20/12/2024
የግብር ግዴታን በውዴታ መፈጸም የህብረተሰቡን ዘርፈ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ለማሳካት ያለው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ በመሆኑ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አደረጃጀቶች ለተግባራዊነቱ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ፣
ታህሳስ 11/2017 ዓ/ም
የከምባታ ዞን ገቢዎች መምሪያ በታክስ ህግ ተገዥነት ለማስፈን ከተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር የምክክር መድረክ በዱራሜ ከተማ በዞኑ ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የከምባታ ዞን ዋና አስተዳደሪ የተከበሩ ዶክተር ዳዊት ለገሰ እንደገለጹት ሁለንተናዊ የልማት እንቅስቃሴያችን ሙሉ የሚሆነው ገቢ ስንሰበስብ ነውና ሁላችንም ተቀናጅተን በመስራት የዞኑን የገቢ አቅም በማሳደግ የተጀመሩ እንድሁም የታቀዱ ልማቶችን ተግባራዊ ማድረግ አለብን በማለት አሳስበዋል።
ገቢ አሰባሰብ ላይ የሚስተዋለውን የግንዛቤ ክፍተቶችን በመሙላት በራሳቸው ፈቃድ የሚጠበቅባቸውን መክፈል ስገባቸው ከመክፈል ይልቅ መሰዎርን የሚፈልጉ ግለሰቦች እየታዩ በመሆኑ ችግሩን ግንዛቤን በመፍጠር ተገቢ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዳዊት ለገሰ ገልጸዋል።
የታክስ እና የግብር ስወራ በመፈጸም የማይገበውን ለመጠቀም መሞከር ትክክል ባለመሆኑ ሁሉም ግለሰብ ተጠያቂ የሚያደርግ ጉዳይ በመሆኑ ከዚህ አስተሳሰብ እና ተግባር መውጣት ያስፈልጋል ብለዋል።
የሚንመኘውን እና የሚናልመውን ልማት ገቢ ካልሰበሰብን ማሳከት አንችልም ያሉት አስተዳዳሪው በአንዳንድ አከባቢዎች መሰብሰብ ያለባቸው ገቢዎች ባለመሰብሰባቸው ሚክኒያት ደመወዝ መክፈል ያለመቻል ይስተዋላል ብለዋል። በአንዳንድ ነጋዴዎች አልፎም ከባለሙያው የሚስተዋሉ የስነምግባር ጉድለቶች እንዲሁም ሸማቹ ደግሞ ግብይትን በደረሰኝ ያለመገበያየት ችግሮች ይታያሉና በየአከባቢው መወያየት እና ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
ደረሰኝ ባለመስጣት ምክኒያት ለመንግሥት መግባት ያለበት ገቢ በግለሰቦች ኪስ እንድውል መደረግ የማይገባውን ጥቅም እንዲያገኝ ማድረግ በመሆኑም ግንዛቤ መፍጠር በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ህብረተሰባችንን ማስተማር እና ለገቢ መቆርቆር እንድችሉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የከምባታ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሪት ሠናይት ለገሰ እንደገለጹት ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፍል የማህበረሰቡን የመልማት ፍላጎትን ለማሳለጥ እና አገልግሎት የሚሰጡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ደመወዝ በወቅቱ በመክፈል የትምህርት፣ የጤና፣ የሰላምና የዳህንነት እንዲሁም ሌሎችም ተቋማት ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ አጋዥነቱ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
ገቢ ከመሰብሰብ አንፃር ደረሰኝ አሰጣጥ ችግር በስፋት የሚታይ ችግር መሆኑን የገለጹት የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሪት ሰናይት ለገሰ ችግሩን ለመቅረፍ ከሻጩ በተጨማሪ ሸማቹም ተጠያቂ የሚሆንበት ስርዓት የተዘረገ በመሆኑ ለየትኛውም ለተገለገሉበት አገልግሎት ደረሰኝ መውሰድን ልምድ መደረግ እንዳለበት፣ ህገ-ወጥ የንግድ ስርዓትን ህጋዊ ማድረግና አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድና ከንግድ ከፈቃድ ውጭ የሚሰሩ አካላትም እርምት የማድረግ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ከሀይማኖት ተቋማት የተገኙ አካላት ግብር መክፈል ሃይማኖታዊ ግዴታም ጭምር መሆኑን በሃይማኖታዊ አስተምሮት ለምዕመናን ግልጽ በማድረግ እና ከተለያዩ ገቢ ከሚሰበሰበው ምንጮች ግብር በመክፈል የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች እንዲሳኩ ግምባር ቀደም አርዓያ መሆን አስፈላጊ መሆኑን ወ/ሪት ሰናይት ለገሰ ገልጸዋል።
ገቢን መሠዎር፣ ሀሰተኛ ደረሰኝ የመጠቀም ሙካራ፣ የቫት ደረሰኝ አለመስጠት፣ የገቢ ሴክተሩ የባለሙያዎችም የቁርጠኝነት ችግር፣ የገቢ ግብር ትመና የፍትሐዊነት ችግር ወዘተ በገቢ አሰባሰብ ሂደት የሚስተዋሉ ችግሮች በመሆኑ ሁሉም አካል ችግሩን ለመፍታት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበት የመምሪያው ኃላፊ ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይ ለተገኙ አካላት በአቶ ጴጥሮስ ፊጣሞ የከምባታ ዞን ገቢ መምሪያ የታክስ ስልጣናና ኮሙንዩኬሽን ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አማካይነት የውይይት ሰነድ ቀርቦ በመድረኩ ላይ የተገኙ አካላት የዞኑ ገቢ መምሪያ ማኔጅመንትና ባለሙያዎች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የገቢ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከሁሉም መዋቅር የተገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ የመምህራን ማህበር ሊቀመንበር፣ የትምህርት መምሪያ ሀላፊና ሌሎችም ተሳታፊዎች አካላት ሀሳብና አስተያየት ሰጥተው ለቀጣይ ተልዕኮ በመውሰድ መድረኩ ተጠናቋል።
የከምባታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ታህሳስ 11/2017 ዓ/ም
ዱራሜ