የአለም ምግብ ፕሮግራም ነዳጅ እና የምግብ አህል ወደ ትግራይ ማድረሱን አስታወቀ‼️
የአለም ምግብ ፕሮግራም በሁለት ኮንቮይዎች በዛሬው እለት መድሀኒት እና ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል ማድረሱን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
ተቋሙ የላከዉ ነዳጅ መቀሌ መድረሱን ገልጾ፤ 2ኛው ኮንቮይ ምግብ ወደ ሽረ ከተማ ይዞ መግባቱን አስታውቋል።
አክሎም ትላንት ወሳኝ የህክምና ቁሳቁሶችን በአየር ልከናል ብሏል ተቋሙ። በእለቱ ድጋፎችን ለማድረስም ለማድረስ ዝግጁ ነን ያለ ሲሆን ያሉ እክሎች እንደሚቃለሉለትም ተስፋ እንደሚያደርግ ጨምሮ በመግለጫዉ አክሏል።
ህውሃትን ወክሎ ደቡብ አፍሪካ የተላከ ሰው የለም 🙅♀️
#Update
የሰላም ስምምነቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ተፈራርመዋል።
ከተፈራረሙ በኃላም እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል።
በአጠቃላይ የተደረሱትን የስምምነት ነጥቦችን የያዘው እና በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል (አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና አቶ ጌታቸው ረዳ) የተፈረመበት ወረቀት እንደደረሰን የምንልክላችሁ ይሆናል።
የሰው ንብረት አትንኩ!! አንደዚችም ያሉ ጀግና እህቶችም አሉን!
በህንድ በኬረላ ማላፑራም አውራጃ ስታድየም ተደርምሶ ከ200 በላይ ተጎዱ
ቅዳሜ እለት በተደረገ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ የተመልካቾች መቀመጫው ሲናድ ትልቅ የስታድየም መብራት ወደ ሜዳው ወድቋል።
ከሜዳው ተቃራኒው ክፍል የመጡ ደጋፊዎች የተጎዱትን ለመርዳት ወደ ሜዳ ሲሮጡ የሚያሳይ ቪድዮ የሀገር ውስጡ ጋዜጣ ኤቢፒ አሳይቷል።
ድርጊቱ የተከሰተው የህንድ ሰቨንስ እግር ኳስ ውድድር የፍጻሜ ጨዋታ በሚካሄድበት በፖንጎድ ስታዲየም ውስጥ ነው።
ክቡርነቶ ባለፈው "ጸልዩልኝ" ብለው ነበር። ምን ብለን እንጸልይሎ? የልቦ ሀሳብ ምንድነው? ጥቂት የጸሎት ርዕሶን ቢያሳውቁን ለመጸለይ አንቸገርም።
አስቴር በዳኔ
ዶ/ር ደብረፅዮን በቢቢሲ ኒውስ ሀወር ላይ ቀርበው ምን አሉ ?
የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ ከቢቢሲ ኒውስ ሀወር ጋር በነበራቸው ቆይታ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር በሌሎች አካላት አማካኝነት (ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ) ንግግርና ውይይት መደረግ መጀመሩን ገልፀዋል።
በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
ከፌዴራል መንግስት ጋር በሌሎች አካላት አማካኝነት (በUN ፣AU እና ኬንያ) የተጀመረው ውይይት ግጭቱ እንዲቆም ተስፋ የሚሰጥ ምልክት መሆኑን ነገር ግን የዲፕሎማሲ ውጤቱ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ዶ/ር ደብረጽዮን አሁንም ለችግሮች ሰላማዊ መፍትሔዎችን እንፈልጋለን ሲሉ ተደምጠዋል።
ቢቢሲ ኒውስ ሀወር በዚህ ዘገባው ከፌዴራል መንግስት በኩል ሰዎችን አላነጋገረም።
ዶ/ር ደብረፅዮን ቃላቸውን የሰጡበት የቢቢሲ ኒውስ ሀወር ፕሮግራም: www.bbc.co.uk/sounds/play/w172xv5kpz8pyk8?s=09
ከሰሞኑን ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ አህመድ ከዳያስፖራዎች ጋር በነበራቸው ዝግ ውይይት የሀገሪቱን ጥቅም የሚያስቀድም ምክንያታዊ ድርድር ይካሄዳል ስለማለታቸው አንድ የዳይስፖራ ተወካይ መናገሩን ኤፒ ዘግቦ ነበር።
ይህንንም ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፤ ይህ እንዳልተባለ፤ ህወሓት አሁንም በህግ ሽብርተኛ ድርጅት በመሆኑ ሽብርተኛ ከሆነ ድርጅት ጋር እንነጋገራለን የሚል አቋም የተገለፀ
ቀሲስ ስንትያሁ የኔአባት ከጽዋ ትዪብ ጋር ያደረጉት ቃላ ምልልስ ችግሩ ቤተ ክርስቲያንን ምን ያኽል ጎድቷታል?
የመተከል ችግር መነሻ ምክንያት ምንድን ነው?
ቤተክርስቲያንን ምን ያህል ጎድቷታል?
ለዚህ መፍተሔ ሀሳብ ምንድነው?
በሚለው ዲያቆን ዓባይነህ ካሤ እና ቀሲስ ስንታየሁ የኔ አባት ከጽዋዕ ትዩብ ጋር ያደረጉትን ውይይት እስከ መጨረሻ ተመልከቱ
በአደባባይ ሚድያ ቀሲስ ስንታየሁ የኔያበት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
በመተከል የጅምላ ጭፍጨፋ በተመለከተ በአደባባይ ሚድያ ቀሲስ ስንታየሁ የኔያበት ጋር በትናንትናው ዕለት የተደረገ መላውን የአገው ህዝብ ልብ የሚነካ ገራሚ ቃለ_መጠይቅ።