10/05/2022
በዓለማችን የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጣራ በነካበት በዚህ ወቅት " ሼል " የተሰኘው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰምቷል።
ሼል በዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 9.13 ቢሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ካገኘው 3.2 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ በሦስት እጥፍ ገደማ ያደገ ነው።
ነገር ግን ድርጅቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ የነዳጅ እና ጋዝ ገበያ መውጣቱ 3.9 ቢሊዮን ዶላር እንዲያጣ እንዳደረገው አሳውቋል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተዳክሞ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ማንሰራራት ሲጀምር የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ እየጨመረ ቢመጣም የቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ጣራ እንዲነካ አድርጎታል።
የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ መጨመር ለኢነርጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ትርፍ እንዲያገኙ እያደረጋቸው ይገኛል።