14/12/2024
🌷🌷🌷የዛሬ ውይይታችን አበይት ጉዳዮች እና ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው ።🌹🌹🌹
""""""""""""""""""""""""""
🌷🌷የመጀመሪያ ዋነኛ መወያያ ርዕስ 🌷🌷
ውጭ ለሚገኙ የትምህርት ቤቱ ደጋፊዎች ሲም እንዲወጣ እና ገቢ ማሰባሰብ እንዲችሉ ለማመቻቸት የሚል የነበረ ሆኖ ።
በተደረገ ከፍተኛ ክትትል እስከ ቴሌ ዋናው መስሪያ ቤት ድረስ ጠይቀን በሲም ካርድ የተሰበሰበን ካርድ ወደ ገንዘብ ለመቀየር የሚያስችል አሰራር የሌላቸው ሲሆን በግል በሚደረግ ሽያጭ ደግሞ በኮሚሽን እየተደረገ ይሸጥ ቢባል እንኳን ከሁለት ሺህ እና ሦስት ሺህ የካርድ ሽያጭ በላይ ማከናወን የማይቻል በመሆኑ እንደ አቅጣጫ ያስቀመጥነው ውጭ ያላችሁ ሁሉ
ግዜ ስላለን ወደ ፊት ቃል በመግባት ማሰብስ እና በእናንተ ኮሚቴዎች በኩል እያደረጋችሁ ማሰባሰብ እና እዚያው ውጭ ላይ ጨርሳችሁ ወደ ገንዘብ በመቀየር መላክ የምትችልበት መንገድ ካለ ብታመቻቹ የሚሻል እንደሆነ ታምኗል ።
በመሆኑ ይሄ በእንዲህ እንዳለ
ሌሎች ጥያቄዎች ደግሞ
👉ደብዳቤን በተመለከተ በፍጥነት ወደሚመለከተው ሁሉ የቅርቦችን በአካል ሩቅ ያሉትን በፖስታ እና በኛ ሰዎች አማካይነት በቅርቡ ተደራሽ በማድረግ ይበተናል።
👉 ሃምሳኛ ዓመቱ የሚከበርበትን ቀን የቀድሞ ተማሪዎች በአብላጫ ድምፅ ተስማምተው ቀኑን እንዲወስኑ ክፍት ተደርጐላቸዋል ።
👉የቲሸርት ህትመት በተመለከተ የሀምሳኛ ዓመት አከባበር ቀን እንደተወሰነ ቀን እየቀረበ ሲሄድ የቲሸርት ፈላጊዎችን ብዛት እና ቁጥር በማየት እንዲታተሙ
በራሪ ፅሑፎች በቅርቡ እየታተሙ ለታክሲ አሽከርካሪወች ለነጋዴ እና ለሱቅ እንዲሁም ሰው ተደራሽ የሚሆንበት ቦታዎች ላይ የሚሰራጩ ይሆናል
👉ኮሚቴዎች እና የስራ ድርሻቸውን በዚህ ገጽ ይገልፃሉ
👉የአሰራር ቅደም ተከተሎችን የትምህርት ቤቱን ሃምሳኛ ዓመት አከባበር ቀንን በመመርኮዝ Action plan proposal ይቀረጻሉ
👉ገቢ የሚሰበሰብበት ዋናው የንግድ ባንክ አካውንት በዝግ ያለምንም ወጪ ገቢ እያስተናገደ ይቀጥላል ።
👉በማቴሪያል ለሚሰበሰብ የዓይነት ድጋፍ ግልጽ መከታተያ ፎርም በማዘጋጀትበየቀኑ ለሚጠይቅ አካል መልስ እንሰጣለን ።
🦋ከውጭ ገንዘብ ለመለገስ ቅድሚያ በቃል ለመግባት ላሰባችሁት በሙሉ የብር መጠን እና ሙሉ ስም በማሳወቅ በማስመዝገብ የሚቻል መሆኑን ኮሚቴዎች በመነጋገር ውሳኔ ላይ ደርሰዋል ።
እናመሰግናለን ።
የገራዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ።
ኮሚቴወች
ቀን ቅዳሜ 05-04-2017 ዓ.ም
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋