meskan media network

meskan media network meskan media network is an online media, focuses on political and social matters. This is official page of meskan media network
(3)

18/04/2024
በበላህ ገብር... በሰማህ መስክር!ከእለታት አንድ ቀን፤ በአንድ የተንጣለለ መስክ ላይ አንዲት  በግ ከነግልገሏ ሳር በመጋጥ ላይ ሳሉ፤ አንድ ግዙፍ ንስር-አሞራ በሰማይ እያንዣበበ፣ በተራበና...
17/04/2024

በበላህ ገብር... በሰማህ መስክር!

ከእለታት አንድ ቀን፤ በአንድ የተንጣለለ መስክ ላይ አንዲት በግ ከነግልገሏ ሳር በመጋጥ ላይ ሳሉ፤ አንድ ግዙፍ ንስር-አሞራ በሰማይ እያንዣበበ፣ በተራበና በጎመዠ ስሜት፣ ከአሁን አሁን ወርጄ ልብላ እያለ ግዳይ - ሊጥል ያስብ ጀመር፡፡ጅው ብሎ በመውረድ ሊውጥ - ሊሰለቅጥ በሚልባት የመጨረሻ ቅፅበት ላይ፤ ድንገት አንድ ሌላ የሱው ብጤ ግዙፍ ንስር መጣ፡፡

ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ
https://www.meskanmedia.com/post/በበላህ-ገብር-በሰማህ-መስክር

ከእለታት አንድ ቀን፤ በአንድ የተንጣለለ መስክ ላይ አንዲት በግ ከነግልገሏ ሳር በመጋጥ ላይ ሳሉ፤ አንድ ግዙፍ ንስር-አሞራ በሰማይ እያንዣበበ፣ በተራበና በጎመዠ ስሜት፣ ከአሁን አሁን...

ችግርህ ላይ ሳቅበት (በሚፍታ ሸምሱ)የሚያጋጥመንን ችግር ከእኛ በታች እንደሆነ ጠንካራ መንፈስ በመገንባት በተግባር እያቀለልን እናሳየው ፤ ጌታችንን እንመነው መንፈሰ ጠንካራም እንሁን።በድሮ ...
16/04/2024

ችግርህ ላይ ሳቅበት

(በሚፍታ ሸምሱ)

የሚያጋጥመንን ችግር ከእኛ በታች እንደሆነ ጠንካራ መንፈስ በመገንባት በተግባር እያቀለልን እናሳየው ፤ ጌታችንን እንመነው መንፈሰ ጠንካራም እንሁን።

በድሮ ግዜ ሁለት የንጉስ አገልጋዮች ጥፋት ማጥፋታቸውን ተከትሎ የንጉሱ ችሎት በማስቀረብ ሁለቱም አገልጋዮች መርዝ ጠጥተው እንዲገደሉ ንጉሱ ያዛል።

በዚያ መሰረት ለሁለቱም አገልጋዮች በዋንጫ ተቀድቶ ተሰጣቸውና የተቀዳላቸውን ቢጠጡም አንደኛው ወድያውኑ ተንፈራፍሮ ሲሞት ሌላኛው ግን አልሞተም....

ለካ ንጉሱ ሊቀጣቸው ሳይሆን ማን መንፈሰ ጠንካራ እንደሆነ ለመፈተን አስቦ ኖሯል ንፁህ ወይን ተቀድቶ እንዲሰጣቸው ያስደረገው

አየህ አንደኛው አገልጋይ ፈተናውን ማለፍ አቅቶት ገና ለገና መርዝ ጠጥቶ እንደሚሞት ሲነገረው ልቡ እና መንፈሱ ቀድሞ በመሞቱ ምንም መርዝ በሌለበት ወይን ጠጥቶ ተንፈራፍሮ የሞተው

ብዙዎቻችን በየቀኑ በሚገጥሙን ጥቃቅን የህይወት ውጣውረዶች የተነሳ ምንም የሚገድል ነገር በሌለበት እራሳችን ላይ አለም የተደፋብን አድርገን በማሰብ ቀድመን እንሞታለን ፤ መታረም አለበት።

የሰው ልጅ ጉልበት ስላለው ብቻ ኪልማንጀሮ ተራራን መውጣት አይችልም ፤ ተራራውን በቀላሉ መውጣት የሚችለው ቅንነት እና እችላለሁ የሚል ልበ ሙሉነት ያለው የመንፈሰ ጥንካሬ ሲገነባም ጭምር ነው።

ቅን ፣ አውንታዊ እሳቤ ፣ ልበ ሙሉና መንፈሰ ጠንካራ ስትሆን ግዙፉን ተራራ ሜዳ ሆኖ እንዲሰማህ ማድረግ ትችላለህ።

የመንፈስ መላሸቅን ተከትለው የሚመጡ የሰነፍ በሽታ የሚባሉት like ቂመኛ ፣ በቀለኛ ፣ ክፉ ፣ ነገር አዋሳጅ ፣ እርስበርስ አጣይ ፣ ነገር አቀሳሳሪ ፣ በሰው ተረማምደው የሚያልፉ የፓለቲካ ደላላ ፣ የራስ የህይወት ግብ አጥተው ሴረኝነትን ማስፈፀምያ በማድረግ መንፈሳቸው የላሸቀባቸው እንኳን ተራራው ሜዳ ሊሆንላቸው ቀርቶ ሜዳው ተራራ ሆኖባቸው ገናለገና ተራራውን እንዳዩት ሀሞታቸው እየሞተ አስቸግሯቸው ሽንፈታቸውን ለመደበቅ እያሰቡ ሌላ ተራራ ለመውጣት የሚጥርን ጠልፈው በመጣል ሁላችንም አንድ አይነት ነን ፕፕፕ የሚያሰኘው የጅል መፅናኛ ወይም me too falacy የሚባል የስነልቦና ቅርቃር ውስጥ ሲገቡ የሚታዩት...

እንደዚህ አይነት ቆሻሻ የሆኑ አፍራሽ ስንፍና ወለድ ቅራቅንቦ ዝንባሌዎች ከሰብኮንሽየስ ማይንዳችን ስናስወግድ በቃላት መግለፅ የሚቸግር አዲስ የሆነ ብሩህ አለምን አስሰህ ያገኘህ እስኪመስልህ ድረስ ካልተሰማህ ውሸታም በለኝ።

ውዷ እህቴ/ወንድሜ

ሁልህም የራስህን ተራራ ድል እያደረግክ ነው ዛሬ ላይ የተገኘኸው ቢሆንም ግን ህይወት አንድ ተራራ ብቻ አይደለም ያላት አንዱን ስትጨርስ ሌላ ይጠብቅሃል ተራመድ አትቁም።

በህይወት መንገድ ችግር ወይም ፈተና ሊገጥምህ ይችላል ምንም ማለት አይደለም ባንተ አልተጀመረም ፤ የችግር አቀባበል ስርዓትን ማወቅና ማሳመር ነው ያለብን ፤ ችግሮች የሚጎዱህ እንዲጎዱህ ስትፈቅድላቸው ብቻ እንደሆነ እርግጠኛ ሁን።

ችግሮች/ፈተናዎች ሲገጥሙህ በተለይ ስሜትን የሚነኩ ሲሆን ምድር ላይ ያለ ቁስ ቢሰበሰብ የማይጠግናቸው እንደመሆናቸው መጠን በምንም ተዓምር በሌሎች ለመጎዳት የማይፈቅድ ጠንካራ ስነ-ልቦና ልትገነባ ይገባል።

ታላቅ ግብ ምንግዜም ቅንነት ፣ ሰዎችን መውደድ ፣ አውንታዊ አስተሳሰብ ፣ አድማሳዊ እይታን የሚያውቅና እይታውን የሚመጥን የመንፈስ ጥንካሬ ዝግጁነት ያለው አላሚነት እንደሚሻ ብቻ ሳይሆን ታላቅ ግብ ቀርፆ መጓዝ አልጋ በአልጋ እንዳልሆነም ያውቃሉ።

ችግሮቻችን የቱንም ያህል የገዘፉ ቢሆኑ የፈጠረንና መቼም የማይተወን አምላክ ክንዶች ከችግሮቻችን እልፍ አእላፍ በላይ የገዘፉና የበረቱ መሆናቸውን ማመንን አትርሳ።

በጭለማ እየሄዱ ጅብ ነገረኛ ነው ይላሉ!ከዕለታት አንድ ቀን ድመት አንድ ጫካ ውስጥ ቀበሮ ታያለች፡፡ ከዚያም ለራሷ እንዲህ ትላለች፡-“ቀበሮ በጣም ቀልጣፋ ነው፡፡ ብዙ ልምድ ያለው ነው፡፡ በ...
15/04/2024

በጭለማ እየሄዱ ጅብ ነገረኛ ነው ይላሉ!

ከዕለታት አንድ ቀን ድመት አንድ ጫካ ውስጥ ቀበሮ ታያለች፡፡ ከዚያም ለራሷ እንዲህ ትላለች፡-

“ቀበሮ በጣም ቀልጣፋ ነው፡፡ ብዙ ልምድ ያለው ነው፡፡ በሰፊውም የተከበረ ነው፡፡ ስለዚህ መልካም ሰላምታ ላቀርብለትና ልቀርበው ይገባል”፡፡ ቀጥላም፤ “እንደምን አደርክ አያ ቀበሮ! እንዴትስ ከርመሀል? ለመሆኑ ሁሉ ነገር በጣም በተወደደበት በዚህ በአሁኑ ጊዜ ኑሮን እንዴት ተቋቋምከው?”

ይሄኔ ቀበሮ በጣም እየተኩራራ ተጎማለለ፡፡ ድመቷንም ሽቅብ ቁልቁል እያየ ገረመማት፡፡ ከኩራትና ከእብሪቱ የተነሳም ለተጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ብዙ ጊዜ ፈጀበት፡፡ በመጨረሻም እዲህ አላት፡-

ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ የሚከተለው ሊንክ ይጫኑ

https://www.meskanmedia.com/post/በጭለማ-እየሄዱ-ጅብ-ነገረኛ-ነው-ይላሉ

ከዕለታት አንድ ቀን ድመት አንድ ጫካ ውስጥ ቀበሮ ታያለች፡፡ ከዚያም ለራሷ እንዲህ ትላለች፡-“ቀበሮ በጣም ቀልጣፋ ነው፡፡ ብዙ ልምድ ያለው ነው፡፡ በሰፊውም የተከበረ ነው፡፡ ስለዚህ .....

ሀገር (ጋሻው ሙሉ)በህብር፣ በደቦ፣ ባንድ ተደጉሶከተመሰረተ ከቆመ ምሰሶጥራናው ተጥሎ ከዞረ ማቶቱጠብቆ ከታሰረ ከላይ ጉልላቱአንድም የሳር ክዳን ሰበዝ ካልመዘዙማገር ከማገሩ፣ ዙሪያ ካጠበቁ፣ ...
15/04/2024

ሀገር (ጋሻው ሙሉ)

በህብር፣ በደቦ፣ ባንድ ተደጉሶ

ከተመሰረተ ከቆመ ምሰሶ

ጥራናው ተጥሎ ከዞረ ማቶቱ

ጠብቆ ከታሰረ ከላይ ጉልላቱ

አንድም የሳር ክዳን ሰበዝ ካልመዘዙ

ማገር ከማገሩ፣ ዙሪያ ካጠበቁ፣ አብረው፣ ከተጓዙ

በፍቅር ከዋሉ በፍቅር ካደሩ

ባንድ እጅ ከበሉ ባንድ ከዘመሩ

ዳስ፣ ድንኳን ተጥሎ «በእልልታ» ታጅቦ

ጉተና ተነቅሶ፣ ጃኖ ተደርቦ፣ ብሎ «ሎጋው ሽቦ»

ሀገር ይሞሸራል!!!

ሀገርም ይዳራል!!!

ሀገርም ይኳላል!!!

ሀገርም ያገባል!!!፡፡

በህብር፣ በደቦ፣ ባንድ ተደጉሶከተመሰረተ ከቆመ ምሰሶጥራናው ተጥሎ ከዞረ ማቶቱጠብቆ ከታሰረ ከላይ ጉልላቱአንድም የሳር ክዳን ሰበዝ ካልመዘዙማገር ከማገሩ፣ ዙሪያ ካጠበቁ፣ አብረው.....

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር.ያውቁ ኖሯል.....?በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆ...
15/04/2024

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር.ያውቁ ኖሯል.....?

በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር......

በ 2ተኛ የኢጣሊያን ወረራ ዘመን በአድዋ በሱሎዳ ተራራ ፊት ለፊት ላይ በፋሺስት ወታደሮች የተገነባው ይህ ሃውልት ቁመቱ 4.80 ሜትር ከፍታ የነበረው ሲሆን ፤ የጣሊያን ወታደሮች በወቅቱ የዚህ ሐውልት በቦታው የመገንባታቸው ዋንኛው ዓላማ እና ለማስተላለፍ የፈለጉት መልዕክት:-

➻ በ 1888 ዓ.ም ላይ የደረሰባቸውን ሽንፈት በውስጣቸው ለነበረው ቁጭት እና እፍረት ማካካሻ ይሆናል ብለው በማሰብ እንዲሁም በሃጉረ አፍሪካ ለነበሩት ለሌሎቹ የቀኝ ገዢዎች የአውሮፓውያን ሃገራት የጠንካራነት ማሳያ የሞራል ማበረታቻ ምልክት ይሆናል በማለት ነበር ከ 40 ዓመት በፊት ሽንፈታቸው ከተጎነጩባት ቦታ ላይ በወርሃ የካቲት 1928 ዓ.ም ላይ ገንብተው ያቆሙት።

ሆኖም ግን አሁን ሐውልቱ በቦታው የለም ሀገራችን ከፋሺስት ጣሊያን ነፃ ከሆነች በኋላ በቦታው ምንም አይነት የሐውልቱ አሻራ እና ፍርስራሽ እንዳይኖር ተደርጎ ሊፈረስ ችሏል።

ክብርና ሞገስ ከወራሪ ነፃ ሀገር ላስረከቡን ጀግኖች አርበኞቻችን

https://www.meskanmedia.com/post/በአድዋ-ተራራዎች-ላይ-የአንባገነኑ-መሪ-የቤኒቶ-ሙሶሊኒ-የፊት-ቅርፅ-ሐውልት-ቆሞ-እንደነበር-ያውቁ-ኖሯል

ምንጭ - አዲስ አድማስ

ይህን ያውቁ ኖሯል.....?በአድዋ ተራራዎች ላይ የአንባገነኑ መሪ የቤኒቶ ሙሶሊኒ የፊት ቅርፅ ሐውልት ቆሞ እንደነበር......በ 2ተኛ የኢጣሊያን ወረራ ዘመን በአድዋ በሱሎዳ ተራራ ፊት ለፊት ላይ...

አባቷ፣ ወንድሟ እና ባሏ የተገደሉባት ምንትዋብ የተሰኘች ሴት ቴዎድሮስን"ጠጅም አያምረኝ ድሮ ጠጥቻለሁሥጋም አያምረኝም ቋንጣ ሰቅያለሁቢሻኝ ከወንድሜ ካ'ባቴ እበላለሁሺ ብረት በግራው ሺ ብረት...
13/04/2024

አባቷ፣ ወንድሟ እና ባሏ የተገደሉባት ምንትዋብ የተሰኘች ሴት ቴዎድሮስን

"ጠጅም አያምረኝ ድሮ ጠጥቻለሁ
ሥጋም አያምረኝም ቋንጣ ሰቅያለሁ
ቢሻኝ ከወንድሜ ካ'ባቴ እበላለሁ
ሺ ብረት በግራው ሺ ብረት በቀኙ
ሺ ፈረስ ከኋላው ሺህ ፈረስ ከፊቱ
ይህን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሻጭ እናቱ
አንድ እግር በርበሬ መንቀል ተስኗችሁ
አቃጥሎ፣ ለብልቦ፣ ፈጅቶ ይግደላችሁ
ይህንን ሲሰማ ያጓራል ላመሉ
ማናት ቢላችሁ ምንትዋብ ናት በሉ"

እያለች በግጥምም፣ በንግግርም ትሰድብ ታሳቅል ነበር፤ ይህ ወሬ ታዲያ ንጉሡ ጆሮ ደርሶ ተይዛ ቀረበች

"እስቲ ያልሽውን እዚህ እፊቴ ድገሚው!" ቢሏትስ
አንድ ሳታስቀር የስድብ ግጥሟን አወረደችው፥ ቴዎድሮስ ይኸነዜ
"በእኔ ኪሳራ ገነት ልትገቢ?" ብለው ስቀውባት ይልቁንስ እድሜ ዘመኗን ሙሉ ቀለብ እየተሰፈረላት ምንም ሳይጎድልባት እንድትኖር ወስነው አስለቀቋት፥ ኋላ ባለሟሎች "ምነው?" ቢሏቸው
"ዘመዶቿን ሁሉ ገድዬ ልታሞግሰኝ ኖሯል? ልክ ናት!" አሉ። ምንትዋብ ግን እስከ እለተ ሞታቸው በሄዱበት እየተከተለች ስታሳቅላቸው ኖራ በመጨረሻ በመቅደላ አናት ላይ የቴዎድሮስን በድን ለመቅበር እንኳ እስክታስቸግር አለቅም ብላ ነበር፥ ያኔ ነው

"የትግራይን ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ
የሸዋንም ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ
የጎጃሙን ንጉሥ ሲንቁ ሲንቁ
ወንድ ያለ ራስሁ ገድለውም አያውቁ፥
አባ ግራኝ ሞተ የሆዴ ወዳጅ
የሚያበላኝ ጮማ የሚያጠጣኝ ጠጅ
መቅደላ አፋፉ ላይ ጩኸት በረከተ
የሴቱን አናውቅም ወንድ አንድ ሠው ሞተ
አባቴን፣ ወንድሜን፣ ልጄን ቢገድሉብኝ ነበር መናደዴ
ባሌን ቢገድሉብኝ ነበር መናደዴ
ጨከኑ በራስሁ ይቅር አለ ሆዴ" አለች።

በ Jemal Abdulaziz

በቀላሉ አንታበይ!! (በሚፍታ ሸምሱ)ዓምና በዛሬው ዕለት የFb ትውስታውዱ ወንድሜ!!ነገሮች እንደረጉም ሆነ እንደ ተናጡ አይቀሩም ሁሉም ነገሮች ይቀያየራሉ ፤ የማይቀያየር ነገር ቢኖር እውነት...
11/04/2024

በቀላሉ አንታበይ!! (በሚፍታ ሸምሱ)

ዓምና በዛሬው ዕለት የFb ትውስታ

ውዱ ወንድሜ!!

ነገሮች እንደረጉም ሆነ እንደ ተናጡ አይቀሩም ሁሉም ነገሮች ይቀያየራሉ ፤ የማይቀያየር ነገር ቢኖር እውነትና ሀቅ ብቻ ነው።

የወቅታዊ ሰዎች የውሸት ከበባ ከእውነት ፣ ሀቅ እና ፍትህ እንዳያስወጣህ!ጥንቃቄ አድርግ በቀላሉ አንታበይ።

ይዘህ ስለተገኘህ የውሸት የሚያጨበጭብልህ የያዝከውን ስታጣ ተሽቀዳድሞ የሚወቅጥህ እሱ መሆኑን አትርሳ ፤ ከእውነት ፣ ከሀቅና ፍትህ ጋር በመቆም እንፅና

ወቅታዊ ሰዎች ዘንድ ሺህ ግዜ ጨዋ ብትሆን ፣ ሺህ ግዜ ሀቀኛ ብትሆን አይደንቃቸውም እነሱ ዘንድ ትርጉም ያለው በማንኛውም መንገድ ይዘህ መገኘትህ ብቻና ብቻ ነው።

እነዚህ ሰዎች ዘንድ በማንኛውም መንገድ ይዘህ እስካልተገኘህ ድረስ ሚናህን ማሳነስ(devaluation) መሳለቅና ማጣጣል ስራቸው ነው ፤ የእነዚህ ሰዎች ትችትም ሆነ ማጣጣል ስሜት እንዲሰጥህ አትፍቀድ።

የወቅታዊ ሰዎች ትችት ጤነኝነትና ቀናነት ማረጋገጥ ከፈለክ በሚሰጡህ ሀሳብ ውስጥ የስነ-ምግባር መገለጫ እሴቶች የማይታዩ መሆናቸውንና ፈተናዎች ሲገጥሙህ ደግሞ በተግባር የሚያሳዩት ፅናት አልባነትና የቁርጠኝነት ማጣትን በመታዘብ አረጋግጥ።

ለእነዚህ ሰዎች በማንኛውም መንገድና ሰዎች ላይ ተረማምደህም ይሁን ብቻ ይዘህ ተገኝ ነው የጨዋታ ህጋቸው ፤ ይዘህ እስከተገኘህ ድረስ አንተ ለእነሱ የኮከቦች ሁሉ ኮከብ ነህ ፣ አንደኛ ነህ ፣ ቅዱስ ነህ ፣ ልዩ ፍጥረት ነህ።

እነዚህ ሰዎች ጋር ፈጣሪን መፍራት ፣ ሀቀኝነት ፣ እውነተኝነት ፣ ፍትሃዊነት የሚባል ቁም ነገር የለም ፤ እነርሱ ዘንድ አዋቂነት ማለት ማታለል ፣ መዋሸትና በሌሎች ቁስልና ዋጋ ተረማምዶ ማትረፍ ወ.ዘ.ተ ነው ያለው።

እነዚህ ሰዎች ሺህ ግዜ የከበዱ ቢመስሉ ቀላል የመሆናቸውን እውነታ ሊቀይር የሚችል ተዓምር የለም ፤ እነሱ ማለት ኩፍስፍስ ያሉ አረፋዎች ናቸው ፤

እነዚህ ሰዎች እውነት ፈርጠም ስትል ብን ብለው የሚጠፋ ውሸቶች ናቸው።

ውዷ እህቴ/ውዱ ወንድሜ

ስለ እውነት እንኑር/ለሀቅ እንቁም።

እውነት እንደ ከዋክብት ናት ፤ ከሌሊቱ ጭለማ ጀርባ ካልሆነ በስተቀር አትታይም።

እውነት ዓለም ላይ ካሉ ውብና ማራኪ ፀጋዎች ጋር ትመሳሰላለች።

እውነት በዕለት ተዕለት ህይወታችን ረክተን እንድንኖር እና ተመሳሳይ ደስታን ለሰዎች እንድናካፈል የሚያስተምረን ጥልቅ ደግነት ነው።

ስነ ምግባርህን አይተው የወደዱህ ፣ ያሞገሱህና ያበረታቱህ ሰዎች ዘንድ በአቋራጭ ይዘህ መገኘት አለመገኘትህ ጉዳያቸው አይደለም ፤ እነዚህ ሰዎች ሁልግዜ ካንተ ጋር አሉ ፤ በምንም ሁኔታ አይቀያየሩም።

በአላህ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በአዋቂ ፍጡራኖችም ዘንድ የምንከበረውና የምንወደደው እውነትና ሀቀኝነትን ከፍ ለሚያደርጉ የስነ-ምግባረ እሴቶች ላቅ ያለ ቦታ ስንሰጥ ብቻ ነው።

ጌታችን እኛን የሚወደን ይዘን የተገኘነውን ውጤት ባገኘንበት መንገድ ጤነኝነትና ያገኘነውን ውጤት በመራንበት የስነ-ምግባር ጤነኝነት ላይ ተመስርቶ እንደሆነ በቅጡ መረዳት የላቀ ጥበብን ያጎናፅፈናል።

ውዱ ወንድሜ/ውዷ እህቴ

ሁልግዜ ለስኬትህ ቀጣይነት ፤ ለውድቀትህ መፍትሄ ምትሻ ከሆነ ስራዎችን የመራህበትን ስነ-ምግባር ፈትሽ ይሄን ስናረጋግጥ ጌታችን ይደሰትብንና የእርሱን ውዴታ እናገኛለን ፤ እርሱን ያገኘ ሁሉን ነገር እንዳገኘ ነውና።

በህልምህና አሁን ላይ ባለህበት ተጨባጭ መካከል ያሉ ስራዎችህ ጥራት ያላቸውና ውጤታማ እንዲሆኑ ከፈለክ ህልምህ ማስገኘት የሚጠበቅበትን ውጤት አላማውን በሚመጥን ስነ-ምግባር ልክ መመራቱን አረጋግጥ።

በመወለዳችንና በሞታችን መሐል ብዙ የማግኘትና የማጣት ዝብርቅርቅ ውጣውረዶችን አልፈናል ፤ እያለፍንም ነው።

የእነዚያን ውጣውረዶች ስም ከፈለክ መሪ ፤ ቱጃር ፣ የከሰረ ፣ የተሳካለት ፣ የወደቀ ፣ የተመራመረ ፣ የነገደ ፣ ያረሰ ፣ የተማረ ፣ ልሂቅ ፣ ደቂቅ ፣ የአለም ገዢ ፣ የቀበሌ ሊቀመንበር ፣ የኔቶ ወታደር ፣ ሚሊሻ ፣ የፔንታጎን ስራ መሪ ፣ ጥበቃ ፣ የICC ዳኛ ፣ የእድር ዳኛ በለው ፈጣሪም የሚጠይቀን በእነዚህ ውጣ ውረዶች ሳይሆን በዋናነት በውጣ ውረዶቹ ሂደት በተከተልነው " የስነ-ምግባር " ጥራት ጉዳይ ነው።

ተግባሮችን በዳበረ የስነ-ምግባር እሴቶች ላይ ተመስርተን በመስራት ከፍታችንን ከማረጋገጥ አኳያ ምን እንመስላለን የሚለውን አሳብ እንይ?

አብዛኛው ችግሮቻችንና እንደ አገር የሚታዩ አገራዊ ምስቅልቅሎቻችን ከስነ-ምግባር ጥራት መጓደል እና ግብረ ገብ ማነስ ጋር የተያያዙ አይደሉም ወይ??

ባህሎቻችን እና እምነቶቻችን ህዝብን ከጥፋት የመታደግ ጉልበት እንዴትና ለምንድን ነው ያነሳቸው????

የእውነት ቤተሰብ ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ ዩኒቨርስቲዎች በተገቢው መልኩ ለስነ-ምግባር እሴቶች ቦታ እየሰጡ ነው??

የስራ ከባቢዎቻችን ላይ የተለጠፉት ታማኝነት ፣ ቅንነት ፣ አሳታፊነት ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት ፣ አገልጋይነት ወ.ዘ.ተ....ተብለው በደማቁ የሚፃፉ የስነ-ምግባር እሴቶች የእውነት እየኖርናቸው ነው ወይ???

አብዛኛዎቻችን ውስጥ ስር ሰድደው የኖሩ ሀገርኛ የስነ-ምግባር እሴቶች ተቋማዊ መልክ ይዘው ሀገራዊ አበርክቷቸው ከፍ ሊል ሲገባ አከርካርካሪያቸው ተመትቶ ሚና አልባ ያደረጋቸው ምንድ ነው???

ስንቶቻችን ነን ከአስተዳደግ ጋር ተያይዞ የተጣባን አፍራሽ የመታበይ እሳቤዎች(negative thought ) መግራት እና የጋራ ሀገርን እያሰብን መንቀሳቀስ የሚያስችለን ኢሞሽናል ኢንተሊጀንስ ያጎለበትነው???እራሳችንን እንጠይቅ።

እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!ኢድ ሙባረክ!!
10/04/2024

እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ!!

 #የአቶ  #ማርቆስ  #ጸጋዬ  #ዱንጋ    #የህይወት  #ታሪክ  #በአጭሩ አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ከአባታቸው አቶ ጸጋዬ ዱንጋ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ በላይነሽ ገ/ማሪያም በ1950ዓ/ም በቀድሞው...
09/04/2024

#የአቶ #ማርቆስ #ጸጋዬ #ዱንጋ

#የህይወት #ታሪክ #በአጭሩ

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ከአባታቸው አቶ ጸጋዬ ዱንጋ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ በላይነሽ ገ/ማሪያም በ1950ዓ/ም በቀድሞው መስቃን እና ማረቆ ወረዳ በምስራቅ እምቦር ቀበሌ ቆቶ ጊዬርጊስ አካባቢ ተወለዱ ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ለወላጆቻቸው የመጀመሪያ ልጅ ሲሆኑ ተጨማሪ ሁለት ወንድሞችን አባታቸው አቶ ጸጋዬ ዱንጋ ወልደዋል ፡፡

በትምህርታቸውም በዘመኑ በአካባቢያቸው ትምህርት ቤት ባለመኖሩ በአካባቢያቸው ከነበሩ እኩዮቻቸው ጋር እስከ ደብረዘይት በመሄድ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ እድሜያቸው ለትዳር ሲደርስ በ1970 ዓ/ም ከወ/ሮ ሙላቷ ምትኩ ጋር ተጋብተው ወግ ማዕረጋቸውን አይተዋል ፡፡ ልጆችም ወልደዋል ፡፡ አቶ ማርቆስ በአጠቃላይ አምስት ወንድ እና አምስት ሴት በድምሩ 10 ልጆችን ወልደዋል ፡፡ ለወግ ለማዕረግም አብቅተዋል ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ በግል ፣ በቤተሰብ እንዲሁም በአካባቢያዊ ጉዳዮች በነበራቸው ተሳትፎ ከሚወደድላቸው ልዩ መገለጫ ውስጥ ሰው አክባሪ እና ሰላምተኛነታቸው ፣ በየትኛውም ቀጠሮ ሰዓት አክባሪነታቸው ፣ ጠንካራ ታታሪ እና ደፋርነታቸው ለሰላም ትልቅ ቦታ ያላቸው መሆኑ ለብዙዎች አርአያ በመሆኑ የሚጠቀስላቸው መልካም ስብዕናቸው ጭምር ነው ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ከግብርና ስራቸው ጎን ለጎን ለረጅም ዓመታት የምስራቅ እንቦር ቀበሌ ሊቀ መንበር በመሆን ህዝብን እና መንግስትን በማገልገል ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ከቀበሌ ሊቀመንበርነት ባሻገር በቀድሞው የመስቃን ማረቆ ወረዳ አስተዳደር ሊቀመንበር ፣ የሀይቆች እና ቡታጅራ አውራጃ ፍርድ ሸንጎ አባል በመሆን ጭምር አገልግለዋል ፡፡

ሁሉ ጊዜ የህዝብ አደራ የሚሰጣቸው አቶ ማርቆስ ጸጋዬ በምርጫ ተወዳድረው የመስቃን ወረዳ ምክር ቤት አባል በመሆን የህዝብ ውክልናቸውን በብቃት ተወጥተዋል ፡፡

በመስቃን ወረዳ ምክር ቤት ውስጥም በተለያዩ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋል ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ከቀበሌ ሊቀመንበርነት እና ከምክር ቤት አባልነት ኃላፊነታቸው በተጓዳኝ በሌሎች በርካታ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን ተወጥተዋል ፡፡

በትምህርት ቤቶች የወመህ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ እንዲሁም አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እንዲሰሩ ከፍተኛ ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ሌላው በጉልህ የሚመሰገኑበት አርአያ ተግባራቸው ለሰላም ያበረከቱት በጎ ስራቸው ነው ፡፡ በተለይም በሰፈር በቀበሌዎች በወረዳ በዞን እና በአገር ደረጃ በተለያዩ የሰላም ሂደቶች በመሳተፍ ሰላም እንዲሰፍን ፣ ችግሮች ሲፈጠሩ በሽምግልና እና በእርቅ እንዲፈቱ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በርካታ መልካም እና አርአያ ስራዎችን ሰርተዋል ፡፡

በቅርቡም በመስቃን እና በማረቆ አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው ችግር በሽምግልና ሰላም እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ሰላም እንዲመጣ ካደረጉ ግንባር ቀደም ሽማግሌዎች ውስጥ አንዱ አቶ ማርቆስ ጸጋዬ ነበሩ ፡፡

በጥቅሉ አቶ ማርቆስ ጸጋዬ በየትኛውም አካባቢ ቤተሰብ ቀበሌ እና ወረዳዎች በሚፈጠሩ ችግሮች እንዲፈቱ ሲጠየቁ ለሰላም ለእርቅ ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት የመነጨ በመሸምገል በማወያየት ጥፋትን በማውጣት ጥፋተኛን በመለየት ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ ከፍተኛ ስራ በመስራት ከፍተኛ ክብር እና እውቅና የተቸራቸው የአገር ሽማግሌም ጭምር ነበሩ ፡፡

አቶ ማርቆስ እስከ ለህዝባቸው አገልግለዋል የአባትነት ፣ የማስታረቅ ፣ ሰላም የማምጣት ፣ የተጣላን የማስታረቅ ፣ ስራን እስከ ህልፈታቸው ሰርተዋል ፡፡

አቶ ማርቆስ ጸጋዬ በቀን 29/7/16 ዓ/ም ከለሊቱ 9 ገደማ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ፡፡

(ከመስቃን ወረዳ አስተዳደር እና የመስቃን ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ገጽ የተወሰደ)

02/03/2024
26/02/2024

ጭንብሉ ይውለቅ

በምስራቅ ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳዎች ውስጥ በህዝብ ውክልና የፖለቲካው ሹመት ወንበር ላይ የተቀመጡ ውስን ግለሰቦች ለግላዊ እና ተራ ፍላጎታቸው ሲሉ ማህበረሰቡን እና አካባቢውን በተለይ ምሁራንን የሚጎዱ ተግባራትን በባለፉት አመታት እንደፈጸሙና ዛሬም ላይ በመፈጸም ላይ እንዳሉ ማህበረሰቡ ጠንቅቆ ያውቃል። ሰንዶም አስቀምጧል። ግና ጉዳይ ገሃድ እንዳይወጣ ወይም ጉዳዩ በገሃድ በማህበረሰቡ መካከል መነሳት አለመቻሉ ወይም የእቤታችን ጉዳይ ወደ ውጪ አይውጣ የሚለው እሳቤ በነዚያ ግለሰቦች የሚፈጸሙት መልካም ያለሆኑ ተግባራት እንዲበዙ አድርጓል።

ግን መዘናጋቱ እና ዝምታው እስከ መቼ ነው?

ምንስ የከፋ እና በጣም መጥፎ እስኪከሰት ነው የሚጠበቀው?

በእኔ አመለካከት ሊከሰቱ የሚችሉ መሰል ጉዳቶችን ለመግታት በየቦታው ተሰግስጎ የሚገኘውን የተኩላ ተኩላነትን ያጠለቀውን ጭንብል በማውለቅ ማጋለጥና ማሳውቅ የግድ ይላል። ጊዜውም አሁን ነው ብዬ አስባለሁ።

ተባብሮ የንጹሃኑን ጉዳይ ከማበላሸት በመተባበር ንጹሃኑን ማገዝና ማዳን እየተለመደ እና እየተተገበረ ቢመጣ ደህና ይሆናል። በፈጣሪም ዘንድ መልካም የሆነ ስራ ሁሉ የተወደደ ነውና።

ኢዱና አህመድ

25/02/2024

"ጥርመቸ" ለመጀመሪያ ጊዜ በመስቃንኛ ቋንቋ በገጣሚ አወል አህመዲን የተዘጋጀ የግጥም መድብል መጽሐፍ የምረቃ ስነስርዓት

20/02/2024

"ጥርመቸ" ያትኬትሙዬ የቁወኘን ቀል ከነው ።
በወህነውታንም እን የመስቃን ጨኘት ዋ የመስቃን ደቦ የኸንኩ በገኝም፣ በሰብም ገኝም ያነኹ አበሮሰና መንገስ 17/2016 በንቡረና ይትኬተሙቡወ ከነው ፣ ዚም ከነ በኺትመይ በቂጦ አደመቅነም ወትረኸቢ ይንመና የኸን።

-----------------//----------------

በገጣሚ አወል አህመዲን ሳሊሃ በመስቃንኛ ቋንቋ የተዘጋጀ "ጥርመቸ" የተሰኘ የግጥም መድብል መጽሃፍ ሊመረቅ የቀሩት ጥቂት ቀናቶች ብቻ ናቸው።
ስለሆነም በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጪ የምትገኙ የመስቃን ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ መጽሐፉ የካቲት 17/2016 ዓም በቡታጅራ ከተማ በሴራና አዳራሽ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት የስራ አመራሮች፣ ምሁራንና ወጣቶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ እና በይፋ ይመረቃል።

በኢትዮጵያ ከወለድ-ነጻ/እስላማዊ ባንኮች የውህደት አስፈላጊነት፡ የተወዳዳሪነት እና ወጪ ቆጣቢነት መንገድመግቢያ፡-ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢስላሚክ ባንኪንግ በመባል የሚታወቀው ከወለድ ነፃ የሆ...
13/02/2024

በኢትዮጵያ ከወለድ-ነጻ/እስላማዊ ባንኮች የውህደት አስፈላጊነት፡ የተወዳዳሪነት እና ወጪ ቆጣቢነት መንገድ

መግቢያ፡-
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢስላሚክ ባንኪንግ በመባል የሚታወቀው ከወለድ ነፃ የሆነው የባንክ ዘርፍ በሥነ ምግባሩና በአሳታፊ አሠራሩ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል። በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የሆነው የባንክ ኢንዱስትሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ቢመጣም በተወዳዳሪነት እና በዋጋ ቆጣቢነት ረገድ አሁንም ፈተናዎች ገጥመውታል። ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያ ውስጥ ከወለድ ነፃ ባንኮች መካከል ውህደት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል።

1. የፋይናንስ መረጋጋትን ያጠናክራል፡-
በኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የሆኑ ባንኮች ውህደት መፍጠር የዘርፉን የፋይናንስ መረጋጋት ለማጠናከር አስተዋፅዖ ያደርጋል። እነዚህ ባንኮች ሀብታቸውን እና እውቀታቸውን በማጠናከር ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን በተሻለ ሁኔታ መቋቋም ይችላሉ። አንድ ትልቅ እና የበለጠ ጠንካራ አካል ብዙ ተቀማጭ ገንዘብ የመሳብ፣ ሰፊ አገልግሎቶችን ለመስጠት እና አደጋዎችን በብቃት ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም ይኖረዋል፣ በዚህም የዘርፉን አጠቃላይ መረጋጋት ያሳድጋል።

2. የተሻሻለ የምርት እና የአገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል፡-
ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የሆኑ ባንኮች ሲዋሃዱ የምርት እና የአገልግሎት አቅርቦታቸውን በማስፋፋት ለሰፋፊ ደንበኛ አገልግሎት ይሰጣሉ። ማህበረሰብ አቀፍ የሆኑ እንደ የቤት ፋይናንስ፣ የመኪና ኪራይ እና የኢንቨስትመንት ምርቶችን ከኢስላማዊ መርሆች ጋር የሚያሟሉ አዳዲስ የፋይናንሺያል ምርቶችን ለማዳበር ሃብቱ እና አቅሙ ይኖረዋል። ይህ ልዩነት ትልቅ የደንበኛ መሰረትን ይስባል እና ከወለድ ነፃ የባንክ መፍትሄ ለሚፈልጉ ግለሰቦች እና ንግዶች ተጨማሪ አማራጮችን ይሰጣል።

3. ወጪ ቆጣቢ እና አዋጭ ነው
ከወለድ ነፃ የሆኑ ባንኮችን መዋሃድ ወደ ምጣኔ ሀብታዊ ደረጃ ያመራቸዋል፣ ይህም የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን እንዲቀንሱ እና ከፍተኛ ወጪ ቆጣቢ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። በቀላሉ ከስድስት CEO እና 75 የቦርድ አባላት ወደ አንድ CEO እና 13 የቦርድ አባላት ይቀንስሳል:: የነዚህን ደሞዝ ጥቅማጥቅምና አበል ማስላት ውጤቱን ማየት ይቻላል:: በተጨማሪም በአንድ ህንፃ ላይ በተለያየ ስም የተከፈቱ አራት ወይም አምስት የባንክ ቅርንጫፎችን ወደ አንድ በመቀነስ አስተዳደራዊ ወጪዎችን በ400% መቀነስ ወይም ተደራሽነቱን በዚያው መጠን ማስፋት ያስችላል:: ይህም ተደጋጋሚ ሂደቶችን ያስወግዳል፣ ስራዎችን ያቀላጥፋል : የሀብት አጠቃቀምን ያመቻቻል። በውጤቱም የተዋሃደው አካል ከተቀነሰ የአስተዳደር ወጪዎች፣ የቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንቶች እና የመሠረተ ልማት ወጪዎች ተጠቃሚ ይሆናል። እነዚህ የወጪ ቁጠባዎች በተወዳዳሪ ታሪፎች እና ክፍያዎች ለደንበኞች ሊተላለፉ ይችላሉ ይህም ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተደራሽ እና ተመጣጣኝ ያደርገዋል።

4. የተሻሻለ የአደጋ አስተዳደር ( risk management)፡-
ውህደት ከወለድ ነፃ ባንኮች የአደጋ አስተዳደር አቅማቸውን እንዲያሰባስቡ እና የበለጠ ጠንካራ የአደጋ አስተዳደር ማዕቀፍ እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል። እውቀታቸውን እና ሀብታቸውን በማጣመር የተዋሃደ አካል አጠቃላይ የአደጋ ግምገማ እና የመቀነስ ስልቶችን ማዘጋጀት ይችላል። ይህም የብድር፣ የገበያ እና የአሰራር አደጋዎችን በብቃት ለመቆጣጠር ይረዳል፣ ይህም በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የሆነው የባንክ ዘርፍ የረዥም ጊዜ ዘላቂነት እና የመቋቋም አቅምን ለማረጋገጥ ያስችላል።

ማጠቃለያ፡-
በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ/ኢስላማዊ ባንኮች መካከል ያለው ውህደት በዘርፉ ያለውን ተወዳዳሪነት እና ወጪ ቆጣቢነትን ለማሳደግ ትልቅ አቅም አለው። የፋይናንሺያል መረጋጋትን ያጠናክራል፣ የምርት እና የአገልግሎት አቅርቦቶችን ያሰፋል፣ ኢኮኖሚን ​​ያሳካል እና የአደጋ አስተዳደር አቅሞችን ያሳድጋል። በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የሆነው የባንክ ኢንዱስትሪ እያደገ በመምጣቱ ስትራቴጂያዊ ውህደት እነዚህን ባንኮች በሀገሪቱ የፋይናንስ ምኅዳር ውስጥ ቁልፍ ተዋናዮች በማድረግ ሥነ ምግባራዊና ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለሰፊው ሕዝብ ማቅረብ ያስችላል።

በተለይ የኡማው ጉዳይ የሚያሳስባቸው ኡለሞች: መሻይኮች: ምሁራንና እና ኡስታዞች በተለያየ ስም በተከፈቱ ባንኮች ማስታወቂያ በመሆን በቦርድ አባልነት በአማካሪነት እንዲሁም በመስራች አባልነት ስም የሚያገኙት ገንዘብ ሳይበግራቸው ባንኮቹ የሚዋሀዱበትን መንገድ መቀየስና ጫና በማሳደር ራሳቸውን ከተጠያቂነት እንዲሁም የማህበረሰቡን ገንዘብ ከኪሳራ የመታደግ ሀላፊነት እንዳለባቸው ማሳሰብ እወዳለሁ::

አቡ ኸጣብ
ከኳታር (ዶሃ)

Abu Khattab

“መስማት በሌለብህ ሰዐት ደንቆሮ ሁን”አንድጊዜ የእንቁራሪቶች ቡድን በጫካ ውስጥ እየተጓዘ እያለ ሁለቱ እንቁራሪቶች ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ ፡፡ ሌሎቹ እንቁራሪቶች በጉድጓዱ ዙሪያ ተሰ...
08/02/2024

“መስማት በሌለብህ ሰዐት ደንቆሮ ሁን”

አንድጊዜ የእንቁራሪቶች ቡድን በጫካ ውስጥ እየተጓዘ እያለ ሁለቱ እንቁራሪቶች ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ ፡፡ ሌሎቹ እንቁራሪቶች በጉድጓዱ ዙሪያ ተሰብስበው ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ባዩ ጊዜ ምንም የመውጣት ተስፋ እንደሌላቸዎ ለሁለቱ እንቁራሪቶች ነገሯቸው ፡፡ ነገርግን ሁለቱ እንቁራሪቶች የሌሎችን እንቁራሪቶች ጩኸትና አጉል ጫጫታ ችላ በማለት ከጥልቁ ጉድጓድ የሚወጡበትን መፍትሄ ማፈላለግ ጀመሩ ፡፡

ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ የሚከተውን ሊንክ ይጫኑ

https://www.meskanmedia.com/post/መስማት-በሌለብህ-ሰዐት-ደንቆሮ-ሁን

አንድጊዜ የእንቁራሪቶች ቡድን በጫካ ውስጥ እየተጓዘ እያለ ሁለቱ እንቁራሪቶች ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ወደቁ ፡፡ ሌሎቹ እንቁራሪቶች በጉድጓዱ ዙሪያ ተሰብስበው ምን ያህል ጥልቀት እን....

የማይቆም ወንዝ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል፤ በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ!የተፈጥሮ አድናቂ ከሆነን የወንዝን ውበት በህሊናችን ለመሳል ባልተቸገርን። ወንዝ ውብት ብቻም ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋ...
08/02/2024

የማይቆም ወንዝ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል፤ በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ!

የተፈጥሮ አድናቂ ከሆነን የወንዝን ውበት በህሊናችን ለመሳል ባልተቸገርን። ወንዝ ውብት ብቻም ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋርም ጥልቅ ግንኙነት አለው። ወንዝ የብዙ ስልጣኔዎች ምንጭ፤ የስነጽሁፎች መጠንሰሻ፤ የፍቅር መጎንጫ ሆኖ በየስነጽሁፉ ተከትቦ እናገኘዋለን። የሰው ልጅ ህይወት በወንዝ ተመስሎ ሲታይ የኑሮዋችን ፍሰት እንዴት እንደሆነ በሶስተኛ አይን ያስመለክተናል።

ስለወንዝ የተለያዩ ድንቅ አባባሎች ተነግረዋል። ለዛሬ መነቃቂያ የመረጥኩት “የማይቆም ወንዝ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል” የሚልውን ነው። አስቡት ከድንጋይ እና ከውሃ የቱ ይጠነክራል? በውሃ የተቦረቦሩ ስንት የድንጋይ አለቶችን አይተናል? ውሃ በምን አቅሙ ድንጋይን ያህል ነገር በስቶ ያልፋል? እውነት ነው ውሃ ድንጋይን የመሰንጠቅ ሃይል አለው። ከድንጋዩ በርትቶ ወይም ከድንጋዩ በላይ ጉልበት ኖሮት ሳይሆን ከድንጋዩ የበለጠ ጽናት ስላለው ብቻ ነው።

ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ https://www.meskanmedia.com/post/የማይቆም-ወንዝ-ድንጋዩን-ሰንጥቆ-ያልፋል-በጉልበቱ-ሳይሆን-በጽናቱ

የተፈጥሮ አድናቂ ከሆነን የወንዝን ውበት በህሊናችን ለመሳል ባልተቸገርን። ወንዝ ውብት ብቻም ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋርም ጥልቅ ግንኙነት አለው። ወንዝ የብዙ ስልጣኔዎች ምንጭ፤ ....

በመስቃንኛ ቋንቋ የመጀመሪያው  #ጥርመቸ (ማስተዋል) የተሰኘው መስቃንኛ የግጥም መድብል መፅሐፍ በቅርብ ቀን ይመረቃል።"ጥርመቸ (ማስተዋል) "ሲንፈ በመስቃንኘ አፍ"
08/02/2024

በመስቃንኛ ቋንቋ የመጀመሪያው #ጥርመቸ (ማስተዋል) የተሰኘው መስቃንኛ የግጥም መድብል መፅሐፍ በቅርብ ቀን ይመረቃል።

"ጥርመቸ (ማስተዋል) "ሲንፈ በመስቃንኘ አፍ"

በአንድ ቀዝቃዛ ምሽት የለየለት ቱጃር _ ያረጀ ያጣ የነጣ ሽማግሌ በውጭ አጋጠመውና የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረለት፦* "ኮት እንኳን አልለበስክም፣ ውጪው አይበርድህምን?"* ሽማግሌውም "ኮት እ...
08/02/2024

በአንድ ቀዝቃዛ ምሽት የለየለት ቱጃር _ ያረጀ ያጣ የነጣ ሽማግሌ በውጭ አጋጠመውና የሚከተለውን ጥያቄ ሰነዘረለት፦
* "ኮት እንኳን አልለበስክም፣ ውጪው አይበርድህምን?"
* ሽማግሌውም "ኮት እደርብ ነበር፣ ዛሬ ግን የለኝም" ሲል መለሰ።
* ቢሊየነሩ፦ "ጠብቀኝ ከቤት ኮት አመጣልሀለሁ"
* ደሀው "በደስታ እጠብቅሀለሁ" የሚል ምላሽ ሰጠ።
* ቢሊየነሩ ቤት እንደገባ በሀሳብና ሥራ ተጠምዶ ደሀውን ረሳው። በቀጣዩ ማለዳ ደሀው ትውስ አለውና ለፍለጋ ወጣ። ይሁንና ሽማግሌው በቅዝቃዜው ሳቢያ ህይወቱ አልፎ ነበር።

* ደሀው ሽማግሌ ከመሞቱ በፊት የፃፈው ማስታወሻ እንዲህ ይነበባል፦ "ምንም እንኳ የሚያሞቁኝ አልባሳት ባይኖሩኝም፤ ብርዱን መቋቋም የሚያስችል አእምሯዊ ጥንካሬ ነበረኝ። በቃልህ ተማምኜ ስለነበር ግን የአእምሮዬ ጥንካሬ ከዳኝ።

* በመሆኑም ለማንፈፅመው ጉዳይ ቃል አንግባ። ለእኛ ብዙም ቁብ ላይሰጠን ይችላል፤ ተስፋ ለሰጠናቸው ሰዎች ግን ዋጋው ታላቅ NEWNA.

ከታዬ ቦጋለ ገጽ የተወሰደ

ሞኝ እንደነገሩት...
07/02/2024

ሞኝ እንደነገሩት...

🚩ተረኛው መጡ! እየሮጡ!~~~~~~~~~~~~~~ እናንተው ሰሞኑን "ማነው ባለሳምንት?" የሚል አርምሞ ካኖርን እነሆ ሳምንትም አልሞላም አቡነ ጴጥሮስ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ መደረጋቸው ተዘገበ...
07/02/2024

🚩ተረኛው መጡ! እየሮጡ!
~~~~~~~~~~~~~~

እናንተው ሰሞኑን "ማነው ባለሳምንት?" የሚል አርምሞ ካኖርን እነሆ ሳምንትም አልሞላም አቡነ ጴጥሮስ ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ መደረጋቸው ተዘገበ።

የተለያዩ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት "ብፁዕ" አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል።
አቡኑ ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል " አሁን አሳፍረው ወደመጣሁበት ወደ አሜሪካ መለሱኝ ፤ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ። " ብለዋል።አክለዉም "የደህንነት ሰዎች ግሪን ካርድህን ብቻ ነው የምንፈልገው ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም በማለት ግሪን ካርዴን ወስደው በሩን ዘጉት !! " ሲሉ ተናግረዋል ነው የተባለው
እኮ የኔ ትዝብት👇
------
መቸም የሀገራችን ነገር እጅጉኑ ግራ አጋቢ ነው፡፡ አንዱ ሌላው ላይ ሲዘምት ቢያንስ "ነግ በኔ!" የሚለዉን ዘንግቶ ነው ፡፡ አቡኑ ከዚህ ቀደም በሌሎች ቄሶች ላይ ተመሳሳይ ነገር ሲፈጸም ይህ ለምን ይሆናል? ያሉት ነገር ስለመኖሩ አልተሰማም! ነገ ለሳቸው ሁሌም ዛሬ ሆኖ ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል፣ ወይንም ሌላ.....
አቡኑ መንግስትን ተደግፈው በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የጦር አዝማች እስኪመስሉ ድረስ የነበራቸውን ሚና በነጌ ሂሳብ አላሰቡትም! የሃይማኖታቸው ተከታይ በሆነው ህዝባቸውና ህጻናት ላይ ያሳዩት ጭካኔ የሌላ እምነት ሰዎችንም ያስገረመ ነበር!
አቡኑ ሙስሊሞች ላይ ድንበር ሲያልፉ ስለ ነገ ምንም አልተጨነቁም!
አቡነ ጴጥሮስ በሃረር ሙስሊሞች ላይ የተሰራዉ ግፍ ላይ ሚናቸው ከፍ ያለ እንደነበር በወቅቱ በገጻችን ስንዘግብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
አቡኑ በስልጤ ቅበት ሙስሊሞች ላይ ሲያላግጡና ሃሰትን ሲመሰክሩ የቅርብ ጊዜ ትዉስታችን ነው!
አቡኑ እንኳን ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመግባት ሊከለከሉ ቀርቶ ኢትዮጵያዊነትን ለፈለጉት እየሰጡ ካልፈለጉት ላይ ደግሞ የሚነጥቁ እስኪመስሉ ድረስ በተለያዩ የብሄር ብሄረሰቦች እና እምነቶች ላይ ድንበር ሲያልፉ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ያኔም እሳቸው ራሳቸዉን የኢትዮጵያዊነት ልክና መመዘኛ አድርገው ያስቡ ስለነበር ሌላው ስለሚያስጨንቀው ነገ አልተጨነቁም፡፡
እነሆ ያ ነገ ዛሬ ሆነና "አይዞህ!" ሲሉት፣ እንደዉም "አሳነስክ!" ሲሉት የነበረው መንግስት ሃገራቸው እንዳይገቡ ከልክሎ ወደመጡበት መለሳቸው የሚለው ዜና ተሰማ ፡፡ ይህ ዜና ነገ ሊከለስና አቡኑም ሃገራቸው ሊመለሱ ይችላሉ ሆኖም ለሁሉም መማርያ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ!
ጎበዝ "ከማንም ጋር ቢሆን በግፍ አትተባበር!" የሚለዉን መርህ መያዝ ያሻል! መንግስትም ቢሆን የኋላ ኋላ የሚያከብረው እየታገሉትም፣ መስዋእትነትን እየከፈሉም ቢሆን "ድንበር አትለፍ፣ ፍትህን አታዛንፍ" የሚሉትን ነው የሚያከብረው፡፡

ያደረገዉን ሲያደርግ "አበጀህ" እያሉ በግፍ የሚያግዙትን አካላት የግፋቸዉን ጥግ ስለሚያይ የኋላ ኋላ ለኔም አይመለሱም ስለሚል እንደሚያስቡት የዘላለም ወዳጃቸው ሆኖ የሚቀጥል ቢመስላቸዉም ጠላት ሆኖ እንደሚጠብቃቸውና በሚችለው ሁሉ ከአይኑ ሊያርቃቸው እንደሚሻ ከወዲሁ ሊረዱ ይገባል! ይህ የአለም መንግስታት ታሪክ ነውና!
ይህ በእንዲህ እያለ!
ምንም አልን ምን አቡኑ ዜጋ ናቸው! መንግስት ዜጋዉን የፈለገ ቢጠላዉ ምክንያቱን ሳይነግርና በህግ ሀገር ዉስጥ እንዳይገባ የሚያሳግድ ተመጣጣኝ ወንጀል መፈጸሙን ሳይገልጽ የሀገሩን መሬት ሊነፍገው አይገባም! መንግስት እኮ የሀገር አስተዳዳሪ እንጂ የሀገር ባለቤት አይደለምና!
አሁንም ቢሆን አቡኑ ላይ የተወሰደው እርምጃ ህጋዊ ስለመሆኑ መንግስት ቢያንስ የሳቸው ተከታይ የሆነዉና በሚልዮኖች የሚቆጠር የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አማኝን በማክበር ብሎም ስለፍትህ የሚጨነቁ ዜጎችንና ተቋማትን (ካሉ) በማሰብ አቡኑን ያገደበትን ምክንያት ይፋ ሊያደርግ ይገባል! ባይ ነኝ!
በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲከኛም ሆነ ቄስ፣ ሼህም ሆነ ቱጃር፣ ምሁርም ሆነ ለፍቶ አዳሪው፣ ኡስታዙም ሆነ ፓስተሩ ራሱን መፈተሽ ያለበት ከመንግስት ጎን መሆኑን ሳይሆን ከሃቅ እና ከፍትህ ጎን መቆሙን ብቻ ሊሆን ይገባል እላለሁ፡፡ ለምን ቢሉ ይሄው:-
🚩መንግስትንም ቢሆን መደገፍ በሃቅና በፍትህ መንገድ ላይ ብቻ ሲሆን ነዉና!
🚩ፍትህ በሌለበት ሃገርም መንግስትም አይጸናምና !

አልያ ግን ማነው ባለ ሳምንት በሚለው ቀመር ሁሉም በቀን ሂሳብ "ተረኛው መጡ እየሮጡ!" እንዳይባል ስጋቴ ነው

ይሄው ነው!
እርሶስ ምን ያስባሉ? ሃሳቦን ያኑሩ!
ሃሳብዎን ያካፍሉን?!
____

ከ RN05 ፔጅ የተወሰደ

መልካምነት ለራስ ነው! ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ እና ከመሬት ያለን የሻ ሁሉ ይጠጣል።  ወንዙም ሳይሰስት ለመጣው ሁሉ ያጠጣል። ያቋደሳል። ደግነታችን እንደወንዝ ይሁን። ሳንመርጥ ለለ...
04/02/2024

መልካምነት ለራስ ነው!

ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ እና ከመሬት ያለን የሻ ሁሉ ይጠጣል። ወንዙም ሳይሰስት ለመጣው ሁሉ ያጠጣል። ያቋደሳል። ደግነታችን እንደወንዝ ይሁን። ሳንመርጥ ለለመነን ሁሉ እጃችንን የምንዘረጋበት። ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ያስመሰክራል። የኛም ደግነት እንደዚሁ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ እና ሁል ጊዜ እንደወንዝ የሚፈስ መልካምነትና በጎነት እንዲኖረን ይሁን።

ሌላው… የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ ወደ ዝቅታው መሬትን ይዞ ከመሬቱ ላይ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ለሌሎች ከፍታ እንደመስራት ያህል ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ... እንደዚህ አይነት ደግ ሰራሁ እያሉ ሁካታ ማብዛቱ የደግነትን ክብር ይነካል። ያረክሳልም። እንደወንዝ በዝምታ እና በዝቅታ ለሌሎች መልካም መሆን የእውነተኛው ደግነት እንዲሁም መልካምነት መገለጫ ነው።

“መልካም እንሁን። መልካምነት ለራስ ነውና”።

ለሸረፋ አደም ኢብራሂምለአመታት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በትጋትና እንቅፋቶች ሁሉ ሳይበግሩህ ሐላፊነትህን ተወጥተሃል። በቆይታህ የመስቃን ማህበረሰብ እውነተኛውን መስቃናዊ ቀለም እንዲይዝና የጋ...
01/02/2024

ለሸረፋ አደም ኢብራሂም

ለአመታት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በትጋትና እንቅፋቶች ሁሉ ሳይበግሩህ ሐላፊነትህን ተወጥተሃል። በቆይታህ የመስቃን ማህበረሰብ እውነተኛውን መስቃናዊ ቀለም እንዲይዝና የጋራ የሆነውን አላማ እንዲያነግብ እንዲሁም የጋራ በሆነው መንገድ እንዲጓዝ በማድረጉ ዙሪያ ያበረከትከው አስተዋጽኦ ወደር አልነበረውም። ለሁሉም በእኩል በሚባል መልኩ የነበረህ ቀረቤታ እና መስተንግዶህ ምን ያህል የቅን እና የቻይነት ምሳሌ እንደነበርክ መገለጫው ነው። በአጠቃላይ የቻይነቱ ብቃትህ እና ጽናትህ ከሰዉ ሁሉ ልዩ ያደርግሃል።

በአመታቱ የመስቃን ማህበረሰብን ድምጽ በማሰማቱ ሂደት ውስጥ የነበረህ ሚና ከፍተኛ እና ዘርፈ ብዙ ነበር። ዛሬ ላይ ህልማችን እውን ሆኗል። ውጥናችንም ሰምሯል። ላበረከትከው አስተዋጽኦ ሁሉ በመስቃን ማህበረሰብ እና በመስቃን ሚድያ ኔትወርክ ስም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

"ሰዎችን ያላመሰገነ አላህን አያመሰግንም"

ኢዱና አህመድ ኡስማን
መስቃን ሚድያ ኔትወርክ

የሙስሊሙ ፈተና
30/01/2024

የሙስሊሙ ፈተና

ጄይሉ ቲቪ Jeilu Tv Ethiopia ለአስተያየትዎና የምርትና አገልግሎት ማስታወቂያ ጥያቄ መቀበያ ጄይሉ ቲቪ ፦ ስልክ 0113 – 69 69 32 /0968 80 80 80 ጄይሉ ቲቪ Jeilu Tv Ethiopia E-mail: jeilumedia@gmai...

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when meskan media network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to meskan media network:

Videos

Share