Amater TV

Amater TV ነፃ መረጃ ተጨባጭ ዕውነተኛ የሆኑ ብቻ ማስተላለፍ በማንኛውም መንገድ ተጨባጭ መረጃ ካሎት ማካፈል ይችላሉ።

ልብ ይበሉ በምድራችን ላይ ብዙ አጭበርባሪዎች አሉ የዚህኛው ግን የባሰ ነው።ይሔንን የቴሌግራም ቻናል ተመልከቱት ብዙ ማጭበርበር የሰራ ቻናል ነው።ቻናሉን የተቀላቀላችሁ ከቻናሉ በመውጣት እና ...
01/01/2023

ልብ ይበሉ በምድራችን ላይ ብዙ አጭበርባሪዎች አሉ የዚህኛው ግን የባሰ ነው።
ይሔንን የቴሌግራም ቻናል ተመልከቱት ብዙ ማጭበርበር የሰራ ቻናል ነው።
ቻናሉን የተቀላቀላችሁ ከቻናሉ በመውጣት እና ሚስጥራቸውን በማጋለጥ ወገኖቻችሁን ከመጭበርበር ታደጓቸው።

አይ ወለጋ አይ ብልፅግና
04/12/2022

አይ ወለጋ አይ ብልፅግና

አጉትን ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎች  የኦሮሚያ ልዩ ሃይልን በመፍራት ብቻ፣ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ሁሉ በምሽት እየተሰደዱ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውኛል። መከላከያ ሰ...
04/12/2022

አጉትን ከተማ እና በአጎራባች ቀበሌዎች ያሉ ነዋሪዎች የኦሮሚያ ልዩ ሃይልን በመፍራት ብቻ፣ህጻናት፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞች ሁሉ በምሽት እየተሰደዱ እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውኛል። መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ዜጎችን ካልታደገ፣ ለሚፈሰው ደምና ለሚደርሰው ስቃይ ሁሉ መንግሥት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው።

ዶ/ር አብይ አህመድ:-

👉የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትር ነው
👉የብልጽግና ፕሬዝዳንት ነው
👉የኦሮምያ ብልጽግና ሊ/መንበር ነው
👉የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ነው

በየትኛውም የስልጣን አቅጣጫ ቢኬድ፣ ዶ/ር አብይ በኦሮምያ የሚካሄደውን የንጹሃ ሞት ጣልቃ ገብቶ የማስቆም ሙሉ መብትና ስልጣን አለው።

አሁን እንደ ዜጋ የምጠይቀው ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ብቻ ነው። የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ በላይ ተቀዳሚ ግዴታና ሃላፊነት ደግሞ የለም።

ከአቅሙ በላይ ከሆነ ደግሞ ይህንን በአደባባይ
መናገር ነው።

እንደ ሃገር ከፍተኛ የመከላከያ አቅም በገነባንበት በዚህ ጊዜ የሚፈጽም የንጹሃን ሞት፣ በየትኛውም አመክንዮ ተቀባይነት የለውም። ይህ የግፍ ሞት እንዲቆም ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በአንድነት ድምጻችን ልናሰማ ይገባል።

Via: Fasil yenealem

04/12/2022

ተለማማጅን የተቀላቀለ ተጠቀመ

31/12/2021

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ።

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሐገራችን በጠና ታማለች አሁን የምትፈልገው መድሐኒት የተግባር ሰው ነው።
ሐብት ያለው በሐብቱ ጉልበት ያለው በጉልበቱ ሙያ ያለው በሙያው ይደርስላት ዘንድ በጠና ትማፀናለች።

01/12/2021

ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ይተባበሩ!!!

አስር ጥያቄዎች ለፌዴራል መንግስት ***ወደፊት ለመዝለል ወደኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል!በመሰሪዎችና ዕብሪተኞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዘር ተመርጦ በተኛበት ከታረደ በኋላ ኢትዮጵያ ተገዳ...
07/11/2021

አስር ጥያቄዎች ለፌዴራል መንግስት
***

ወደፊት ለመዝለል ወደኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል!

በመሰሪዎችና ዕብሪተኞች የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በዘር ተመርጦ በተኛበት ከታረደ በኋላ ኢትዮጵያ ተገዳ ወደ ጦርነቱ የገባችበትን አንደኛ ዝክር ዓመት ስናከብር አንድና ብቸኛ ህይወታቸውን ለሃገራቸው መስዋዕት ያደረጉ ምርጥ የኢትዮጵያ ልጆችን ስናስብ ጦርነቱ ከተጀመረ አሁን እስከደረስንበት ድረስ ያጋጠሙንን ድሎችና ፈተናዎች ወደኋላ ሄደን መገምገም አለብን። ሶስት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ አፈር ድሜ ማስበላት የተቻለው ህውሃት ከአፈርነት ተነስቶ እንዴት አሁን ላለበት ደረጃ ደረሰ የሚለው ጥያቄ መመለስ ይገባዋል ። ይህ በዚህ ወቅት መንግስትን ለመውቀስ ፣ ለማሳጣት ወይም ነገሮችን ዝም ብለን ለታሪክ መዝገብ ለመሰነድ ሳይሆን እስካሁን ከተሰሩ ስህተቶች ተምረን ዳግም እንዳይፈፀሙ ለማድረግ እንዲቻል ነው። ለምሳሌ በእኔ እይታ መንግስት ይህን ጦርነት በአግባቡ ለመጨረስና ኢትዮጵያን በማይነቃነቅ አለት ላይ በፅኑ ለማቆም የሚከተሉትን አስር ጥያቄዎች በአግባቡ መመለስ አለበት።

1) ህውሃት የሰሜን ዕዝን ለማጥቃት የወሰነው ጦርነቱ ከመጀመሩ ሶስት ቀን በፊት ''ማዕከላዊ ኮሚቴ ታላቅ የሚባል ታሪካዊ ውሳኔ አሳልፏል'' ብሎ ከነገረን በኋላ ነው። ይህ ውሳኔ እንደተወሰነ ወይም ከመወሰኑ ቀደም ብሎ በወቅቱ የነበረው የመከላከያ መረጃና ደህንነት ቢሮ የማጥቃት ሃሳቡ እንደነበረ ለምን አልደረሰበትም? ደርሶበት ከሆነ ለምን ቀድሞ ወታደሩን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ስራ አልሰራም?

2) ለጦርነቱ ህውሃት ከ150 ሺ በላይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አሰማርቶ እንደነበር ይገመታል። ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ግን መንግስት ከተሞችን ለመቆጣጠር ባደረገው ጥረት ይህ ሃይል ምንም ሳይነካ ከነመሳሪያው ወደገጠርና ማህበረሰቡ እንዲቀላቀል ሆኗል። ይህ የሆነበት አንዱ ምክንያት መንግስት ትንሽ ሽፍታና ወንበዴ የገጠመ ይመስል አንዴ 24 ሰዓት አንዴ 72 ሰዓት እጅ እንድትሰጡ ዕድል ሰጥቻችኋለሁ እያለ ራሱን ማዘናጋቱ ነበር። ይህ ለምን ሆነ? የህወሓት የትግል ታሪክ ከገጠርና ገጠር እንደሆነ እየታወቀ ለምን ገጠሩን ትቶ ከተማው ላይ ትኩረት ማድረግ አስፈለገ? የትጥቅ ማስፈታት ስራ ለምን በእያንዳንዱ የገጠር ቀበሌ ሳይቀር በወጥነት አልተሰራም ?

3) የትግራይን ዋና ዋና ከተሞች የኢትዮጵያ መከላከያ ወታደር ከያዘ በኋላ በጊዜያዊ አስተዳዳሪነት የተሾሙት ሰዎች አብዛኞቹ በአስተሳሰባቸው ከህውሃት ያልተሻሉ እንዲያውም የሚብሱና ከህውሃት ጋር አብረው የሚሰሩ ሆነው ሳለ የደህንነት መስሪያ ቤታችን ለምን በቅርበት ክትትል አላደረገባቸውም?

4) ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በመጀመሪያ ሶስት ወራት የህውሃት ሰዎች እንኳንስ የሳተላይት ስልክ የሚጠጡት ውሃ እንኳ እንዳልነበራቸው ከራሳቸው አፍ ሰምተናል። ታዲያ አራቱም የትግራይ መግቢያና መውጫ በሮች ዝግ ሆነው እያለ የሳተላይት ስልኮች፣ ዘመናዊ ሬዲዮ መገናኛዎች፣ ተጨማሪ ዘመናዊ መሳሪያዎችና ''የሌላ ሃገር ተዋጊ ዜጎች'' (mercenaries) እንዴትና በየት ወደትግራይ ሊገቡ ቻሉ? ማንስ አስገባቸው?

5) መከላከያ ትግራይን ከተቆጣጠረ በኋላና በህይወት የተረፉ የህወሓት ሰዎች ተምቤን በርሃ ከከተሙ በኋላ በአስር ሺዎችና መቶ ሺዎች አዲስ ሃይል አሰልጥነው ሲያስመርቁ መንግስት ምን ሲሰራ ነበር? የአየር ሃይሉና የደህንነት መዋቅሩ ተምቤን ከኢትዮጵያ ግዛት ውጪ ያለ ይመስል እንዴት ቢያንስ እየተደገሰ ያለውን ችግር ለምን ማወቅ ተሳነው?

6) በሰኔ ወር መጀመሪያ አካባቢ መንግስት መከላከያ ሰራዊቱን ከትግራይ እንዲወጣ ሲወስን ህውሃት መረጃው ወዲያው እንደደረሰውና ለመውጣት የተዘጋጀውን መከላከያ ሰራዊት ማጥቃት እንደጀመረ ሰምተናል። የመንግስትን መከላከያ ሰራዊቱን የማስወጣት ውሳኔ ለህወሓት ሲያቀብል የነበረ ማን ነው? ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወይስ በመከላከያ ውስጥ ያለ ባንዳ? ማንነቱ ተመርምሮ ለምን ህጋዊ እርምጃ አልተወሰደም ? አሁንም የመከላከያ መረጃና ስለላ ዲፓርትመንት ምን ሲሰራ ነበር?

7) የመንግስት ሰራዊት በህውሃት ለሁለተኛ ጊዜ በሰኔ ወር ውስጥ ሳይታሰብ ጥቃት ሲፈፀምበት መንግስት ለምን የአማራና የአፋር ክልሎች ወዲያውኑ እንደአማራጭ መከታ እንዲሆኑ እንዲዘጋጁ አላደረገም ? የችግሩን አሳሳቢነት ተረድቶ አንዴ ሞቅ አንዴ ቀዝቀዝ ለማድረግ ለምን ፈለገ? በተለይ የአማራ ክልል ካለበት ልዩ ስጋትና ተጋላጭነት አንፃር መደራጀቱና መዘጋጀቱ መደገፍ ሲገባው እንደስጋት ለምን ታየ?

8 ) ህውሃት ከትግራይ ክልል ወጥቶ አማራና አፋር ክልሎችን መውረር ሲጀምር ሁለቱ ክልሎች ምንም ሳይዘጋጁ ነበር የጠበቁት። ይህ በመንግሥት እንዝላልነት እንደሆነ ግልፅ ነው። ጥያቄው ግን ህውሃት ወረራ እንደጀመረ ለምን መንግስት ሃገርአቀፍ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በቶሎ አላወጀም? ለምን ሁሌ ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ አይነት አካሄድ ይሄዳል ? ነገሮችን 'አይሆኑም' ከማለት ቢያንስ ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ አስቦ ለሁሉም ቢሆኖች ለመዘጋጀት አልቻለም ?

9) መንግስት የዓለም አቀፍ ጫናው እንዲበረታበት ካደረጉ ነገሮች ውስጥ ዋናው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች በጦርነቱ መሳተፋቸውና የሰብዓዊ መብት ጥሰት አካሂደዋል መባሉ ነው። በመጀመሪያ መንግስት የኤርትራን መግባት ሲክድ ቆይቶ በኋላ እንደገና መግባታቸውን አምኗል። ይህ ትልቅ የሆነ ያለመታመን ችግር በአለም አቀፉ ማህበረሰብና በዲፕሎማሲያዊው መድረክ ፈጥሮበታል። ለምን የኤርትራን መግባት መንግስት መካድ ፈለገ? በዓለም አቀፍ ህግ መንግስታት በአስቸጋሪ ጊዜ የወዳጅ ሃገሮችን እርዳታ የመጠየቅ መብት አላቸው። አሜሪካ እንኳ በኢራቁና አፍጋኒስታን ጦርነት የ46 ሃገራትን ርዳታና ተሳትፎ በግሃድ ጠይቃ አግኝታለች። ኢትዮጵያም የኤርትራን እርዳታ መጠይቅና ማግኘቷ መብቷ ሆኖ ሳለ ለምን በሳተላይት ዘመን የተለያና የሚጋጭ መግለጫ መስጠት አስፈለገ? (በነገራችን ላይ የመንግሰት የተምታታ ትርክት ኤርትራን በተመለከተ ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገሮች ላይ ነው። ይህም መንግስት እምነት የማይጣልበት እንዲባል አድርጎታል )

10) ሃገሪቱ ለህልውናዋ ከሚያሰጋ ሃይል ጋር ጦርነት እያካሄደች መንግስት ለምን ሁሉ ነገርን እንደአዘቦት ለማየት ምንም እንዳልተፈጠረ ለማድረግ ሞከረ? ህዝብንና ሃገሪቱ ያላቸውን ሙሉ ሃይልና አቅም በአግባቡ ለጦርነቱ ማዘጋጀት ሲገባው ለምን ነገሮችን 'ሁሉም ሰላም ነው' አይነት መንገድ ለማየትና ሁሉም 'ከልኩ አያልፍም' አካሄድን መረጠ?!

መንግስት እኝህንና መሰል ጥያቄዎች በአግባቡ መልሶ ውስጡን አጥርቶ ከተንቀሳቀሰ እንደምንለው ኢትዮጵያ ታሸንፋለች። ያኔ (ኢትዮጵያ ስታሸንፍ ደግሞ) አላግባብ በግፍና በክህደት ለተጨፈጨፉት መከላከያ ሰራዊት አባላትና በጦርነቱ ለተሰው ሁሉም ዕንቁ የኢትዮጵያ ልጆች ትክክለኛና መስዋእትነታቸውን የሚመጥን መታሰቢያ እንደተደረገላቸው መቁጠር እንችላለን።

ድል ለኢትዮጵያ! ዘላለማዊ እረፍት እርሷን ለማቆየት አንድያ ነፍሳቸውን ለሰጡ ብርቅ ልጇቿ ይሁን !

ሸዋ ሸዋ አሸዋ የምትሆኝበት ቀኑ ደርሷል  ከበርሽ ላይ ነው፡፡የአዲስ አበባ መከራና ሰቆቃ ከ---- በኀላ ይጀመራል፡፡(መቼ እንደሆነ አልናገርም) ያኔ ምድር ትንቀጠቀጣለች፡፡እንደ ምጻት ትገለ...
04/11/2021

ሸዋ ሸዋ አሸዋ የምትሆኝበት ቀኑ ደርሷል ከበርሽ ላይ ነው፡፡የአዲስ አበባ መከራና ሰቆቃ ከ---- በኀላ ይጀመራል፡፡(መቼ እንደሆነ አልናገርም) ያኔ ምድር ትንቀጠቀጣለች፡፡እንደ ምጻት ትገለባበጣለች፡፡የሸዋ ምድር ኡኡታ የመከራ ቀንበር ፤ሰቆቃ ይወርዳል በማን አቅም ይቻል ይሆን? እንጃ!! አምላከ ቅዱሳን አንተ እወቀው በምንም ቃል መግለጽ አይቻልም መከራው ከባድ ነው፡፡ ሚያዝያ 7/8/2013 ዓም ከተጻፈው
ከአባ አምሃ ኢየሱስ ገ/ዮሐንስ ድንገተኛ የማስጠንቀቂያ መልእክት አምስት ገጽ
💚💛❤️💚💛❤️💚❤️💚💛❤️
ከአባ አምሃ ኢየሱስ ገ/ ዮሐንስ መደበኛም ሆነ ድንገተኛ መልእክት እንደ ተረዳነው ፡፡ መከራው የሚጀምርበትና የሚያበቃበት ወሩም ሆነ ቀኑ ሰአቱም ሆነ ሴኮንዱ ፡፡በእግዚአብሔር እና በቅዱሳን ልጆቹ ዘንድ የታወቀ እና የተወሰነ፡መሆኑን ነው፡፡እግዚአብሔር ከወሰነው ደግሞ ምንም ፈቀቅ የሚል ነገር የለም፡፡የመከራው ጊዜ መድረሱን ደግሞ መረዳት ያለብን በእውነተኞች እና በሐሰተኞቹ ወይም በእግዚአብሔር ልጆችና በዲያብሎስ ልጆች መካከል ያለው ውጊያ እና ፍልሚያ በተለይ በተለይ ከሐምሌ አምስት በኀላ የበለጠ እየጠነከረ መምጣቱ አንድ ምስክር ነው እና ሁላችንም በጥቃቄ በማስዋል እግዚአብሔር በመፍራት የበለጠ እውነትን በልባችን ውስጥ በማንገስ እምነትን ጋሻ በማድረግ በንስሐ ሕይወት በመላለስ በጾም በጸሎት በአጠቃላይ በበጎ ስራ በመትጋት፡፡የልዑልና የድንግል ወታደሮች በመሆን፡፡መልእክታቱን ፤ ደብዳቤዎችን ፤ ተምህርቶችን ፤መግለጫዎችን እና ማሳሰቢያዎችን እንዲሁም ምክሮችን ዘወትር በማዳመጥ ማስረጽ ጠላት በሐሰት ሲከሰን በመልእክቱ ያልተባለውን ተባለ ሲል የቱ ላይ በማለት ጠላትን በብቃት እንድንዋጋ የጦር መሳሪያዎችቻን ናቸውና
እንጠቀምባቸው፡፡እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም በእናቱና በቅዱሳኑ ጸሎትና ምልጃ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን፡፡

27/10/2021

ደባርቅ ያችን ሰዓት...
🔥
....ማንም ሰው ከተማውን ለቆ መሄድ ይችላል! እኛ ግን በደምና በአጥንታችን ከተማችንን በአሸባሪው ትህነግ ሳናስደፍር እንደምናተርፋት አንጠራጠርም! የአሰላለፍ ስምሪት እንደሚከተለው ነው...የወጣቱን አሰላለፍ በዝርዝር አቀረቡ!.... እ... እ... እ... ማንም ሰው ልብ አድርጉ ማንም ሰው ባለሥልጣንን ጨምሮ ከከተማዋ እንዳይወጣ እነ እከሌ ጎንደር በር ላይ ኬላ ጥላችሁ ጥብቅ ፍተሻ አድርጉ....

ከፊቱ እልኸ ይታያል! አይኑ ድልዝ በርበሬ መስሏል... እ...እ.. እና የመጨረሻ የምነግራችሁ አባቶቻችን በትውልድ ቅብብሎሽ እዚህ ያደረሷትን ከተማ ጥላችሁ ወደ ዬትም አትሂዱ... እዚሁ በጋራ እንሙት (ድምጹ ሞቀ!!) ሰማችሁ ወይ? አለ አሁንም አይኑን አጉረጥርጦ... ሰምተናል አለ የሀገሬው ኮበሌ... ጦሩን፣ ገጀራውን፣ ፈራዱን፣ አንካሴውን፣ እያጋጨ... ሰምተናል!! አለን... አለን... አለን... በእውነት እኔ እንደዚች ቀን ሰውነቴ በሐሴት ሲርድ አላስታውስም!!

ተናጋሪው ቀጥሏል... የደም ስሩ በግምባሩ ላይ ተረተር ሰርቷል! የጦር ሜዳ መነጽሩ ደረቱ ላይ ይታያል... ሙሉ ትጥቅ በወገቡ ላይ አስሯል... ክላሽንኮቩን ሻጥ አድርጓል! በሙሉ ወታደራዊ ልብሱ ቁመናው ይማርካል! እውነት እውነት እላችኋለሁ ግርማው ያስፈራል... እና ከተማችሁን ለቃችሁ አትሂዱ! ግን አለ... ድምጹ ጨመረ.... ግን ዛሬ ከተማው ስትሻው ጥሏት የሄደ ሰው ነገ እኛ ልጆቿ በደምና በአጥንታችን ከተማችንን በአሸባሪው ትህነግ ሳናስደፍር ካተረፍናት በኋላ ሀብት ንብረት አለኝ ብሎ ተመልሶ አይመጣም.... ቅልጥ ያለ ጩኸት... ጭብጨባ... እልልታ... የመሳሪያ ሁካታ... የራስ ውብነህ አሞራው ልጆች ፉከራ... ሽለላ.... ኦህህህህ....

ይህ ሰው ይህ ጀግና የደባርቅ ከተማ ከንቲባ የወንዶች ቁና ሰለሞን ተዘራ ነው!! ያልተዘመረለት እንዲወመርለትም የማይሻ ልበ ሙሉው ጀግና ግንባረ ኮስታራው ግንባራ መራራው ሰለሞን ተዘራ...

ሰሌ እኛ ጀግንነትህን በአካል ያየን ወንድሞችህ በዘመናችን ሙሉ እናከብርሃለን‼️

ዛሬ ምራባውያ እና አውሮፖውያ የሚያራምዱት አስተሳስብ ሰለባ እንዳንሆን ደፋ ቀና የሚል ሀያል መንግስት ነበረን ነገር ግን ጪራሽ ከሀገር ተባሮ ጎረቤት ሀገር  ተሰደደ .... ኢትዮጲያ ቀጣይ ...
22/10/2021

ዛሬ ምራባውያ እና አውሮፖውያ የሚያራምዱት አስተሳስብ ሰለባ እንዳንሆን ደፋ ቀና የሚል ሀያል መንግስት ነበረን
ነገር ግን ጪራሽ ከሀገር ተባሮ ጎረቤት ሀገር ተሰደደ .... ኢትዮጲያ ቀጣይ ምን ይሆን???

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪፋኖ ሞገስ ሞላ ይባላል። በአማራነት ትግሉ የታወቀና በጥሩ ስነምግባር የታነፀ ታጋይ  ነዉ። ፋኖ ሞገስ ከባለፈዉ ከጥቅምት 24 እስከ አሁን አሸባሪው ህዋሐትን ለመደምሰስ...
20/10/2021

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ

ፋኖ ሞገስ ሞላ ይባላል። በአማራነት ትግሉ የታወቀና በጥሩ ስነምግባር የታነፀ ታጋይ ነዉ። ፋኖ ሞገስ ከባለፈዉ ከጥቅምት 24 እስከ አሁን አሸባሪው ህዋሐትን ለመደምሰስ እየተደረገ ባለው ጦርነት ለሀገር እየታገለ የነበር ጠንካራ ፋኖ ነዉ።

ፋኖ ሞላ በባሻ ስር የሚተዳዳር የነበር ልበ ሙሉ ጀግና ነዉ። ፋኖ ሞላ ጭና ላይ በነበረዉ ጦርነት ብዙ የህዋሐትን ወታደር ከደመሰሰ በሗላ በመጨረሻም ከኋላዉ በመጣ የጠላት ዲሽቃ ተኩስ እጉሩን ተመታ። አሁን ጎንደር ሆስፒታል ሲታከመ ከቆየ በሗላ ወጥቶ ከቤቱ ይገኛል። ነግር ግን አጥንቱ ስለተመታ እስካሁን መንቀሳቀስ አልቻለም።

ስለሆነም ለሀገር ከከፈለው መስዋትነት አንፃር ካለው የወጣትነት እድሜ አንፃር የታሻለ ህክምና እንዲያገኝ ብናገዘዉ ለህሊናችንም እረፍት ልጁንም በዚህ እድሜው ከማንከስ እንድንታደገው ጥሪያችንን እናቀርባለን ።

ወንድማችን ማገዝ ለምትፈልጉ

ሞገስ ሞላ መኮንን 0918234485

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000069092342

መርዳት ባትችሉ ሼር በማድረግ ተባበሩ !!

18/10/2021
17/10/2021

ኢትዮጵያ፤ እንኳን ኤርትራን ከመሰለ ጎረቤቷ ጋር ይቅርና ከፈለገችው ሀገር ጋር የመተባበር መብት አላት“- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ፤ አሁን ላይ ነጻ የውጭ ግንኙነት ማራመድን የማይወዱ አካላት አሉ ብለዋል

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ኢትዮጵያ ከሀገሮች ጋር ባላት ግንኙነትና በሕዳሴ ግድብ ሰበብ ጫና እየተደረገባት ነውም ተብሏል

“ኢትዮጵያ እንኳን ከጎረቤት ሀገር ኤርትራ ጋር ይቅርና ከፈለገችው ሀገር ጋር በትብብር የመስራትና የማደግ መብቷን ምንም ሊነፍጋት እንደማይችል” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ቃል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከአል ዐይን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ከፈለገችው ሀገር ጋር የውጭ ግንኑነትን ማከናወን መብቷ መሆኑን ማንም ሊገነዘበው እንደሚገባ ተናግረዋል።

አሁን ላይ እየመጣ ያለው ጫናም ሀገሮችን የመግዛት አባዜ እንደሆነ የገለጹት ቃል አቀባዩ ፤ አንዳንድ አካላት ነጻ የውጭ ግንኙነት ማራመድን እንደማይወዱም ለአል ዐይን ተናግረዋል።

አንዳንድ ወገኖች በኢትዮጵያ ላይ ጫና የሚያደርጉት በሕዳሴ ግድብ እና ከሀገሮች ጋር ባላት ግንኙነት መሆኑንም አምባሳደር ዲና አንስተዋል።

አዲስ አበባ፤ ከሞቃዲሾ እና አስመራ ጋር የፈጠረችው ጥምረት ጫናው እንዲመጣ አድርጓል ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢትጵያ ላይ ጫና የማድረጊያው አንዱ መንስኤ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ይህ የሆነውም አንዳንድ በሚል ስማቸውን ያልገለጿቸው ወገኖች ሀገሮችን የመግዛት አባዜ ስላለባቸው መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም መሰረት አንዳንድ አካላት ነጻ የውጭ ግንኙነት ማራመድን እንደማይወዱ ያነሱት ቃል አቀባዩ፤ የሀገሮችን ትብብር ሰፍሮ መስጠት የሚፈልጉ እንዳሉም ተናግረዋል።

በተለይም “ከዚህ ጋር ተገናኝ፤ ከዚህ ጋር አትገናኝ ፤ ከዚህ ጋር ሂድ፤ ከዚህ ጋር አትሂድ“ የሚል ትዕዛዝ መሰል መልዕክት የሚናገሩም እንዳሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የውጭ ግንኙነት ስራ የምታካሂደው በራሷ መብት መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ዲና ይህንን የኢትዮጵያን መብት መከበር የማይፈልጉ ወገኖች በተለያየ መንገድ ጫና ለማድረግ መሞከራቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌላኛው ኢትዮጵያ ላይ ጫና የማድረጊያው ስልት የሕዳሴ ግድብ መሆኑን የሚናገሩት ቃል አቀባዩ “የሕዳሴ ግድብን አጉል እንደሚጎዳቸው አድርገው የወሰዱ አሉ”ብለዋል።

ፕሮጀክቱን ያለ አግባብ በመረዳት እንደሚጎዳቸው አድርገው የወሰዱ አካላት መኖራቸውን የተናገሩት አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለውን የሕዳሴ ግድብን “በእኛ ላይ የመጣ ነው“ በሚል እንደ ስጋት የሳሉ መኖራቸውን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በሚገባ ባለማወቅ አሊያም ሆነ ብሎ ጫና እየተደረገ መሆኑ በተደጋጋሚ በመንግስት በኩል ተገልጿል። ጫና የሚያደርጉ አካላትን በደፈናው ምዕራቡ ዓለም ብሎ ከማስቀመጥ ይልቅ አንዳንድ ወገኖች ቢባል እንደሚሻል ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ይህም ከፖለቲከ፤ ከመንግስት እንዲሁም ከሚዲያ ሰዎች መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።

ባለማወቅ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚሞክሩ ኃይሎች “የውሸት ወሬ የሚያሰራጨውን ኃይል“ ማንነት እየተደረዱ የሚሄዱበት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነና አሁንም እየተረዱትም እንደሆነ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። “ውሸት ሚሲራጨው ኃይል ራቁቱን ሲቀር ዕውነታው ሲገለጽ ኢትዮጵያ ወደፊት ትሄዳለች“ ብለዋል።

ዘገባው የአል-ዐይን ሚዲያ ነው
በ16/10/2021 ዓ.ም እንዳወጣው።

"ይህ ሌላ ሀገር ሳይሆን ኢትዮጵያ ነው‼"ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ነጮች ከኬኒያ ዝዋይ ለአበባ እርሻ እንደገቡ በኬኒያ የለመዱትን አፍሪካውያንን በጥፊ የመምታትና የማሸማቀቅ ሥራቸውን ሊጀምሩ የፈለ...
10/10/2021

"ይህ ሌላ ሀገር ሳይሆን ኢትዮጵያ ነው‼"
ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ

ነጮች ከኬኒያ ዝዋይ ለአበባ እርሻ እንደገቡ በኬኒያ የለመዱትን አፍሪካውያንን በጥፊ የመምታትና የማሸማቀቅ ሥራቸውን ሊጀምሩ የፈለጉ ይመሥላል።

በዝዋይ የሼር ኢትዮጵያ የአበባ እርሻ ሳይት ኢንጂነር ሆኜ ተቀጥሬ እየሠራሁ ነው። በርካታ ሆላንዳዊያን፣ እስራኤላውያንና ኬንያውያን ከኬኒያ ናይቫሻ ወደ ዝዋይ ከትመዋል። እነዚህ ከኬኒያ የመጡ የተለያዩ ሀገር ዜጋዎች በአበባ እርሻ የተሻለ ልምድ ያላቸው ነበሩ።

ኬኒያውያን ነጮች ሲጠሯቸው መሄድ ብቻ ሳይሆን ከፊታቸው የሚቆሙት በመንቀጥቀጥ ነው።

አንድ ሆላንዳዊ ፒተር የሚባል እና ቤን የሚባል እስራኤላዊ አንዱን የአርሲ ኦሮሞ ልጅ ይጠሩታል።

የያዘው እቃ ስለነበር ያንን እቃ አድርሶ ወደ ጠሩት ፈረንጆች ይሄዳል።
"እንደጠራንህ ለምን አልመጣህም?" ይሉታል።

"እቃ ይዤ ስለነበር ላድርስ ብዬ ነው" ሲላቸው፣

"ሁለተኛ እኛ ስንጠራህ ምንም ሥራ ብትይዝ አቋርጠህ መምጣት አለብህ። ለምን ብትል እኛ ነጮች ነን" ብለው በጥፊ ያጠናግሩታል።

በጥፊ ሲመታው አይኑን ይዞ ሲያጎነብስ እሩጬ ሄድኩ በኦሮምኛ እንዳታለቅስ አልኩት። ማልቀስ ተሸናፊነት ነውና ያሸነፉን እንዳይመስላቸው ነበር።

አጠገባቸው ደርሼ "ለምን መታኸው" ስለው
"He does not listen to me" አለኝ።

እኔም አጠገቡ ነበርኩና በጥፊ አጠናገርሀሁት።
" አንተን ለመስማት ሳይሆን ለመሥራት ነው የመጣው" አልኩት።
ነጭ በጥቁር ሲመታ አያውቅምና ደነገጠ።

በኦሮምኛ "ሃሌላ" አልኳቸው። በሉት ማለት ነው በኦሮምኛ። የኦሮሞ ልጆች (ኢትዮጵያውያን) አጢሰው አጢሰው ለቀቁልኝ::

አንድ ቀን ምሣ ስንበላ
"ሌላ አገር ተደፍረን አናውቅም ነበር" አለኝ።

"ይህ ሌላ ሀገር ሳይሆን ኢትየጵያ ነው" አልኩት።

ከዚያን ቀን ጀምሮ የሚፈልጉት ነገር ካለ እነርሱ ይመጣሉ እንጅ "ኑ!" ብለው በንቀት አይጣሩም ነበር።

በሕይወቴ ምን ያስደስተሃል ብባል በዝዋይ የቀበጥ ፈረንጆች ቅብጠት በኢትየጵያውያን የበላይነት ዝቅ ማድረጌና ፈረንጅና ኬኒያያውያን ይዘውት የመጡትን የአበባ ዕውቀት በአጭር ጊዜ በኢትዮጵያውያን መተካቴ ነው።

 !      [ !*****-*******አብዛኛው መልዕክት ለአፋር ህዝብ ሆኖ አገኘውት፤ከአፋር ህዝብ ጋር መጣላት አንፈልግም የሚል ሀሳብን ያንፀባረቀ ነው።ከዚህ በተጨማሪም" የአፋር ልዩ ሀይል...
23/09/2021

!
[ !
*****-*******
አብዛኛው መልዕክት ለአፋር ህዝብ ሆኖ አገኘውት፤
ከአፋር ህዝብ ጋር መጣላት አንፈልግም የሚል ሀሳብን ያንፀባረቀ ነው።ከዚህ በተጨማሪም" የአፋር ልዩ ሀይል በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀመብን ነው፤" እባካችሁ ተውን!" የሚል መልዕክትም ተጨምሮበታል።

እኔ ያልገባኝ፣ ቀድሞ ጦርነቱን እኮ የጀመረው የአፋር ህዝብ እንዳልሆነ ይታወቃል።አፋር ሰውን አይነካም ከነኩት ግን በቀላሉ አይፋታም።አፋር በታሪክ ተሸንፎ አያውቅም።እራሱን የመከላከል ህጋዊም ሆነ ሞራላዊ መብት ደግሞ አለው።ለእርዳታ መንገዱን እናስከፍታለን ያለው ሀይል ሌላ ወንጀል ፈፅሟል።አፋር ጋሊኮማ ላይ ህፃናት እና ሴቶች በግፍ ተጨፍጭፎባቸዋል። ዜጎችን ከጥቃት የመከላከል ግዴታ ደግሞ በዋናነት የተጣለው በአፋር ልዩ ሀይል ላይ ነው።የሆነውም ይሄው ነው።

በእውነት አፋርማ ጀግና ህዝብ ነው!

22/09/2021

‼ ድሮኖች ስራ ጀምረዋል ‼

ከተከዜ አቅራቢያ 9ኪ.ሜ ርቀት 'ዱራ' በተባለ አካባቢ ላይ በተወሰደ የተቀናጀ የማጥቃት ኦፕሬሽን አብዛኛው የህወሓት ታጣቂ ዶግ አመድ ሲሆን ተርፎ የፈረጠጠው ሀይል በሰቆጣ በኩል በመከላከያ እና ልዩ ሀይሎች ክፉኛ እየተቀጠቀጠ ይገኛል

22/09/2021

‼ የነጩ ቤተመንግሥት ጭንቀት ውስጥ መግባት ‼
በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ የምዕራባውያን ጥላች በከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ እንዳሳሳባቸው ተነገረ በአሁን ሰአት በአፍሪካ ቀንድ እንደዚህ አይነት ሆኔታ መፈጠሩን አይፈልጉም። ለችግሩ ምክንያት አሜሪካ ማዕቀብን ጨምሮ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መግባቷ እንደሆነ ከአሜሪካ ደህንነት ቢሮ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።(ዝርዝሩ እንደደረሰ እንመለስበታለን)

በህልውናው ዘመቻው የአማራ ክልል መደበኛ የፖሊስ ሰራዊት ተጋድሎ በሰሜን ጎንደር ዞን ከምስራለማኝ እስከ ጭና በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ በነበረው የትግራይ ተስፋፊ ቡድኖችን የማፅዳትና...
21/09/2021

በህልውናው ዘመቻው የአማራ ክልል መደበኛ የፖሊስ ሰራዊት ተጋድሎ በሰሜን ጎንደር ዞን ከምስራለማኝ እስከ ጭና

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ በነበረው የትግራይ ተስፋፊ ቡድኖችን የማፅዳትና የመደምሰስ ዘመቻ ላይ መደበኛ ፖሊሱ ከሃገር መከላከያ፣ ከአማራ ልዩ ኀይል እንዲሁም ሚሊሻና ፋኖ ጋር በመቀናጀት የራሱ የውጊያ ቀጠና በመያዝ በሻንበል እና በመቶ በመደራጀት ከምስራለማኝ እስከ ጭና የጠላትን ኀይል ወደ ስበት ቀጠና በመሰብሰብ የመደምሰስሻ ወረዳ አስገብተው የማያዳግም እርምጃ ወስደውበታል።

ረዳት ኢንስፔክተር አባተ ጠጁ እና ረዳት ኢንስፔክተር አስፋው ካሰዬ የነበረውን የውጊያ ውሎ እንደገለፁት የጠላት አጠቃላይ እንቅስቃሴ በሰው ኀይል ቁጥር እና በመሳሪያ አቅም የበላይነት ነበረው ከነሃሴ 11/2013 እስከ ነሃሴ 29/2013 ዓ.ም ድረስ ደባርቅ እና ደባትን በማያዝ የጎንደርን ጥርጊያ ጎዳና በመዝጋት ከፍተኛ ወታደራዊ ድል ለማስመዝገብ እና ወደ ሌሎች ትልልቅ ከተሞች ለመጓዝ አስቦ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ቅዠቱ እውን እንዳይሆን በከፍተኛ ሞራልና ወኔ በመተናነቅ መቃብሩን በመረጥነው መግደያ ወረዳ(ጭና) ውስጥ አድርገነዋል ብለዋል።

ሳጅን ነጋ ያለውለት እና ረዳት ሳጅን ጌቱ ሸዋ በበኩላቸው የጠላት አሰላለፍ ምንም እንኳን አላማቢስ እና ተራ ያጥፍቶ መጥፋት ከንቱ አስተሳሰብን አንግቦ በድፈረት መሬታችንን ቢረግጥም እዚሁ ተወቅቶ ቀርቷል ብለዋል።

በዚህ የህልውና ዘመቻ ላይ በመደበኛ ፖሊሶቹ እና በሌላው የፀጥታ ኀይል የተባበረ ክንድ ድባቅ ተመቶ የፈረጠጠው የወንበዴው ቡድን በነበረው ከ4 ቀን ያልበለጠ ቆይታ በመንግሥት ተቋማትና በአካባቢው ነዋሪ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ እነደነበር ገልጸዋል።

በየህልውና ዘመቻው የአካባቢው ህብረተሰብ እና ወጣቱ ከጎናቸው በመሆን ላደረገላቸው ዘርፈ ብዙ አስተዋፅኦ ምስጋና እናቀርባለን ሲሉ የሰሜን ጎንደር ዞን መደበኛ ፖሊሶች ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ሳጅን ሙሃመድ አህመድ-ከማይፀብሪ ግንባር

"ለመኖር ከሚበቃኝ በላይ ገንዘብ ባካብት ተከትሎኝ አይሄድም። ወገኔን ካልረዳሁበት ሀጥያት ይሆንብኛል። ሀጥያትን ተሸክሜ መኖር አልፈልግም። ወገኔን የምረዳው ለራሴ ስል ነው ወገኔ ተቸግሮ መድ...
20/09/2021

"ለመኖር ከሚበቃኝ በላይ ገንዘብ ባካብት ተከትሎኝ አይሄድም። ወገኔን ካልረዳሁበት ሀጥያት ይሆንብኛል። ሀጥያትን ተሸክሜ መኖር አልፈልግም። ወገኔን የምረዳው ለራሴ ስል ነው ወገኔ ተቸግሮ መድረስ ካልቻልኩ አማራም ኢትዮጵያዊም አይደለሁም"
አቶ ወርቁ አይተነው

19/09/2021

በዚህ 2 አመትና 3 አመት ዉስጥ ወደ መተማ ወረዳ ጉባይ ሌንጫ ጀጀቢት መቃ ቀበሌ ዉስጥ ከጭልጋና አካባቢ በሰራተኛ ስም እየመጣ ተሰግስጎ የተቀመጠና ቅማንት ሽፍታ ጋር በጥቆማ በስለላ በመግደል በመዝረፍ በማገት ወንጀል ቀጥተኛ ተሳታፊና ተባባሪ የነበረ እና በተለያየ ሃገር አፍራሽ አደረጃጀት ዉስጥ ተሳታፊ የነበረ የጭልጋ ጽንፈኛ ቅማንት ሙሉ በሙሉ ምእራብ ጎንደርን ለቆ መዉጣት አለበት።

የጉባይ የጀጀቢት የዘዉዴ ባድማ የሌንጫና መቃ ነባር ነዋሪዎችም በቀን ሰራተኛ ስም በእነዚህ ቀበሌ ተሰግስጎ የተቀመጠን ጽንፈኛ ቅማንት ጠራርገህ ካላባረርክና ካልስወጣህ አሁንም ነገ ጦሱ ላንተ ነዉ።።
አራት ነጥብ !

‼ "የሁለት ደብዳቤዎች ወግ" - ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ የተፃፎ ‼አንደኛው ከአዲስ አበባ የተጻፈ ነው። ሁለተኛው ከመቀሌ የተከተበ ነው። ሁለቱ ደብዳቤዎች በይዘት የሰማይና የምድርን ያህል...
19/09/2021

‼ "የሁለት ደብዳቤዎች ወግ" - ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ የተፃፎ ‼

አንደኛው ከአዲስ አበባ የተጻፈ ነው። ሁለተኛው ከመቀሌ የተከተበ ነው። ሁለቱ ደብዳቤዎች በይዘት የሰማይና የምድርን ያህል ይራራቃሉ። የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር የተጻፉበት ቋንቋ እንግሊዘኛ መሆኑና መዳረሻቸውን ከአንድ ቦታ ከነጩ ቤተመንግስት ማድረጋቸው ነው። ሁለቱም ለአንድ መግለጫ መልስ ለመስጠት የተጻፉ ናቸው። የይዘት ልዩነታቸው የሰሜንና ደቡብ ዋልታዎች ዓይነት መራራቅ እንኳን የማይገልጸው፣ አንደኛው ድፍረትና ሀገራዊ ቁርጠኝነት የነገሰበት፣ ሌላኛው ልምምጥና ልፍስፍስነት ያጠቃው፣ አንደኛው ደጄን አትርገጡ ሲል ሌላኛው ጓዳችን ድረስ ዘልቃችሁ ፈትፍቱ ብሎ የሚጋብዝ ነው። አንደኛው በሀቅና እውነት የተንቆጠቆጠ፣ ሌላኛው በውሸትና ቅጥፈት የተሽሞነሞነ ነው። አንደኛው አትድረሱብን ብሎ ሲያስጠነቅቅ፣ ሁለተኛው ደግሞ ድረሱልን እያለ የሚማጸን ነው። ሁለቱም የተላኩት ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ነው።

ከአዲስ አበባ የተላከው ደብዳቤ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የተጻፈ ነው። የመቀሌው ከህወሀት ጽ/ቤት በደብረጺዮን ፊርማና ማህተም የተተዘጋጀ ነው። ባለፈው ዓርብ ጆ ባይደን ጦርነቱን አቁሙ፣ አለበለዚያ ሁላችሁንም እቀጣለሁ ብለው ላስተላለፉት ማስፈራሪያ የተሰጡ ምላሾች ናቸው። ጆ ባይደን በአንዲት ልዑዋላዊት ሀገር ጉዳይ ምን ኮነሰራቸውና ነው እንዲህ የሚውረገረጉት የሚለውን ለጊዜው ተወት አድርገን ስለሁለቱ ደብዳቤዎች ትንሽ ወግ እንጠርቅ።

ጠ/ሚ አብይ ታሪካዊ ደብዳቤ ስለመጻፋቸው የሚስማሙት ጥቂቶች አይደሉም። አጼ ቴዎድሮስ ለእንግሊዟ ንግስት ቪክቶሪያ የጻፉትን ቆፍጠን ያለ ደብዳቤ የሚያስታውስ እንደሆነ ይነገርለታል። የጠ/ሚሩ ዋንኛ ጭብጥ እኛ ለራሳችን አናንስም፣ እዚያው በቅጥራችሁ ተሰብሰቡ የሚል ነው። የኢትዮጵያን ታሪክ በማጣቀስ ለውጭ ሃይሎች ሳትንበረከክ ዛሬን የደረሰች መሆኗን ለባይደን ግልጽ በሆነ ቋንቋ አስቀምጠውላቸዋል። የእሳቸው የፍርድ ሚዛን በአሉባልታዎችና በአንዳንድ ሸቃይ ጎትጓች ተቋማት የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመግለጽ አሜሪካንን ከምታህል ትልቅና ሀብታም ሀገር የማይጠብቅ አቋም ማራመዳቸው እንዳሳዘናቸው የገለጹበት ደብዳቤ ነው። ኢትዮጵያ ህወህትን አጥፍታ፣ ከመቃብር አስገብታ፣ ሰላምና ደህንነቷን ለማረጋገጥ የማንንም ቡራኬና ይሁንታ እንደማትፈልግ በመግለጽ እጃቸውን እንዲሰበስቡ የሚያሳስብ መልዕክት ያዘለ ነው። በአጭሩ ኢትዮጵያ የተገለጸችበት፣ የህዝቧ ጀግንነትና አይበገሬነት የተንጸባረቀበት፣ ለየትኛውም ጫና የሚሰበር አንገት የሌለን መሆኑ ጎልቶ የተነገረበት ደብዳቤ ነው ማለት ይቻላል። በትክክልም በታሪክ ቅብብሎሽ ለትውልድ የሚተላለፍ ድንቅ ደብዳቤ ነው።

ከመቀሌ ህወሀት ጽ/ቤት ደብረጺዮን የጻፈው ደብዳቤ በተቃራኒው ፍርሃት፣ ቅጥፈት፣ ልመናና ድረሱልን በሚሉ ስሜቶች ሊገለጹ በሚችሉ መልዕክቶች የተሞላ ነው። ህወሓት እንደልማዱ ቆርጦ ቀጥል መረጃዎችን በአሰልቺ አቀራረብ ያዘጋጀው ተመሳሳይ ዲስኩር ነው። የእምዬን ለአብዬ እንዲሉ የህወሀትን ሀጢያትና ኩነኔ እንዳለ መንግስት ላይ ለጥፎ የሚያለቃቅስበት ደብዳቤ ነው። ከህሊናና ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ የቀረው አማራጭ የአሜሪካን አማላጅነት ነው ብሎ ተስፋ የቆረጠ ቡድን የጻፈው ደብዳቤ እንደሆነ ከጅማሬው እስከፍጻሜው በተሰገሰጉት መልዕክቶች መረዳት ይቻላል። ህወሓት በደብዳቤው የባይደንን የማዕቀብ ውሳኔ ከፈጣሪ የተላከ የህይወት መዳኛ በረከት አድርጎ ከልቡ እንደተቀበለው ሳያቅማማ አስታውቋል። መንገድም ብርሃንም አሜሪካ አንቺው ነሽ ሲል ያሞካሻል። ማዕቀቡ የህወሀትን መሪዎች የሚነካ መሆኑ አላስጨነቀውም። ይልቅስ አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብታ መንግስት እንድትሾም፣ መንግስት እንድትሽር ተንበርክኮ የሚለምን የሚመስልበት ደብዳቤ ነው። ተስፋ መቁረጡን፣ አሜሪካ አንዳች ነገር ካላደረገች መጥፊያው እየተቃረበ መሆኑን በመግለጽ 'ድረሺልን' የሚል የተማጽኖ ደብዳቤ ነው የሚመስለው። በአጭሩ ተለማማጭነት የሚታይበት፣ በተስፋ መቁረጥ ስሜት የተሞላ፣ ተንበርካኪና ሰጋጅ ደብዳቤ ነው ማለት ይቻላል።

ዋናው ነገር አሜሪካን መሄድ የምትችለውን፣ በአቅምና ጉልበቷ ማድረግ የምፈልገውን ሁሉ ብታደርግ ከኢትዮጵያ ሀገራዊ የግዛት ልዑላዊነት ጋር በእኩል ሚዛን የምናስቀመጠው አይደለም። ህወሀትን ለማዳን ብላ ኢትዮጵያን በሚያፈርስ እንቅስቃሴ ውስጥ የምትገባ ከሆነ እንግዲህ የሚመጣውንም አብረን የምናየው ነው። በእርግጥ አሜሪካኖቹ ሁኔታውን አይተው መንገዳቸውን ማስተካከላቸው አይቀርም። ልክ እንደሻርክ ፍርሃትን ያነባሉ። ሻርክ ከሌላው እንስሳ የሚለየው የባላንጣው ፍርሃት የሚለይበት የስሜት ህዋስ አለው። ከፈራህ ይሰለቅጥሃል፣ አለበለዚያ አይነካህም። አሜሪካም እንደዚያው ናት። የሚፈራ መንግስት ካገኘች በነፍሰ ስጋው ትጫወትበታለች። ቆፍጠን፣ ኮራ ጀነን ካልክባት ደግሞ እጥፍ ትልና ሸሪክህ ሆና ትመጣለች። ከዚያ ያለፈ ነገር የለውም። የጠ/ሚር አብይ አቋምና የዓርብ ዕለቱ ደብዳቤ ታሪካዊ ነው ያስባለውም ለዚህ ነው።

የኪውባው ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ ከመኝታቸው ተነስተው ልብሳቸውን ከለበሱ በኋላ ጫማቸውን ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ ፡ ተወልውለው በስርአት በሚቀመጡት ጫማዎቻቸው ላይ አቧራ መሰል ብናኝ ተነስንሶ...
18/09/2021

የኪውባው ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ ከመኝታቸው ተነስተው ልብሳቸውን ከለበሱ በኋላ ጫማቸውን ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ ፡ ተወልውለው በስርአት በሚቀመጡት ጫማዎቻቸው ላይ አቧራ መሰል ብናኝ ተነስንሶ ተመለከቱ ። ተጠራጣሪው ካስትሮ ጫማቸውን ለማንሳት የተዘረጉ እጆቻቸውን ሰብስበው ከሳቸው ጋር በአንድ ጊቢ የሚኖረውን የልዩ ጥበቃ ሃላፊያቸው ጋር ደወሉ ።........................

የቀድሞዉ የኩባ መሪ ፊደል ካስትሮ ወደ ስልጣን እንደወጡ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙት አሜሪካንን ነበር ። በዚያ ተገኝተው አሜሪካ ኪውባን እንድትደግፍ እና ስለሁለቱ ሃገራት ወዳጅነት ላይ ለመምከር በነጩ ቤተመንግስት የተገኙት ካስትሮ የሃገር መሪን ክብር በሚመጥን መልኩ የሚያስተናግዳቸው ፕሬዝደንት ጠፋ ።

የወቅቱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ዴቪድ አይዘአወር የልኡካን ቡድናቸውን እየመሩ አሜሪካንን ለመጎብኘት የሄዱት ካስትሮን ጋዜጠኞች ባልተገኙበትና በዝግ በተካሄደ የአንድ ሰአት የመወያያ ጊዜ ከመስጠት ውጭ በቂ የመነጋገሪ መድረክ አላመቻቹላቸውም ነበር ።

ይባስ ብሎም ከካስትሮ ጉብኝት በኋላም አሜሪካ ለኪውባ የወዳጅነት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ ካስትሮን ከስልጣን ወይም ከምድር ለማስወገድ በስለላ ድርጅቷ CIA በኩል የኪውባ ስደተኞችን አስታጥቃ የእጅ አዙር ጦርነት ከፈተች ።

ለዚህ የአሜሪካ ተግባር ኪውባም በሃገሯ የሚገኙ የአሜሪካን ኩባንያዎች ዘግታ የቀሩትንም ወረሰች ። አለመግባባቱ ጦዞ አሜሪካ የኪውባን ስደተኞችና ቅጥረኛ ወታደሮችን አሰማርታ መጠነ ሰፊ ወረራ ከፈተች ። ኪውባ ይህን የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ለመገዳደር ከኮሙኒስት ሃገር ሶቪየት ጋር ወዳጅነቷ አጠበቀች ።

የካስትሮ መንግስት ከቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ባገኘው የጦር መሳሪያ እርዳታ ተቃዋሚዎቹን ከማጥቃት አልፎ ትላልቅ ድንበር አቋራጭ ሚሳይል ወደ አሜሪካ ከተሞች አነጣጥሮ ጦርነቱን በአሜሪካ በኪውባና በሩሲያ መሃከል እንዲሆን አድርጎ መጠባበቅ ጀመረ ።

የአሜሪካ ከተሞች ከኪውባ በሚሰነዘር የኒውክሊየር ጥቃት ሊፈፀምባቸው እንደሚችል ስጋት በመፈጠሩ አሜሪካ ሶቪየት ህብረትን ኪውባን መርዳት እንድታቆም አለበለዚያ ግን ፀቧ ከኪውባ ሳይሆን ከሶቪየት ህብረት ጋር እንደሆነ ማስጠንቀቅ ያዘች

አሜሪካ የተፋጠጠችው ከድሃዋ ኪውባ ጋር ሳይሆን ከምንጊዜም ተፎካካሪዋ ( ሶቪየት ህብረት ( ሩሲያ ) ጋር መሆኑን ስታውቅ ወደቀልቧ መመለስ ጀመረች ። በሁለቱ ሃያላን ሃገራት መፈራራትም በኪውባ ሊፈፀም የታቀደው የአሜሪካ የእጅ አዙር መጠነ ሰፊ ወረራ እቅድ ተሰረዘ ።

ኪውባ ከጎኗ ቆማ እስኪ የሚነካሽን አያለሁ ባለቻት ሩሲያ አማካኝነት ከአሜሪካን ወታደራዊ ጥቃት ተረፈች ። ይህን የተገነዘቡት የአሜሪካ መሪዎች ኪውባን በኤኮኖሚ አሽመድምዶ እግራቸው ስር ለማንበርከክ ሌላ እቅድ አወጡ ። ማእቀብ መጣል ።

አሜሪካ በኪውባ ላይ ያኔ የጣለችው ማእቀብ ከዛሬ ነገ ኪውባን እጄ ላይ ይጥልልኛል ብላ ብታስብም በፊደል ካስትሮ ጠንካራ አመራርና በህዝቧ ብርታት ማእቀቧ ሊሰራ አልቻለም ። ይህን የተረዱት የአሜሪካ መሪዎች ሁሉም ነገር የሚጠናቀቀው ካስትሮ ከዚህ አለም በሞት ሲሰናበት ነው ብለው በማሰብ ካስትሮን የመግደል ተልእኮ ለስለላ ድርጅቷ ለ CIA ተሰጠው ።

ይህ ተልእኮ በየጊዜው ዩናይትድ ስቴትስን በመሯት ሰባት መሪዎች ሳይቀየር ከስድስት መቶ ጊዜ በላይ ካስትሮን ለመግደል CIA ወገቡን አስሮ ዶላሩን መንዝሮ መሞከር ጀመረ ።.................................................................................................................

ፊደል ካስትሮ በመኖሪያ ቤታቸው በሚገኘው የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ጥቂት ደቂቃዎች ለማሳለፍ የመዋኛ ቁምጣቸውን ለብሰው እየሄዱ ሳለ ከብዙ የግድያ ሙከራ ያዳናቸው የልዩ ጥበቃ ክፍል ሃላፊው ካለወትሮው አስቆማቸውና ።
" ውሃውን መመርመር ሳይኖርብን አይቀርምና ጓድ ፕሬዝዳንትእባክህ አረፍ በል " አላቸው ።.........................
የውሃው ናሙና ተወስዶ በላቦራቶሪ ሲታይ በርግጥም የመዋኛ ገንዳው ውሃ ለሞት በሚያደርስ የቆዳ በሽታ በሚያመጣ ፈንገስ ተመርዞ ነበር ።................
የአሜሪካው C.I.A ይህ የግድያ ሙከራ እንደከሸፈ ሲያውቅ botulinum የሚባል አደገኛ ኬሚካል ፕሪዝዳንቱ በሚወዱት ቶስካኖ ሲጋራ ውስጥ በመክተት ወደ ፕሬዝዳንቱ መኖሪያ በስውር አስገብቶ የፕሬዝዳንቱን መሞት መጠበቅ ጀመረ ። ነገርግን ይሀው የጥበቃ ክፍል ሃላፊ በሲጋራዎቹ ላይ ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ ሲጋሮቹ እንደተመረዙ ታወቀ..................
በተለያየ መንገድ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል ሳይታክት የሚሞክረው C.I.A ፕሬዝዳንቱ የሚውጡትን አይነት ተመሳሳይ ክኒን በመድሃኒት ብልቃጣቸው ውስጥ በመክተት ለመግደል ያደረገውም ሙከራ ከሸፈ ።..........
በስለላ ድርጅቱ በተመለመለች የሚወዷት ፍቅረኛቸው ተመርዘው ይህችን አለም እንዲሰናበቱ የታሰበውም ሙከራ ሳይሳካ ቀረ ።
ይህ ሙከራ ይሳካል ተብሎ የታሰበው የካስትሮ የቀድሞ ፍቅረኛ በነበረችው በማሪታ ሎሬንዝ ነበር ፡ ካስትሮን ለመግደል ከምትኖርበት አሜሪካ ወደ ኪውባ ሃቫና የተመለሰችውና ድርጊቱን ከፈፀመች በዶላር እንደሚያንበሸብሿት በCIA ሰወች ቃል የተገባላት ማሪታ ሎሬንስ ካስትሮን ለማግኘት ብዙም ችግር አልገጠማትም ነበር ።
ሆኖም ካስትሮን አግኝታ ፊት ለፊቱ ስትቆም ፍቅር አሸነፈና ያንን ክፋት የመፈፀም ወኔዋ ከዳት ። እቅፉ ውስጥ ሆና እያለቀሰች ፊደል አንተን እንድገድል ነው የመጣሁት ነገር ግን ልገድልህ አልችልም። ምንም ያደረከኝ ነገር የለም ብላ የስለላ ድርጅቱን እቅድ ነግራ የታሰበውን እቅድ አከሸፈችው ።
....................
በስለላ ድርጅቱ በልዩ ትእዛዝ ተመርቶ ካስትሮ ቢሮ እንዲገባ ተሞክሮ የነበረው እስክርቢቶም ወደቢሮው ሳይደርስ በቁጥጥር ስር የዋለው ግቡን ሳያሳካ ነበር ። ይህ እስክርቢቶ እጅግ መርዛማ ኬሚካል እንዲያመነጭ ተደርጎ የተሰራ በመሆኑ ፡ ፕሬዝደንቱ በስክርቢቶው መፃፍ ሲጀምሩ ኬሚካሉ መትነን ይጀምርና መተንፈሻ አካላቸውን መርዞ ከመቅፅፈት ለሞት የሚያበቃቸው ነበር ።...............
አንድ ቀን ደግሞ ፕሬዝደንት ፊደል ካስትሮ ከመኝታቸው ተነስተው ልብሳቸውን ከለበሱ በኋላ ጫማቸውን ለማድረግ ጎንበስ ሲሉ ፡ ተወልውለው በሚቀመጡት ጫማዎቻቸው ላይ አቧራ መሰል ብናኝ ተነስንሶ ተመለከቱ ። ተጠራጣሪው ካስትሮ ወዲያውኑ እጆቻቸውን ሰብስበው ከርሳቸው ጋር በአንድ ጊቢ የሚኖረውን የልዩ ጥበቃ ክፍል ሃላፊ ጋር ደወሉ ። ጫማዎቻቸው በጓንት ተይዘው ወደላቦራቶሪ ተልከው የተገኘው ውጤት ልማደኛው CIA ፕሬዝደንቱን በአቧራ መሰል ገዳይ ኬሚካል በጫማቸው ውስጥ በመበተን ያቀደው ሙከራ እንደነበር ታወቀ
....................
ከገዳይ ባክቴሪያ በተሰራ መሃረብ ........................
ለሃቫናው ሂልተን ሆቴል ዌይተር ማባበያ በመስጠት ፕሬዝዳንቱ የሚወዱትን ሚልክ ሼክ በመመረዝ ለመግደል መሞከር...................
በአልሞ ተኳሾች .....................
ለንግግር በሚወጡበት ፖዲየም ስር ፈንጂ በመቅበር..............
እና በሌሎች ብዙ ሙከራዎች በተለያዩ የአሜሪካን ፕሬዝዳንቶች ትእዛዝ ማለትም
በፕሬዝዳንት Eisenhower: 38 ጊዜ
በ Kennedy: 42 ጊዜ
በ Johnson: 72 ጊዜ
በ Nixon: ዘመነ መንግስት 184 ጊዜ
በ Carter: 64
በ Reagan: 197
Bush Sr: 16
በመጨረሻም በ Clinton: 21 ጊዜ የመግደል ሙከራ የተደረገባቸውና ኩባን ለግማሽ ክፍለዘመን የመሩት የኩባው ፊደል ካስትሮ ከተደረገባቸው ከ 600 በላይ ሙከራዎች ተርፈው በ90 አመታቸው በተፈጥሮ ሞት መሞታቸው አስገራሚ ነው ። ኪውባም ለሃምሳ ምናምን አመት በተጣለባት ማእቀብ ሳትበገር ዛሬም ብርቱ ሆና ቀጥላለች ።

 #ራሺያ‼‼‼@ኢትዮዽያ ሉአላዊት ሀገር በመሆኗ በውስጥ ጉዳዮቿ ላይ ጣልቃ መግባት የሚፈልጉ ሀይሎች ከንቱ ድካማቸውን ሊገቱት ይገባል!!" ቭላድሚር ፑቲን የሩስያ ፕሬዚደንት።@" በሰሜኑ የኢት...
18/09/2021

#ራሺያ‼‼‼

@ኢትዮዽያ ሉአላዊት ሀገር በመሆኗ በውስጥ ጉዳዮቿ ላይ ጣልቃ መግባት የሚፈልጉ ሀይሎች ከንቱ ድካማቸውን ሊገቱት ይገባል!!" ቭላድሚር ፑቲን የሩስያ ፕሬዚደንት።

@" በሰሜኑ የኢትዮዽያ ግዛት የሽብር ጥቃት መፈጸሙን እና እየተፈፀመ መሆኑን የኢትዮዽያ ህዝቦች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለአለም ህዝብ አሳውቀዋል።

@ሽብርተኞችን በመዋጋት የዜጎቹን ደህንነትና ሰላም የማረጋገጥ ግዴታ ደግሞ በመንግስቷ ላይ የወደቀ ነው።

@በዚች ሉአላዊት ሀገር ሽብርተኞችን የመዋጋትተጋድሎ ውስጥ አጋዥ መሆን ያልቻሉ የውጭ ሀይሎችም ቢያንስ ዝም ሊሉ ሲገባቸው በውስጥ ጉዳዮቿ ውስጥ ጣልቃ በመግባት ለአሸባሪው ቡድን የሚወግኑ ሀይሎች ከከንቱው ድካማቸው ሊገቱ ይገባል።
ኢትዮዽያ በአለም እውቅና ያለው እና በህዝቦቿ ምርጫ ስልጣን ያገኘው

@መንግስቷ የህዝብን ጥያቄ በአፋጣኝ በመመለስ ሽብርተኝነትን እና ድህነትን ከመሰረቱ ለማጥፋት በሚያደርገው ጉዞ የሩስያ ህዝብና መንግስት ግንባር ቀደም ተሳታፊና ደጋፊ መሆኑን መግለጽ እፈልጋለሁ።"
ምን ጭ :CGTN

18/09/2021

አሸባሪው ህወሃት ምርት ገበያ በመጋዘኖች ውስጥ ያከማቻቸውን ምርቶች ዘርፏል

መስከረም 07/2014 ዓ.ም አሸባሪው ህወሃት የምርት ገበያ ቢሮዎችን ከጥቅም ውጭ ከማድረጉም በላይ በመጋዘኖች ውስጥ የተከማቹ ምርቶች መዝረፉን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የተዘረፈው የግብርና ምርቶች ከ24 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ተጠቁሟል።

ባለሥልጣኑ በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉት 27 ጥብቅ መጋዘኖች ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶች አከማችቶ ለሽያጭ ያቀርባል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኢሌሮ ኡፒየው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ አሸባሪው ህወሃት በሁለት ማከማቻ መጋዘኖች የነበረ ከ24 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ምርት ዘርፏል። የተቋሙን ቢሮዎች አውድሟል።

ቡድኑ ከሽራሮ እና ሑመራ የምርት መረከቢያ መጋዘኖች ከ4 ሺ 822 ኩንታል በላይ ምርት መዘረፉን ነው የገለጹት።

አርሶ አደሩ ምርቱን በመሰብሰብ ላይ እንዳለ አሸባሪው ቡድን “በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ለውንብድና ተግባሩ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮለታል” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ።

ይህ ተግባሩ በአገር ኢኮኖሚና በምርት ገበያው ስራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከመፍጠሩ ባሻገር አርሶ አደሩንም ለኪሳራ መዳረጉን ተናግረዋል።

በምርት ገበያው መጋዘኖች ላይ የተፈፀመው ዘረፋ የምርቱን ባለቤቶች በተለይም አርሶ አደሩን ለመጉዳትና ተጠቃሚ እንዳይሆን ለማድረግ መሆኑን ሕብረተሰቡ መገንዘቡንም አንስተዋል።

አሸባሪው ቡድን የዘረፈውን እህል የቻለውን በመውሰድ ያልቻለውን በየቦታው በመበተን ከጥቅም ውጭ ማድረጉንም ጠቁመዋል።

የጥፋት ቡድኑ ከዘረፋው በተጨማሪ ምርት ገበያው አርሶ አደሩ ለገበያ የሚያቀርበውን እህል ሰብስቦ የሚያስቀምጥባቸውን መጋዘኖችም ማውደሙን ኢንጂነር ኡሌሮ ተናግረዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ በምርታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው አካላት ለመንግስት የካሳ ጥያቄ እያቀረቡ ነው።

ባለስልጣኑ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሳውቆ ምላሽ እየተጠባበቀ መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ለመከላከያ ሠራዊቱ የአንድ ወር ደመወዝና የደም ልገሳ ያደረጉ ሲሆን ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኢዜአ ገልጿል።

አበበ ገላው የበፊቱ የኢሳት ጋዜጠኛ፣ መለስ ዜናዊን በመብረቃዊ ድምፁ በተገቢ መድረክ ላይ የከሰሰው፤ ብሎም የመለስን ህመም አባብሶ ለሞት ያበቃው ጀግና ሰው ነው። ዛሬ ግን የአዲሱ አሸባሪ መ...
18/09/2021

አበበ ገላው የበፊቱ የኢሳት ጋዜጠኛ፣ መለስ ዜናዊን በመብረቃዊ ድምፁ በተገቢ መድረክ ላይ የከሰሰው፤ ብሎም የመለስን ህመም አባብሶ ለሞት ያበቃው ጀግና ሰው ነው። ዛሬ ግን የአዲሱ አሸባሪ መንግስት ደጋፊ ነው። በየቀኑ በመቶ የሚቆጠሩ አማሮች መንግሥት መዋቅሩን ተጠቅሞ ፣ ሃላፊነቱን ችላ ብሎ እዲጨፈጨፉ እንዲሁም በሞታቸው የሚሳለቀውን መንግስት ደጋፊ ነው።
ዛሬ ደግም ብልፅግናን ወክሎ ኤርሚያስ ለገሰን ፍርድ ቤት ከሶታል። 900000 ብርም እንዲከፍለው ጠይቋል። አጃይብ ነው።

16/09/2021
11/09/2021

Today is 01/01/2014, new year in the Ethiopian Calender.

In North Wollo, Amhara region Ethiopia, this Elderly Mother seen in the picture was displaced from her home by the TPLF terrorist forces, she lives now in the woods sick and Hungry.
This is how the new year begins for millions of Ethnic Amharas in Ethiopia .

 !  !*********************ጀግናን_ጀግና_አለማለት_ንፉግነት_ነው!በእውነት እላችዋለሁ፣ ይህን የአፋር ህዝብ እስከ ዛሬ ድረስ በጭራሽ አናውቀውም ነበር። በቃ ምን ልበላቹ ፦   ...
11/09/2021

!
!
*********************
ጀግናን_ጀግና_አለማለት_ንፉግነት_ነው!
በእውነት እላችዋለሁ፣ ይህን የአፋር ህዝብ እስከ ዛሬ ድረስ በጭራሽ አናውቀውም ነበር። በቃ ምን ልበላቹ ፦
በጀግንነቱ ፈፅሞ ተወዳዳሪ የሌለው ህዝብ ነው፣
ዛሬ ላይ የራሱንና የሌሎች ኢትዮጵያውያንን ዳር ድንበር ሳያስደፍር እየኖረ ያለ ጀግና እና ጨዋ ህዝብ ነው።አፋር ፌስቡከኛ የለውም፣ አፋር ሚዲያም የለውም፤አፋር ያለው ልብ ብቻ ነው።
ሆነ ሲጠቃ ካልተጠየቀ በቀር ለሰው አያወራም፣ ጠላቱንም ጭምር ክፉ አይናገርም።የሚያምነው በተግባር ብቻ ነው። እኛ ነን እንጂ ስለ አፋር የምናወራው እነሱ በሚዲያዎቻቸውም ጭምር ትንፍሽ አይሉም።
አፋር ሁሌም ማድረግ ያለበትን ነገር ብቻ አድርጎ ድልን ይቀናጃል።እሱን መንካት አፀፋው ከባድ እንደሆነ ትላንትና እና ዛሬ በተግባር አይተናል።
ባለ ሽርጣሙ የሌላውንም እገዛ ቢሆን ፈፅሞ አይፈልግም። በጊሌ ታንክ ሲማርክ አይተናል፣ አንድ ሰው ለብቻው ከ5 በላይ ሞርታርና ዲሽቃ ቀምቷል። አስር ሆነው 4000 ሺ ወታደር ማርከው 2 ሺውን እጅ አሰጥተዋል።ዛሬ ደግሞ በስህተት የተያዙ ሁለት ወረዳዎችን ነፃ አውጥተዋል።
ይህን ሁሉ ገድል የሰማ ሰው ያለ አይመስለኝም።ምክንያቱም ደግሞ እነሱ ሞያ በልብ ብለው ስለማይናገሩ።
የኢትዮጵያዊነት የውሃ ልክማ ከምር እነዚህ የሉሲ ልጆች ናቸው።
*******አሁንም ድል ለአፋር ህዝብ ተመኘው!*****

Address

Asella

Telephone

+251901539393

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amater TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amater TV:

Videos

Share