ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት

ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት Deacon

24/12/2024
"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ። ብቻችሁን አትምጡ። ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ ፣ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቁም ። ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም ። ወራሾቻ...
24/12/2024

"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ። ብቻችሁን አትምጡ። ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ ፣ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቁም ። ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም ። ወራሾቻችሁ አይሆኑም ። ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ። አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ፣ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ ፣ በእምነት አሻሹአቸው መስቀል እንዲስሙ አስተምሯቸው ፣ ዕጣኑን ያሽትቱ ፣ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ፣ ቃጭሉን ይስሙ ፣ ደውል ሲደውል ይስሙ ፣ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ቤተ ክርስትያናቸው ምን እንደሆነች ፣ በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ፣ ይማሩ ። ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ፣ ወደ ማኅበር ስትሔዱም ይዛችኋቸው ሒዱ ፣ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ ። እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ።"

አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ

 "እውነት ምንድን ነው?"ዮሐ.፲፰፥፴፰  ጳላጦስ ክርስቶስን ሲጠይቀው ጥያቄ ስለ እውነት ነው።እውነት ክርስቶስን ስለ እውነት ጠየቀው። እውነት ከባለቤቱ መገለጥ የተነሣ የሚታወቅ እምነት ነው።...
23/12/2024



"እውነት ምንድን ነው?"ዮሐ.፲፰፥፴፰ ጳላጦስ ክርስቶስን ሲጠይቀው ጥያቄ ስለ እውነት ነው።
እውነት ክርስቶስን ስለ እውነት ጠየቀው።
እውነት ከባለቤቱ መገለጥ የተነሣ የሚታወቅ እምነት ነው።
እውነት ክርስቶስ ነው።
እውነት መስቀል ነው።
እውነት ኦርቶዶክሳዊ፦ኅብረት፣ሐዋርያዊነት፣አንድነት፣ኲላዊነት ነው።
እውነት ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ማፍቀርና ምረረ ገሀነመ እሳትን መጥላት ነው።
እውነት ዘለዓለማዊነት ነው።
እውነት ምንድን ነው?

ለወገን ደራሹ ወገን ነው ❗                  በመቄት ወረዳ በ018 አግሪት ቀበሌ አባትና ልጅ በአንድ ቤት ሁለት አካል ጉዳተኞች ወገን ድረሱልን ለወገን ደራሹ ወገን ነው እያሉ ይማ...
22/12/2024

ለወገን ደራሹ ወገን ነው ❗

በመቄት ወረዳ በ018 አግሪት ቀበሌ አባትና ልጅ በአንድ ቤት ሁለት አካል ጉዳተኞች ወገን ድረሱልን ለወገን ደራሹ ወገን ነው እያሉ ይማጸናሉ ‼️

አቶ ደመቀ ያረጋል ዘውዱ የሚኖረው በአግሪት ከተማ ሲሆን ከ8 አመት በፊት የአናጺነት ስራ እየሰራ ሳለ ከቤት ጣራ ወድቆ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምና ቢያደርግም ሊሻለው ባለመቻሉ ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተባብሶበትት ለከፍተኛ የአካል ጉዳት ዳርጎታል ። አሁን ላይ ከ6 በላይ ቤተሰቦች ቢኖሩትም የእለት ጉርስና ልብስ እርዱኝ ወገኖቸ እያለ ይማጸናል ‼️

ህጻን አበበ ደመቀ ያረጋል ገና በአራት አመቱ ድክ ድክ እያለ በድንገተኛ ህመም ታሞ ጸበልና ህክምና ቢወስዱትም እግር እና እጁ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ በቂጡ እየተንፏቀቀ ነው ለመንቀሳቀስ የሚሞክረው ።

ህጻን አበበ እንደ ጓደኞቸ ትምህርት ቤት ሄጄ መማር እፈልጋለሁኝ ፤ አስተምሩኝ ገና በህጻንነቴ እንዲህ መሆኔ አለመታደል ነው ለተባባሰው ማጭድ አታውሰው እንደሚባለው በአንድ ቤት ሁለት የአካል ጉዳተኛ መሆን እጅግ ያሳዝናል ያማል ያውም የቤቱ ራስ አባታችን እንደኔ ከቤት ሲውል እጅግ ይዘገንናል ስለዚህ ወገኖቸ ደግነት ለራስ ነውና ወገን ድረሱልኝ ፤ እንደጓደኞቼ እኔንም ትምህርት ቤት አስገቡኝ አስተምሩኝ ይለናል ህጻን አበበ ደመቀ ።‼️

መርዳት የምትችሉ ሁሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ1000 56 07 02 926 ደመቀ ያረጋል ዘዉዱ ብላችሁ ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን
ለበለጠ መረጃ 📲📲📞📞ስ.ቁ 09 70703823 ደውላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እገልጻለን ‼️

ዳናዊት መክብብ 200,000 ብር ሰጠችዳናዊት መክብብ ለወንድሟ ዘማሪ አቤል መክብብ አዲስ ላሳተመው "ተመስገን" የተሰኘ  አልበም ሕትመት ማገዣ ይውል ዘንድ 200,ዐዐዐ (ሁለት መቶ ሺህ ብር...
22/12/2024

ዳናዊት መክብብ 200,000 ብር ሰጠች

ዳናዊት መክብብ ለወንድሟ ዘማሪ አቤል መክብብ አዲስ ላሳተመው "ተመስገን" የተሰኘ አልበም ሕትመት ማገዣ ይውል ዘንድ 200,ዐዐዐ (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሰጥታለች።

ለዘማሪ አቤል መክብብ "ተመስገን" የዝማሬ አልበም እገዛ እየተደረገ ያለው በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ዛሬ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 በተዘጋጀ ልዩ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ነው።

አቤል መክበብ በተለይ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ "ኃጢያተኛው ድንኳን" በተሰኘው መዝሙሩ ይታወቃል።

የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብዛሬ የምክክር ጉባኤና  ቅድመ ምርቃት ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል::በአዲሱ አልበሙ ዙሪያ የምክክርና የቅድመ ምርቃት መርሐ ግብር ኮሚቴው አዘጋጅቷል::ተወዳጁ ዘማ...
22/12/2024

የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ዛሬ የምክክር ጉባኤና ቅድመ ምርቃት ዝግጅት እየተከናወነ ይገኛል::

በአዲሱ አልበሙ ዙሪያ የምክክርና የቅድመ ምርቃት መርሐ ግብር ኮሚቴው አዘጋጅቷል::

ተወዳጁ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ከአዲሱ የዝማሬ አልበሙ ከተካተቱ ዝማሬዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ ከወዳጆቹ ጋር የሚዘምረው ዛሬ ነው::

ከጥቂት ደቂቃዎች በኇላ መርሐ ግብሩ ይጀምራል::

ተመሰገን ተመስገን

ለምስጋና ስላሰባሰብከን

እግዚአብሔር ተመስገን

ሠላም ቤተሰብ ባላችሁበት ይሁንላችሁ🙏በቅርቡ profile ሥም  .ye.kelil ወደ አሁኑ☝☝☝ ስቀይር😂😀😀 አንዱ ጃብኖስ😀  ቻት ገብቶ 👇👇👇👇
21/12/2024

ሠላም ቤተሰብ ባላችሁበት ይሁንላችሁ🙏

በቅርቡ profile ሥም .ye.kelil ወደ አሁኑ☝☝☝ ስቀይር😂😀😀
አንዱ ጃብኖስ😀 ቻት ገብቶ 👇👇👇👇

🌹 #እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ📌✅ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራ...
20/12/2024

🌹 #እንኳን አደረሳችሁ ቤተሰብ📌

✅ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤል የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ «አምላክ» ማለት ነው። ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ በአማልክት መካከል (በስም አማልክት ከሚባሉ፥ በስመ አማልክት ከሚጠሩ፥ አንድም አማልክት ዘበጸጋ ከተባሉ ከነቢያት ከካህናት መካከል) አንተን የሚመስል ማነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማነው?» ብሏል። ዘጸ ፲፭፥፲፩። ቅዱስ ዳዊትም፦ «አቤቱ፥ ከአማልክት የሚመስልህ የለም፤» ብሏል። መዝ ፹፭፥፰።

❤የቅዱስ ሚካኤል በረከቱ ይደርብን❤🙏

በመንግሥትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ትኩረት የተነፈገው የሽርካ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ !በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና ...
19/12/2024

በመንግሥትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ትኩረት የተነፈገው የሽርካ ኦርቶዶክሳውያን ግድያ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ !

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ታኅሣሥ 5 እና 6 ቀን 2017 ዓ.ም የወረዳ ቤተ ክህነቱን ሥራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ግድያና እገታ እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ከታገቱት ውስጥም የወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ሌሎች 8 ኦርቶዶክሳውያን ገንዘብ ከፍለው የተለቀቁ ሲሆን ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ግድያ እንደተፈጸመባቸው እንዲሁም ያሉበት እንደማይታወቅ አክለዋል፡፡ በዚህ ዕለት ብቻ ከ80 በላይ የኦርቶዶክሳውያን ከብቶች በታጣቂዎች ተወስደዋልም ተብሏል፡፡

ሀገረ ስብከቱ በየዓመቱ በሚካሄደው በ43ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በ2016 ዓ.ም 271 ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

በተጨማሪም ከ10 ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ 91 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ምእመናን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ሲል በጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤው ሪፖርቱ መጥቀሱ አይዘነጋም፡፡

በጀጁ ወረዳ ቡርቃ ጉራቻ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖሩ 150 ምእመናን በጉሬ ደቢኖ ቅ/እግዚአብሔር አብና አርጆ ቅ/ጊዮርጊስ ከ30 በላይ ምእመናን መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን 499 አባወራና እማወራ ለስደት መዳረጋቸውም ተገልጿል፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ሆነ በመንግሥት ትኩረት የተነፈገው የኦርቶዶክሳውያን ግድያ ተባብሶ ኅዳር 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም የ13 ዓመት ታዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ ተወስደው መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ኦርቶዶክሳውያን ያለማንም ከልካይ በተገኙበት ሁሉ በሚገደሉበት በዚያ ሀገረ ስብከት የ45 ቀን አራስ ሕጻንን ጨምሮ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና አብያተ ክርስቲያናት ላይም ጥቃት እየተፈጸመ መቆየቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም የኦርቶዶክሳውያን ግድያና ስደት እንዲሁም የሀብት ዝርፊያ ሰሚ ያጣና በወረዳው ተጠናክሮ የቀጠለ በመሆኑ የአካባቢው ምእመናን በትልቅ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መሆናቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገልጸዋል፡፡

“የማይጠቅሙና ፋይዳ የሌላቸው ጉዳዮችን ሲዘግቡ የሚስተዋሉ ሚዲያዎች የእኛ ሞት እንደምን ቀለላቸው?” ያሉት ኦርቶዶክሳውያን ነዋሪዎች ከሀገረ ስብከቱ ጀምሮ እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በወረዳችን እየተፈጸመ ያለው ግፍ ትኩረት አለመሰጠቱ እጅጉን አሳዝኖናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሰብዓዊነት የሚሰማችሁ ግለሰቦችና የግፍ ግድያውን የምትቃወሙ ሚዲያዎች ሀብት ንብረት ባፈራንበት ወልደን ከብደን በተቀመጥንበት ሀገራችን እንዳውሬ እየታደንን ስንገደል ድምጽ ትሆኑን ዘንድ እንማጸናችዋለን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አስተያየት ሰጭዎች አክለውም መንግሥት የዜጎቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት በመገንዘብ ሞታችንን ሊያስቆምና መፍትሔ ሊያመጣ ይገባዋል ሲሉም አሳስበዋል፡፡

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

18/12/2024

በዚህ አለም ቀን ስጨልምብህ እንኳን ሰው የአንተ ጥላው ራሱ አንተን እንደምሸሽ አስበሀል?

18/12/2024

.....ስለዚህ
መኑ ይመስለከ እምኔ አማልክት እግዚኦ
እንዳንቴ ያለ አማልክት ማነው
አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ
ተምራትን የምታደርግ አንተ ነህና

18/12/2024

ሰው ከሰው ጋር ለመጣላት ስፈልግ ምክንያት
ይፈልጋል
እግዚአብሔር ከሰው ጋር ለመታረቅ ምክንያት ይፈልጋል።

" በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ...
18/12/2024

" በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤"

(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:8)

 #የቅድስት ስላሴ ታቦተ ህግ ጥር 6 ቀን 2017 አመት ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል #ላለፉት ሁለት አመታትና ከዛ በላይ ለሚሆኑ ጊዜያት እድሳት ሲደረግለት የቆየው የቅድስት ስላሴ ካቴድራል ...
18/12/2024

#የቅድስት ስላሴ ታቦተ ህግ ጥር 6 ቀን 2017 አመት ወደ መንበረ ክብሩ ይመለሳል

#ላለፉት ሁለት አመታትና ከዛ በላይ ለሚሆኑ ጊዜያት እድሳት ሲደረግለት የቆየው የቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እድሳት ወደ መገባደዱ መድረሱን ተነግሯል።

የካቴድራል የዕድሳት እና የጥገና ስራ ከተጀመረ 773 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን በየጊዜው በገጠመው የሲሚንቶ ችግር እና ሌሎችም ሁነቶች ምክንያት ተጨማሪ 225 ቀናት መውሰዱን ተጠቁሟል።

የህንጻውን ግንባታ ለሚያከናውነው ኮንትራክተር እስካሁን ድረስ ከ124 ሚሊዮን ብሮ በላይ ክፍያ እንደተከፈለው የተነገረ ሲሆን ቀሪ ክፍያ እንደሚቀረው ነው የተገለጸው።

ታቦተ ህጉ በተባለው ቀን ወደ መንበሩ ለማስገባት ለኮንትራክተሩ የሚከፈለው ከ47ሚሊዮን ብር በላይ ህዝበ ክርስቲያኑ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ተደርጓል።

የቤተክርስቲያን ህንጻው ግንባታ ሂደት 95 በመቶ ደርሷል።

የቤተክርስቲያኑ እድሳት ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ አገልግሎቱ ባሻገር ትልቅ ሃገራዊ አበርክቶ ያለውን ካቴድራሉን እና ቅርጻቅርጾቹን ኪነ ጥበባዊና ቅርሳዊ ይዞታቸውን በጠበቀ መልኩ መታደሱንም ተነግሯል።

የአጼ ኃይለ ስላሴን የንግስና በዓለ ሲመት ያስተናገደው ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የመሪዎች፣ የጀግኖች አርበኞች እና የታዋቂ ሰዎች ዘላቂ የማረፊያ ስፍራ ነው፡፡ በብዙዎች ይጎበኛልም፡፡

የካቴድራሉ ግንባታ በ1922 ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን በፋሽስት ጣሊያን ወረራና በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ በ1936 ዓ/ም መጠናቀቁን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

18/12/2024

አንማረር! ያልሆነን ነገሮችሁን በማሰብ።

የተሰጠነውን ቢናስብ የጎደለብን ምንም ነገር የለም።

ያልተሰጠህን አትሻየተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፡፡ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል። አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ...
17/12/2024

ያልተሰጠህን አትሻ

የተሰጠህን ጸጋ እንዳታጣ ያልተሰጠህን አትሻ፡፡ ወደ ጸጋ ወደ ክብር ለመድረስ እግዚአብሔር ቢያበቃህ ያሳየህን እይ ያላሰየህን አያለሁ አትበል። አንድም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፣ በተሰጠህ ጸጋ ለእግዚአብሔር ተገዛ፡፡ ማር አብዝቶ መመገብ እንዳይመች እንደዚህም ሁሉ ያልተሰጠውን መሻት አይገባም አያስመስግንም፡፡

ነፍስ ያልተሰጣትን ጸጋ በመሻት እንዳትደክም ያልተሰጠህን ጸጋ አትሻ፡፡ የምታየው ማየት ቢኖር እውነተኛውን ምትሐት ሆኖ ታየዋለህ ፤ ሕሊና ያልሰጡትን ጸጋ በመሻት በማውጣት፣ በማውረድ የተሰጠውን ያጣል፡፡

ሰሎሞን መልካም ነገር ተናገረ "በሰጡት ጸጋ የማይኖር ሰው ቅጽር የሌላትን አገር ይመስላል" ብሎ ያን ማንም እየገባ እንዲዘረፈው እሱም የተሰጠውን ጸጋ ያጣል ፤ አንተ ብሩህ አእምሮ ሰውነትህን ያልተሰጣትን ጸጋ እንዳትሻ ከልክላት፡፡

ከቁመተ ሥጋ የወጣ አብዝቶ መገበርን ከአንተ አርቅ ያልተሰጠህን መሻት ከአንተ አርቅ፡፡ ባልተሰጠህና በተሰጠህ ጸጋ መካከል ትሕትናህን፣ ንጽሕናህን መጋረጃ አርጋቸው:: አንድም በተሰጠህ ጸጋ ላይ ያልተሰጠህን ጋርደው፡፡ በንጽሕና፣ በትሕትና፣ በልቡናህ የምታስበውን መንፈሳዊ ክብር ታገኛለህ::

Address

Line
Arba Minch'
YEM

Telephone

+251938784121

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዲ/ን ይሁን ዘደብረ ገነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share