘው ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በመሄድ በእውቀ...
24/09/2022

"የነቁ እና ለአማራ ህዝብ መኖር የጀመሩ በሙሉ የዘመነ ካሴ አይነት ፈተና እንደሚገጥማቸው የታወቀ ነው" ጌትነት ይርሳው

በዛሬው ዕለት ባህርዳር ከሚገኘው ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በመሄድ በእውቀት፣ ህዝባችን ላይ የተደቀነውን ብርቱ ፈተናን በጥልቀት በመረዳት እና የአባቶቻችን መንፈስ በመውረስ ብቅ ያለውን ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሴን አግኝቸዋለሁ።

ለማለት የምችለው በአሁናዊ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ዘመነ ብቻ ሳይሆን የአማራ ህዝብ በደል ከልብ ዘልቆ የሚሰማቸው፣ የነቁ እና ለህዝብ መኖር የጀመሩ እህት እና ወንድሞቻችን ሁሉ እንዲህ አይነቱ ፈተና እንደሚገጥማቸው ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው።

ሀሳብና መንገዳችን የሚጠሉትን ሰበባ-ሰበብ ፈልጎ ከመጥላት ይልቅ የሚጠሉብንን መጥላት ላይ ብናተኩር ብዙ ችግሮቻችን በተቀረፉ ነበር።

ለማንኛውም ዙሪያውን በችግር ክምር የተከበበው አማራው ወገናችን፣ በአንድነት መካሪ፥ አንድ ቃል ተናጋሪ ይሆን ዘንድ ልዩነቶቻችንን በውይይት እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ መፍታት የተሻለ አማራጭ መሆኑን በማመን ቆም ብለን ማሰብ ብንችል መልካም ነው እላለሁ።

ፋኖነት የአባቶቻችን አኩሪ ዕሴት!

Address

Riverland
Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guang Intercept ጓንግ ኢንተርሴፕት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share