Firew Bogale SE

Firew Bogale SE Economist AND Activist

09/02/2024
03/02/2024

ሰበር ዜና !

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወላይታ(አረካ) ለሚያስገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የአማካሪ ግዢ ጨረታ አወጣ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አረካ ከተማ አቅራቢያ ለሚያስገነባው የወላይታ አውሮፕላን ሜረፊያ ፕሮጀክት የምህንድስና ዲዛይን፣ የግንባታ ቁጥጥር፣ የኮንስትራክሽን አስተዳደርና የግንባታ ማማከር አገልግሎት የሚሰጡ ደረጃ 1 የመንገድና አጠቃላይ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት በትናንትናው ዕለት ማለትም በ24/5/2016 ዓ.ም ግልጽ ጨረታ አውጥቷል።

Xoossi immin assi diggi ?
Xoqqis kaaqin kani ekki ?

Biroona Biroona hagaadani hashshu gaanabay,
Hagaappeka aruwaa be'anabaay,
Nu oyshshawu zaaroy yaanabay,
Nu bittaay (Wolaytti) biroon shiccanaay.

Dendoy yaana nu Wolayttawu mantiyaara!!!
Zaaroy yaana Wolayttawu mataara!!

Xoossawu Wolaytta gujaa gujaadakka Xomoosa !!

06/01/2024

ዉቢቷ፣ ህብረ ብሔራዊቷ፣ ወላይታ ሶዶ

ወላይታ ሶዶ የወላይታ ዞን ዋና ከተማ እና የደቡበ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ እና የአስተዳደር ማዕከል ናት።

ከተማዋ በዞኑ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዕምብርት መመላከቷ ፣ ከዞኑ ፣ ከ ከአጎራባች ፣ ከክልሉና ከሀገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ጋር በሰባት ዋና ዋና መንገዶች የሚትገናኝ መሆኗ ከተማዋ ተመራጭ የንግድ ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል።

የደጋ የአየር ንብረት የታደለችው ፅዱና አረንጓዴዋ እና ህብረ ብሔራዊቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ ለኑሮ ፣ ለሥራና ለመዝናኛ ተመራጭ መሆኗ ምስክርነት አያሻም።

ከተመሠረተች ወደ 130 ዓመት የሚጠጋ ዕድሜ ያስቆጠረችው ዕድሜ ጠገቧ ወላይታ ሶዶ ከተማና አካባቢዋ የአቡነ ተክለ ሀይማኖትና የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳማት፣ ፣ የቀደምት ፕሮቴስታንት ዕምነት አምልኮ ስፍራ/' ጠረጴዛ ' /፣ ከተማዋን ታኮ በዳሞታ ግርጌ የሚገኘው ጥንታዊው የሰው ዘር ከአስከፊው የበረዶ ቆፈን የተጠለለበትና የአካባቢው ነዋሪዎች የዕደ ጥበብና የእርሻ ሥራ አሻራ የተገኘበት የሞቼና ቦራጎ ዋሻ ፣ Biittaa Baattaa /የመሬት ውስጥ ጎተራ/፣ ምሽጎች፣ የወላይታ ባህላዊ ሙዚዬም ፣ የማህበረሰቡ የሥራ ፣ የአመጋገብና የአለባበስ ስርአቶችንና ክብረ-በዓላትን ጨምሮ በአፍሪካና በተለያዩ የአሜሪካ ሀገራት ባቀረበው ትዕይንት ዝናን ያተረፈውን የወላይታ ባህላዊ የውዝዋዜ ቡድንን ጨምሮ በአካባቢው አጆራ እና ሳንጋና ፏፏቴዎች ፣ አባያ ሀይቅና አካባቢው ፣ አሞ ወንዝና ተያያዥ የግልገል ጊቤ ሀይድሮ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፣ገዳማትና መስጊዶች ፣ የማንኢሳ እና የባንባላ ድልድዮች ፣ ፍል ውሀዎችና ትክል ድንጋዮችናየዳሞታ ተራ ራ ፣ ክብረ በዓላትና የማህበረሰቡ በክፉና በደጉ ጊዜ የመተጋገዝና የመተሳሰብ ዕሴቶች፣ የአለባበስና የአመጋገብ ስርአቶቹ የተመልካችን ቀልብን ይስባሉ።

በከተማዋ መርካቶ ፣ አሮጌ አራዳ ፣ አዲስ ከተማ ፣ጎላ፣ ገነሜ ፣ ጊሸን ፣ወይራ ሰፈር ፣ ቂጣ በል እና የሌሎች ሰፈሮች መጠሪያቸው ነዋሪዎቿ ዳራ ፣ መልክአ ምድራዊ አሰፋፈርና በጊዜ ሂደት ያከናውኗቸው የነበሩትን ተግባራትና ለውጦች ጠቋሚና የህዝቦቻችንን የቆየ የአብሮነት አሻራ አመላካች ናቸው።

ጂማንና ጂረኝን ጨምሮ የተለያዩ የደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ ፣ ሰሜን ምሥራቅና ምስራቁን የሀገራችንን ክፍሎች አቋርጦ ወደ ሱዳን ፣ ቀይ ባህር ፣ ዘይላ እና በርበራ ወደቦች በተዘረጋው ጥንታዊው ረጅም የንግድ መስመሮች በኩል ከወላይታ ቡልኮ ፣ ቡና እና ዝንጅብልን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች እስከ ውጭ ድረስ ይላኩ እንደነበር መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን መስተጋብሩ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎቹ በተጓዳኝ ለዘላቂ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ለባህል መወራረስ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል እያበረከተም ይገኛል።

በከተማዋ ግርጌ ላሾ የሚገኘው የኢትዮ -ኬንያ ኤሌክትሪክ ሀይል ማሰራጫ ኮንቨርተር ጣቢያ ፣ የተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮችና የኢንሹራንስ ካምፓኒዎች ፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሰዶ ዲስትሪክት ለከተማዋና ለአጎራባች ዞኖችና ክልሎች ግልጋሎት ይሰጣሉ።

ለከተማዋ ፣ ለአጎራባች ክልሎችና ሀገራት ግልጋሎት ከመስጠት በተጓዳኝ በህክምና ቱሪዝምም የታወቁ የግልና የመንግስት ሆስፒታሎችና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በከተማዋ በርካታ በግልና በመንግስት የሚተዳደሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ወላይታ ሶዶ እና አካባቢው ተግ

Address

Areka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Firew Bogale SE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share


Other Digital creator in Areka

Show All